Wednesday, November 17, 2021

ዛሬ ደግሞ ኢንተርሃሙዌው እጅግ የምወዳትን እህቴን አስሯታል! ጌታቸው ረዳ ዕለተ ዕሮብ 11/17/2021 ETHIO SEMAY

 

ዛሬ ደግሞ ኢንተርሃሙዌው  እጅግ የምወዳትን እህቴን አስሯታል!

ጌታቸው ረዳ

ዕለተ ዕሮብ 11/17/2021

ETHIO SEMAY

አገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለው “በነገድ ለይቶ የማጽዳት” አዋጅ ካላሰጋችሁ ፡ አገር ከፈረሰ ወዲያ መቆጨት ግን ምንም አይረባም። አገራችሁ ከእጃችሁ እያፈተለከች ነው።

በሌሎቹ እየተበሳጨሁ መሆኔን ስለሚያውቁ ደብቀውኝ ኖሮ፤ የተቀሩትም ፍርሃት ውስጥ ስላሉ “ትታው የሄደቻት” ህጻን ስላለች እያለቀሰች ስታስቸግራቸው እንንገረው ብለው ሁለት ቀን ይሆናታል እህቴን አስረዋታል ብለው ነገሩኝ። እስካሁን ድረስ በጠቅላላ ወደ 3 ቤተሰብ ተይዘውብኛል።ሌሎቹም ይታፈሱ ይሆናል።

ይህችኛዋ ደግሞ ምንም አታውቅም። በህይወትዋ ፖለቲካ የሚባል አልነካትም።ፖለቲካ ወያኔ ምን እንደሆነ የማታወቅ ከአዲስ አባባ ወደ ባሕርዳር ለሥራ ሄዳ 15 አመት ኖራለች።

አገሬ ብላ በኖረችበት አገር ልክ በዘመነ ናዚ “የጀርመን ጌስታፖዎች” ቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ አይሁዶችን ሲያጸዱ በነበረበት መልክ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ከደርግ ዘመን በባሰ ‘በአዋጅ” /ኦሩሙማው እና አማራዊው እንዲሁም ለዚህ ቡድን ያደሩ ጥቂት የትግሬ ኢንተርሃሙዌ ቡድኖች/ በጋራ ባሳለፉት “ንጸሁ ትግሬን” የማጥፋት አዋጅ፤ “ከማስር አልፈው”፤ አስረው “ከስራ የማፈናቀል’’
ስልት እየገፉበት ነው”።

ምንም የማታውቅ ዜጋ እቤትዋ ድረስ መጥተው መታወቂያ ጠየቅዋት፤ ትግሬ ይላል፡ ያለ ፍርድቤት የመያዣ ወረቀት “እየገፈተሩ ወሰድዋት”። ሦስት ታዳጊዎች እና ህጻን ልጅ ትታ ታስራለች።  እነሱም በፍርሃት ህጻኑን ይዘው ተራቸው እየጠበቁ ነው።

ሁሉም ምንም የፖለቲካ ንክኪ ሌላቸው ናቸው። ማንም እርግጠኛነት መልስ ሊያገኝ የማይችለው ጥያቄ የሚከተለው ነው። እናንተ “ብልጽግና” ብላቸሁ የምታቆለጳጵስዋቸው “ኢንትረሃሙዌው  ኦሮሙማው እና አማራዊው ኢንተርሃሙዌው ቡድን” ንጹሁን ትግሬ በማፈን “ኢትዮጵያን” ማስቀጠል ይቻላቸዋል ወይ? ነው ጥያቄው።

መልሱ “ባለፈው ሁለት ሳምንት እንደነገርኳችሁ” የሆነ ታአምር ካልተከሰተ “ኦሮሙማው ኢተርሃሙዌው እና አማራዊው ኢንትርሃሙዌው ቡድን” ተሎ ከሥልጣን ካልተወገዱ ትግሬ እንደ ኢትዮጵያ የመኖርዋ ሁኔታ “ተደምድሟል”።

ኢንትርሃሙዌው ሳይታወቀው ለፋሺሰቱ ወያኔ ትልቅ ስጦታ ነው እየተሰጠ ያለው። እኛ ኢትዮጵያ ነን የሚሉትን እያስቆጣ ሙጥጥ ብሎ “ትግራይ ትዕወት፡ (ትግራይ ያሸንፋል/ ትግራይ ትገንጠል/ ወደ እሚለው “ካምፕ” ጡንቻ እንዲያገኝ እየተደረገ ነው። የኤርትራ  “አገር ፍቅር” “የአንድነት ማሕበር” በመጨረሻ እንዴት እንደሟሸሸ የሚታወስ ነው።

አዝናለሁ፡ ግን እውነታውን ስነግራችሁ ላትወዱት ይሆናል፤ ወይንም እንደ “ሱስ” የተያዘው ትግራይ “ትሂድ ትገንጠል” “ምን ልትበላ ነው? ድንጋይ ልትበላ ነው” ወደ እሚለው የጨቅላ አስተሳሰብ ታራግቡ ይሆናል፡ ከቦታ አትኖሩበትምና፡ “እውጭ አገር የምትኖሩ እንደ “ትሂድ ትገንጠል፡ “ቀላል” ሊሆንላችሁ ይሆናል። አገር ውስጥ የሚኖር ያንን አይመኘውም። ሰበቡ እንደ ፌስቡክ ቁጭ ብሎ መሞነጫጨር ቀላል ሳይሆን፤ ትግሬ ስትገነጠል፤ አማራው ኦሮሞው ሶማሌው ይከተላል፡ “ቻው ቻው” ይሆናል!  ዕልቂቱ ቀጣይ ይሆናል፤ ኢትዮጵያ የሶርያ፤ የየመን ዕድል ይገጥማታል።

ምኞቴ ባይሆንም፤ እውነታው ግን ያንን ስለሚያሳይ ትግሬ ያልሆናችሁ ወገኖች ይህ አደገኛ እርምጃ እንዲቆም ካላደረጋችሁ፤ አገራችሁ “ሶርያ” ትሆናለች። ከዚያ የኔ የምትሉት ሕዝብ “የሲኦል ህይወት” ይጠብቀዋል። ኢትዮጵያ ‘’በአምላክዋ አትበተንም” ስንል ነበር፡ ዛሬ አምላክዋም አሽሸውታል፡ የራስዋ ሰይጠኖች ስለከፍዋት ¾ኛው አካላትዋ ፈርሷል።

ፖሊቲካ ውስጥ በጣም ቆይቻለሁ፡ ነገሮች ሲበላሹ አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶች የማየት ልምድ አለኝ። “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው የጥላቻ መነሻ ከምን የመነጨ ነው?” የሚለው መጽሐፌ “ብክላ/ሳብቨርዥን ምንድ ነው?” በሚለው ምዕራፍ በደምብ ይነግራችሗል። በአራተኛው ምዕራፍ ላይ የተጠቀሰው “ሰላም” አሁን ወደ አለው “ክራይስ” ቀውስ እና “ፍጻሜ” እንዴት እንደደረስን እዛው ታዩታላችሁ። ይህ እንግዲህ በ2010 የጻፍኩት ነው።

 አስፈሪ ነው። አማራው ሲፈናቀል፤ ሲታሰር፤ ሲገደል እንደ ጮህኩላችሁ ሁሉ የተቀራችሁ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን “አማራዎች” (ኦሮሞዎችም ሌሎቻችሁም) ይህ የዘር ማጽዳት እንዲቆም “አንድ ነገር” ካላደረጋችሁ፤ ሰበቡ ሁሉንም አካባቢያችሁ እንደ ሰደድ ይለበልበዋል። በነገድ እና በሃይማኖት ሰበብ ሁሉንም በገፍ ማሰር አገሪቷ ወደ እማትወጣበት ሁኔታ ያስገባታል።

የተቻለውን ሁሉ አድርገናል። ሰሚ ከታጣ “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው!” የሚለው ሁሉም ይቀምሰውና በለ አሁን እያስጠነቀቅኩት ያለሁትን ምክር እኔኑን ታስታውሳላችሁ። ችግሩ ግን  አገር ከፈረሰ ወዲያ መቆጨት ቢቻልም መልሶ መጠገን ግን አይቻልም።

ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY