Tuesday, January 19, 2021

“በዙ ወጪና ጊዜ የሚሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያን እንዲያውቋት “ሃ” ብለው እንዲማሩ አዲስ ት/ምህርት ቤት ካልተመሰረተ አለን እያሉ አገሪትዋንም እየናዱ እነሱም በቁም የመፍረሳቸው ክስተት ቀጣይ ነው!” (የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው) 1/19/2021 ትንተና በጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethopian Semay

 

 

በዙ ጪና ጊዜ የሚሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያን እንዲያውቋት “ ብለው እንዲማሩ አዲስ ት/ምህር ቤት ካልተመሰረተ አለን እያሉ አገሪትዋንም እየናዱ እነሱም በቁም የመፍረሳቸው ክስተት ቀጣይ ነው!”

(የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው)  1/19/2021

ትንተና በጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethopian Semay

 


ጥቅስ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፤ ተወናይና የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊት ዓለም አቀፍ ሞዴሊሰት የሐረር ወርቅ ጋሻው (የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው)

በርዕሱ የተመለከተው ጥቅስ የተናገረቺው ከላይ የተጠቀሰው የሐረር ወርቅ ናት።እንደምናውቀው ከ1966 ዓ፣ም ጀምሮ ወደ ፖለቲካው መድረክ የተከሰቱ የኢትዮጵያ ምሁራን ራሳቸውን ሲያዩበት የነበረው መስተዋት የትምህርት ቤታቸው ዘመናዊው መስተዋት እንጂ ያደጉበት ማሕበረሰብ መስተዋት አራሳቸውን አዋህደው ለመመልከት ሰላልጣሩ በኢስያ፤ በምስራቁና በምዕራቡ አገር የቀሰሙትን ትምህርት ብቻ በመመራት ሕዝባችን እርስ በርስ እንዲገዳደልና እንዲለያይ አድርገዋል።

አስረጅ የተባለ ሎስ አንጀለስ ሲታተም የነበረ የቆየ መጽሔት የኢትዮጵያ ምሁራን ምን እንደሚመስሉ የተነጋገሩትን ጠቅሼ ላስጨብጣችሁ፡

ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤

የሰሞኑ የሎስ አንጀለስ አካባቢ የኢትዮጵያውያን ውይይት ከኢሕአዴግ እንዴት ዲሞክራሲ ይገኛል የሚለውን ጉዳይ አስመልክቶ ነው። አንዱ የተሟጋች አይነት ‘ከወያኔ ዲሞክራሲ ይገኛል ብሎ ማሰብ ‘ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች እንደደተባለው፤ ነው፡” ብሎ ትችቱን ሊቀጥል ሲያዛጋ አንዱ የኢሕአዴግ ደጋፊ የስብሰባውን ሰብሳቢ ፈቃድ ሳይጠይቅ ከመቅጽበት ብድግ ብሎ “ወንድሜ ንግግርህ ልፊ ያላት ውርንጫ እናትዋን ተከትላ ገበያ ትወጣለች እንደተባለው አይነት ነው፡ ‘ቆለጥ’ አዲስ አበባ ላይ ወደቆ ይገኛልና ሞኝ አትሁን” ብሎ አደናገረው” ይላል መጽሔቱ ከስብሰባው የዘገበው ንግግር፡

 እነሆ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ባለ የእርስበርስ ልፊያ እየገቡ የሕዝቡን መከራ ለ30 አመት አስፍተው አባባሱት።ያኔ ‘ቆለጥ’ አዲስ አበባ ላይ ወደቆ ይገኛልና ሞኝ አትሁን” ያሉት እነሆ ዛሬ ከ30 አመት በሗላ ዝንጀሮ ዋሻ ውስጥ ገብተው በመጫኛና በቃሬዛ እየተጎተቱ ፍጻሜአቸው በእንሰሳት አለም የሚታይ ትራጀዲያዊ ፍጻሜ ሆነው ኢትዮጵያንም በሚያስጨንቅ የገደል ጫፍ አስቀምጠዋት እነሆ ለማመን በሚከብድ “አልጋ ቢሉዋቸው አፈር ተመኝተው” በአስገራሚ ስንብት ተሰናበትዋት።

አገራችን እንዲህ ባሉ የምሁራን እንሰሳዎች እየታወከች እስከመቸ እንዲቀጥሉ በቸልተኛነት እንፈቅዳለን? በጣም ጥቂት ሰዎች አገራችን እየተናጋች ነች እያልን ጥቂቶቻችን ስንገልጽ ነበር። የጥቂቶች ድምጽ በማፈን ከፈተኛ ሚና የነበራቸው የዘመናዮቹ ባለሥልጣኖች ብቻ ሳይሆኑ በሚገርም ሁኔታ ከጠላት ጋር እየተሞዳሞዱ አሁን ላለነው አስቸጋሪ ሁኔታ የዳረጉን መሪ ተዋናዮቹ የነበሩት በተቃዋሚው በኩል የተሰለፉ ውጭ አገር የሚኖሩ የፖለቲካ መሪዎችና ብዙዎቹ የተቃዋሚ የዜና ማእከሎች/ሚዲያዎች ናቸው።

በወቅቱ እኔም ሆንኩ የሐረር ወርቅ በተደጋጋሚ ያሰሰብነው ነገር ቢኖር “ለውጥ ከመጣ እኛን የሚታገሉን ዛሬ ከኦነግና ከመሳሰሉ የነ ጃዋር አምላኪ አክረሪ እስላሞች ጋር እየተሞዳሞዱ በየ አዳራሹ ስለ አክራሪዎቹና አገር አፍራሾቹ “ስለ አፍቅሮተ ኢትዮጵያዊነታቸውን” እየሰበኩና እየመሰከሩ የነበሩ ፖለቲከኞችና የድረገጸና የራዲዮን ጋዜጠኞች የዲያስፖራውን ማሕበረስብ እያጃጃሉት ያሉ ክፍሎች ናቸው” ብለን ነበር! ያኔ ገና ይህ ለውጥ ከመታየቱ በፊት ዱሮ! ገና ድሮ!። እነሆ አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛው መንገድ ሲገቡ አንዳንዶቹ ግን አገር  ቤት ካለው “ኢ ቲ ቪ”  ብሰው የተረኞቹ የውጭ አገር” ኢቲቪ” ቱለቱላዎች ሆነው አረፉት። ይሆናሉ ብለን የተነበይነው ቃል እ ያልነው እውን ሆኖ አየናቸው!   

እነሆ ልክ እንዳልነው “አንዳንዶቹ የጭባሪዎቹን መጫሚያ ጫማ ሰር ወድቀው ሥልጣን ላይ እስካሉ እስከመጨረሻ ሕይወቴ አገለግለዎታለሁ ብለው ቃል ገብተው ሲሳለሙ፤ዛሬ ያ ሁሉ ግፍ እየወረደም ቢሆን ፈራ ተባ እያሉ ድፍረት አጥተው ድምጻቸውን ላለማሰማት ድምጽ አልባ “አሽከርነትን” የመረጡ “ሁለቴ የታዩ” ማፈሪያዎች እና እንዲሁም ፤ ከነዚህ ማፈሪያዎች ጋር አብረው በየአገሩ አዳራሾች እየዞሩ ‘ኢትዮጵያ በኮሎኒ ይዛናለች’ ብለው ሲሉ የነበሩት ኦነጎች ሮጠው አገር በመግባት አሁን ላለው የኦሮሙማው መሪ አጋርነታቸው በመግለጽ ተረኛነታቸውን ለማጠናከር የፋሺሰቱ መሪ “የግል አማካሪ” ሆነው፤ እነሆ እኛን ሲያፍኑና የሕዝቡን ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ወደ ጭቃ እየረገጡ፤ የክርስትያን ማተብ በፖሊሶቻው እየበጠሱ እነሆ ሕዝቡ በተረኛው የጅማው አገር በቀል ቅኝ ግዛት መሪ ሥር ወድቆ እነሆ ለሁለተኛ ዙር ለዋይታና ለእሪታ ዳረግዋት።

እነሆ ጥቂት የቁርጥ ቀን ልጆች ወደ ወህኒ በተረኞቹ ታፍነው ታስረዋል።  አብዛኛዎቸ ምሁራን ተብየዎች ግን ዛሬም ይህ ሁሉ የአገር ውርደት የባሰ ገፍና ልቅሶ እያዩ ጀሮ ዳባ ያሉ ብዙ በሚሊዮኖች ናቸው። ምሁራኖቹ በሕዝባቸው በነገዳቸው እንኳ ልዩ የዘር ጭፍጨፋ ግፍ ሲደርስበት ጭጭ ብለው ለ27 አመት ቃል ያለመተንፈሳቸው ሲገርምን፤ ዛሬም ሕዝቡን በማንቃትና ለዘመናት ሲሰበኩ የነበሩ የጠላቶች የውሸት ፕሮፓጋንዳ በሚያስደንቅ ብስለትና ምርምር ጠላቶቹን በሰላ ብዕሩ ያሸማቀቃቸው አቻምየለህ ታምሩ ከፌስ ቡኩ በተደጋጋሚ በሴራ እንዲታገድ ሲደረግ ምሁራኖች እና የሕግ ጠበቆች ተሰባስበው ይልተማረውን ማሕበረሰብ በመጥራት ፌስ ቡክ ዋና መ/ቤት በመምጣት ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግ አልቻሉም። እኛ ከምሁራን የምንጠብቀው የነሱ ወደ ግምባር መምጣትና እኛም በጥሪው መሰረት ድምጽ እንድናሰማ እና ሁኔታውም በሕግ እንዲታይ ያደርጉ ይሆናል ብለን ሰንጠባበቅ ዝምታን ለምን እንደመረጡ አስገርሞኛል።

 የትግራይ ሕዝብ ማፈሪያ የሆኑ የወያኔ የነ አሉላ ሰለሞን የሩዋንዳ መሳይ ጥሪ በፌስ ቡክ ሲተላለፍ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሕግ እንድንጋፈጠው ጥሪ አቅርቦ አንድም ምሁር መልስ ሳይሰጥ በመቅረቱ ስመለከት እውነትም የዚህ አገር ምሁራን የኢትዮጵያ ወርቅ ጋሻው እንዳለቺው በዙ ጪና ጊዜ የሚሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያን እንዲያውቋት “ ብለው እንዲማሩ አዲስ ት/ምህር ቤት ካልተመሰረተ አለን እያሉ አገሪትዋንም እየናዱ እነሱም በቁም የመፍረሳቸው ክስተት ቀጣይ ነው!”

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethopian Semay