Friday, April 7, 2023

አማራውን በሚመለከት ሁለት ርዕሶች አሉኝ ጌታቸው ረዳ Abiy Ahmed Ethiopian PM most wanted criminal

 

አማራውን በሚመለከት ሁለት ርዕሶች አሉኝ 

ጌታቸው ረዳ

 

Abiy Ahmed Ethiopian PM most wanted criminal

(Ethio Semay) 

4/6/2021 በድጋሚ የታተመ (4/7/23)

 

(1)-አማራዎች ሰልፍ ስታደርጉ ሰልፉ አማራን ብቻ ያተኮረ ይሁን

(2)-የአማራውን ነገድ ማጥፋት ለምን ቀጣይ ሆነ?

በ2ኛው ረድፍ ልጀምር ከዚያም በ 1ኛው ረድፍ ጽሑፌን እደመድማለሁ።

እየተነጋገርንበት ያለው ርዕስ በፎቶግራፉ ስላለው በ1ኛ ደረጃ ተከሳሽ የሆነው የወንጀለኞች መሪ ስለሆነው አብይ ነው። ሰውየው አክራሪ ብሔረተኛ ነው። ጽንፈኞች የመንግሥትን መዋቅር ሲቆጣጠሩ የዘር ማጥፋት ወንጀል የመፈፀም አቅም አላቸው። ትግራዋዊው ወያኔ 17 አመት በጫካ 27 አመት በሥልጣን ዘመኑ፤ አሁን ደግሞ 3 አመት በኦሮማዊው ኦነጋዊው የኦሮሙማው ቡድን መሪ በሆነው በኮለኔል አብይ አሕመድ ተባባሪነት “አማራው ማሕበረሰብ” የዘር ጥቃትና መፈናቀል ተፈጽሞበታል። አሁንም እንደቀጠለ ነው። ለምን ዕደል እንዳገኘ ብዙ ምክንያት ቢኖሩትም ዋናው ምክንያት የምላቸው ሁለት ነጥቦችን እንመልከት።

2ኛው ረድፍ ስንመለከት ለአማራው ዘር ጭፍጨፋ ዋናው ተዋናይ ቡድን እና ምክንያት የሆነው “አክራሪ ነገደኛ” እና “አክራሪ ሃይማኖተኛ” ቡድን የመንግሥት ሥልጣን በመቆጣጠሩ ነው። በዚህ መጠራጠር የለባችሁም። ያለ ይህ ቡድን አቀናባበሪነት የዘር ጥቃት ቀጣይነት አይኖረውም።

ከተመክሮ የታዘብነው ፤ እንዲህ ያለው ቡድን ከተለያዩ ነብሰ ገዳዮች ጋር ሲነጻጸር በባህሪና በዓላማ የተለየ ሆኖ የሚፈጽመው የጭካኔና የማጥቃቱ ስፋት እንኳን ከተራ ነብሰገዳይ በእንስሳት አለምም እንዲህ ያለው ቡድን እጅግ አስፈሪና ጨካኝ ፍጡር የለም።

ይህ ኃይል መንግሥት ሲሆን፤ የቁሳዊ ሃይልና አጥቂ ሃይል ስለሚኖሮው በገፍ መግደልና ማፈናቀል የሚያስችለው አቅም አለው። አማራውን እያጠቃ እና እንዲጠቃ እያደረገ ያለው አብይ አሕመድ አማራውን ለማጥቃት እንዲመቸው ከአማራ ማሕበረሰብ የተወለዱ እንደ እነ አገኘሁ ተሻገር እና ደመቀ መኮንን ዓሊ እንዲሁም ገዱ አንዳርጋቸው... የመሳሰሉትን ሺዎቹ “ሆድ አደር” የወንጀል ድርጊቱ ተባባሪዎቹና ጀሌዎች በውጭም በውስጥም በማስሰለፍ የወንጀሉ ተባባሪዎች በማድረግ “አማራዎች በከፍተኛ ሥልጣን በተሾሙበት መንግሥት ውስጥ 'አማራውን' አሳልፎ ለጥቃት አይሰጥም” የሚሉትን ሞኞች እንዲከተሉት በማድረግ “አጥቂው መንግሥት” አማራውን በማስጨፍጨፍ እየተሳካለት ነው።

ጥቃቱ ሲፈጸም “እርዳታ ለሚጠይቁት ገለልተኛ የከተማም ሆነ የገጠር ሹሞች “እቤታቸው ገብተው አርፈው እንዲተኙ” በማስጠንቀቅ ጥቃቱ እንዲከናወን ያደርጋሉ። ክስተቱ የሚከሰተው ሁኔታውን ካለመረዳት ሳይሆን እንዲህ ያለ የተሰላ ምላሽ የሚሰጥ ቡድን “ተጠያቂ እንደማይሆን ያወቀ፤ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው የአክራሪ መንግሥታዊ ቡድን አባል ሲሆን ነው። የኦሮሞ ክልል ፕረዚዳነት" ሽመልስ አብዲሳ እየተፈጸመ ላለው ከፍተኛ ወንጀል ተጠያቂና የአክራሪው ቡድን አስተባባሪና ተዋናይ ነው፡

የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽሙ ሥልጣን ያልተቆጣጠሩ ተራ ቡድኖች ጥቃት ሲፈጽሙ ሁሌም ተከታታይነት የለውም። የመንግሥት ድጋፍ ስለማያገኙ ዕድል ሲያገኙ ብቻ ያጠቃሉ። አክራሪው ሃይል የመንግሥትን ስልጣን የተቆጣጠረ ከሆነ ግን 30 አመት ሙሉ አማራው እያጠቁት አንዳሉ ሁሉ ግባቸው እስኪያጠናቅቁ ድረስ ጥቃቱ በዘገናኝ ጭፍጫፋ እየተካሄደ ለረዢም ጊዜ ይከናዋናል። የጅምላ ጭፍጨፋ ሲከናወንም የገዢው ባለ ሥልጣኖች ስለሚመሩት አንድም ሰው ተጠያቂ አይደረግም።

ተጠቂዎችም ጥቃት ሲፈጸምባቸውም ሆነ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሲያገኙ የዘር ማጥፋት ወንጀል በላያቸው ላይ እንደሚካሄድ መቼ እና የት እንደሚከሰት ለመንግሥት አቤት ብለው "የነብስ አድን እርዳታ እንዲደርስላቸው" ቢጠይቁም “ጥቃቱ” ልክ እንደ ርዋንዳ ኢትዮጵያ ውስጥም በመንግሥት እውቅና ስለሚከናወን ሰላማዊ አማራዎች የጭፍጨፋው ሰለባ ሆነዋል፡፡

ስለሆነም የአማራው ተከታታይ ጥቃት እየተፈጸመበት ያለበት ምክንያት አክራሪው ሃይል የመንግሥትን መዋቅር ከላይ እስከ ታች በቁጥጥሩ እጅ ስላስገባ ነው። ለዚህም በአብይ አሕመድ ዘመን በተለይ በአማራ ላይ “የባሰ ጭፍጨጫ” በመካሄዱ ሰውየው በጸረ አማራነቱ የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ በዘር ማጥፋት ወንጀል በ1ኛ ደረጃ ወንጀለኛነት መከሰስ አለበት።

በዚህ ከተማመንን ሌላኛው ምክንያት ላስቃኛችሁ፦

አማራዎች ሰልፍ ስታደርጉ ሰልፉ አማራን ብቻ ያተኮረ ይሁን የምልበት ምክንያቴ በጣም ብዙ ምክንያት ቢኖሩም፤-

(ሀ) የፖለቲካ ድርጅቶች፤

 

(ለ) አማራዎች እራሳቸው የማስተዋል ግንዛቤ

ስላልነበራቸው በሕዝባቸው እና በራሳቸው ህይወት እንቅፋት የመሆናቸው ክስተት ጥቃቱ እንዲቀጥል መጥፎ ተዋናዮች ሆነው ቆይተዋል።

የአማራ ዘር ጥቃት ለማስቆም ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ ያንን ሰላማዊ ሰልፍ በመጥለፍ ድምጹ እንዲዋጥ ለበርካታ አመታት የተለያዩ ተዋናዮች ሰልፉን ጠልፈው ለፖለቲካ ድርጅታቸውና መሪዎቻቸው ፎቶግራፍ በመለጠፍ የመሪዎቻቸው የቆሸሸውን ተክለሰውነታቸውን ለማሳመር ሲጠቀሙበት አይቻለሁ። ለዚህ ተዋናዮቹ ብዙዎቹ አማራ መሆናቸውን እጅግ አሳዛኝ ክስተት ያደርገዋል።

(ሀ) - የፖለቲካ ድርጅቶችን እንመልከት፤

የአገር ውስጥ ፖለቲካ ድርጅቶችና ምሁራንን ለጊዜው ትቼ ፤ ካሁን በፊት በተደጋጋሚ እዚህ ውጭ አገር የታዘብኳቸው ሁለት የፓለቲካ ድርጅቶችን ልጥቀስ፡

 

1)            ኢሕአፓ

 

   2) “ግንቦት 7” ዛሬ “ኢዜማ”

እንደምታውቁት ዛሬ፤ዛሬ ግልጽ እንደሆነው ‘ኢትዮጵያ ውስጥ’ አማራው ተገድሎ ኩላሊቱና ሥጋው ተቀቅሎ ተበልቷል” የሚል ዜና ከ6 አመት በፊት ብዙዎቹ አማራዎችም ሆኑ ድርጅቶች የዜናውን እውነተኛነት በተጨባጭ በድምጽ ቢሰሙትም አልተቀበሉትም ነበር። ደርጅቶቹ ውስጥ የተሰገሰጉት ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው። ዜናውን ሲያጣጥሉት የነበሩት ደግሞ ብዙዎቹ አማራዎች ናቸው። አስገራሚው ክስተት ይህ ነው። ይህንን ሃቅ ከጥቂት አማታት በፊት በአቶ ተክሌ የሻው ሞረሽ ወገኔ የሚመራው ድርጅትም ሆነ በግል እኔም ይህንን ዜና እውነተኛነቱን ለማሳመን ስንጥር የኢሕአፓ ጀሌዎች በተለይም በኔ ላይ እኔን በሃሰተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተውብኝ ለረዢም ጊዜ ስንከራከር እንደነበር አስታውሳለሁ።

ያኔ የተነገረው ዛሬ በተደጋጋገሚ በግሃድ አማራን ገድለው ስጋው እየተበላ መሆኑን እውነቱን የምታዩት ነው። ያኔ ከስንት አመታት በፊት ስሜን በማጠልሸት የሰደቡኝ ዛሬ በግልም በፓርቲያቸውም ይቅርታ አልጠየቁም። (ለኔ ክብር ሳይሆን ለአማራው ማሕበረሰብ እንኳን ሲሉ )።

 

ጥቂት ማስረጃ ልጥቀስ፡

 

የ “ፍኖተ-ዴሞክራሲ” የተባለው የኢሕአፓ ራዲዮ ጠቢያ በርዕሰ አንቀጹ “በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው” በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን መግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በሬዲዮ በማስተላለፍ እኔም ሆንኩ አቶ ተክሌን በአማራ ስም “ሌሎችን” እየዘለፍን አድርጎ በሚገርም ሁኔታ እኛን ለማሳጣት ወደ ኢትዮጵያ በሳተላይት አስተለለፈ። በጽሑፍ ደግሞ በተባባሪ ድረ-ገፆች “በአሲምባ” እና “በደብተራው” ድረገጽ አሠራጨው።

አከታትሎም “በጉምዝ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጸያፍ ዘመቻ የአማራን ሕዝብ ተገን አድርጎ በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው።” በማለት የቻለውን ያህል የተፈጸመውን ወንጀል እንዳልተፈጸመ አድርጎ እኔንም ሆነ አቶ ተክሌ የሻውን እንድንወገዝ ጣረ።

“በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው” ለሚለው ስም የማጥፋት ዘመቻ ፤ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት “በዐማሮች ላይ በሚፈፀመው አሰቃቂና ዘግናኝ ዕልቂት ላይ መሣለቅ በታሪክና በሕዝብ ያስጠይቃል” በማለት ‘ማክሰኞ መስከረም ፬ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፩ በፍኖተ-ዴሞክራሲ ሬዲዮ ለቀረበው ውንጀላ መልስ ሰጠ።

“ቤንሻጉል ጉመዝ ውስጥ አማራውን ገድለው ጉበቱን፣ ኩላሊቱን፣ የታፋ ሥጋውን ጠብሰው በሉት” ከግድያው አምልጠው በየዱሩ ተደብቀው ያዩ የዓይን ምስክሮች የሰጡትን ምስክርነት ‘ሕዝቡ ለማሳወቅ የጻፍኩትን ጽሑፍ’ አሲምባ የተባለው ድረገጽ ለኔ መልስ የሚሆን “ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ፣ ለዐማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሊሰጥ የሚገባው አደለም።” በማለት አሲምባ የተባለው ድረገጽ መልስ ሰጠ።

በዚህ ሳይወሰን ከኢሕአፓ አንድ ጀሌ ደግሞ፤

“አማራ፤ አማራ ፤ የሚሉ ፡ስለ አማራ የወገኑ ሰዎች” አማራዎች ሳይሆኑ ከሌላ ጎሳ የተወለዱ የወታደር ልጆች ናቸው” በማለት የአማራን ጥቃት ለሕዝብ በመግለጻችን ከኤርትራዊያን በባሰ መልኩ የዘቀጠ “ዘረኛነቱን” በማንጸባረቅ ዘለፈኝ። ይህንን ያነበበው ሞረሽ ደግሞ ለአሲምባም ሆነ ለፍኖተ ራዲዮ መልስ እንዲህ ሲል ጻፈለት

“እዚህ ላይ መግለጫውን ያወጣው የ “ፍኖተ-ዴሞክራሲ” ዝግጅት ክፍል ያሳሰበው የዐማራውን ሥጋ ጠብሰው የበሉት ገዳዮቹ ጉምዞች፣ “ለምን የሰው ሥጋ በሉ ተባሉ?» ብሎ ነው። ሥጋቸው ተጠበሶ የተበሉት ዐማሮች ለእነርሱ ምናቸውም አይደሉም” ሲል ተገቢውን መለስ ሰጠ።

ይህ የማስታውሳችሁ በፖለቲካ ፓርቲ የተሰገሰጉ አማራዎችም እራሳቸው ምን ያህል ርቀት እየሄዱ የአማራውን ጥቃት ለመሸፋፈን አጉል እወደድ ባይነት ተወናይ እንደነበሩ ለማስታወስ ነው። ችግሩ በነ ኢሕአፓ አላበቃም ግንቦት 7 የተባለው ጸረ አማራ እና የፖለቲካ አሰናካይ/መሰሪ/ ድርጅትም ስለ አማራ ጥቃት ሰልፍ ሲጣራ ወደ ራሱ የፖለቲካ ጠቀሜታ በመጥለፍ ከፍተኛ ሚና ነበረው።

ይህንን በሚመለከት አንድ ምሳሌ ልስጣችሁና ልደምድም።

2ኛው ምክንያት የአማራው ወጣትና 98 ከሞቶው ምሁሩ አማራን እንመልከት።

ለ30 አመት አመራው ሲገደል፤ሲባረር፤ሲታሰር፤ሲሰደድ ከማንኛው ነገድ ይልቅ ምንም ያልተሰማው የአማራው ወጣትና አማራው ምሁር ስለ ሰቆቃው “ጀሮ ዳባ” ብሎ ነበር። የሆነውን አንድ ምሳሌ ላጫውታችሁ።

አሜሪካ ውስጥ ኢትዮጵያዊያን የሚሰባሰቡበት የኢትዮጵያዊያን የእስፖርት በዓል ሳንሆዜ /ካሊፎርኒያ ተዘጋጅቶ ነበር። ሁለት ሕዝባዊ ስበሰባዎች ተዘጋጅተው ነበር። ቦታውም “ማርዮት ሆቴል” በተባለ ትልቅ ሆቴል ባንድ ቀን ፤በተመሳሳይ ሰዓት ሁለት የተለያዩ ጎን ለጎን በሚገኙ የስብሰባ አዳራሾች የተለያዩ ሰብሰባዎች ጥሪ ተከናውኖ ነበር። በወቅቱ ስለ አማራ ሰቆቃ ጥቂቶች ስንጮህ እንደ ሞኞችና አቅመ ቢሶች የታየንበት ወቅት ነበር።

በተመሳሳይ በሚገርም ክስተት “አንዳርጋቸው ጽጌ” ታሰሮ ስለነበር፤ ብዙ በሃዘኔታ የተንጫጫበት ወቅት ነበር።በዛው ቀን እና ተመሳሳይ ሰዓት “ሞረሽ” የተባለ የአማራ ድርጅት የጠራው ስብሰባ እየረገጡ እነ ታማኝ በየነ እና ብዙዎቹ ታዋቂ አክቲቪስቶች “ግንቦት 7” ወደ አዘጋጀው አዳራሽ ነበር ሲገቡ የነበሩት። ወቅቱም በፈረንጆች በ2014 ነበር። እኔ ዶከተር ጌታቸው ሃይሌ እና ዶከተር ሃይሌ ላሬቦ የአማራውን እልቂት ሕዝብ እንዲያውቀው በእንግዳነት ተጋብዤ “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? በሚል ርዕስ ለማስሰማት የተጋበዝኩበት መድረክ ነበር። ቦታው ሳንሆዘ (ካሊፎረያ) ውስጥ። ወቅቱ የስፖርት ፈሰቲቫል በዓል ዝግጅት (በወቅቱ ስለ የሚሊዮኖች አማራ ሳይለቀስ ስለ አንድ አንዳርጋቸው ጽጌ” በሚል ይህንን ቅሬታየን በሚዲያ ገልጨለሁ)

ሌላው ስለ ሰልፍ ነው።

በአማራው ኮለኔል ስም የአንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ያሸበረቀበት የዲሲው ሰልፍ ጌታቸው ረዳ (Editor Ethio Semay) በሚል TUESDAY, AUGUST 9, 2016 ርዕስ ኢትዮ ሰማይ ላይ የጻፍኩትን ብዙ ማስረጃ የያዘውን ጽሑፌን ጉጉል አድርጋችሁ ማንበብ ትችላለችሁ።

ወቅቱ ጎንደር ውስጥ ከፍተኛ ጸረ ወያኔ ሕዝባዊ አመጽ የተነሳበት ነበር። ይህንን በማስመለከት ዲሲ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ። ዋናው ሰልፍ አማራን ሰቆቃ እና እያደረገው ስለነበረው ተጋድሎ “ዓለም” እንዲያውቀው ድምጽ ይሰማል ተብሎ በጉጉት ሲደመጥ፤ የግንቦት 7 እና ኦነግ በቀለ ገርባ ቡድን ጠለፉት።

ዛሬ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ የተባለው ሞኝ ሰው፤ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነውን አሳምነው ጽጌን የመሰለ ጀግና “ከሃዲ” ብሎ ሲዘልፈው በመስማቴ “ይቅርታ” እስካልጠየቀ ድረስ ፍጹም ይቅርታ የማላደርግለት ሰው ነው። ያኔ በ2016 በፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር (ማለትም ከአምስት አመት በፊት) ግን ጀግና ብየ በሚከተለው ጠቅሼው ነበር፡ (የዲሲውን ሰልፍ አስመለክቼ ማለት ነው)፡

“የአማራውን አስደናቂ ትግል ክርቢት ጭሮ ያደመቀው ጎንደሬው ጀግናው ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ስሙም አልተነሳም፤ፎቶግራፉም ይዞ የተሰለፈ ሰልፈኛ አልነበረም፤ ገድሉም አልተወሳም። በምትኩ የግንቦት 7ቱ መሪው በነገዴ ‘ኦሮሞ’ ነኝ ብሎ የነገረን የኢሳያስ አፈወርቅ አወዳሽና ጸረ አማራው “የአንዳርጋቸው ጽጌ” እና “አማራው ኦሮሞን ይቅርታ ይጠይቅ” ብሎ “ኢሳት” ላይ ቀርቦ የተናገረ የኦነጉ በቀለ ገርባ ፎቶግራፉ ተይዞ በተደጋጋሚ ከፍ ብሎ በካሜራ ሲቀረጽና ሲታይ ነበር (የሁለቱም ብቻ)። ይባስ በሎ የኢሳያስ ሻዕቢያ ባንዴራም ሲውለበለብ እዛው ዋለ። የአማራው ድምጽ መጥለፍ እስከመቸ? ብየ ጽፌ ነበር።

ሙሉውን ከላይ ያስቀመጥኩትን ርዐስ ጉጉል ብታደርጉት ድረገጼ ላይ ታዩተላችሁ (አስገራሚ መረጃ እና ፎቶግራፎችም እዛው ታገኙዋቸዋላችሁ)።

ይህ ያልተማረው አማራ ባለፉት አመታትም ሆነ ባለፈው ወር ተደጋጋሚ የሰላመዊ ሰልፍ ጥሪ ጠለፋ በተደረገ ቁጥር ጥቂቶች ካልሆኑ ጠለፋው ተባበሪዎች ነበሩ። የዋህ እና ተንኮለኛ አብረው መጎዳኘት ስለሌለባቸው ይህም እየቀጠለ እንዳለ ባለፈው ወር ስላየሁኝ፡ ካሁን ወዲያ የራሳችሁን አማራዎች ብቻ እና ተቆርቋሪ ግለሰቦች ብቻ በመተባበር ሰላመዊ ሰልፍ በመጥራት የአማራውን ደምጽ ብቻ አስተጋቡ። ሃቁ እና አዋጩ መንገድ ብቸኛ ይህ ነው ። እኔ ጨርሻሉ፤ ሓሰቤን ባመሰራጨት ሓለፊነታችሁ በመወጣት “ሼር” ማድረግ የናንተ ድርሻ ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

(Ethio Semay)