Wednesday, September 25, 2019

አየ መምህርት መሰረት አበራ! ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)


አየ መምህርት መሰረት አበራ!
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
የግብጾቹ የነ ጃራ የነ ኦነግ ባንዴራና ምስል ለብሰሽ ላማረብሽ መሰረት ሆይ!
የፌስ ቡክ ተከታዮቼ መልስ ከመጻፌ በፉት እኔ የአብንም ሆነ ያማንም ፓርቲ/ድርጅት አባል እንዳልሆንክ ይታወቅልኝ። አሁን ወደ ፀሓፊት መሰረት አበራ (አዲስ አበባ) ጥቅጥቅ ጽሑፍ ልውሰዳችሁ። በፌስ ቡክ ለማግኘት ጌታቸው ረዳ ብላችሁ ፕሮፋይል ጉግል ብታደርጉ ታገኙኛላችሁ። ድረገጼም ኢት ሰማይ ብላችሁ ማየት ትችላላችሁ።

“የአማራ ብሄርተኝነት ስንክሳር እና ያዘለው አደጋ (በመስከረም አበራ)September 25, 2019” በሚል ጽሑፍ ሳተናው ላይ ወጥቷል። የኔ ጽሑፍ በሳተናው ስለማይወጣ በራሴው ነፃ መድረክ ላይ ወጥቷል። መሰረት አባራ በብዙ መልኩ ታስገርመኛለች።
“የአማራ ብሄርተኝነት ስንክሳር እና ያዘለው አደጋ (በመስከረም አበራ)September 25, 2019” በሚል ጽሑፍ ላይ
እንዲህ ትላለች:-

“የአብን በአማራ ምሁራን ዘንድ ሞገስ ማጣት፡የአብን ቁጥነትና ፖለቲካዊ ክህሎት ማነስ…” እያለች የምታሳምረው ግሩም አማርኛዋ/ ተችትዋ/ ግራ ያጋባል።

ለመሆኑ የአማራ ምሁራን የምትያቸው ከቁጥነት የተቆጠቡ ትሁት አንደበቶች 28 አመት ሙሉ በትሁትነታቸው የማን ጸጉር ሲያበጥሩ ነበር? መልስ ቢኖርሽ ብትነግሪኝ ደስታውን አልችለውም። አንቺ እኔን ላታውቂኝ ይሆናል፤ 28 አመት ሙሉ ከቁጣ የራቁ እና በፖለቲካ የተካኑ ጠበብቶች (ላንቺ ደስ እንዲልሽ) ያንቺው ባለ ለዛዎቹ ምሁራን አማራ ‘እባካችሁ ሕዝባችሁ ችግር ላይ ነው ተንሱ ‘ ብየ ብኮርኩር ብኮረኩር ጀሮ ዳባ ብለው ሲያንኮራፉ የነበሩ ያንቺው “ምሁራን አማራ”  ኦነግን እና የግንቦት 7 መሪዎች ሲያቆለጳፕሱ“ ነበር የዘበኑት።  የምሁራን አማራ ሞገስ ያጣ ብለሽ የምታንኳስሺያቸው የአብን መሪዎችን ከመጠበቅ “ቁጡ ያልሆኑ ባለሞገስ አማራ ምሁራኖችሽ” ሜዳውም ፈረሱም ይኼው ክፍት ነው ለምን ባለ ሞገሶቹ ምሁራን “አብን እንዲታሰርላቸው እና እንዲከላከልላለቸው ይጠብቃሉ?“

ብስለት የሌላቸው ቁጡዎች” ብለሽ የምታበጥሪያቸው “የአብን ወጣቶች” የሚመራቸው ምሁር አማራ ስላልነበረ ራሳቸውን ማደራጀት ጀምረዋል። ይሰንፍጣቸው ይምረራቸው ሜዳው ክፍት ስለነበረ ያንን ሜዳ ይዘውታል። አንቺ ምሁራን አማራ የምትያቸው አብን ማበረታታት እና መምከር፤ማገዝና ማረም ካልቻሉ አንቺ እንደምትይው ‘አማራጭ’ ብለው ወደ ደመቀ መኮንን (የወያኔና ኦነግ አሽከር) ከሄዱ ተወቃሹ እንዴት አብን ሊሆን ይችላል? 


ልጥቀስ እንዲህ ነበር ያልሺው፦

“በዚህ መሃል ከኦሮሞ ብሄርተኝነት መጦዝ የተነሳ የአማራ ብሄርተኝነት እንዲኖር የሚፈልገው የተማረውን ጨምሮ በርካታው የአማራ ብሄር ተወላጅ ወደ አዴፓ እንዲያዘነብል እያደረገ ነው ፡፡”

አብን ጠልቶ ወደ ኦነግ አገልጋይ መሄድ ከመረጠ ድሮም ከእጅ የማይሻል ዶማ ስለነበር የሚያመጣው ለውጥ የለም። አንቺ የምታሞግሺያቸው አማራ ምሁራን “የአብን ቁጥነት ጠልተው፤ ችለታቸው መዝነው ” አዴፓ ጋር ሆነው ከነ አበራ አዳሙ ጋር ሆኖ  አማራውን ማሰርና ማሳሰር ካማረው ምሁሩ መንገዱ ጨርቅ ያድርገለት እላቸዋለሁ።”

አስገራሚ የሚያደርገው ጽሑፍሽ ደግሞ የሚከተለው ነው።-

“….ይህ ሳይሆን ቀርቶ ውህዱ ፓርቲ በሲቪክ ፖለቲካ ስም ለተረኛ ነኝ ባዩ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ሸብረክ የሚል ከሆነ የአማራ ምሁራንም ሆኑ ሌላው አብንን ለመቀላቀል እየተሸኮረመመ ያለው አማራ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ አክራሪ ብሄርተኝነት መንጎዱ አይቀርም፡፡” ብለሻል

አብን አክራሪ ነው በለሽ ስትከሺ በሽብረተኝነት /አክራሪነት/ ስም እየለጠፈ በየ ጨለማ ማጎርያ ቤት እያሰቃያቸው ያሉትን የአብን አመራሮችና አባላት “አክራሪዎች” ናቸው ብለሽ በይፋ ስለወነጀልሺያቸው ሰሞኑን ያመሰገንሺው “ያንቺው ሰዋዊ፤ሰዋዊ የሚሸትሽ አብይ አሕመድሽ” ስለ አብን አክራሪነት የምታውቂውን ለፍርድ ቤት ለምስክርነት ሊጠራሽ ስለሚችል ተዘጋጂ።

“ይህ ደግሞ የአማራ ክልልን ምናልባትም ታጣቂ ሸማቂዎች ጭምር የሚንቀሳቀሱበት ግልፅ የአመፅ ቀጠና ሊያደርገው ይችላል፡፡” ብለሻል

በፋሺሰቶች ላይ የትጥቅ ትግል አመጽ ማድረግ በየትኛው መጽሐፍ ያገኘሺው ሕግጋት ነው አንቺ አመፅን የምታወግዢው? 

መልካም የፍርድ ቤት ምስክርነት እንዲሆንልሽ እመኛለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)