Friday, February 10, 2023

አማርኛ ቋንቋ በትግራይ ቤተክርስትያናት እንዳይነገር ያገደው የትግራይ ፋሺስታዊው የኦርቶዶክስ ተገንጣይ ቡድን አማራን እና የኢትዮጵያን ምእመናኖችን ስለ አፓርታይዳዊ አዋጃቸው ይቅርታ መጠየቅ አለበት! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 2/10/23

 

አማርኛ ቋንቋ በትግራይ ቤተክርስትያናት እንዳይነገር ያገደው የትግራይ ፋሺስታዊው የኦርቶዶክስ ተገንጣይ ቡድን አማራን እና የኢትዮጵያን ምእመናኖችን ስለ አፓርታይዳዊ አዋጃቸው ይቅርታ መጠየቅ አለበት!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

2/10/23

ሃገረ ትግራይ የተባለ አገር እንመሰርታለን ብለው ከኢትዮጵያ ኦርቶዲክስ ቤክርስትያን በመገንጠል የራሳቸው የትግራይ ኦርቶዶክስ መስርተው “ኢትዮጵያን ስም በማጠልሸትና በመርገም” አገር የማፍረስ ሂደት እየዛቱ ያሉ “የማሌሊት ግርፍ ጳጳሳት” ሰሞኑን 48 አመት የተጓዙበት አፓርታይዳዊ አዋጅ አውጀዋል።

ይህ እንዲህ እያለ የተገንጣዮቹ  የዜና አራጋቢ ማዕከላት ከአዲስ አባባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጽ/ቤት “የይቅርታ” ደብዳቤ ተልኮ ተገንጣይ ጳጳሶቹ “አባ ማስያስ” ከሚመርዋት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ግንኙነታችን ማቋረጣችን እንቀጥላለን” በማለት የተገንጣይነት ትዕቢት ያዘለ መልስ እንደሰጡ ሰምተናል።

የኔ ጥያቄ ፤ ሲጀመር ለምንድነው የኢትዮጵያ ሲኖደሱ ወደ ተገንጣይ ጳጳሳቱ የይቅርታም ሆነ የመሞዳሞድ ደብዳቤ የሚልከው? ምን ለማግኘት ነው? ትግራይ ውስጥ ያሉ ብዙዎቹ ቀሳውስት ነን ባዮች አሁን ሽበት የተላበሱ ሽማግሌዎች መስለው መስቀል ይዘው እየባረኩ የካህን ልብስ ቢለብሱም  በ17 አመቱ የፋሺዝም ትግላቸው ዘመን ጠመንጃ ታጥቀው ሰልጥነው ሲዋጉ እንደነበር ባለፈው ሁለት ሰሞን የለጠፍኩት የወዳጄ ገብረመድህን አርአያ ሰነድ ያሳያል። (በነገራችን ላይ ስለ ወዳጄ ገብረመድህን ስጨነቅ ያነበበኝ ወዳጄ ደውሎ ገብረመድህን የጤና እክል ገጥሞት እንዳለ ስከነገረኝ ይህን ዕድል ተጠቅሜ ለማማስገን እወዳለሁ)።

 

በአንዳንድ ጽሑፎቼም የትግራይ ቀሳውስት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ በትከሻቸው መስቀል ይዘው ሲባርኩና ሰው ሲያሳልሙ በፎቶ እንዳሳየሁዋችሁ ታስታውሳላችሁ። ሌው አዲስ ቪዲዮ ደግሞ ዛሬ እዚህ ጽሑፍ አያይዤ ለጥፌዋለሁ። ስለዚህ የትግራይ ቀሳውስ በተለምዶ የምናውቃቸው ቀሳውስት ሳይሆኑ ብዙዎቹ በትግል ያለፉ የወያኔ ፖለቲካ ተቀብለው ሲሰብኩ የነበሩ በሚያሰዝን ሁኔታም የወያኔ ኮሚኒዝም አንቀበልም ያሉ ዲያቆናት፤ቀሳውስት ሲረሸኑና ሲደበደቡ ከብቶቻቸው ሲወረሱ ምንም ያላሉ ወይንም ተባባሪዎች የነበሩ ቀሳውስት ታጋዮች ትግራይ ውስጥ አያሌ ናቸው።

ዛሬ ከ48 አመት በላይ ሲያመልኩት የነበረው የወያኔ ፖለቲካ እና ሰንደቃላማ በመከተል ወያኔዎች ትዕቢት ወጥሯቸው አገር ለማፍረስ ጦርነት ከፍተው የሰሜን ዕዝ ሲጨፈጭፉት በተነሳው ጦርነት ከህወሓት ወታደር (ቲ ዲ ኤፍ ይሉታል ባዲሱ መጠሪያው)  ጎን ቆመው ፖለቲካ ሲሰሩ የነበሩ ቀሳወስት ዛሬ ኢትዮጵያ ቤተክረስትያን በትግራይ ላይ ጦርነት አውጃ በትግራይ ስለደረሰው የጦርነት ጉዳት አላወገዘችም የሚል ለግንጣላ ሽፋን “ቅብጥርጥሮሽ” ምክንያት ፓርቲያቸውና ሰንደቃላማቸው ባዘዛቸው ውሳኔ መሰረት ተገንጥለናል ብለው ግንጠላን እና ለዳግም አስከፊ ብጥብጥ ጠንስሰው እነሆ አቋማቸው አጠናክረዋል። ይህንን እናውቃለን።

ለመሆኑ እነዚህ “ዘረኛ ካህናቶች” አማራ እና ዓፋር ውስጥ የትግሬ  “ዱርየ ተዋጊዎች” ገብተው መስጊዶች ቤተክርሰትያናት ፤ትምህርት ቤቶች፤ሕክምና ቤቶች እና ላሊበላ ገብተው ሲዘርፉ ፤ አየር ፖርቱ ሲያፈርሱት (እራሳቸው አክሱም አየር ፖርት ንዳፈራረሱት) ሲሸኑበትና ልጃገረዶች ሲያምጹና ባለትዳሮች ሲደፍሩ፤ ቀሳወስት ሲደበድቡ’ ከብቶች እያረዱ ሲበሉ፤ በርበሬ፤ ሽሮ ፤ሳና፤ ዘይት ሲዘርፉ እነዚህ ተገንጣይ ጳጳሳት ተብየዎች አውግዘው ያውቃሉ? አላወገዙም!

ምክንያቱም የፓርቲያቸው ወንጀል ሊያራግቡት አይፈልጉም እንጂ ትግራይ ውስጥ የሰሜን ዕዝ ሲጨፈጨፍ ያውቃሉ። ምን አሉ? ምንም። ቀሳወስት ሳይቀር የተማረኩ ወታደሮች ወደ ገል ሲገፈትሩ የነበሩ ቀሳውስቶች በድምጽ የተዘገበ ሰነድ አንብበናል። የተከዳው ሰሜን ዕዝ የሚል መጽሐፍ ያነበበ ሰው እነዚህ ከሃዲ ጳጳሳት የሚለፋደዱበት እውን ሊታመን ይቻላል?

የሚገርመው ያ ሁሉ ጉድ ይዘው፤ ሰሞኑን ያወጁት አዋጅና ወሳኔ ደግሞ ትግራይ ውስጥ ትግርኛ እና ግዕዝ ክልሆነ በስተቀር  “አማርኛ ቋንቋ” በመላ የትግራይ አብያተክርትያናት ውስጥ እንዳይሰበክ፤ እንዳይነገር አውጀዋል።  

ይህ የሰው ልጆች ቋንቋ የሚያከብሩ የፈጣሪ አገልጋዮች የተሰከሰተ ሳይሆን ከፖሊካ እና ጸረ አማራ ሕዝብ የመነጨ 48 አመት የተጓዙበት ዲያብሎሳዊ ባህሪ ነው። 

አማራው ብቻ ሳይሆን፤  አማርኛ እንደመገናኛ የሚጠቀሙ በኢትዮጵያ ምዕመናን ላይ የታገደ የብሔራዊ መገናኛ ቋንቋ ነፃነት የተጋፋ አዋጅ ነውና የትግራይ ካህናት ለመላው ኢትዮጵያ ምዕማናን እና ለአማራ ሕዝብ የቅርታ መጠየቅ አለባቸው።

እኔ ተወልጄ ያደግኩት አክሱም የትግራይ ተወላጅ ነኝ። ከተማዋ ውስጥ  ሁለት የሴቶች ቤተክረስትያን (አርባእቱ እንሰሳ ቤክርስትያን እና አጼ ሃይለስላሴ ያስሩት ዘመናዊው ቤክርስትያን( እንዲሁም አጼ ፋሲል ያሰሩት ሴቶች የማይገቡበት ጥናታዊው ቤተክርስትያን እና ብዙም ሰው የማይጠቀምበት አንድ ሌላ ቤተክርሰትያን ናቸው። እነኚሀ የተገነቡት በትግሬ ነገሥታት ሳይሆን የፋሺሰት ፓርቲ ተከታይ ትግሬዎች አማራ በሚልዋቸው ነገሥታት የተገነቡ ናቸው።

እነዚህ አማራዎች የገነቡዋቸው ቤተክርስትያናት ልሳናቸው እንዲታገድ ሲደረግ፤ ትግራይ ውስጥ ከትግርኛ ተናጋሪ ማሕበረሰብ ቀጥሎ በቁጥር ብዛት “አማራ” በሁለተኛ ደራጃ ሲሆን ኩናማ ፤ሳሆ እና የመሳሰሉ በሦስተኛ እና አራተኛ ደራጃ ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ ኗሪ በየትኛው ቤተ-ጸሎት ሄዶ እምነቱን እንዲያከናውን ነው የተፈለገው?

እነዚህ የወያኔ ካህናት ጽላቱን የወያኔ ባንዴራ አልብሰው “ለትግራይ ሃገርነት  ውዳሴ“ እያስሙ የምናያቸው ቀሳውስት  አማሮች ለሆኑት  ወይንም አማርኛ የሚሰሙ አማራ ያልሆኑ ምዕመናኖች በስራ ጉዳይ ወደ ትግራይ የተመደቡ ዶክተሮች ፤ ሰራተኞች ተማሪዎች ወዘተ… የጥንት ነገሥታቶቻቸው ያናጹላቸው ቤተ ጸሎት በሚናገሩትና በሚሰሙት ቋንቋ አግልግሎት እንዳያገኙ ከተነፈጋቸው እነዚህ ሰዎች ለህንጻዎቹ እና መገልገያዎቹ ግብር ከፋዮች ስለሆኑ አማራጭ ካልተገኘለት የትግራይ ሕዝብ በገንዘቡ አዋጥቶ ለነዚህ ነጻነታቸው የተገፈፉ ምዕመናን  የራሳቸው ቤተጸሎት እንዲኖራቸው በየቦታው እንዲያሰሩላቸው መገደድ አለባቸው።

 ወይንም አማራዎችና አማርኛ እንደ መገናኛ የሚጠቀሙ ምዕመኖች  ከጥላቻ እና ከፖለቲካ የመነጨ አፋኝ የሃይማኖት ነጻነት አዋጅ  ስለታወጀባቸው ፍትህ እንዲያገኙ የሕግ አዋቂዎች ጣልቃ መግባት አለባቸው። ካልሆነ ነገሥታቶቻቸው የሰሩላቸው ህንጻዎች ለትግሬ ብቻ መገልገያ የሚውልበት መንገድ የለም።

ይህ ከቀጠለ ከመላ ሕዝባችን የተሰበሰበ የምዕመናን መዋጮ አልባሳት፤ግብር… ስለሚመለከት፤ ለተገንጣዩ ማንኛቸውም የገንዘብ ደሞዝና አልባሳት ድጋፍ ወይንም ባጀት ከዋናው ኢትዮጵያ ሲኖዶስ እንዳይፈቀድ የሕግ አዋቂዎች ክስ መመስረት አለባቸው። እነዚህ ካህናት ተገንጥለናል ካሉ፤ የቴሌፎን እና ጭራሽ ካህናቱ በኢትዮጵያ ባንክ ማንኛውንም የአየር መንገድ፤አገልግሎት መታገድ አለባቸው። ኢትዮጵያ የምትባል አገር አውግዘው ረግመው ተለይተናል ብለው አዋጅ አውጥተው በቪዲዮ ያሰራጩት ማስረጃ ስላለ፤ ከማንኛውም አገልግሎት ይታገዱ።ይህ የማያደርግ አስተዳዳር፤ የሴራው ተጋ ነው ማለት ነው።

በዚህ ጉዳይ በሚቀጥለው ሰፊ ሃተታ ስለማቀርብ ለጊዜው ግን አማርኛ ከጠሉ ያሬድ የፈለሰፋቸው አስሩ (10) የቅዳሴ ኖታዎች “አማርኛ” ስለሆኑ ከሚሰብኩበት የትግርኛ መጽሐፍ ወይንም አስተምህሮ አማርኛ ናቸው እና ማስወጣት ይጠበቅበባቸዋል ማለት ነው።  << መረቁን ስጭኝ ከስጋው ጾመኛ ነኝ >> አብሮ አይሄድም።በጥብቅ የማሳስበው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዋና ጽ/ቤት  ለትግራይ ተገንጣይ ቀሳውስት ቡድን መሪዎች “ከሚያብዱት ዘረኛነትና ፖለቲካዊ ዕብደት” ካልታቀቡ የክህነት ማዕረጋቸው ተገፍፎ ሊጠሩበት በነበረው “የብፃይነት” ማዕረግ ወይንም “አቶነት” እንዲጠሩ መወሰን አለበት ብቻ ሳይሆን የመሞዳሞድ ደብዳቤም መላክ ማቆም አለበት።

ይልቅኑስ እነዚህ ጳጳሳት ነን የሚሉ ተገንጣይ “ወያኔዊ ጳጳሳት” የሚጠበቅባቸው ነገር የወያነ ትግራይ ዱርየ ተዋጊዎች (TDF)  በአማራ ሕዝብ ፤ በዓፋር ሕዝብ በወታደሩ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አምነው ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው።

ትግራይ ውስጥ የተካሄደው ጦርነት የጣሊያኖች ዕቅድ የሆነው የትግራይ ትግሪኚ  “የሃገረ ትግራይ የምስረታ ጦርነት” ስለነበር “ኢትዮጵያ ጳጳሳት፤ቀሳውሰት፤ሴት ወንድ አረጋዊ፤ ወጣት ዜጋ ሁሉ” ጦሩን ቢደግፉ አገር የሚያፈርስ ጥቁር ጣሊያንን ማውገዝ የሚደገፍ ነውና፤ ጳጳሳቶቻችን እና ቀሳውስቶቻችን ምንም ይቅርታ የሚጠይቁበት አባዜ የለም። አበዛችሁት! እጅግ በጣም ከረፋችሁ!

ጽሑፉን ተቀባበሉት

አመሰግናለሁ

 ጌታቸው ረዳ