Monday, December 8, 2008

ጀንራል ጠዓመ ጎይተኦም ማነዉ?

ጀንራል ጠዓመ ጎይተኦም ማነዉ? ጌታቸዉ ረዳ አስመሮም ከተባሉ አንድ ኤሪትራዊ በhttp://asena-online.com በተባለዉ የህዋ ሰሌዳ በለጠፈዉ ሰነድ መሰረት የትግርኛዉ ቋንቋ ወደ አማርኛ በመመለስ ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ “መቐለ” በሚል ቅጽል ስም የሚጠራ የሻዕቢያ ሹም ማን መሆኑን እና በምን ተግባራት ተሰማርቶ ምን እንደፈጸመ እና እየፈጸመ እንዳለ የሚያሳይ ሰነድ ይቀርባል። ተጠቃሹ ካሁን በፊት በኢሳያስ የባሕር ዉምብድና እና የመሳሰሉት ሕገ ወጥ የመሳሪያ ሽግግር ተግባሮች ንክኪ ተሰማርቶ እንደነበር ቀደም ብሎ ከወጡት የምስጢር ሰነዶች እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል። በዛ መሰረት ሰዉየዉን በቅርብ የሚያዉቁት የሰዉየዉን ማንነት በመጠኑ የዘረዘሩትን ታሪክ እንሆ። ለአቅራቢዉ ለአቶ አስመሮም በአንባቢዎች ስም እና በ“ኢትዮጵያን ሰማይ” ስም በቅድሚያ እያመሰገንኩ አሁን በቀጥታ ወደ ትርጉሙ እንሆ፦
“ጠዓመ ጎይተኦም (መቐለ) (ቅጽል ስሙ መቐለ ወደ ህዝባዊ ግምባር በ1977 ተቀላቅሎ በ80ዎቹ ከተራ ተዋጊነት ወደ “ክፍል 72” ወደ ሚባለዉ ማለትም ወደ ስለያ እና ጸጥታ ክፍል ተመድቦ አስከ ነጻነት ድረስ በዚሁ ክፍል ሲሰራ ቆይቷል። ከነጻነት በሗላ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄድ ተመደቦ ማዕከሉን አዲስ አበባ በማድረግ የኤርትራ የሻዕቢያ ተቃዋሚ ሃይሎችን እያፈነ እና እየገደለ የቆየ ነዉ።የመግደል እና የማፈን ተልዕኮዉ የሚተላለፈዉ ትዛዝ በቀጥታ ከኢሳያስ አፈወርቅ ነዉ። የሚታፈኑ እና የሚገደሉ ግለሰዎች ስም ዝርዝር ተሰጥቶት ከነጻነት በሗላ አዲስ አበባ ሄዶ የወንጀሉን ተግባር ፈጽሞ የግድያዉ እና የአፈናዉ ሰላባዎቹ ከሆኑት መሃል ጥቂቱን ብንጠቅስ፦
· ታዋቂዉ አቶ ተስፋሚካል ጆርጅዮ
· በደረግ ጊዜ የደርግ ደጋፊዎች እና በኤርትራ የራስ ገዝ አስተዳደር አካባቢዎችና የመሳሰሉት ለደርግ በመቆም ፓሊሲዉን ተግባራዊ ለማድረግ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰዎች፦
· ትግሉን ጥሎ የወጣ ይሕደጎ ወልደጊዮርጊስ የተባለ የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት የዓንደብርሃን ወልደጊዮርጊስ ወንድም
· ከተለያዩ የኤርትራ ነፃነት ግምባር ከድተዉ ወደ ደርግ የገቡ እና በርከታ ሌሎች ሰዎች ሰለባ ሆነዋል።
አያሌ ሰዎች በኢሳያስ ትዕዛዝ በጠዓመ ጎይተኦም ፈጻሚነት ከተገደሉ በሗላ በ90ዎቹ አካባቢ በኢሳያስ አፈወርቅ ምስጢራዊ ሌላ ከፍተኛ የግድያ ስራ ለመፈጸም ወደ ዚምባቡዌ ሐራሪ ከተማ በመሄድ በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ላይ የጥይት ተኩስ ከፍቶ የከሸፈ የግድያ ሙከራ ሲያደርግ እጅ ከፍንጅ በመያዙ በሃራሪ ፖሊስ ተይዘዉ ፍረድ ቤት ቀርቦ አሱ እና ሌላ ተባባሪዉ ግለሰብ ሁለት ዓመት ታስረዉ ተለቅቀዉ ወደ አስመራ ሄደዉ በቀጥታ ኢሳያስ ጋር በመቅረብ ልዩ ሙገሳ ተደርጎለት ከጥቂት ጊዜ ራሱን ካደላደለ በሓላ ተመሳሳይ ለሌላ ዝግጅቶች ከኢሳያስ አፈወረቅ ትዕዛዝ እየተቀበለ ተመሳሳይ ድረጊቶችን ለመፈጸም የተመደበ ሰዉ ነዉ።
ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ከኢሳአስ አፈወረቅ ሌላ ማንም አያዘዉም።ከሌሎች ባለ ስልጠኖችም ጋር የ አዛዥ ታዛዥ ግንኙነት የለዉም። ከዝምባቡዌ መልስ በሗላ -ምድብ ስራዉ አሲያስ እንዲፈጸሙ የሚፈልጋቸዉን ነገሮችን በቅጽበት ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ነዉ።ኢሳያስ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ወይንም እንዲፈጸሙ የሚፈልጋቸዉ ድርጊቶች ካሉ ተልዕኮዉ የሚሰጠዉ ለጠዓመ ብቻ ነዉ።
በአዉሮፓ፤በ አሜሪካ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮች ያሉት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች እየሄደ የሚያደራጃቸዉ እና የሚገናኛቸዉ ጠዓመ ጎይተኦም ነዉ።ኦሮሞ ነፃነትን (OLF) አደራጅቶ ወደ ኢትዮጵያ በቀጥታ ሰርገዉ በመግባት ወታደራዊ ጥቃቶችን እንዲፈጽሙ የሚያቀናብረዉ እሱ ነዉ። ለተልዕኮዉ ማስፈጸሚያም ሆነ ሌላ አስፈላጊ በጀት የሚመድበላቸዉ እና የሚፈቅድላቸዉ የበላይ ባለ ስልጣን እሱ ነዉ።
አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በአንዳንድ ቦታዎች በድብቅ ተጠምደዉ የሚፈነዱት ቦምቦች ( ወያኔ ለ ፕሮፖጋነዳ ጠቀሜታ ከሚለፍፈዉ ዉጭ ወደ ጎን ትተን) ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ ጎይተኦም በሚሰጠዉ መመሪያ የሚፈጸሙ ናቸዉ። ከዚህ ሌላ ሶማሌዎችን ከዘመነ ዓይዲድ ጀምሮ አስካሁን ድረስ ያሉትን የተለያዩ የሶማሌ ቡድኖችን እንቅስቃሴ እየተከታተለ የሚያስተባብራቸዉ እና ከኢሳያስ የተሰጠዉ መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርገዉ ጠዓመ ነዉ።
የኢትዮጵያ ጦር ሶማሌ ድረስ ገብቶ የእስላማዊዉን ሃይል ሲመታ ከሶማሌ ሸሽተዉ ወደ ኬኒያ ሲገቡ የተያዙ ኤርተረዉያኖች ለማስፈታት ኬኒያ ድረስ ተጉዞ ጉቦ ከፍሎ በማስፈታት ወደ አገራቸዉ እንዲመለሱ ያደረገም አሱ ነዉ።
ብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ በዓይኑ ያላየ አያምንም። የሚያንቀሳቅሰዉ የዉጭ ምንዛሪ ገንዘብ መጠኑ በጣም ብዙ ነዉ፡ የፈለገዉ የገንዘብ መጠን ቢያንቀሳቅስም ኢሳያስ ሙሉ መብት ስለሰጠዉ የተመደበ የበጀት መጠን የለዉም።የፈለገዉ የገንዘብ መጠን ወደ ፈለገዉ ነገር ቢያዉለዉ ጠያቂ የለዉም።ነገ ጎህ ሲቀድ ፈትህ ሲሰፍን ገሃዱ ሲወጣ በንቅዘት ከተበላሹት የኤርትራ መንግስት በላስልጣነት ጠዓምን የሚያክል ብልሹ ባለስልጣን እንደማይኖር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።