Monday, April 28, 2008

Ethiopia Loosing Borders to Enemies For Lack of leaders

አማን ነሽ ወይ ጎንደር የናጅሬን አገር!

በደርጉ ምክትል ሊቀመንበር በሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግ ደረስ ርዕሱ በትክክል ባላስታዉሰዉም ተመሳሳይነት ያለዉ “በቅጡ ያልተመረመሩ አደጋዎች” የሚል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፉት ማስጠንቀቅያ በርካታ አደጋዎች እያንዣበቡብን መሆናቸዉና በወቅቱ ያኔ ያልታዩን ለወደፊቱ (ላለንበት ጊዜ ማለት)ነዉ እንደሚደርሱ ተንብየዉ ፤ ሕዘቡ በጥንቃቄ አንዲመረምራቸዉ አስገንዝበዉ እንደነበር የኢትዮጵያን ደህንነት ሲከታተሉ የቆዩ ሁሉ ያሰታዉሱዋልታ።

ሊደርሱ እንደሚችሉ የተገመቱት አደጋዎች ሁሉ ያኔ ቀዠትና የፖለቲካ ማታለያ መስለዉን ብዙዎቻችን አንደ ተረታዊ ማስጠንቀቅያዎች የወሰድናቸዉ ዛሬ አማናዊ ሆኖዉ ደርሰዉብን ስንመለከት ያኔ መደረግ የነበረባቸዉ ጥንቃቄዎችያ ስርዓት ላደጋዎቹ መድረስ በር ከፋች፤ አልያም አፋጣኝ በሞኖሩ፤ አገር ወዳዶቹ /ናሽናሊሰቶቹ ምኑን ያክል ቢጥሩ አንኳ ኖሮ አደጋዎቹ ያዘገዩት እንደሆን አንጂ ከስርዓቱ አልሰማ ባይነት ባህሪ ማስቆም ላይቻላቸዉ ነበር።

ሊደርሱ ናቸዉ የተባሉት አደጋዎች፤ ስንዘናጋ አንደ ኩፍ አዉሬ እያደቡ እኛኑንና ከእኛነታችን ጋር የተያያዘዩትን ሁሉ እያጠቁ አንድናጣቸዉ አዳክመዉ ድዉይ አርገዉናል። በቅርቡ ለሱዳን ተሰጡ አየተባለ ያለዉ የጎንደር፤የጎጃም ለም እርሻና የግጦሽ መሬት፤ይባሰ ብሎ ባካቢዉ ኗሪዎች ላይ በሱዳን ወታደሮች እየተገፋ መሆኑን እየደረሰን ያለዉን ዜና ስናገናዝብ ህልዉናችን ላይ እየተሰነዘሩብን ያሉት የባንዳዎቹ ጥቃቶች ያለ ምንም የመልስ ምት አሁንም አሁንም እንዲቀጠሉበት ስንፈቅድ አንጀት ያበግናል። ምሁሩ የት ሄደ? ምን በነካዉ ነዉ? ይባል ነበር ድሮ ገና፤ገና የምሁሩ አምታቺነት ሳና’ቅ። በገበሬዉ ላብ የተማሩ ምሁራን ተብየዎቻችን፤ ፈረንጆች ተራራ ላይ ወ’ተህ ተፈላሰፍ ብለዉኛል እያሉ የሕዝበቸዉን ስቃይ አጃቢ ማእጠንት ሆነዉ የሕዘቡን ሕሊና እያፈኑ ስቃዩን ለግል ዝናቸዉ አየቸረቸሩበት እጀርበዋይ ላይ ለመዉጣት እየተጣደፉ የወዳጅ ጠላት ሆነዉ እያምታቱት ከባንዳዎቹ ብሰዉበታል። የፓለቲካ “መ ዓምኖችና ነጋድያን” አንድነቱን አናግተዉ በጦፈ ትግል መሀል እንደ ገራገር ላም ቆሞ አንዲቀር በሰርቀ ሌሊትና በሰርቀ ማዓልት ለጅቦቹ አጋልጠዉ ሃይለኛ ቅጣት ቀጥተዉታል! ያ ኩሩ፤ መጎሳዊ ሕዘብ ግን አንድ ቀን በሰረቀ ብርሃን ተላቶቹ ሲሰግዱለት ማየቱ አይቀርም! ።

ከጥቃት ወደ ጥቃት! መልሰዉ መላልሰዉ እያጠቁን ነዉ! ዛሬ አደጋዎቹ በቅደም ተከተል እያነዣበቡ ያለምንም ከልካይ በተዘጋጀላቸዉ የጥቃት ሥፍራ እየረፉ ነዉ።ያለፈዉ ሥርዓት ከዚህኛዉ ከወያኔዉ ሥርዓት በጭካኔም በዉሸትም ተመሳሳይነት አለዉ። ይኼኛዉ ለየት የሚያደርገዉ ክህደቱ ነዉ። የክህደቱ መጠን ሆን ብሎ አቅዶ በጠላቶቻችን ጫማ ሥር እንድንወድቅ አድርጎናል። ቁጭታችንና ሀዘናችን መራራ የሚያደርገዉም ይኼኛዉ ጥቃት ነዉ።

በትግራዊነታቸዉና በኤርትራነታቸዉ ቅድመያ መድበዉ ኢትየጵያዊነታቸዉኑን በሁለታኛ ደረጃ በመመደባቸዉ፤ በጎንደርና በጎጃም ገበሬ ድመበር ላይ ኗሪ ጥቃት ሲደርስ እንደራሱ መንደር አንደ ትግራይ ያልተንገበገቡበት ምክንያቱም ይኼነኑ “የቅደሚያ ትግራዊነት ቀጥሎ አትዮጵያዊነት” የሚለዉን የወያኔዎች የብሄረተኝነት ፍለስፍና መስመሩ በመከተሉ ነዉ። እዉነትነቱን ለማረጋገጥ Identity Jilted or Re-Imagining Identity? The Divergent Paths of the Eritrean and the Tigrayan Nationalist Struggles’- Authored by Alemseged Abbay) የሚለዉ መጽሃፍ መላዉ የወያነ ትግራይ አመራሮች የሰጡትን ቃለመጠይቅ አስቀድሞ በሕሊናቸዉ የሚቀረጸዉ የመቆርቆርና የዜጋነት ሰዕል በትግራዋይነትና በኢትዮጵያዊነት የሰጡትን አስተያየት ይመልከቱ። In my mind, Tigray comes first before anything else. I can’t be Ethiopian before I bcame Tigrayan” (ጸጋይ በርሃ- የትግራይ መንግሥት ፕረዚደንት በዚያዉ መጽሃፍ ዉስጥ).። የህ ሰንካላ እይታ-‘ ከኦሮሞዉ፤ከጋምቤላዉ ከአማራዉ ከሶማሊዉ ከአፋሩ….ሰው ለትግራይ ሰዉ ቅድምያ ይሰጣል። እዚህ ላይ ሰዉን በሰዉነቱና በሰብዓዊነት እኩል እይታ፤ የመዉደድና ፍትህ የማሰራጨት ሚዛኑ በጎሰኝነት ተጋርዶ ይታያል። በዚህ ፍለስፍና በመታወራቸዉ ነዉ ኢትዮጵያና ትግራይ እኩል የማየት ችግራቸዉ የበረታዉ። ለዚህም ነዉ ጎንደርና ጎጃም በሱዳን ወሮበሎች ሲደፈር ደንታ ቢሶች ሆነዉ ለብዙ አመታት እንዲጠቃ አጋልጠዉታል።ባድመ ሲባል ግን ምቱ ይቀየራል! ፡ዓሰብ ያልን ጊዜ ግን ጦራቸዉ ኤርትራን ለመከላከል ዝግጁ ነን ወዮላቹህ ይሉናል!

ይኼኔ “ንጉሥ ዮሐንስ” አልያም አሉላ አና ደፋሩ “ወዲ ጭቁን” ትግራይ ዉስጥ ቢኖሩ ኖሮ ሕዘቡ ማሳዉ እየተነጠቀ ዜጋ ተጎትቶ ወደ ሱዳን ሲጠለፍ፤ አንዲህ አንደዋዛ አያስጠቁትም ነበር። የጎነደር ሕዝብ በ አረመኔዉ ድረቡሽ በተመቅደሶቹ ካህናቶቹ ሲቃጠሉና ሲደፈሩበት ጊዜ ዮሐንስ ድረስ ሲሉት አነገታቸዉ ላረመኔ ቢላዋ አሳልፈዉ ሰጡ። ዛሬ ዮሐንስም፤ አሉላም ወዲጭቁን ከኢትጵያ ሰማየ ሰማያት ይምጡ? የነበሩንን ጀግኖቻችን ከዉጭ ቅጥረኞች ጋር ተመሳጥረዉ ከመከላከያዉ ጦራችን ጉያ ዉስጥ ሰርገዉ እየመለመሉ በሚስጢር የተነኮል ድር በሚያደሩ የጦር ካዳተኞች (መርስናሪ) በአለጌና በናቅፋ በከረን በምጽዋ ፈጁተዉ አስፈጁት።የተቀረዉም አንደማያንሰራራ ወገቡን ሽባ አረጉት። ጎንደር ጎጃምና ወሎ ሲደፈሩ “ጃሎ” ሸዋ ሲደፈር “ጃሎ”፤ የጅማ የሐረር የካፋ የአርሲ ገበሬ አዛዉንት ሲደፈሩ “ጃሎ በል ኢትዮጵያ ተነስ!” የሚል ወንድ ሲያጡ “በነጭ አጋሰሶች” እየተነዱ አገሪቷን የሚንዱ ወያኔዎቹ ምን ያርጉ?

ከሰባት ዓመት በፊት አገሪቷን ለኤርትራኖች በጉቦ መልክ ክፍት አ’ርገዉ ያስመዘበሩን ጥቃታችንን ወደሗላ መለስ ብየ አገር ወዳድ ጸሃፍት የመዘጉትን ታሪክ ላስታዉሳችሁ። <ኢትዮጵያ የሚሞትላት አንዳላጣች ሁሉ የሚያዋርዳትም ተቸግራ አታቅም..> ይላሉ ጸሃፊዉ። <በድርድር ወቅት ከኢትዮጵያ ይልቅ የሚታያቸዉ የሌላዉ አገር ጥቅም ነዉ። ታስታዉሱ አንደሆን ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢንሹራንስን በተመለከተ በአዲሲቱ ኤርትራና በኢሕአዴጊቱ ኢትዮጵያ መካከል ድርድር ተካሄደ ተባለ። ኤርትራዊዉ ሥራ አስክያጅ ከኤርትራዊዉ ኢነሹራንስ ድርጅት ሥራ አስክያጅ ጋር ተደራደሩ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስክያጅ (ባንድ ወቅት ሦስት ምክትል ሥራ አስክያጆች) ኤርትረዊያን ነበሩ። አንድ አይሮፕላን ወይም ድርጀት የሌላት ኤርትራን እኩል ሽርክና ዉስጥ ለማስገባት ተሞከረ።ያ ባያዋጣም አየር መንገዱን አስከሚችሉት ድረስ አድክመዉ ወደሚሄዱበት ሄዱ።>> ጸጋየ ገብረመድህን አርአያ- ጦቢያ ቅጽ 5 ቁጥር 10 1990 “የነጻዎቹ አገር የጀግኖች ቤት ይዘጋ? ተዋርደናል! ”

ወያኔዎችን ይህ ክህደት ለመፈጸም ያስገደዳቸዉ ሁኔታ፤ ሻዕቢያ የወያኔ መስራቾችን በተከታታይ ዙር አሰልጥኖና የራሱን የሻዕብያ ተዋጊዎች የነበሩትን ሰላዮቹን ድርጅቱን እንድያጠናክሩ በመላክና አልፎም ከዓረቦቹ ከጠላቶቻቸንና ከምዕራቡ ዓለም አስተዋዉቆ መሸጋገርያ ድሮቹን ስለዘረጋለት ኢትዮጵያን ክፈት አድርጎ አንድትበዘበዝ ማድረጉ ለዉለታዉ ብድር የመመለስ ዘዴዉ ነበር። በጉቦ ዉለታ የመመለሱ ሱሱ ዛሬ አልተጀመረም። ሱዳን ዉስጥ ሴቶች እህቶቻችን ለሱዳን ጋጠወጥ የደህንነት ወታደርና ሹማምነት አንደ እጅ መንሻ አሳልፎ ይሰጣቸዉ እንደነበር በዛ ያለፍን ስደተኞች ህያዉ ምስክሮች ነን። አንዳንዶቻችሁ ይህነኑ ታሪክ ከተጎጂዎቹ እህቶቻችን ሳትሰሙት አልቀራችሁም። ዛሬ ጎንደርና ጎጃም ለም መሬቶች ለሱዳን አሳልፎ ለመስትጠት ሲዘጋጅ ዜጎች በሱዳን ሶጥ (አለነጋ) ሲደፈሩ ዝም ማለቱ፤በትግሉ ወቅት የዋሉለትን የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን የመግደልንና የማፈኑን ሥረዎቹን ያለ ችግር በማካሄዱና ሱዳን ዉስጥም ሰፋፊ የእርሻ ማሳዎች ሰጥተዉት አንደልቡ አነዲፈነጭ ያደረጉለት ዉለታዎች ብድር መመለሱ ነዉ።

በፊት ወየኔ ከሱዳን መንግሥትና የደህንነት መኮንኖች ጋር የነበራቸዉ የጠበቀ ወራዳ ግንኙነት በጊዜዉ የነበሩ ዉስጡን የሚያቁ አቶ ግደይ ባሕሪሹም ባሞራ መጽሃፋቸዉ ያሰፈሩትን አንዳስስና ቁጭታችን በዛዉ እናጠቃልል። በተጠቀሰዉ ጽሁፍ ከራሴ በኩል መጠነኛ ማስተካከያ አድርጌበታለሁ።
<< የሱዳን ሕዝብ ደግ ህዝብ ነዉ። ለባለስልጣኖች ክፋት ያስተማርናቸዉ እኛዉ ነን። መጀመርያ በገራገርነት ልብ ስያስተናግዱንንና ወደመጨረሻ ወደ ሗላዉ ጊዜ ሲሸኙን ያሳዩን ልብ እንደፉተኛዉ አላገኘናቸዉም።ወየነ ትግራይ ለእነ “ዛቢጥ አሲር” (መቶአለቃ አሲር) አና መሰሎቹ ገንዘብና ኮረዳ/ ወጣት ልጃገረዶችን በጉቦ መልክ በማበርከት ኢትዮጵያዊ በሆነ ወገን ላይ ግፍ ፈጸሙ። አነኚህ ዛሬ ኢትዮጵያዊያን ነን የሚሉ “አላዉያን ተጋሩ” በወቅቱ የሱዳን ዛቢጦች አጉራሽ ሆነዉ ስደተኛዉ በስደት አገር፤ በቀን ጨለማ ዉጦት የቁም ስቅሉ እንዲያይ አድርገዉት ነበር። የትምክህት ስድብ ከአፉ የማይለየዉ “መቶአለቃ አሲር” ብዙ ወገኖች ገርፏል። በዙ ሴት እህቶቻችን ለግብረስጋ ግንኙነት እያስገደደ ደፈሯል። በግፍ ሌሊት ተጸነሶ በግፍ የተወለደ ስዳደግ መጥፎ ስለነበር ፤ አሱም በተራዉ ቀኑ አለቀበትና አል-ኒመሪ ሲገለበጥ አብሮ ተገልብጦ ደብቁኝ ሲል አየሁት። ገዳሪፍ ከተማ የኖረ በዛብጥ አሲር ያልተሸበረ ቢኖር ጥቂት ነዉ።አሲር ስልጣኑ መከታ በማድረግ በድርጅቶችና በኢትዮጵያ ነክ ማህበራት ዉስጥ ጣለቃ እየገባ ቀን በጣለዉ አትዮጵያዊ የድርጅት አባል ስደተኛ በወያኔዎች ተልኮ ብዙ በቀል ብዙ ግፍ ፈጸመ።ወየኔ ትግራይ አግሯን ወደ ሱዳን ብቅ ያደረገችበት ወቅት ገዳሪፍ በዘመነ ዛቢጥ አሲርና በግማሽ ጎኑ ሱዳን በሌላ ትውልዱ ደግሞ ከሰሜን ኢትዮጵያ ከሚንአሚር በኩልሚወለድ ከአንዲት የትግራይ ሴትሥስት ልጆች የወለደዉ (ሩጣናዉ) ኮሎኔል ሩፋኤል (በሗላ የጀነራል መዓረግ) የተባለዉ ሱዳናዊ ባለስልጣን ፡ በኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች መሃልና በሱዳን የጸጥታ ጉዳይ እነዲያስተባብር ተመድቦ በነበረበት ወቅት የኢዲህ አመራሮች እርስ በርስ አንዲጋጩ በማሃል ጣልቃ እየገባ ጥላቻ አንዲስፋፈ በወያኔዎች እየተላከ አዲህ (EDU) አንዲፈርስ እያበጣበጠና ፡ ኢሕአፓም ሱዳን ዉስጥ ቦታ አንዳይኖረዉ <<ሹዒ>> ነዉ (ኮምዩኒሰት ነዉ) እያለ የበላይ አለቆቹን እያምታታ እያሞኘ አስከ ጀኔራልነት ማዓረግ የደረሰ፡ብለጦቹ ወያኔና የሸዕብያ መሪዎች አንከክልህ እከከን እያሉ አንደኛዉ አኛ እኮ ዘመዶችህ ነን ሲሉት ወያኔም እኛም “አማቾችህ” ነን እያሉ የዘረኝነት መልክታቸዉ በእጅ አዙር እያስተማሩ በወገን ላይ ጥቃትአንደፈጸሙ እነሱም አሌ ማይሉት ነዉ።

ጉቦ ማቅረብ ያልቻለ አትዮጵአዊ የድርጅት በአካባቢዉ ሙዲር (አስተዳዳሪ) አና በፖሊስ ደህንነት ተይዞ በሶጥ (ባለነጋ) አየተሞሸለቀ ጉቦ አስክያቀርብ ድረስ አስር ቤት ይማቅቅ ነበር።

አስገራሚዉ ሌላዉ ሴራቸዉ ደግሞ፡- ወያኔዎች አገሪቱን አንደተቆጣጠሯት አዲሱ የትግራይ ክልል ብለዉ ደጋግመዉ ባወጡት መለከአ ምድር/ካርታ፤ የትግራይ ሕዝብ ከአማራዉ ሕዝብ ጋር ለማጋጨት ወልቃይት ጠገዴን ተሻግረዉ አዲስ ድንበር ቀይሰዋል። ትናንት ደጃዝማች ገብረስላሴ በወጨፎ ጠመንጃ የሸጡትን የአዉጋሮ፤ የእምኒሓጀር፤የጉሉጅ የተሰነይንና የከሰላን በር የኤርትራን ከ/ሃገር ኩታ ገጠም ድንበር ለምን አላስታወሱትም? ወይስ የአያታቸዉ የደጃች ገብረስላሴን ዓይነት “ወጨፎ ብረት” ለትግላችን ባለዉለታችን ነዉ ተብሎ? ወይስ የትግራይ ህዝብ ንቀዉ ሞኝ ነዉ ፤ እኛ ካልነዉና ከደነገግነዉ ነገር አይወጣም ተብሎ? የትግራይ ሕዝብ የሚንቃቸዉን ያህል እየናቁት መሆኑ ግን ያሳዝናል።

ወያኔዎች ሲያልፉ የሚያልፍ፤ ይህ ለጊዜዉም ቢሆን እየተመኩበት ያሉት የተቆጣጠሩት ሠራዊት፤ በሌላ ትዉልድ ተተክቶ አንድ ቀን ንብረቱንና መሬቱን የሚጠይቅ ሌላ የትግራይ ሠራዊት የሚነሳ መሆኑንም የተገነዘቡት አይመስሉም። በነሱ ቤት ካለ’ነሱ ሌላ ብልህ የለም። የመጀመርያና የመጨረሻ ዘመን መስሏቸዋል። የትግራይ ሕዝብ ለጊዜዉ አፉና እጁ ታስሮ ዝም ይበል አንጂ አንድ ትዉልድ ታሪክ እንደሚሰራ ምስክርነቱ አይነፍገንም።>> (ግደይ ባሕሪሹም)።

ወያኔ የጎነደርንና የጎጃምን መሬትና ሕዝብ በሱዳን ወታደርና ነጭ ለባሽ ሲደፈር፤ቤት ንብረቱ ሲቃጠል፤ዜጎች እየተጠለፉ ሱዳን ድረስ አሻግረዉ ሲደበድቡት “ማነህ አንተ ቁም!” የሚልለት አገር መንግሥት ያጣበት ምክንያትም ለዘሁ ነዉ። ሱዳኖች ለወየኔ ዋሉለትን ዉለታ ብድር መመለሻ ነዉ። አሁንም ይበልጥ ተቃዋሚዎቹ አየጠለፉና እያፈኑ እንዲያስረክቡት እጅ መንሻ መደለያ ነዉ።

መቸም ቢሆን የጀግኖች አገር አንደተደፈረ አንዲሁ አንደተዘጋ ዝንተዓለም አይኖርም። አንድ ቀን ጀግና ይወለዳል ያኔ የጀግኖች አገር ይከበራል፤ የተዘጉብንን በሮቻችን ክፍት ይሆናሉ! ጥቃቱ ይቆማል!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ጌታቸዉ ረዳ
ሳን ሆዘ ካሊፎርንያ
አሜሪካ

ሚያዝያ 2000