Monday, October 16, 2023

መልስ ለኢትዮ-360 ስለ ቀይ ባሕር ጉዳይ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/16/23


መልስ ለኢትዮ-360 ስለ ቀይ ባሕር ጉዳይ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

10/16/23

 

በዚህ ጥቅስ ልጀምር

“There is no tomorrow and there was no yesterday; if you truly want to accomplish your goals you must engulf yourself in today.” ― (Noel DeJesus_

ነገ የለም ትላንትም የለም፤ ያለው ዛሬ ነው። ስለ ነገው ግብ ለማሳካት ከፈለግክ ዛሬውኑ እራስህን በጥረት ውስጥ ማስጠመድ የግድ ይላል። (ኖኤል ዲጀሱስ)

ይህ ትችት ሳቀርብ አብይ ያነሳውን ሓሳብ በመደገፌ << ቀለማቸው እያዩ በየቀለማቸው ረድፈው እንደሚከንፉ ኣዕዋፍነገዳቸውን እያዩ እየነጎዱ ያሉት የተቃዋሚ ጎራዎች ትችቴን እንደማይወዱትሳይታለም የተፈታ ነው ሆኖም እንደምታውቁኝ ተቃዋሚውም ሚዲያቸውም ሆኑ ጀሌዎቻቸው የለመደኩዋቸውና የማውቃቸው ስለሆኑጨዋታቸው አልቆ እኔ ወደ እምለው እስኪመለሱ ድረስብቻየን መጮህ መብቴ ነውና በዚህ እንስማማ።

ካሁን በፊት የግንቦት 7 ሲሳይ አጌናን፤ ታማኝ በየነን፤ ግንቦት 7 እንዳለ እና መሪዎቹ አንዳርጋቸውና ብርሃኑ ነጋኦነግድምጻችን የሰማ የውሃቢው እስላማዊው ቡድን ወዘተስቃወም በኔ ላይ ሲወርድ የነጎደብኝ ናዳ ይታወቃል። ሆኖም ግድግዳውን ብቻየን ለመግፋት አስቸጋሪ መስሎ ቢታይም አሸናፊ እንደምሆን ስለማወቅ እነሆ ተጋለጡና ብዙዎቹ እኔ ወደ እምለው ጎራ ገቡ።

ከዚያም አብይን መደገፍ ጀመሩ (ገንጣዩ ወያኔ በከፈተው ጦርነት እኔም ደግፌዋለሁ፤ መደገፉ ልክ ነበርና፤ አንዳንዶቹ እንዳልደገፉት ሸርተቴ መጫወት ጀምረዋል) ከዚያ በኋላ አብይ ክሕደቱን ሲያሳይመደግፍ አልነበረበትምና ደገፉትየቀጠሉትን ስቃወም ነበር። ውለው አድረው እነሱም ወደዚህኛው ጎራ መጡ። አሁን ደግሞ ቀይ ባሕር ጉዳይ ተነሳግድግዳው ለመግፋት እንደዘወትሩ ከባድ ቢሆንም ጉዳዩ እንደማይሞት ድመፅ ማስሰማቴን ይቀጥላል

ስለ ወደብና ስለ ቀይ ባሕር የይገባኛል ባለቤትነት ጥያቄ <<ለነገ በይደር ፤ለነገ፤ ለነገ>> ለምትሉ <<ነገ ዛሬ እንጂ ነገ የሚባል የለም>> ነገ ምን እንደሚወልድ አናወቅም፤ ነገን የሚወልድ ዛሬ ነው። ጉልበት ቢቀር ቢያንስ <<ሕጎችን ጠቅሶ ለሚመለከታቸው አቤት ለማለት መዘጋጀቱ ለምን በይደር ያድራል? ሕጎችን ጠቅሶ ለሚመለከታቸው አቤት ለማለት መዘጋጀቱ ለምን ማንኳሰስ ተፈለገ? አስፈላጊነቱ ምንድነው? የግድ ጥያቀው ስለ ጦርነት ብቻ ተደርጎ ለምን ይተረጎማል?

አብይ ጦርነት እንጀምር ካለአዋጋለሁ የሚል ካለ ይዋጋ መብቱ ነው። ነገር ግን መጀመርያ ያሉትን ሕጎች አሰባስበህ ወደ ተባባሩት መንግሥታት፤አፍሪካ ሕብረትና የመሳሰሉ ተቋማትና አገሮች ለድጋፍና ለሕግ ክርክር ማቅረብና መክሰስ እንዴት ነውስለ ቀይ ባሕር አንነጋገርም፤አይሆንየሚባለው?

አብይ አሕመድ መጥላት ሌላ ነገር ነው፤አጀንዳችን <<ቀይ ባሕር ሳይሆን የአማራ ሕልውና ማስረገጥ ነው ይላል ኢትዮ 360 ትንታጉ ሃብታሙ አያሌው። በዚህ ተቃውሞ የለኝም። የአማራ መገፋትና የሕልውና ትግል ከሃብታሙ አያሌው አስቀድሜ ስታገልበት የነበረ አጀንዳ ነው። ነገር ግን አብይ ሳለቀረበው ስለ ቀይ ባሕር እና የወደብ አገልግሎትና ባለቤትነት አንገብጋቢነቱ5 ክፍል ትምሕርት ተማሪ አደረገንብሎ ማናወዝና ፍሬ ነገሩን ለማጥላላት ማቃለሉ ለምን አስፈለገ? ፕሮፌሰሮች ሆይ 30 አመት እኮ ጠበቅናችሁ! ሌላ ቀርቶ አማራውንና ሰንደቃላማችንን እንኳ ማዳን አልቻላችሁም! ተቃዋሚ ሆናችሁ <<ነጭና ሰማያዊ>> ጨርቅ እያውለበለባችሁ ነበር አዲስ አበባ ውስጥ ስትቃወሙ የነበራችሁት፤ አደለም እንዴ? የያኔ ትችቶቼን አንብቡ።ሁሉም በነገ ነበር በይደር ሲከናወን የነበረው።

ነገ ምን እንደሚፈጠር ሁላ ስለ ነገ ስላልተዘጋጀን አላወቅንምና በደካማ ጎናችን ገብቶ ሥራውን ሳናይ ነበርና ድጋፍ የተሰጠው አብይ አሕመድ የተባለ ዲያብሎስ ብቅ ብሎ መጣ። ልክ ነው አደለም እንዴ? አጃጃለን ተጫወተብን። አሁንስ ቀይ ባሕር ስላለ ይጫወትብን ይሆን? የሚለው ጥያቄ ተገቢ ነው። በሰላማዊና በሕግ እስኪያደርገው ድረስ ግን እንጠብቅና ያኔ ትችታችን ይቀጥላል። እስኪይሞክረው፤ ያሳየንማለት ለምን ይከብዳል?

የግድቡ ጉዳይ ዲሞክራሲ ስለሌላ መጀመርያ ዲሞክራሲ ይመስረት እያልን ተቃዋሚው ግድቡን እስኪበቃው ሲቃወም ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ግድቡ እየገፋ ሲመጣሰከንብሎ ተቆርቋሪ ሆኖአብይ አሕመድ ግድቡን ሸጠው! ሸጠው!” እያሉ ዋና ተቆርቋሪዎች ሆነው እያደመጥን ነው።

ትናንት በለጠፍኩት ክፍል 1 ላይ አብይ አሕመድ እንደማንኛችሁም እቃወመዋለሁ፤ እንኳን ኤርትራን መውጋት ቀርቶ ዜጎቻችን ገድላ ሕጋዊ ድምበራችን እና ለም መሬቶቻችን የወሰደቺው ሱዳን መውጋት አልፈለገም። ያንን አውቃለሁ። ነገር ግን የባሕር በርን በሚመለከት ኢትዮጵያን የሚደግፉ ሕጎች ሁሉ በሕግ አዋቂዎች ተዘጋጅቶ ወደ እሚመከታቸው አለም አቀፍ የሕግ ተቋማት ስለ የባሕር ወደብ መዘጋትና ማስከፈትን አስመልከቶኢትዮጵያ 30 አመት የተፈጸመባት አለም አቀፋ ወንጀልአቤቱታ ቀርቦ እንዲታይ እንነጋገርበት ማለት ሃሳቡን ማንቋሸሽን ምን አመጣው? እስኪ ሞክረው እንይህ ማለት እንዴት ይከብዳል? አብይ ሞላጫ ነው፤ ግን እስኪ ምላሱ በዚህ ተመልሶ ይቆርጥምና እንደገና እንየው። ወደ አለም አቀፍ ሕግ የሚሄደው አሱ እንጂ እናንተ ከኔ ጋር አላለም፤ ቢላችሁ ጥሩ ነው። እውነታውን ትነግሩናላችሁ።

አማራዎችም ሆኑ እኛ ደጋፊዎቻው የአማራን ሕልውና ለመታደግ የተጀመረው ትግል ቆሞ ስለቀይ ባሕር እናስቀድም ያለ የለም። ትግሉ ይቀጥል፡ ግን አብይን ለመጣል ሥራችሁን እና መተኮሳችሁን አቁሙ ያለችሁ የለምና፡ አብይ ደግሞ ስለ ወደብ ጉዳይ በዲፕሎማሲው በኩልና በሕግ ትግሉን እጀምረዋለሁ ካለብርታቱን ይስጥህ እስኪ እንይህማለት አይበጅም?

 

ከዚህ አልፎ << ይህ ከተነሳ ኤርትራኖች እንደዋዛ እንዳይመስልዋችሁ ተቃወሚውም የኢሳያስ ደጋፊም አንድ የሆናሉ ወዮላችሁ ብሎ 360 ትንታጉ ሃያሲ ሃብታሙ አያሌው የሚናገረው ንግግር ምን ማለት ነው? የምን ጥብቅና እና መስፈራራት ነው? ኤርትራኖቹ ወደ ተባባሩት መንግሥታት ክስ ለምን ተመሰረተብን ብለው ኢትዮጵያን መውረር ከጀመሩና መንፈራገጥ ከጀመሩ አንተ ዝም ብትል እኛስ ዝም እንላላን ብለህ ታስባለህ? በትግራይ ጦርነት እኮ አይተነዋል! አንድ ሰው አይገባለትም እየተባለ የሰሜን ዕዝ ተጨፈጨፈ ሲባል ያየነው የቅርብ ትዝታ ነው።

ኤርትራኖች ስለ ባሕር ጉዳይ ሲነሳ አብይም ያንሳው ሰይጣንም ያንሳው አንተ ሃብታሙ አያሌውም ጉዳዩ ነገ አንሳው የኢሳያስ ደጋፊም ተቃዋሚ የኤርትራኖች አንደ ተረገጠች አይጥ ግምባር ፈጥረው ሁሉም እንደ ተረገጠች አይጥ <<ፂው ፂው>> ማለታቸው አይቀርም (ልምደናቸዋል) ግን ሁሉም ግምባር ስለሚፈጥሩ ስለዚህወዮላችሁ ብሎ ማስፈራራት (ማሳሰቢያ?) ምን ማለት ነው? ነገን ዛሬም <<ፂው- ፂው>> ማለታቸው ስለማይቀር ይልቁኑ እነሱን ማባባሉን ይቆይልን እና ወደ ሕግ እንዲቀርብና ሕያውና መሰረት ያለው ድንጋይ እንድንጥል ለነገው ዛሬ እንዴት እንጀምረው? ማንስ ቢጀምረው ያምራል? አለም አቀፍ መድረክ ሲጮህ የሚደመጠው ከተቃዋሚው ይልቅመሪ” (ሕጋዊም ሆነ አልሆነ) የሚደመጠው መሪ ነው!

360 ትንታጉ ሃያሲ ሃብታሙ አያሌው ያደመጥኩትን (Zare Min Ale "የብርሃኑ ጁላ ሠራዊት መፈራረስ እና የቀይ ባህር ፖለቲካ የጀርባ ገፅ" Saturday Oct 14, 2023) በሚለው ክፍለ ጊዜው ትንትናው እንደዘወትሩ ብወድለትምሁሉም ኤርትራኖች ይነሱብናልአይነቱ ማሳሰቢያናነገ የሁለቱ አገሮች ባንዴራ እጅ ለእጅ ተያይዘን እናውለበልባለንየሚለው ሕገ ወጥ የሃብታሙ ንግግር ባይደግም ጥሩ ነው። ለሌሎቹ ባላውቅም ለኔፅያፍንግግር ነው።ካሁን በፊት በዚህ ጉዳይ የሃብታሙ አያሌው አይነት ንግግር ሲናገሩና ሲጽፉ የተቸሁዋቸው የማከብራቸው ውድ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ (ነብሳቸው ይማርልን) እንዲህ ብየ ጽፌ በኋላ ያንን መጻፋቸው እና የኔን መልስ አንብበው በግል እንደተቆጩና እንደገባቸው ነግረውኛል።

ከሰፊው ጽሑፌ መግቢያዋን ትንሽ ልጥቀስ እንዲህ ብየ ነበር፡

<<የተከበሩ ፕሮፌሰር ሆይ!

ለእርስዎ ያለኝ አክብሮት ዛሬም የተቀነሰ ስላልሆነ አክብሮቴ እንዳለ ሆኖ ቅር የተሰኘሁበዎትን ትችትዎትን ለመተቸት እፈልጋለሁ። በቅርቡየሰሞኑ ሁኔታበሚል የተቹበትን ሁኔታ አንብቤ እጅግ ካዘንኩበዎት አንዱ ይኼኛው የከፋው ነው።አለፍ እያልኩ ካልሆነ እንደው ልጥቀስ ካልኩኝ አንጀቴ ስለሚቃጠል ጥቂቶቹን እምነትዎን ብቻ ልጥቀስ።ዶክተር ዐቢይ አሕመድበሚል ንዑስ ርዕስ ውስጥ እንዲህ ያሉትን ሃሳብዎ ልጥቀስ፡-

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በቅርብ ጊዜ በባንዲራው ምክንያት ስለተነሣው ብጥብጥ የተናገረው ብዙዎችን አስቈጥቷል። ይኸ ብቻ አይደለም፤ የኢሕአዴጉ መሪ የኢሕአዴግን ባንዲራ ሲያውለበልብ ሲያዩም የሚገረሙ አሉእነዚህ ሰዎች የኢትዮጵያ ባንዲራ በመንግሥት ደረጃ 1964 . . ጀምሮ ሁለት ጊዜ እንደተለወጠ ልብ አላሉትም።ብለዋል።

የወያኔው ፋሺስት እና አሁን ያለውየዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ የራስዎ /ሚኒስቴር አብይ አሕመድ ቡድን እያውለበለቡት እና እያከበሩት የሚታየው ሰንደቃላማ ሕጋዊ ነው ብለን አልተቀበልነውም። ትክክለኛ የመገለጫ ቃልኢሕጋዊነው። ትናንትም ዛሬም ለወደፊቱም ሕጋዊነቱን አንቀበለውም (በግልጽ አነጋጋር ኢሕጋዊ ነው) ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ ቡድኖች የቀረጹት ሰንደቃላማየአገሪቱን እሴቶች ለማፍረስ የታገሉ እና በተግባርም ጣሊያን ያቀዳቸው ፖሊሲዎችን የተገበሩ ስለሆኑ ሰንደቃላማን በሚመለከት የወስደዋቸው እርምጃዎችበሙሉጸረ ኢትዮጵያ ስለሆነ ሕጋዊነቱን እርስዎ እና የሚጋሩዎትን ቡድኖች ካልሆነ በስተቀር በኔ በኩል ሕጋዊ አይደለም።

ሰንደቃላማ ለዋጩ ባንዳው መለስ ዜናዊለሰንደቃላማው መለወጥ ምክንያት ሲገልጽከሰንደቃላማው በስተጀርባ በመቃወም ነውብሎ ነግሮናል። በስተጀርባ ያለው ማን ነው የሚለው እራሱ መለስ ሲነግረን? “አማራ፤ኢትዮጵያ እና ኦርቶዶክስ የፓርላማው አጽዳቂዎችም እነዚህ በስተጀርባ የተባሉትን ክፍሎች እየጠቀሱ የተናገሩዋቸውን ንግግሮች በሙሉ ቱቡበተንቀሳቃሽ ምስል እና በድምጽ ተቀርጾ እየታየ ነው። ፋሺስቶቹ ያጸደቁት ባንዴራ የነዚህ ሦስት ክፍሎች መብት እና ሕግ በመጣስ የተሰራ ሰንደቀላማ ስለሆነ ሕጋዊ አይደለም።>> ብየ ቅሬታየን ጽፌ በድረገጽ ተለጥፎ ነበር።አሁንም የማከብረው ሃብታሙም ሆነ ሌሎቻችሁ እንዲህ አይነት ንግግር አንዲያሰውኑ የደከመው የዚህ ትውልድ ወጣት ሕሊና ማለማመድ ብንቆጠብ እመክራለሁ። እንዲያውም እኮ ጎንደር ቴድሮስ አደባባይ ሃውልቱ ዙርያ የሻዕቢያ ባንዴራ ተከለውበት እነሱም ለብሰው እስክስታ ሲጨፍሩ 2 አመት በፊት ይመስለኛል (ካልተሳሳትኩ) በቪዲዮ አይቻለሁ። በማጭበርበር፤ ገጉልበትና በሴራ የተተከለው -ሕጋዊ አገር እና -ሕጋዊ ባንዴራአለም አጽድቆታልሕጋዊ ነው ብላችሁ ስለ ኤርትራ (ሻዕቢያ) ባንዴራ ማክበርና መውለብለብ ካልቀፈፋችሁ ማክብርን የራሳችሁ ጉዳይ ነው፡ በኔ እና በመሰሎቼ ግንየማይጠጉት ግምእናኢሕጋዊነው።

እነሱወደቦቻችን እና ነፃነታችን በጉልበት አገኛናትእንደሚሉት እኛም ሕጉን ሞክረን ካልተሳካ << አንድ ቀን ቴድሮስን፤ አሉላን፤ ዮሓንስን፤ ሃይለስላሴን መንግሥቱ አይነቶች መሪዎች ሲወለድ በሕግ ወይንምበጉልበት የሄደን በጉልብት እስኪመጣ>> የሚገባንን ካገኘን በኋላ በዛው እንቀጥልና የየራሳችን እናውለብልብ ካሉ ያኔ እንስማማለን።

አብይንም ሆነ ወያኔን በጠመንጃ ለመቃወም ስለፋበት የነበረ አጀንዳየ ነው፤ የብረት ትግሉ ይቁም ያለ የለም፤ ይቀጥል፤ በተጓዳኝም የሕጉን ነገር እንደ መለስ ዜናዊ እንደ ግድቡ የወደቡን ጉዳይም በሕግ መጠየቅ እጀምራለሁ ካለ አብይንይቅናህማለት ነው። ጦርነት ለማስጀመር ነው የሚለው ጫጫታ <<ፂው ፂው>> ማለት አያስፈልግም! <<፡የትም ፍጪው ብቻ ዱቄቱን አምጪው!!!>>

በሰላም እንሰንብት

ጌታቸው ረዳ