Tuesday, June 29, 2021

በርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ቴድሮስ ጸጋየ ዛሬም ቅሬታ አለኝ (ክፍል ሁለት) ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/29/2021

 

በርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ቴድሮስ ጸጋየ ዛሬም ቅሬታ አለኝ

(ክፍል ሁለት)

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/29/2021

ዛሬ ጥዋት ከዚህ ጽሑፍ ሌላ አብይ አሕመድ መጨረሻው ላይ “ሕዝብ አስጨርሶ ሸብረክ ይላል ብያችሁ ነበር፤ ይኼው እንታረቅ አለ!” የሚል ጽሑፍ የለጠፍኩት ስላለ እሱም እንዳያመልጣችሁ አንብቡት””

 አሁን ወደ እዚህ ትንተና እናምራ።፡ይህ ጽሑፍ ክፍል ሁለት ያልኩበት ምክንያት ከወራት በፊት ተችቼው ስለነበር ይህ እንደ ቀጣይ ክፍል ሁለት ተብሎ ይወሰድ። ለሁላችሁም ማሳሰብ የምፈልገው ቴድሮስ ጸጋዬ ካሁን በፊት በክፍል አንድ እንደገለጽኩት ኢትዮጵያዊነቱን በፍጹም ለድርድር የሚያቀርብ አይደለም ብያለሁ። ሆኖም ካነጋገር ወይስ እኔ ግራ ከገባኝ ውስጣዊ የትግራዋይ ብሔረተኛነት ስሜት እየገፈተረው የሚለው ጥያቄ መልስ ላገኝ አልችልኩም። ላሁኑ ማለት የምችለው ንግግሮቹን ማረም እንዳለበት ግን እርግጠኛ ነኝ፡ ጥንቃቄ እና እርማት ማድረግ አለበት እላለሁ። ለዚህም ወደ ትችቴ ልግባ፦

ከዚያ በፊት አንድ ነገር ልበል።

መቀሌ ለቅቆ የወጣው አብይ አሕመድ በሽብርተኛ የከሰሰውን ወያኔ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ለትግራይ ሕዝብ አሸባሪ ስላልሆንክ ወድዶ የመረጠህ ነህ እና አንተ አስተዳድር ብሎ “ባንክ ፤ ስልክ፤ አይሮፕላን፤መብራት፤ማጓጓዣ፤ ከነደሞዛቸው “ለሕዝብ በሚል ማመካኛ ሽፋን” ይከፍትለታል። ቃሌን እመኑ።

አሁን ወደ ትችቱ እንግባ!

 ትናንት በርዕዮት ሚዲያ “የመቀሌ ሁኔታ እና የአብይ አሕመድ የቶክስ አቁምልኝ ልመና” በሚል ርዕስ በ6/28/2021 ያስተላለፈውን የርዕዮት ክፍለ ጊዜ አድምጫለሁ። በንግግሩ ውስጥ ያደመጥኳቸው ጥቂቶቹን ልጥቀስ እና ከዚያ ክርክሬን ልስጥ።

እንዲህ ይላል፡

“የተካሄደው ጦርነት በህወሓት እና በብልጽግና ነው የሚል ሰው ለኔ የተገደሉት ያልታጠቁት ህወሓት ናቸው፤ የተገደሉት ቀሳውስት “ህወሓት ናቸው” ፤ ያ በማለቱ “የትግራይ ሕዝብ ሁላ ማንኛውም ትግርኛ ተናጋሪ ሁሉ” “ህወሓት ነው” እያለ ነው፤ “ህወሓት በዚያ መልክ ድጋፍ አግኝቶ ከሆነ ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው አጋንንት ጥምረት ነው።ማለትም የበልጽግና (ኦሆዴድ) (ብአዴን) ፤የሻዕቢያ የነ ብርሃኑ ነጋ ጥምረት ነው የትግራይ ሕዝብ “ወያኔን እንዲደግፍ ያደረገው”። “ወደ በረሃ የገባው በእነዚህ ክፍሎች ምክንያት ነው” ብሏል (ቴድሮስ ፀጋየ ርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጅ)።  ስለዚህም ይላል ንግግሩን ይቀጥል እና “ለዚህ ነው አንድ “እፎይታ” “ፌርማታ ነው” የምልበት ምክንያት።” ይላል (ወያኔ መቀሌን መቆጣጠሩ እፎይታ ነው ይላል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋየ)።

ካሁን በፊት ደግሞ በራሱ ክፍለጊዜ አቶ የሱፍ ከተባለ ወዳጁ ጋር በርዕዮት ሚዲያ ሲናገር የላይኛውን አባባሉ በተጻራሪ ሲናገር አድምጡ፡

እንዲህ ይላል፦

“የአማራ ጥቃት የአማራ ብሔረተኛ (ጉዳይ) ብቻ ነው ብየ አልልም፤ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ጥቃት ነው ብየ ነው የማስበው። ማንኛውም ማሕበረሰብ የሕልውና አደጋ ሲገጥመው የሁሉም ማሕበረሰብ የሕልውና አደጋ ነውና የሁሉም ማሕበረስ ግዴታ ነው ብየ ነው የማስበው።……የተፈራረቀ የታጠቀ ሁሉ የአማራን ደም ሲያፈስ የኖረ ሁሉ ማንም ጤናማ ሰው ሊከራከር/ሊክደው አይችልም። የሕልውና አደጋ ያለበት ሕዝብ፤ አማራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልሞተበት ቦታ የለም፤ (ነገር ግን) እንዴት ግፍ መሮኛል፤ ከዚህ ግፍ መውጣት እፈልጋለሁ የሚል ሕዝብ እንዴት ይህንን ይፈጽማል? እንዴት ለሌላው አደጋ ሊሆን ይችላል?  ተከዜን እያሻገረ ይጥላል? ችግር አለብኝ የሚል ሕዝብ፤እንዴት የተገፋ ሕዝብ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ይጨቁናል፤ ወዘተ….” ይላል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ፤

መጀመሪያ ከላይ ያስቀመጥኩት ንግግሩ ግን ያለው፦

 ““የተካሄደው ጦርነት በህወሓት እና በብልጽግና ነው የሚል ሰው ለኔ የተገደሉት ያልታጠቁት ህወሓት ናቸው፤ የተገደሉት ቀሳውስት “ህወሓት ናቸው” ፤ ያ በማለቱ “የትግራይ ሕዝብ ሁላ ማንኛውም ትግርኛ ተናጋሪ ሁሉ” “ህወሓት ነው” እያለ ነው፤….” ሲል ጦርነቱ ታዲያ በማን እና በማን ነው የሚል ጥያቄ ብናቀርብለት ልክ እንደ ወዳጁ ኢትዮ-ሚዲያ ባለቤት አቶ አብርሃ በላይ እንዳለው ካሁን በፊትም እራሱ ቴድሮስ ጸጋዬም እንደተጋራው “ጦርነቱ በአማራ እና በትግራይ መካከል ነው” የሚል ነው። ከጻድቃን ወ/ተንሳኤ እስከ ወዘተ… ወዘተ ጀምሮ እምነታቸው እና ንግግራቸው የቴድሮስ እና የአብርሃ በላይ ነው። ሁለቱም የትግራይ ተዋለጆች እና ምሁራን ናቸው። ይህንን እምነታቸው ከወያኔወ መሪዎች በጋራ ይጋራሉ። በግልጽ ነግረውናል።

ስለሆነም ችግሩ በብልጽግና እና በህወሓት አይደለም ጦርነቱ በትግራይ ሕዝብ እና በነዚህ አጋንንት መካከል ነው የሚለው ክርክሩ ጉልህ አድርጌ ላስቀምጠለት። ለማለት የፈለገውም ያ ነው። ግን ጦርነቱ “ብልጽግና፤ ሻዕቢያ እና ብ.አ.ዴ.ን.” የትግራይ ሕዝብ ለማጥፋት የመጡ ናቸው የሚለው መስመሩ እንዳለ ቢያስቀምጥ እና ጦርነቱ ከወያኔ ጋር መሆኑንንስ ለምን አይገልጸውም? ጥፋት ተደርጓል? አዎ፡ ግን በሁለቱም በኩል ማን ጥፋት እንደፈጸመ ገለልተኛ አጣሪ ይቋቋም፤ ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ነው። ያም ቢሆን አሁን አስቸጋሪ የሚሆነው “ወያኔ ትግራይን መልሶ ይዞታል” ስለዚህ መረጃው ያጠፋዋል፤ አፉን ከፍቶ ጸረ ወያኔ የሚመሰክር ሰውም የለም። እነ አሉላ ሰለሞን ባሁኑ ሰዓት ባንዳዎች እየለቀማችሁ አጥፏቸው የሚል መልእክት ስያስተላልፍ ሰምተነዋል፡ አብይን አምኖ ወያኔን ሲቃወም የነበረ ፤ ትንሽ ንፋሽ ሲተንፍስ የነበረ ሁሉ ባሁንዋ ሰዓት ሰንት ሰው እንደታፈነ እና በቢላዋ ተቆራርጦ እንደተገደለ የኼኔ ቤቱ ይቁጠረው።

አንድ ነገር ማወቅ ያለብን መሪ ነኝ የሚለን ምስጡሩና አሰራሩ የማይታወቅ ከመለስ ዜናዊ የባሰ አደገኛ እባብ እና “ለምዕራባዊያን ተሸብራኪው” አብይ አሕመድ ከሕግ ውጭ ፆታዊ ጥቃት እና የመሳሰሉ ወንጀሎች ተሳትፈዋል የሚባሉ ወታደሮች “በከፊል” ለጾታ ጥቃት ተጠያቂ አድርጓል። ይህንን ሰምተናል በራሱ በመንግሥት ሚዲያ። በቂ ነው አይደለም? መከራከር ይቻላል። ግን ወያኔዎች በራሳቸው ዱርየ ፖሊሶቻቸው እና ዱርየ ተዋጊዎቻቸው የተፈጸመ ወንጀል እና ዘር ማጥፋት ግን ምርመራ አላደረገም። የህንን ጥያቄ እነ ጸጋዮ እና “የትግራይ ትዕወት” መፈክር አስተጋቢዎች እነ አብርሃ በላይ “ለምን” የሚለው ጥያቄአችን  ወያኔዎችን ይጠይቁ ይሆን?

ወንጀለኛ ድርጅት ነውና እስካሁንዋም ሆነ ለወደፊቱ ወያኔ አንደም ሰው እንኳ ተጠያቂ አላደረገም/አያደርግም። ለምን? እነ ቴድሮስ እና አብርሃ በላይ ትኩረታቸው “ትግራይ ትዕወት” ላይ ብቻ ነው ትኩረት ያደረጉት። ለዚያም ነው ቴድሮስ ጸጋየ በዛው በትናንቱ ክፍለ ጊዜ ንግግሩ “ለዚህ ነው መቀሌ ነፃ መውጣትዋ አንድ “እፎይታ” “ፌርማታ ነው” የምልበት ምክንያት።” ይላል (ወያኔ መቀሌን መቆጣጠሩ እፎይታ ነው ይላል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋየ)።

ወያኔ እኛ በምንጠራው ቋንቋ “አሸባሪው ወያኔ” ለትግራይ ሕዝብ እፎይታ የሰጠው ከሆነ ለኛ ኢትዮጵያዊያን ግን የማይለቅ አደገኛ “የኒኩልየር ንጥረ ነገር” ነው። ወያኔ መቀሌ ተሰጠው አልተሰጠው ጉዳዩ አደለም “ተፈጥሮው” ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዳትቀጥል ማፈራረስ ነው። አማራን ማጥፋት ነው! እርኩሱ አብይ አሕመድ “ከሲ አይ ኤ” ጋር ተመሳጥሮ “ጦር አስፈጅቶ” ሙሉውን ክ/ሃገር ለቀቀላቸው። ክላሽ ብቻ የታጠቀ አንደ ዓይጥ ሲሸሸግ የነበረ “የሽምቅ ተዋጊ” አሸንፏል ብየ አልቀበለውም። ምንም ጥርጥር የሌለው የአብይ እና የ ሲ አይ ኤ  እንዲሁም ኦነጋዊ ወታደራዊ አዛዦች ውስጠዊ ምስጢር እና ጣልቃ ገብነት እጅ አለበት። ናትናኤል አስመላሽ እኮ “ሲ አይ ኤ” መቀሌ ጽ/ቤት ከፍቶ አይቻለሁ ብሎ ነግሮናል። “ሲ አይ ኤም” ምን ሥራ አለው “የማንስ ዳቦ” ይጋግራል እዛ ቁጭ ብሎ?

እንግዲህ ጦርነቱ በማን እና በማን ነው የሚለው በቴድሮስ ጸጋየ እና በአብርሃ በላይ “ጦርነቱ በአማራ እና በትግሬ ሕዝብ መካካል መሆኑን” ነግረውናል። ስለዚህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተፈጸመ የሚባል ሁሉም ወንጀል በአማራ ሕዝብ መሆኑን በግልጽ ቴድሮስ እና አብርሃ በላይ ነግረውናል።

ስለዚህ የቴድሮስ ክብ ቀለቤቶች ሁለት ናቸው 1) የአማራ ሕዝብ 2) የአጋንንት ጥምረት የሚላቸው ሦስቱ ክፍሎች ናቸው። ቴድሮስ አምርሮ በየቀኑ ሲያነሳው የነበረው ወያኔ የሚለው ቃል ከምላሱ ከተወገደ 6 ወር ሆኖታል።

ይቀጥል እና  

የትግራይ ሕዝብ “ወያኔን እንዲደግፍ ያደረገው “…. የሻዕቢያ የነ ብርሃኑ ነጋ ጥምረት ነው የትግራይ ሕዝብ “ወያኔን እንዲደግፍ ያደረገው”። “ወደ በረሃ የገባው በእነዚህ ክፍሎች ምክንያት ነው” ይላል። በተዘዋዋሪ ምን ማለት ነው “እነዚህ ክፍሎች የጾታ አመጽ እና ግድያ፤ዝርፊያ ባይፈጽሙ ኖሮ የትግራይ ሕዝብ ወያኔ ወደ በረሃ ሲሸሽ አይከተላቸውም ነበር የሚል ሞኝ ክርክር እያቀረበ ይመስለኛል።

በሌላው ሦስተኛ ክፍል ይህንን በሚመለከት ስለምመለስበት ላሁኑ እስኪ ቴድሮስ ጸጋዬ መቀሌ በወየኔዎች እጅ በመውደቋ ደስታውን ለመግለጽ መቀሌ ውስጥ በትምክሕት ሲጨፈር የነበረውን የተለመደው የመቀሌ የእንደርታዎቹ የዘፈን ጭፈራ ንግግር በቪዲዮ ለአድማጮቹ ያሰማውን ላሰማችሁ፡

ብዙዎቻችሁ ሄዳችሁ ስታደምጡት በደስታ የቀለጠው ትምክሕታዊ የደስታ ጭፈራ እንዲህ ይላል፦

“ናዓና ዝመስል የለን” (እኛን የሚመስል ተወዳዳሪ የለም) ፤ “ትግራዋይ ዝመስል ባዓል ስረ የለን” (ትግሬን የሚያክል ባለ ሱሪ ወንድ የለም) ፤ “ሃ! ሁ! ምስ ወየነ እየ ዝዓበኹ) ፤ ሃ! ሁ! ከወያኔ ጉያ ነው ያደጉት!) “ሃ! ሁ~ ወያነ እንዳበልኩ እየ ዝዐበኹ” (ወያኔ እያልኩ ነው ያደግኩት) …መቐለ ፤መቐለ!!! (መቀሌ! መቀሌ!) “ናይና! ናይና ናይና!!” (የኛ ነች የኛ!!) “ኣየኹም ናይና!!” (የኛዎቹ ኣይዝዋችሁ!!)

ይህ ኣየኹም ናይና “ወገናዊ መፈከር” ካሁን በፊት እኔው “የመቀሌ ሕዝብ የመገንጠል አባዜ
 በሚል (Ethiopian Semay) 2/13/2021) የጻፍኩትን ዛሬ ደግመውታል። ያህንን በሚመለከት ‘’የትግራይ ሕዝብ ወያኔ ወደ በረሃ ሲሸሽ ወጣቱ ለምን ተከተለው?’’ ራሱ በቻለ ርዕስ ሰሞኑን እምለስበታለሁ።

ቴድሮሰ ጸጋየም ይሁን የለየላቸው የወያኔ “ፓፒ” ምሁራን እንደሚሉት የክርቢቱ ማቀጣጠያ ምክንያት በሕዝቡ ላይ የተለያዩ ወንጅሎች የተፈጸመበት ጉዳይ እንዳለ ሆኖ “ወንዙን የሚያናግረው ከውስጡ ያለው ድንጋይም” በቀላሉ የሚገፈተር ጉዳይ አይደለም። 

እንደ ቴድሮስ ጸጋዬ “ትናንት እንዳለው “ሕዝብ መተች የለበትም ሳይሆን ሕዝብ ወኪል (አጄንሲ የለውም) ብየ ስለማምን ነው።” ያለውን በኔ በከል አልቀበለውም። የትግራይ ሕዝብ ወኪል አለው። ሌላው ማለትም “እየተከሰሰ ያለው የአማራ ሕዝብ ግን ወኪል የለውም። ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ ስለ አማራ የምናገረው።

በክፍል 4 የትግራይ ሕዝብ ለምን የወያኔ ፍቅር አልለቅ አለው? ይቀጥላል……….. ሼር አድርጉት ሕዝቡ ይነጋገርበት!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


አብይ አሕመድ መጨረሻው ላይ ሕዝብ አስጨርሶ ሸብረክ ይላል ብያችሁ ነበር፤ ይኼው እንታረቅ አለ!

 

አብይ አሕመድ መጨረሻው ላይ ሕዝብ አስጨርሶ ሸብረክ ይላል ብያችሁ ነበር፤ ይኼው እንታረቅ አለ!

ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)

6/18/2021

ዛሬ ሁለት የተለያዩ ዜናዎችን ተመለከትኩ።  አንደኛው አንዲህ ይላል። መቀሌ ነፃ ወጣች እንኳን ደስ ያለን!” የሚል “Cyber Power of Tigray” በሚባል ውጭ አገር የሚገኝ የዩቱብ ሚዲያ ውስጥ ውጭ አገር የሚኖሩ የወያኔን የሚከተሉ “ፓፒዎች” መቀሌ ነጻ ወጣች እያሉ ዕልለታቸውን እያቀለጡት አረፋ ሲያደፍቁ ሰማሁኝ (ትምክሕታቸውን ብትሰሙ አብየት፤ ዕድለኞች ናችሁ እንካን ትግርኛ አላወቃችሁ! ትበሳጩም ትስቁም ነበር!)። ሌለው የትግራይ መንግሥት መግለጫ (“መግለፂ መንግስቲ ትግራይ“) የሚል ወያኔ ያስተላለፈው በ 06-28-2021 መቀሌ ነፃ መውጣትዋን የአዋጅ መግለጫ አወጣ። አዲስ አባባ የሚገኘው የአብይ አሕመድ አገልጋይ የሆነው “ኢ ቢ ሲ” የተባለው የመንግሥት ሚዲያ ደግሞ አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኣፍ ቢ ሲ/  -ፋና) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።” የሚል ዜና አስደመጠን።

የሚገርም ነው!

ጦርነቱ በወያኔ ተገባደደ ማለት ባይሆንም፤ ይህ ሁሉ የተለያዩ ውሸቶች እየነዛ “ሽብርተኛ ጋር መደራደር አይታሰብም” ሲል የቆየ መንግሥት በራሱ ቴ/ቪዥን ሸብረክ ብሎ የቶክስ ስምምነት እናድርግ ብሎ ሲያውጅ፤ መስማት ከሓፍረትም ሓፈርተኛ መንግሥት ነው። የወያኔ ፋሺሰቶችና የኦሮሙማ ፋሺሰቶች በሚያደርጉት ጦርነት ሁለቱም ያጋጫቸው አገር በመጠበቅ ሳይሆን፤ “ሥልጣን” ሽምያ እንደሆነ የምናውቀው ሃቅ ነው። አሁንም ሥልጣን ለመጋራት ከተስማሙ ሽበረክ ማለታቸው የግድ ነው። በተለይ አብይ አሕመድ አቋመ ቢስ ስለሆነ “ዕርቅ እያለ ‘ሸብረክ” ማለቱ አይቀሬ ነው ብየ በዚህ ፌስ ቡክ ላይ ጽፌ አለሁ። ይኼው ችሎታ ቢሱ ማፈሪያ “መንግሥት” ተብየው “የቶከስ አቁም ስምምነት ጠየቀ። በማን ሰም ነው የቶክስ አቁም ስምምነት እናድርግ እያለ ያለው? በትግራይ ገበሬ በከርምት እርሻ ሥራ ስም። ይህ ግን ግልጽነት የሌላው ውሸት ነው። ተሸንፎ ከሆነም ተሸንፌአለሁ ማለት እንጂ ዝባዝንኬ አያስፈልግም። ያውም ወዳጄ አምሳሉ ገብረኪዳን እማ ከኔው አስተያየት በዘለቀ የሚለው “ሁለቱም ሕዝብን ለማስጨረስ አማራውን ለማጃጃል እንጂ የምር ጦርነት አልነበረም፤ስለዚህ ውሎ አድሮ ይታረቃሉ፤ ጥላቻም አልነበራቸውም” ይላል። ይህ አስተያየት አሁን አሁን ስንመለከት “አሌ’ ማለት አንችልም። 

በዚህ መሃል ተጠቂ የሆነው፤ ለጭለማ ህይወትና ስደት የተዳረገው ሕዝብ ተጠያቂዎቹ ‘የትግሬ ምሁራን’ በዘረጉት ትምክህት የማሕበረሰብን አንድነትና የተረጋጋ ህይወት የሚያደፈርስፋሺስታዊ ማኒፌስቶበመቀበላቸው ሰበብ እንደሆነ ግልጽ ነው።  የነገድ ፖለቲካ አስተማሪዎቻቸውን ወያኔዎች በማምለካቸውለሕዝቡ የችግር ሰበብ ሆነውታል። እነሆ ዛሬ መራራው አማራጭ ከፊታቸው ተደቅኗል። መቀሌ ነጻ ወጥታ ትግራይ ነፃ አገር ሆና ሕዝቡ በሰላም በደስታ ይኖራል ብሎ የሚለው ከሞኝነትና የደንቆሮ አመለካከት ካልሆነ በተግባር የማይሆን ቅዠት ስለሆነ የሚሳካ አይሆንም።

የሕዝቡ መከራ ሊረዝም የሚችልበት ምክንያት ግን አርግጠኛ ሆኜ የምላችሁ “እንደምታውቁት ልክ እንደ ኦሮሞ ማሕበረሰብ 95% በሚያስብል ግምት ኦነግን እንደተከተለ ሁሉ በተመሳሳይነት ቁጥር ትግሬዎችም እንዲሁ 1928 . ጣሊያኖች ለኢትዮጵያዊያን ትተውልን የሄዱት የቀየሱትን የፋሺዝም ርዕዮትየአንጎል አጠባተጠቂዎች ናቸው። የትግራይን ሕዝብ ከኢትጵያዊነት ስነ ልቦና ለማላቀቅ ረዢም ጊዜ ተወስዶ በርካታ የአእምሮ ማጠቢያ ቴክኒኮችን (ዘፈኖችን፤ተውኔቶችን፤መጽሐፍቶችን፤ንግግሮችን….ወዘተ) ተካሂደዋል። አሁን ደግሞ በዚህ ጦርነት እውነታን እና ውሸትን ተጨማምሮበት የሕዝቡን ልቦና ይበልጥ ወደ ፋሺሰቶቹ ርዕዮት በመደገፍ ከወያኔ ጋር ቆሟል።

ትግራይ ውስጥ በተቃዋሚነት የቆሙ ብዙዎቹ “የወያኔ የውስጥ አርበኞች ናቸው”” ትግራይ እንዲያስተዳድር የተላከው የቶክስ አቁም ስምምነት ይደረግ ብሎ አለ፤ የሚባልለም ያው ዶ/ር አብርሃም በላይ የተባለውም ሳይቀር ደደቢት በረሃ ውስጥ ወያኔ የመሰረተው የየካቲቱ 11/1967 . የኢትዮጵያን የባሕር ወደቦችን ለጠላት ለመስጠት እና ፋሺዝም ለማንገስ ፤ አማራን ለመጨፍጨፍ የተመሰረተው የትግል ቀንና ወር መከበር አለበት ብሎ ባፈው የካቲት መቀሌ ውስጥ የሰማእታት ክብር ሲያከብር ውሏል። እርሱም ድሮ ወያኔ መኖሩን እናውቃለን፤ አሁንም የውስጥ አርበኛ  ወያኔ አለመሆኑ ማስረጃ የለንም። ጸረ አማራው አደገኛው አብርሃም ገበርመድህን የተባለው ዓድዋዊው ዘረኛ “ዘፋኝም” (ብዙ ከብት ኢትዮጵያዊ አብራሃም አብርሃም እያለ በየ እስፖርት ሜዳ ለይ የእሱን መናኛ ዘፈን ሲጨፍር የሚውልለት ሞልቷል) ከወያኔዎች ጋር አድብቶ መቀሌ ከተማ እና በራሃ ውስጥ እየተመላለሰ ሲደበቅ ወራት አሳልፎ ከተደበቀበት ተገኝቶ እጁን ሲሰጥ ዶ/ር አብርሃም ተብየው መቀሌ ውስጥ “አንድ ቀን አስሮ ለቀቀው” ይኸየው ዛሬ እርቅ ምናምን እያለ አብይ ያዘዘውን ዕርቅ  ዶ/ር አብርሃም የተባለው የትግራይ ጊዜዊ አስተዳዳሪ ነው አሁን የቶክስ ስምምነት እናድርግ እያለ ያለው።  ለዚያ መስዋዕት የሆኑትን እና ለነመለስ ዜናዊ ጭምር የቆመው የመቀሌው ሃውልትም በክብር መያዝ አለበት እያሉየወያኔ ፖለቲካ ተቃዋሚ ነንእያሉ ነገር ግን የወያኔንአርቲፋክት” (ቅርስ/አሻራ) የሚያከብሩ የፋሺዝም አሽቃባጮች በብዛት አብይ አስተዳደር ውስጥ አሉ የምንለው ለዚህ ነው።

አብይ እነ ዓረና ፤ባይቶና ወዘተ….የተባሉ የትግሬ ተቃዋሚ ተብየ ወያኔዎች  አዲስ አባባ ቁጭ ብለው በየሚዲያው ስለ ወያኔ ጉብዝና ሲያወሩ አብይ አሕመድም የጸጥታውም ምንም አይላቸወም። አብይ የሚጎብዘው ጠምነጃ የሌለው በብዕር የሚታገለውን እስክንድር ነጋ ላይ ነው። አምሳሉ ገብረኪዳን የሚለውም ይህ ነው። አብይ ከወያኔ ጋር ድብቅ ነገር ከሌለው እንዴት እነዚህን መርዘኞች አዲስ አባባ እየኖሩ በየሚዲያው መርዝ ሲረጩ ዝም አላቸው?

የም ሆነ ይህ የትግራይ ሕዝብ ዛሬም ከዚህ ወያኔ ከተባለው ድረጅት እራሱን ካላላቀቀ በተደጋጋሚ እንደምታውቁት የትግራይ ምሁራን ራሳቸውን ለፋሺዝም አምልኮ ስለሸጡ፤ የሕዝቡን መከራ በዚህም በዚያም አባብሰውታል፤ ችግሩም ቀጣይ ነው።  አሁን መቀሌ ነፃ ወጣች “ቱማታ፤ዕልልታ” የወያኔ ፋሺቶች እያስጮሁት ያለው አጉል ጉራ ተመሳሳይነቱለብ/ሞቅ ባለው/ ድሰት የተጣደቺዋን የእንቁራሪቷ ታሪክ የተሰማት ደስታ እና መጨረሻ ውሃው ቀስ እያለ እየፈላ እንዴት ጠብሶ እንዳቃጠላት ሁሉ፤ የትግራይ ሕዝብም ሆነ ወጣት በወያነ ምሁራን የተሳሳተ ርዕዮት በጭፈራ ጦዞ የትዕቢት ሐረጎችን ያዘሉ ዘፈኖችን እያመነዠከ ቀስ እያለ በቀበኞቹ ተንኮል እራሱን ማቃጠሉ አይቀሬ ነው።

በዚህ አጋጣሚ “የኢትዮ ሚዲያ “የትግራይ ትዕወት” (ትግራይ ታሸንፋለች) ፈካሪዎች እነ “አብርሃ በላይም” እንደተመኛችሁት መቀሌ ነፃ ወጥታለችሗለች፤ አብይ አሕመድም ሸብርክ ብሎላችሗል እና እንከን ደስ አላችሁ እላለሁ!! ነፃ አገራችሁ አሸንፋችሗል እና ነጻ አገራችሁን ይኸየው “በትግራይ ትዕወት” መሰረት ተረከቡዋት “በብሩር የወርቅ ሳሕን” እነሆ አብይ አሕመድና ቡቹሎቹ ሰጥቶአችሓል! አንኳን ደስ አላችሁ!

የሚያሳዝነኝ የሚስኪኑ የአማራው ጦር ደም መቀለጃ መሆኑን! ልቤ ውስጥ ብትገቡ ጭሱ ያፍናችሗል፡ ልቤ እንዴት አየጨሰ ያለ መሰላችሁ!?

አስገራሚ አገር!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ