መቸስ የትግራይ ነጻ አዉጭ የተባለዉ በኢትዮያ ምድር ላይ የወረደ እርግማን አስካለ ድረስ ማረፍ-አልቻልንምና፣መለስ ዜናዊ-የአክሱም-ሃዉልት ለሀዲያዉ ምኑ ነዉ!? እንዳላለ ሁሉ፣ሰሞኑን-ደግሞ ይግረማችሁ ብሎን ያንዱ አፍሪካዊ ችግርና ዕድገት-የሁላችን-ችግርና ዕድገት ነዉ በማለት አህጉሪቱን እወክላለሁ ብሎ እንግሊዝ አገር ሄዶ ፊቱን ለጌቶቹ ሲያስመታ መሰንበቱ የምታዉቁት ዜና ነዉ።
የዚህ ኩታራ ሰዉ አጨብጫቢ የሆኑት የህዋ ሰሌዳ (ኢንተረኔት)እና ቴሌቪዥኖቹ አገልጋዮቹ ሲያቀርቡት የነበሩትን መለስ ዜናዉ የተባለዉ ጸረ ኢትዮጵያ ቅጥረኛ ዓለም ከረገመዉና ካወገዘዉ “የቀድመዉ ያሜሪካ ፕረዚዳንት “ቡሽ” ከተባለዉ አረመኔ ሰዉ ጋር ጎን ለጎን ተመችቶት መመሪያ ሲቀበል የተነሳዉ የቆየ ፎቶግራፍ ሳይቀር መለስ ዜናዊ ምንኛ “ከፍተኛ መሪ”እንደሆነ የዋሆቹን ለመማረክ በፎቶግራፍ አስደግፈዉ አሳፋሪ ፎቶግራፎቹን ለሕዝብ ሲለጥፉለት አለማፈራቸዉ ሲገርመኝ ይባስ ብሎ መለስ ዜናዊ “ያፍሪካ እርግማኖች” በተባሉት በአፈሪካ ጨቋኝ መሪዎች ፎቶ ተከብቦ በጉንጉን አበባ ያሸበረቀ ፎቶግራፍ እንደትንግርት ሆኖባቸዉ በኩራት ለጥፈዉት ስታዩ እኔ እንደገረመኝ እናነተንም እንደገረማችሁ አልጠራጠርም።
ጌቶቹም አፍሪካን ለመጨቆኛ የሚጥሉለት ፍራንክ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት ትዛዝና መመሪያ ሲሰጡት ከተለያዩ አዉሮጳዊና አሜሪካ ጌቶቹ ጋር ቆሞ ሲነጋገር ጣቶቻቸዉ በረዢሙ ወደ ሆዱ ሲቀስሩበት የተነሳዉ ፎቶ ሁሉ እንደ ኩራት ቆጥረዉት ሲለጥፉትና ሲኩራሩበት ስመለከት፣ ለካ ይሄ በየሚዲያዉ ሃላፊ እና ወኪል እያለ የሚሾማቸዉ ሙያም የላቸዉ! አልኩኝ። ለካ የምሩ ነበር “የኛን ዓለማ አስካራመደ ድረስ ዘበኛም ማንበብ መጻፍ የማይችልም ሚኒስትር መሆን ይችላል” ያለን ለማለት በቃሁኝ።
“ቤን ዌብ ሳይት” የተባለዉ “የወያኔ ትግራይ አጋፋሪ” ‘ማ በዌብሳይቱ ላይ ኦባማ የተባለዉ ያሜሪካዉ መሪ በመለስ ዜናዊ ሆድ ላይ ረዥም አመልካች ጣቱ ቀስሮ መመርያ ሲሰጠዉ የሚያሳየዉ ፎቶ እንዳይታይ ለጌታዉ ክብር ሲል “ከወገቡ በላይ ቆርጦ አቅርቦታል” በሱ ቤት የሱ ጌታ በታችነት ስሜት እንዳይታይ ሲባል ነዉ። ወይ ጊዜ!
አምርሮ የገረመኝ ግን የነዚህ አልነበረም። ከሕግ ዉጭ ሆኖ ሕብረተስብን ባሕልን አገርንና ሕግን በመናቅ አማራ ያልሆነ የአማራ ወኪል ነኝ ብሎ ብዙ ግፍ የፈጸመ በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የቀለደዉ ኤርትራዊዉ በረከት ስሞን በለንደን ከተማ ስበስባ ጠርቶ ባንዲት ጠባብ ክፍል “እንደተሸበቡ ዉሾች” በመቁጠር ናላቸዉን ሲያሻቸዉ፣ ያሳዩት የነበረዉን ስሜት ለታዘበ ሰዉ.፣ የሰዉ ልጆች ደካማነት ምን ያህል እንደሚጓዝ ምሳሌ የሆነን መሰለኝ። ሰዉ እንዴት ድፍን 18 ዓመት አይማርም? እንዴት ሰዎች ከሕግና ከእዉነት የተጣሉ፣ በሕገ አራዊት በጫካ ባሕሪ እና ትእቢት-የሚጓዙ እነ በረከት ስመኦን የመሰሉ ራሳቸዉን በጊዜያዊ ጥቅም አሳዉረዉ፣በመጪዉ ሕይወታቸዉ ላይ መዉጫ ቀዳዳ የተደፈነባቸዉ ፣ተስፋ የቆረጡ በራሳቸዉ የፈረዱ “ፈሪዎችን”ባሕሪ መገንዘብ ያቅተዋል? ኤርትራዊዉ ስሞን አማራ ሳይሆን አማራ ነዉ ብለዉ እነ መለሰ በአማራ ሕዝብ ላይ ጭነዉ የመለስ አጀንዳ አስፈጻሚ ሆኖ ብሔራዊ ወንጀልና ሰብአዊ መብት ረገጣ የፈጸመ ለከት የሌለዉ የዉሸት ቱጃር ምን ይረባናል ብለዉ በዛች ክፍል ዉስጥ ተሸብበዉ እየተቁለጨለጩ ጊዜአቸዉ አንዳጠፉ ለኔ ይገርመኛል።
ይህ ግለሰብ መጀመርያ በኢሕአፓ የሻዕብያ ሰላይ የነበረ ነዉ ይባላል። ኖረ አልኖረ ያ አደለም ጉዳዩ። አሳሰቢዉ ግን፣ ግለሰቡ እዉነትን ምን ያህል ረግጧል ነዉ። ስለ ኢትዮጵያ እታገላለሁ ብሎ ወጥቶ የሗላ ሗላ ወያኔ ወደ ጎሳ ድርጅት ሲያዞሮዉ “እሺ”ብሎ በአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ወጥቶ በስሙ ተተከለ። ብእዴን በረከት ስማኦንን (ኤርተራዊ-) ኦሆዴድ ሰለሞን ጢሞ (ህወሓት-ትግሬ) ደሕአዴግ ቢተዉ በላይ (ህወሓት-ትግሬ) ሕላዌ ዮሴፍ (ብእዴን- ኤርትራዊ/ትግሬ)እነዚህ በደም በቋንቋ ወያኔ የሆኑ ሰዎች በተጠቀሱት ብሔረሰቦች እንዲወክሉ ማድረግ ተወካዮቹ (እነ በረከት)እና ወካዮቹ(እነ ስብሐትና መለስ) ከዉሸት ጋር ምንኛ እንደተጎዳኙ ሰዉ እንዴት ይህነን ለመረዳት የማያዳግት ሴራ መረዳት ያቅተዋል? ይሄ መሆኑ እያወቁ በረከት ሲሰበስባቸዉ ቅንድቡ እንደታሸ ቡችላ እየተርገበገቡለት በካሜራ ተቀርጸዉ ለታሪክ ማሕደራቸዉ ሲዘገብ ትንሽ አፍረት አይሰማቸዉም ወይ?
ጂ-20 ብለዉ ራሳቸዉን የሚጠሩ ቱጃሮች ሲሰበሰቡ በለንደን ላይ ተገኝተዉ ከየዓለማቱ የተሰበሰቡ በ IMF ላይ ቅሬታቸዉን ያስሰሙት ሰላማዊ ሰልፈኞች “ዓይጋ-ፎረም” የተባለዉ የመለስ ዜናዊ ዌብሳይት አዘጋጅ የሰልፈኞቹን ፎቶ በመለጠፍ “Anarchists and Anti Capitalist” በማለት ሰልፈኞቹን ሲዘልፍ ያነበባችሁ አንደኔዉ ተደንቃችሁ ይሆን?ይህ የህጻናት ድረ-ገጽ ስለ የካፒታሊዝም ትርጉም የገባዉም አልመሰለኝም። ጌታዉ መለስ ዜናዊ የካፒታሊዝም ስርዓት ሳይሆን “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” እንደሚከተል ያወቀዉም አልመሰለኝም። ወያኔ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አራማጅ መሆኑ እያወቅን ለማሞኘት ሲቃጣዉ “የወንዙን የዓድዋዉ ልጅ”መለስን ብቻ ለመከለከል ሲል ሊታመን የማይችል ጭፍን መከላከል እያደረገ ስመለከተዉ ልጁ ምን እሚሉት ሕሊና እንደተሸከመ ሁሌም ይገርመኛል። ልጁ የኢሐአፓ ታጋይ እንደመኖሩ መጠን የካፒታሊዝምና የሶሻሊዝም ልዩነቶች አበጥሮ ማወቅ ነበረበት የሚል ግምት አለኝ፡ነገር ግን የራሱን መሪ ለመከላከል ሲል ብቻ ኮሚኒሰት/ፋሺስቱ የመለስ ዜናዊን ስርዓት “ካፒታሊሰት“ አስመስሎ ሊነግረን ይሞክራል።
“የአብዮታዊ ዲመክራሲ መሰረታዊ መርሕ ደግሞ የተወሰነ መደብ ነጻነት በማርክሲሰት ሌኒኒስት ፍልስፍና በእዝ ኢኮኖሚ ላይ የተመሰረተ ነዉ። ይህም የሊቤራል ዲሞክራሲ የመሠረት ድንጋይ የሆኑትን የግለሰብ ነፃነትን፣ የግል ሀብት ባለቤትነትና ነፃ ኢኮኖሚ የሚፃረር ነዉ። በመሆኑም ወያኔ የሕዝብን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ነፃነት የገፈፈ ዘረኛ መንግሥት ነዉ። ፖሊሲዎቹ ከቀድሞዎቹ ሶሻሊስት መሪ ኢንቨር ሆጃ አመለካከት የተቀዱ ናቸዉ። (ተክሌ የሻዉ-ገጽ406)፤ በዛ ፍልስፍናም ነዉ መሬትን በመንግሥት ቁጥር ስር እንዲሆን ያደረገዉ።“መንግሥት”ማለት ደግሞ ልዩ ክስተት ማለት ሳይሆን “ወያኔ” ማለት ነዉ። ነጻ ገበያ የሚያራምድ አገር ደግሞ ከቶዉንም መሬት በመንግሥት ቁጥጥር ለማድረግ የማያስበዉ ነዉ። ታዲያ ጸረ-ካፒታሊዝም መባል የሚገባዉ-ሰልፈኞቹ-ወይስ የመለስ ዜናዊ “አብዮታዊ ዲሞክራሲ”የወያኔ መንገሥት? በዚህ አቋሙ “ጸረ ግለሰብ”-ስለሆነ-ግለሰቦች-ባላቸዉ ፖለቲካዊ አቋም “በቀጣሪዉ” “መንግሥት/ወያኔ” በሚያዝዛቸዉ-ወይንም"ባለንብረት-በሆነበት የእርሻ መሬቶች/መስርያቤቶች/ተቁዋሞች እንዳይሰሩ ተደርጓል/ታግደዋል።
“የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትና መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ ነዉ።"(የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ40(3)በሚለዉ ሶሻሊሰስታዊ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መርሕ መሠረት የተቃኘዉ ሕገ መንግሥት የሀብት ምንጭና መሠረት የሆነዉን መሬት መንግሥት (ወያኔ) በቁጥጥር ሥር አዉሎ ገበሬዉን ጭሰኛ አድርጓል። ይህም ነፃ ገበያ ዋልታ የሆነዉን የግል ሀብት በባለቤትነት የሚፃረር በመሆኑ ወያኔ ለነፃ ገበያ መርሕ ያልቆመ ተቃራኒ መሆኑን ያሳያል።
ወያኔ የገጠርና የከተማ መሬትን የመንግሥት እንዲሆን ያደረገበት ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች አሉት፣አንደኛዉ የሚያራምደዉ ርዕዮት የማርክሲስት የመርክሲሰስት ሌኒንስት ርዕዮተ ዓለም አካል የሆነዉ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መሆኑ ሲሆን፣ ሁለተኛዉ በመሣሪያ ተግል ያገኘዉን የፖለቲካ ሥልጣን ይዞ ለማቆየት ኢኮኖሚዉን በባለቤትነትመቆጣጠር የግድ ይለዋል። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ የኢኮኖሚዉ ምሰሶ-ግብርና ነዉ።85-በመቶዉ የሚተዳደረዉ በግብርና ነዉ። የህም ያገሪቱ ያኮኖሚ የጀርባ አጥንት ብቻ ሳይሆን አብዘዛኛዉ ህዝብ ኑሮ መሠረት መሆኑን አሳያል። ስለዚህ ወያኔ ይህን ሠፊ ሃይል በቁጥጥሩ ሥር አዉሎ የሥልጣን ማስጠበቂያዉ መሣርያ ማድረግ ካልቻለ ሲቋምጥለት የኖረዉ ሥልጣንና በእርሱም መሣሪያነት ኢትዮጵያ የመናድ ዓላማዉ ግብን አይመታም።…በሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚችለዉ መሬት በዜግነት መብት ሳይሆን በፖለቲካ አቋሙ መስፈርት ለደጋፊዎቹ ሲሰጥና ተቃዋሚዎቹ ወይንም ይቃወሙኛል የሚላቸዉን ሲከለክል ነዉ።”(የሥልጣን ተሻሚ ትግሬዎችና የ ኢትዮጵያ አንድንት ተክሌ የሻዉገጽ 407..)
አንጀቴ! የመለስ የነፃ ገበያ! እንዲህም ብሎ ካፒታሊዝም የለ! በባዶ ሜዳ የሚጮሁለት የመለስ ነፃ ገበያ-“ጉድ”አብዮታዊ-ዲሞክራሲ ቅራቅንቦ ዉስጥ ቀሚሱ ከላይ ካዋቂዎቹ ያነብነዉ በቅርብ ባገሬዉ የነበሩ የተሰቃዩ ያይን ምስክሮች ሰነድ ነዉ። እነኚህ የፈረንጅ አጎብዳጆች ግን እንደ “ሕዳር-ጽዮን እንደ አስተርዮ እንደ ቁልቢ በዓል” ወደ ለንደን እየሮጡ ተኳኩለዉ ሲመጡባቸዉ “እዉነትም የነፃ ገበያ ወኪሎች ይመስል “ኩሪቱ ኢትዮጵያ” ዛሬ፣ ዛሬ በነዚህ “የፈረንጅ ቡችሎች” ምክንያት ዜጎቿ “ፈረንጅ አምላኪ” እየሆኑ “ህሊናቸዉን” ሊያስገዙ ኮሚኒዝም እያራመዱ የካፒታሊዝም ሰባኪዎች ሆነዉ አዲሱን ትዉልድ በላቲን ቋንቋ እንዲጽፍ እያደረጉ ታዳጊ ወጣቶች ሕሊናቸዉ የሚያየዉ በነቀዘ “የልማት ስበከት” ሃብት እያካበቱ ዋነኛ ግባቸዉ ያገር ደህንነትና ኩራት መጣል ነዉ። ለዚህም ነዉ “የዛሬዉ ኢትዮጵያ ትዉልድ ለአዉሮፓ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አዉስትራሊያ ያለዉ ናፍቆትና ጉጉት እበረታ የሄደዉ። በቅኝ ገዢዎች ቀንበር ሥር ያለፉት አፍሪካዉያን ታዛቢዎች “አዉሮፓዉያን ቅን ገዢዎች “እኛን” የገዙት “አካላችንን” ሲሆን “ኢትዮጵያዊያንን” ግን “ሕሊናቸዉን” ነዉ” ከሚል ድምዳሜ እንዲደርሱ ያስገደዳቸዉ መለስ ዜናዊ ከነገሰ ወዲህ ነዉ።” (ሥልጣን ተሻሚ ትግሬዎችና የኢትዮጵያ አንድነት” ተክሌ የሻዉ ገጽ 390)።
የጎሳ ፖለቲካ ቀያሽ የሆነዉ ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከፈረንጅ ጋር መሮጥ የጀመረዉ ገና የዛሬ-33-ዓመት ሆኖታል።ከታሪካዊ ጠላቶቿ የተሰጠዉ የቤት ሥራ-ደግሞ በሚገባ እየተወጣዉ ነዉ።አንድነታችን ለማፍረስ የተላኩት “ኢሳያስ፣ መለስ፣ ስብሓትና ስዩም” እንደሆኑም አትዘንጉ።
“እጅ የሚያስቆረጥም ዶሮ-ወጥ ካሻችሁ
ኢሳያስ አፈወርቅ ከባረከላችሁ
ለመበለቱማ መለስ አለላችሁ”
(ምንጭ እንደላይኛዉ ገጽ 392) ያለዉን ያገሬ ገጣሚ ስንኝም ልብ በሉ።
www.ethioppiansemay.blogspot.com
Saturday, April 4, 2009
Subscribe to:
Posts (Atom)