Wednesday, February 6, 2019

የችግሩ ፈጣሪዎች የመፍትሔው አካል መሆን እንዴት ይችላሉ? በነዚህ ሰዎችስ ዕውነተኛ የአገሪቱ ችግሮች መፍትሔ ያገኛል ወይ? Ethio Semay

ከኢትዮ ሰማይ ዝግጅት ክፍል ማስታወሻ፦
ለአብይ አህመድ ተከታዮች፦
መሪያችሁ የአብይ አህመድ፤ የኦነግ እና የወያኔ ጥምር ሴራ ዛሬ “እነ ሌንጮን እና እነ ነጋሶ ጊዳዳን የመሳሰሉ የሰሩትን ወንጀል ሰይጠየቁበት” በድጋሚ ሌላ ሴራ ለመስራት ተፈቅዶላቸዋል። ቀደም ብየ ከሦት አራት አመታት በፊት በግልጽ እንደጻፍኩት “የኦሮሞ ፋሺታዊ ስርወ-መንግሥት ሦሰተኛውን የመሬት እና የሥልጣን ሽሚያቸው ይፋ ለማድርግ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀውታል” በማለት ስለ ኦሮሞና ትግሬዎች ጥምር ፋሺስታዊ ስርወ-መንግስት ሰፊ ሐተታ ደጋግሜ መጻፌ ይታወሳል። ዛሬም ኦሮሞዎች ከትግሬ ፋሺሰቶች ጋር በጣምራ ያቀዱት ‘የመሬትና የሥልጣን ወረራ’ ፤ ኦሮሞዎች በይዞታቸው ስር ያደረጉትን የመላ የኢትዮጵያ ዜጎች 3/4ኛውን የመሬት ወረራቸውን ለማስጠበቅ በአብይ እና በለማ አማራር ለማስጠበቅ በርትተው እየሰሩ ነው። ከአራት አመት በፊት (ከዚያም ከ10 አመት በፊት) የተነበይኩትን “ኦሮሞዊ አጀንዳቸው” እውን ለማድረግ እንዲመቻቸው የናንተንም  የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁን መንግዱን ለመቀየስ ከላይ የተጠቀሱ ሰዎች በናንተ ስም “የአብይ አህመድ እርካብ” ፈቅዶላቸዋል።
 እጃቸው በሰው ልጆች ደም የተጨማለቁ ሰዎች እና አልፈውም የትግሬዎች የፋሺሰት አፓርታይድ ሥርዓትን በፕረዚዳንትት ያገለገሉ ሐፈት ምን እንደሆነ የማይሰማቸው ማፈሪያዎች ዛሬም በድጋሜ ወደ መድረክ ብቅ ብለው በሕዝብ እርካብ ላይ ተንጠላጥለው ማየት እጅግ ያማል። ለማንኛውም ከታች የቀረበው ሰነድ አንብቡና የኦሮሞዊው አብይ አህመድ “ኢትዮጵያዊነት ዲስኩር” ጣፋጭነት ስካራችሁ ሲለቃችሁ ይህንን ሰነድ አንብቡ።

ኢትዮ- ሰማይ

                                                                                      
ጥር 28 ቀን 2011 ዓም
የችግሩ ፈጣሪዎች የመፍትሔው አካል መሆን  እንዴት ይችላሉ? በነዚህ ሰዎችስ ዕውነተኛ የአገሪቱ ችግሮች መፍትሔ ያገኛል ወይ?
      ይድረስ ለዐማራ ሕዝብ፣
      ይድረስ በዐማራ ስም ለተደራጃችሁ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅቶች፣
      ይድረስ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣
      ይድረስ ለዶር ዐቢይ አሕመድ ``የኢፌዴሪ`` ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢሕአዴግ ሊቀመንበር፣
ጉዳዩ፦ የማንነትና የወሰን ጉዳዮችን እንዲያጠና የተቋቋመውን ኮሚሽን አባላት ማንነት ይመለከታል
 የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት፣የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅትና የኤርትራ ነፃ አውጭ ድርጅት የአገሪቱን ማዕከላዊ መንግሥት እና የአንድነት ኃይሉን እንዴት በታትነው፣ የጋራ ጠላታችን ነው  ያሉትን ዐማራ ከተቻላቸው ለማጥፋት፣ ካልሆነም ለማዳከም የሚያስችል የጋራ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል። ይህ ስምምነታቸውም`` የተሰኔ ማንፌስቶ`` በመባል ይታወቃል። በዚህ ስምነት መሠረት ባካሄዱት የእርዳ ተራዳ የጥፋት ዘመቻ፣ ማዕከላዊ መንግሥትን አዳክመው ፣የአንድነት ኃይሉን በታትነው በ1983 ላይ ሻዕቢያ አሥመራን፣ ወያኔና አጋሮቹ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ የሆኑት ቡድኖች አዲስ አበባን መቆጣጠራቸው ግልጽ ነው።
እነዚህ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ የሆኑ ቡድኖች ለጥፋት ዘመናቸው መራዘም  የሚበጅ የሽግግር መንግሥት  የሚያዋቅርና መንግሥቱ የሚመራበት ቻርተር  የሚያጸድቅ፣ አብዛኛዎቹ በዚህ የማንነትና የወሰን ኮሚሽን በተባለው የተካተቱበት ሰዎች የተካፈሉበት ጉባዔ ሰኔ 24 ቀን 1983 በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ  ተሰየመ። ይህ ጉባዔ በመለስ ዜናዊ ተመርቶ፣ ቀደም ሲል በሦስቱ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ ቡድኖች የተስማሙበትን የተሰኔው ማንፌስቶ የተባለውን ለሥልጣን አወጣጥ፣ አጠባበቅና አያያዝ  እንዲሁም ኢትዮጵያንኢትዮጵያ ያሰኙት የወል ዕሴቶች ደረጃ በደረጃ ሊያከስም  በሚችል መልኩ በሕወሓት ተቃኝቶ የቀረበውን ሰነድ አንድም ማሻሻያ ሳይደረግበት የኢትዮጵያ ሕዝብ መገዣ እንዲሆን አጽቆ መነሳቱ አይዘነጋም። ይህን አገር ከፋፋይ፣ ፀረ-ዐማራና ኢትዮጵያ የሆነ ሰነድ ያዘጋጀው አቶ ሌንጮ ለታ መሆኑም ይታወቃል። ራሱ ሳያፍር በአደባባይ ያዘጋጀው እንደሆነ ነግሮናል።
የሽግግር ቻርተር የተባለው መገዣ፣ መረገጫና የዐማራና የኢትዮጵያ መጥፊያ መሣሪያ፣ ዳብሮ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊት ረፐብሊክ ሕገመንግሥት ሆኖ እስካሁን በማገልገል ላይ እንዳለ ከማንም የተሰወረ አይደለም። በሕወሓት ሁለተናዊ አመራር፣ በኦነግ ያልተቆጠብ የባለድርሻነት  ሁሉ አቀፍ ትብብር የተዘጋጁት የሽግግር ቻርተርና ሕገመንግሥት ተብየዎች፣ ይህም በሕዝቡ ላይ ባስከተለው የማንነት ረገጣ፣ የመሬት ነጠቃ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች፣ የተፈጸሙ ኢሰባዊ ድርጊቶች፣ በአገሪቱና በሕዝቡ ኢኮኖሚ ላይ የተካሄደው ድርጅታዊ ምዝበራ፣ የፓርሪና የመንግሥት ፍፁም ውኅደት የወለደው ሌብነት ያስነሳው የቄሮ፣ የፋኖ እና የዘርማ እንዲሁም በውስጥና በውጭ የተጋጋመው የለውጥ ማዕበል፣ ከኢሕአዴግ ማዕቀፍ ውስጥ ዶር ዐቢይ አሕመድና ቡድናቸው ወደ አገሪቱ ፖለቲካ ቁንጮ እንዲዘልቁ  እንዳስቻላቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
ዶ/ር ዐቢይና ቡድናቸው የኢሕአዴግ አባላትና አመራር ሰጭዎች በመሆን በአገሪቱ እና በሕዝቡ ላይ ለተፈጸመው ግፍና በደል ከሚጠየቁት  መካከ  እንደሆኑ በማመን፣ ሕዝቡ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው በይፋ በመጠየቅ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ሆን ተብሎ እንዲጠፉ የተደረጉትን የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ዕሴችን በማንሳት ፣አንድነት፣ ሃይማኖት፣ ዕኩልነት፣ መቻቻል፤ ይቅርታ፣ አብሮነት፣ ወዘተ የተባሉትን በመደመር ``ፍልስፍናቸው`` ሕዝቡ የሚሻውንና መሆን የሚፈልገውን በመናገሩ፣ የታሰሩትን በመፍታታቸው፣ የተሰደዱትን በመመለሳቸው፣ የመናገርና የመደራጀት ነፃነትን በመፍቀዳቸው፣ ለሀሳብ ልዕልና በመቆማቸው፣ የተበደለው ሕዝብ፣ ``እንባ ጠራጊ አገኘን``፣ ``ተነፈስን``፣ ``አንድ ሊያደርገን ነው``፣ ``ከፈርኦን ቤት ያደገ ሙሴ ነው``፣`` ከአምላክ የተሰጠን ፀጋ ነው`` በማለት ምላተ ሕዝቡና ተቃዋሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሞገሥና ክብርን እንዲያገኙ ከማድረጉም በላይ፣ ሁሉም መሪያችን ነው ብሎ መቀበሉን በቃል፣ በጽሑፍ እና በሰላማዊ ሰልፍ አረጋግጧል። ይህ ለዶር ዐቢይ እና ለቡድኑ ከሕዝብ የተሰጠ በረከት ከጊዜአዊነት ወደ ዘላቂነት እንዲሸጋገር፣ አመራሩ ከሀሳብ አፈላለቅ እስከ አፈጻጸም ድረስ የሕዝቡን ቀጥተኛ እና ኢቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ተገቢ ብቻ ሳይሆን፣ የዲሞክራሲ ዋልታ ነው። ይህ ካልሆን ዶ/ር ዐቢይ `` እርካብና መንበር`` በሚለው መጽሐፋቸው፣ ``ሕዝብን ፍላጎቱን ተከትልህ ገደል ልትከተው ትችላለህ፤ አያ በሬ ሆይ፣ ሳሩና አየህን ገደሉን ሳታይ`` ሲሉ ያስፈሩት ሀሳብ፣ በዚህ የማንነትና የወሰን ኮሚሽን አባላት አመራረጥ ላይ በግልጽ የወጣ ይመስላል።
ማንም እንደሚገነዘበው፣የኢትዮጵያ ችግር የብሔረሰብም ሆነ የመደብ ጭቆና አይደለም። የአገሪቱ ችግር የመልካም አስተዳደር ችግር ነው። የአገሪቱና የሕዝቡ ተከታታይነት  የሌለው፣ የወል ዕሴቶች፣  ኢኮኖሚ፣ አስተዳደር፣ የአገዛዝ ፍልስፍና፣ የሕዝብ አደረጃጀት ወዘተ ነው። የዛሬው የኢትዮጵያ ችግር ቋጠሮም የመነጨው፣ ከተከታታይነት የወጣው የመንግሥት አደረጃጀትና በቋንቋላይ የተመሠረተው ፌደራላዊ አወቃቀር፣ አብሮነትን፣ አንድነትንና ኢትዮጵያዊ ማንነትን  በአውራ ጠላትነት ፈርጆ የተራመደው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የዓለም አመለካከት፣ ያስከተለው የማንነት ጥያቄና የመሬት ቅርምት መሆኑ ግልጽ ነው። የዚህ ሁሉ ምንጭ ደግሞ ሕገመንግሥቱ ነው።

ችግሩ ሕዝባዊ ማዕበልን አስነስቶ ለውጥን ወልዷል። ለውጡን  የሚመሩትን ደግሞ ሕዝቡ ከልቡ ወዷል። ተቀብሏል። ይህ ዕውነት ነው። ይህን ዕውነት ሥር እንዳይሰድ፣ ቅርጫፍ እንዳያወጣ፤ ግንዱ እንዳይደነድን የሚያደርጉ የራሱ የለውጡ ተፈጥሮአዊ ባሕሪይ ከፖለቲካውና ኢኮኖሚው የበላይነት ያሳጣቸውና ጥቅማቸውን የሚነካባቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ከሚፈጥሩት መሰናክል ውጪ፣ በራሱ በለውጥ አመራር ውስጥ ፣ለውጥ አደናቃፊ የሆኑ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ጥብቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠይቃል።

ለዚህ አባባል መነሻ የሆነን፣ ለማንነትና ወሰን ኮሚሽ አባልነት የተመረጡት ሰዎች የአመራረጥ ሁኔታ  ሕዝቡ እንዲያውቅ አልተደረገም። የተመረጡበት መመዘኛ ምን እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም። የሰዎቹ ያለፈ የፖለቲካ ታሪክ በበጎም ሆነ  መጥፎው ተመዝኖ ለዚህ ተግባር ብቁ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ የለም። በሕዝቡ ዘንድ ያላቸው ታማኒነትና ቅቡልነት እስከምን እንደሆነ አይታወቅም። እንዳውም አብዛኞቹ የችግሩ ፈጣሪዎች እንደሆኑ ሕዝቡ ያውቃል። እነርሱም አይክዱ። ሕዝቡ ዛሬ መሆን የሚሻውን ትክክለኛ የአንድነትና የአብሮነት ስሜት ዕውን እንዲሆን የማድረግ ቁርጠኝነታቸው እስከምን ሊሆን እንደሚችል ማረጋገጫ የለም። በተቃራኒው ሕዝቡ፣ በተለይም የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት ዐማራ ``በጡት ቆራጭነት፣ በትምክህተኝነት፣ በመጤነት፣ በአድኃሪነትና በዝባዥነት`` ፈርጀው ዕልቂት የፈጸሙበትና ያስፈጽሙበትን ግለሰቦች በዚህ ኮሚሽን ውስጥ መካተት``ትናንት ጦምክን ያደርክ ዛሬም ድገም ብለውሃል`` ዓይነት እንደሚሆንበት መጠራጠር አይቻልም።  በማንነታቸው ከፍተኛ በደል የተፈጸመባቸው የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ሠቲት፣ ራያ፣ ደራ; መተከልና መሰል አውራጃና ወረዳዎች ሕዝብ ዕውነተኛ ጥያቄ ተገቢ መልስ ለማስገኘት ከሆነ የኮሚሽኑ መቋቋም ፋይዳ፣አረጋዊ በርሄ፣ ሌንጮ ለታ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሙላቱ ተሾመ፣ገብሩ ታረቀኝ፣ዘገየ አስፋው ቦታቸው ወይም አገልግሎታቸው ጠቃሚ የሚሆነው በዚህ ኮሚሽን ውስጥ ነው ብለን አናምንም። ለፍርድ ይቅረቡ እንኳን ባንል፣ ሊፈርዱብን ግን አይገባም። ችግሩን የፈጠሩት ሰዎች ለችግሩ መፍትሔ ያመጣሉ ብለንም አናምንም! ከእነዚህ ሰዎች አዕምሮ፣ በዐማራው ላይ የዘር ዕልቂት እንዲፈጸም ሀሳብ ያፈለቁ፣ ያቀዱ፣ የመሩና ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች አመራር አባሎች፣ የሕዝቡን ቁስል የሚያጠግግ የመፍትሔ ሀሳብ ያመነጫሉ ብሎ ይቀበላቸዋል ማለት ``ሸንበቆ ያፈራል፣ ገለባ ያብባል`` ከማለት የተለየ አይሆንም፣

በሌላ በኩል የአገሪቱ ፖለቲካ የሚያጠነጥለው በማንነት እና በነገዶች ዙሪያ ነው። ይህ ባለበት ሁኔታ የማንነትና የወሰን አጥኝ ኮሚሽን አባላት መመረጥ ወይም መሰየም የነበረባቸው፦

 አንደኛ፦ አጣሪ ኮሚቴ ተሰይሞ በሕዝባችን በአብዛኛው በመልካም ሥነ-ምግባራቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በችሎታቸው፣ከፖለቲካ ገለልተኛነታቸው፣የሚታወቁ ምሑራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የአገር ሽማግሌዎች መካከል በዕጩ ተወዳዳሪነት ቀርበው ምርጫው በግልጽ ወይም በሚስጢር በተወካዮች ምክር ቤት ቢመረጡ:

ሁለተኛ፦ አጠቃላይ የኮሚሽኑ አባላት ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች ዘርዝሮ፣በአገሪቱ የጎሣ/ቋንቋ አስተዳደር ያሉት ምክር ቤቶች በወከሉት ሕዝብ መጠን ተሰልቶ ዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች መርጠው ቢያሳቁና ምክር ቤቱ ተወያይቶ ቢያጸድቀው፣

ሦስተኛ፦በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የፖቲካ፣ የሃይማኖት፣ የሲቪክና መሰል ድርጅቶች ለኮሚሽኑ ይጠቅማሉ ያሏቸውን አባሎች ለምክር ቤቱ አቅርበው ምክር ቤቱ ተወያይቶ ቢያጸድቃቸው የተሻለ ታማኒነት ከማትረፉም በላይ፣ ዘለቄታን ያሳይ ነበር። የዲሞክራሲ አንዱ መርሕ የሆነውንም የተሳትፎ ሁኔታ በተጨባጫ ማሳየት ያስችል ነበር።

በሌላ በኩል የማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች እንደሚሉት ከሆነ ከኮሚሽኑ አባላት ውስጥ 20ው ኦሮሞች፣13 ትግሬዎች እንደሆኑና የቀሩት ከሌሎች ነገዶች እንደሆኑ ያስረዳሉ። ይህ ከሆነ የኮሚሽኑ የጥናት ውጤት የኦነግ  እና የሕወሓት ፍላጎት የበላይነቱን ይዞ እንደሚወጣ መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። ምክንያቱም  የችግሩን ጉድጓድ አጥልቀው የቆፈሩት ሁለቱ ድርጅቶች በመሆናቸው ለዘመናት የታገሉለት የማንነት ፖለቲካ እና የቋንቋ  ፌደራሊዝም በሌላ እንዲተካ ይሻሉ ለማለት አይቻልም። ይህም ግልጽ አቋማቸው፣ ዶር መረራ ጉዲና፣ ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ ዶር አረጋዊ በርሄ እና ዶር ዐቢይ አሕመድ `` ውይይት ስለኢትዮጵያ`` (Dialogue on Ethiopia) በሚል ርዕስ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ላንድ ቀን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቭል እና መሠል ድርጅቶች አመራሮች ጋር ባቀረቡት ጥናት ባብዛኛው አካዳሚካዊ ቢሆንም፣ ሕገመንግሥቱና የመንግሥቱ አደረጃጀት ችግር የለበትም፣ ችግሩ አመራሩ ዲሞክራሲያዊ አለመሆኑ ነው በማለት አቋማቸውን ገልጸዋል። ይህ ስብሰባ በተካሄደ ማግሥት የማንነትና የደንበር ኮሚሽ አባላት ይፋ መሆንና ፣ ኮሚሽኑ ለግባት የሚሆነው መረጃ ቀድሞ እየተሰጠውና የጥናቱ ውጤት ምን መሆን እንዳለበት ማመላከቻ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።
      በጥቅሉ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት፣ሠቲትና ራያ ወደ ትግራይ እንዲጠቃለል ካርታ የሠራው ፣ሕወሓትን ከመሠረቱት አንዱ የሆነውና ለረጅም ጊዜ የመራው  ዶር አረጋዊ በርሄ፣
      የሽግግር መንግሥቱን ቻርተር ካፀደቁት፣ ሕገመንግሥቱን ካረቀቁትና ካጸደቁት ፣በኋላም ፕሬዚዳንት ሆነው ተግባራዊ ያደረጉት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣
      የሽግግር መንግሥቱን ቻርተር ያዘጋጀና ያጸደቀ፣ በሕገመንግሥቱ ዝግጅትና ጽድቀት ወሳኝ ሚና የተጫዎተው  አቶ ሌንጮ ለታ፤
      ፀረ-ዐማራ የሆኑት  አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዶር መራራ ጉዲና፣ አቶ ዘገየ አስፋው፣ ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ
      የአገሪቱ ፕሬዚንዳንት ሆነው ለሕገመንግሥቱ ተፈጻሚነት ብዙ የደከሙት ዶር  ሙላቱ ተሾመ በዚህ የማንነትና የወሰን ኮሚሽን አባልነት መካተት፣ በዐማራው የኅልውና ጥያቄ ላይ፣ በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ሰቲት፤ ደራ:  መተከል እና ራያ ሕዝብ የማንነት  ጥያቄ ላይ ተገቢ መልስ እንዳይገኝ ከወዲሁ ሠፊ እና ጥልቅ መሰናክል የተዘጋጀ መሆኑን አመላካች ነው። ይህም አገራችን እና ሕዝባችን ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበት የለውጥ ሂደት እንዳለፉት የለውጥ ጅማሮች ወደ ማይፈለግ አቅጣጫ ሊያመራ እንደሚችል መጠራጠር አይቻልም።
ስለሆነም፣ ትግሉ ሰላማዊና ሕዝባዊ እንዲሆን በማድረግ፣ የዐማራ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክና የሙያ ማኅበራት፣ ወጣትና አዛውንቱ፣ ከተሜውና ገጠሬው፣ እነዚህ ሰዎች ቢቻል ራሳቸውን ከኮሚሽኑ እንዲያገሉ፣ ካልተቻለ የለውጥ አራማጁ ቡድን ከኮሚሽኑ አባልነታቸው እንዲገለሉ  ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጫና ለማድረግ ተግተን ልንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ረገድ፣ በፌስ ቡክ፣ በቲዊተር፣ በኢሜል፣ በስልክ፣ በቴክስት፣ እና ባሉን የብዙኃን መገናኛዎች ሰላማዊ ተቃውሞአችን ማጋጋል ይገባል። ``ቁጭ ብሎ የሰቀሉት ቁሞ ለማውረድ ያስቸግራል``ና፣ በኋላ በነዚህ ሰዎች የሚቀርበው ጥናት ዐማራውን የዘላለም ተጠቂ ያደርገዋልና ፣``ሳይቃጠል በቅጠል`` ልንል ይገባል።
የዐማራ ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!
ዐማራው የአባቶቹን ማንነትና ክብር በትግሉ ያስጠብቃል!
 Posted at Ethio Semay