Monday, August 8, 2011

Asgede G/Selassie’s Letter of Appeal


ቀለቤቴን ስጧት

Kelebeten Sitwat is a new book by Beljig Ali. I recommend any one to read this book- this book left unforgettable memory in me, I urge everybody to read this book and judge the writers skill of writing and the shocking biography of ourselves and our country. Once you start to read the book, you do not want to put it down; you will forget everything else surrounding you. What a book indeed! Oh! A must read book. Those who want to buy the book please do use the following email beljig.ali@gmail.com

                 Asgede G/Selassie’s Letter of Appeal

From the Editor:      


PLEASE LISTEN TO BISRAT AMARE ON THE SECOND PART OF THE AUDIO posted below YOU WILL HEAR HOW HE GOT SO NERVEOUS AND PARANOID AND LOST ATTENTION WITH NO ANSWER WHEN AN AUDIENCE ASKED HIM “HOW MUCH MONEY HE SNATCHED FROM ETHIOPIA WHEN HE CAME HERE, IF NOT WHERE THE HELL HE GOT THE MONEY HE HAVE NOW AND SO MANY PERSONAL QUESTIONS!!!!!! LORD HAVE MERCY!!

The following letter of appeal from Asgede G/Silassie the author of Gahdi indicated he  is sued by the former TPLF spy and security apparatus Chief Bisrata Amare.  A friend  contacted me and asked me if I know anything about the information that Besrat sued Asgede in Mekele even though the plaintiff is an American citizen living in America Ohio State as a High School teacher and the defendant ‘s resident is still in Tigray Mekele and an Ethiopian citizen.  I said, “I read the news in regard to the issue you are referring, but I did see Ethiopians or the Tigrayans nor even the weak brother of his or the ego maniac friends around him spread the news or did a rigorous campaign to help him”. My friend said “you are right. I asked him back, where is his letter of appeal?  He said it was posted only once as news at the ethno/elitist websites- and that was it. Sad. I asked him, if he can forward me the letter of appeal written to the Diaspora Ethiopians. He did. It was PDF format  hard to post it, on my web in words format and rewrote as it is and also needed to be edited. I did some editing due to the badly written language issue, but I do not want to retouch it too much, so I left it alone as it is. Amazingly also, the letter is short of address where or who to contact (no eamil, no phone, no nothing!).
I know he has a brother and a few circles around here in America- unfortunately they are worst than the TPLF ethno group. Instead of spreading the letter with emails and available contacts- they simply throw it as news. And that was it. Sad indeed! How can these elements challange TPLF when they can't perform such easy task?  Anyway, though his brother never response to the calls I did many times in the past for variety reasons, even left a message to Asgede himself through his brother in DC few months back when he was touring here- they ignore my calls. I am not upset, I expected from such, since I am not an ethno groupie fellowship. So, here I am as an activist, I am posting Asgede’s letter of appeal to all of you my lovely readers- help him if you can in any way you can. He is challenging a notorious group. Remember, those EFM and Ethiomedia group websites? They report about their journalist friends’ situation day in day out- but, they never let us read the situation about Asgede's who challenged TPLF extensively in a regular bases. I ask why?   getachre@aol.com
 www.ethiopiansemy.blogspot.com
    
Note-  After reading Ato Asgede's letter of Appeal come back and read Bisrat Amare's article during the election http://www.ethioobserver.net/victory_vs_havoc.htm  (Victory vs. havoc  By: Bisrat Amare ) and listen to his interview with Hager Fikir Radio
http://www.aigaforum.com/audiovideo_1.html  Hager Fikir Radio
TPLF Tegadali/Tagay Bisrat Amare
Part I Part II  
                                                           ኣግራሞት!!!    
ሁለም ኢትዮጵያዊ ኣውቆት እንዲጠይቃቸው
                                                   ኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል 
እኔ ኣቶ ኣስገደ /ስላሴ /ሚካኤል እባላለሁ ዜግነት ኢትዮጵያዊ ትውልድ ቦታ ትግራይ ኣውራጃ ሽረ እንዲስላሴ ወረዳ መደባይ ዛና (ሰለኽለኻ)የተወለድኩበት 1944/ ኣሁን 60 ኣመት እዴሜ ባለፀጋ ነኝ ከየካቲት 1967. እስከ 1985. ከህወሓት ጋር በመሰለፍ 20 ኣመታት ታግያለሁ 1986. ህወሓት ራሴን ኣገለልኩ፡፡ ከዛ ግዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በማክበር በተለያዩ መንገድች ያለኝን የፖለቲካ ኣስተሳሰብ ለህወሓት ኢሕአዴግ በመወቃወም 18 ኣመት ሙሉ ታግያለሁ ኣሁንም በኣረና መድረክ ተደራጅቼ በመታገል ላይ ነኝ። በሌላ በኩል ያን ደርግ ያስወገደ 17 ኣመት መራራ ትግል የሚገልፅ የህወሓት እና የትግራይ ህዝብ ሃቀኛ የትግል ጉዞ ታሪክ የማውቀው ያየሁትና በተግባር የነበርኩበት የታሪክ መፅሓፍት ጋህዲ 123 ፅፋያለሁ፡፡ እነዚህ መፀሓፍቶች ለህወሓት ታጋዮች፣ ለትግራይ ህዝብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ያረኩ እና ጥያቄ እንዱያነሱ ያደረጉ ናቸው፡፡
በትግሉ ወቅት የተለያዩ ስራዎች የሰሩ ለኣብዛኞቹ ኣስደስቶ ለጥቂቶቹ ግን ኣላስደሰተም፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ የታሪክ መፅሃፍ ከሆነ ሁሉም በኣንዴ ላይ ስለማያስደስት ነውና፡፡ ጋህዲ መፅሓፍቶች ከመፃፊቸው በፉት የህወሓት ታሪክ ኣንዴ ኣንዴ ግለሰዎች ለህወሓት ባለስሌጣናት ባሌነበሩበት ባልሰሩት እየኳኳሉ ይፃፉ ነበር፡፡ ከዛ ግን ለህወሓት ባለስሌጣኖች የሚያሞጉሱና የሚያሽሞኖሙኑ ለጋህዴ መፅሃፌቶች በኣሽሙር ጨረፍ እያደረጉ የሚፅፉ ወደ መድረክ ብቅ ኣሉ፡፡ በተጨማሪም የጋህዲን ኮቴ በመከተል በልብ ወለድ፣ በግጥም ጠንካራ መፅሃፍቶች ተፃፉ፡፡ ኣንዳንድ ግለሰዎች ደግሞ ፍፁም ግብረገብነት በጎደለው ለጋህዲ በመኮነን ከዛ ባለፈም ኣንድ ኣንድ ፀሃፉዎች በመፅሓፋቸው ሽፋን ምሊስ ሲቆረጥ የሚያሳይ ምስሌ በማስቀመጥ ኣትፃፉ የሚል መልእክት ያለው ሽፊን ኣሰቀምጠዋል።ታሪክ ሳይሆን የፕሮፖጋንዳ ይዘት ያላቸው መፅሃፍቶች ሲፅፉ ታይተዋል ።እነዚህ የህወሓት መሪዎች የሰሩትና ያልሰሩትን የለጠፉላቸው ለጋህዲ መፅሓፌቶችን የኮነኑ መፅሓፉቶች ከፍተኛ የብዙሃን መገናኛ ሽፋን ተሰጥቷቸው በሂልተን ሆቴል፣በሸራተን ሆቴል፣በመቐለ ሰማእታት ሃወልት የኣገራችን ርእሰ ብሄር ግርማ ወልደጊዮዎርጊስ ሳይቀሩ ሚኒስትሮች፣የክልሉ ኣስተዳደሮች ተመርቀው በገበያ፣በመንግስት መወቅሮች፣መከሊከያ ሚኒስትር፣በት/ ቤቶች፣የኢፈርትና ሌሎች የእርዲታ ድርጅቶች እንዲሸጡ ተደርጓል።ለህትመት ኣብዛኛው ወጭ የሸፈኑት የኢፈርት ድርጅቶችና የመንግስት መስርያ ቤቶች፣በመንግስት ገንዘብ የታተሙት ናቸው።
የመፅሓፉቶቹ ውስጣዊ ይዘት ምስክርነቱ ለኣንባብያን ሆኖ በእኔ ጥናት ግን እነዚህ ፃሓፍቶች ለማያውቃቸው ኣንባብያን ብቻ ሳይሆን የህወሓት ታሪክ ለሰሩና ለሚያውቁት የህወሓት ኢህኣዳግ ታጋዮችና ኣባላት ኣላስደሰተም።
የጋህዲ መፅሓፌቶችና ሌሎች ግን ምንም የህትመት ደጋፊ ያላገኙ በድህነት፣በፃሓፉዎች ልብ የታተሙ በምርቃታቸው ለጥቂት ሰዎች ያላስደሰቱ ለብዙሃን ያስደሰቱ ለኣንባብያንም የተመቹና ቡዙ ጥያቄ ሊያስነሱ የቻለ ናቸው። ለምሳሌ በብዙሃን ኣንባብያን የተወደደ ለጠቂቶቹም ያልተመቹ መፅሓፍቶች
1. ማፍያ ማለፍያ(ግጥም በታጋይ ኣለማዮህ ገዘሀኝ ኣውዓሎም)
2. ክስታይ(እንደወረደ ፅሑፉ በጋዜጠኛና ደራሲ ግርማይ ገብሩ)
3. ከሃገር በስተጀርባ በኣስራት ኣብርሃም
4. ጋህዲ 123 ሰበር ጋህዲ በኣቶ ኣስገደ /ስላሴ ናቸው
እላይ ከተዘረዘሩት መፅሓፍቶች ምንም እንኳ በሁለም / ህዝብ ይወደድ እንጂ በኣሁን ጊዜ ሃቁን ስለፃፈ  ከማመስገንና ከመሸለም፣ ሞራል ከመስጠት ከማበረታታት ፈንታ ኣንዳንዶቹ ፀሃፊዎቹ እንደወንጀለኛ በሞቁጠር ማሰርና መከሰስን እየገጠማቸው ነው፡፡
ከተከሳሾቹ ኣንዱ እኔ ኣስገደ /ስላሴ ነኝ።
እኔን የከሰሱ ኣቶ ብስራት ኣማረ ገብርየ
ዜግነታቸው ኣሜሪካዊ
ትው ኢትዮጵያዊ
የሚኖሩበት ኣገር ኣሜሪካ ኦሃዮ ስቴት፡፡
ወደ ኣቶ ብስራት ኣማረ ክስ ከመግባቴ በፊት ኣቶ ብስራት ኣማረ ማን ናቸው? ስለሳቸው ጥቂት ላብራራ፤ ኣጠር ኣድርጌ ለመግለፅ እሞክራለው፡፡
ኣቶ ብስራት ኣማረ በትውልድ ኢትዮጵያዊ  ሆነው በኣሁን ጊዜ ከላይ እንደተገለፀው አሜሪካዊ ናቸው፤ ትውልድ ቦታቸው በኣክሱም ኣውራጃ ወረዳ ዓድየት ጅራ በተባለች ገጠር ሲሆን፤ 1969. መጀመርያ ወደ ህወሓት ተቀላቅለው ደርግ እስኪወገድ በህወሓት የእስር ቤት ፊ፤ የፀጥታ (ዴህንነት) ሆነው ሰርተዋል፡፡ 1983. ደርግ እስከተወገደበት ጊዜ በዛ በጠቀስኩት የስራ መደብ እየሰሩ ቆይተው 1983. መጨረሻ ኣካባቢ እስከ 1985. በክልል 14 (ኣዲስ ኣበባ ከተማ)ፀጥታና መረጋጋት ተመድበው እየሰሩ ቆይተው ምክንያቱ ባልታወቀ ወደ ኤሜሪካ ፈርጥጠው ሄዱ። እዛው በፈረጠጡበት ኣገር ብዙ ሳይቆዩ የ ዩ.ኤስ.ኤ (USA) ዜጋ ሆኑ፡፡ ኣቶ ብስራት በኤሜሪካ በቆዩበት ዘመን በaሜሪካ ባገኙት የብዙሃን መገናኛ በኣገር ውስጥም በኢትኦጵና በሌሎች ጋዜጦች የህውሓት ኢሕአዴግ ተቃዋሚ ሆነው ብዙ ይጽፉ እንደነበር ይታወቃል። ኣንዴ ኣዋዛጋቢ ጉዳይ ግን እኚህ ሰው / ህወሓት ኢሕአዴግ በመወቃወም ወደ ኤሜሪካ ፈርጥጠው ወደ አሜሪካ አገር በመሄድ  ጥገኝነት ጠይቀው ግሪን ካርድ በማግኘት ቆየት ብለው ደግሞ ዜግነት ሲያገኙ ህወሓት/ኢሕአዴግን በጠላትነት ፈርጀው ነው። በተጨማሪም ኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች ከሚላቸው ጋር በማበር በብዙ መድረኮች ብዙ ዲስኩር ኣሰምተዋል በተለይ በደጀን ሬዴዮ ጣብያ ፣በኣሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ እና በኢንተርኔት ብዙ ተናግረዋል(ፀረ ኢሕአዴግ ዘመቻ ኣካሂደዋል)
ይህ ሁሉ ሲያካሄዱ ከቆዩ በ ህወሓት ኢሕአዴግን እንደ ጠላት የፈረጁ ኣቶ ብስራት ወደ ትዮጵ በመመለስ ከህወሓት ባለስልጣናት በመገናኘት በኣዲስ ኣበባና በትግራይ የመንግስት ኮብራ መኪና ተሰጥቷቸው እስከ ትውልድ ቦታቸው ፤ዓዴት ሲንሸራሸሩና በኣኩሱም ኣሮጌው ኣውሮፕላን ማረፊያ ብዙ   ካሬ ሜትር መሬት ተስጧቸው ህንፃው እየተገነባ ነው፡፡ እንደገና ወደ አሜሪካ ተመልሰው ኑሯቸው ቀጠሉ። እንደገና ወደ ኣዲስ ኣበባ ተመልሰው በመሄድ እንደተለመደው በህውሓት ባለስልጣኖች ኣቀባበል ተደርጎላቸው የሚንቀሳቀሱበት መኪናም ኣልተለያቸውም። በተለያዩ ቦታዎች ግብዣ ተደርጐላቸው ከኣንዳንድ ሚንስትሮች በስተቀር ከሁሉም ባለስልጣኖች መልካም ግንኙነት ኣላቸው በተለይ ከቀድሞ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሃለቃ ፀጋይ በርሀ እና ስብሓት ነጋ በመቐለ ከተማ ከኣቶ ዘኣማኑኤል ለገሰ (ወዲ ሻምበል) ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ከኣቶ /ገብርኤል ትግራይ ክልል ደህንነት ሃሊፉ፣ ከጠበቃ ማሩ /ስሊሴ መንሸራሸር ቀን ተቀን የተለመደ ስራቸው ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ ተደማምሮ ሲታይ ኣቶ ብስራት ኣማረ እውን ከህወሓት ተጣልተው ነበር ወደ ኤሜሪካ የኮበለሉት? ኤሜሪካ ሄደው ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ተቃዋሚ ኮሚኒቲዎች ሆነው ሲያደርጉት የነበረው ጸረ ኢሕአዴግ እንቅስቃሴ በርግጥ የኢሕኣዴግ ተቃዋሚ ነበሩን?
ከመጀመርያ ጀምሮ ወደ ኣሜሪካ ጥገኝነት ሲጠይቁ የኢሕኣዴግ ጠላት ሆነው ነበር? በጣም የሚገርመው ኣቶ ብስራት ጠሊቴ ወደሚሉት ኢሕኣዴግ ወደ ሚመራው ኣገር ሲመለሱ የዩ.ኤስ.ኤ (USA)መንግስት በተለይ  ዩ. ኤስ. ሲ. አይ. ኤስ. (USCIS- United States Citizenship and Immigration Services) ለምን ኣልጠቃየቸውም? ይህ ሁሉ ከሚዛን ሲቀመጥ በአሜሪካ አገር የሜሪካሲትዝን አሰጣጥ ደምብ አልተጣሰም ማለት ይቻላል? ወይስ አቶ ብስራት ሌላውን የሚመለከት እሳቸውን የማይመለከት ደምብ እና ሌላ ምክንያት ኖሮ ይሆን ? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ይጭራል። ያም ሆነ ይህ መልሱ ሁለቱም አገሮች የሜሪካ እና የኢትዮጵያ መንግስት መልስ እንዲሰጡበት ወደ እነሱ ላስተላልፈው፡፡  ወጣም ወረደ ኣንዳንድ ሰዎች ኣቶ ብስራት ኣማረ በትግል ያካበቱት የስለላ ስራ ስለነበር ያንን ስራ እየቀጠለበት ነው የሚል ግምገማ ይሰጣሉ፡፡ ለሁሉም ነገር ግምገማውና ትእዝብቱ ወደ ዲያስፖራው /ሰብ ልተወው፡፡
ኣቶ ብስራት ኣማረ ኣዲስ ኣበባ ምን ሲሰሩ ከረሙ??
ኣቶ ብስራት ኣማረ ኣዲስ ኣበባ እንደገቡ ከምርጥ ጓደኞቻቸው በመሆን በብዙ ቦታዎች፣ መናፈሻዎች፣ሆቴሎች እንደነ ሸራተን እና ሂልተን በኣሮጌ ፖሊና ቦሌ መድሃኒኣለም በጎልፍ የመከሊክያ መናፈሻ በመሳሰሉ ምርጥ ምርጥ ቦታዎች ይንሸራሸሩና በተለይ በኣዲስ ኣበባ ከኣቦይ ስብሓትና ከኣቶ ፀጋይ በርሄ ኣቶ ኣባይ ፀሃየ እና ከመሳሰሉ ከፍተኛ ባለስልጣኞች ይገናኙ ነበር፡፡
ኣቶ ብስራት በኣዲስ ኣበባ ቆይታቸው ዋና ኣጀንዳቸው በኣቶ ኣስገደ የተፃፈ መፅሃፍቶች ምክንያት ኣድርገው ኣስገደ እንዴት ይከሰስ እንዴትስ ይቀጣ በሚል ከብዙ ሰዎች ከሕግ ባለሞያዎች ተማከሩበት፣ ተወያዩበት በተለይ ማታ ማታ ሁሉም ሰው ሞቅ ሲለው ስለ ኣስገደ የሚነገረው ብዙ ነው፡፡
ሴራው በአዲስ ኣበባ ብቻ ኣላቆመም፡ በመቐለም ከኣቶ ማሩ ሃይለስላሴ ጠበቃና ከዘኣማኑኤል ለገሰ(ወዲ ሻምበል) ውይይቱ ቀጠለበት ቀንም ማታም ተመካከሩበት፡፡ እኔም የሚሰሩት የሚጠነሱሱት ሴራ ሰው ኣይጥላህ እንደሚባለው ዕዴሜ ለቴክኖልጂ በየሰኣቱና በየደቂቃው ዘገባዎቹን ኣገኝ ነበር፡፡ ዘገባው ኣስገደ በየትኛው ፖሊስ ጣብያ በማን መርማሪ በማን ኣቃቤ ሕግ ክሱ ይመስረት የትኛው ወረዳ ፍርድ ቤት ይየው እስከ ማለት ነበር፡፡ክሱም ምን ምን ነጥብ ይያዝ ተብሎ ኣቶ ማሩ /ስላሴም ሌሎች ኣጋዦቹም ኣቀናበሩት በኣንድ ኣንድ ባለስልጣኖች መኖርያ ቤት ግብዣ ተደርጎ በግብዣውም የክሱ ጥንሰሳ ስራቸውን ቀጠለበት፡፡
              ኣቶ ኣስገደን ለመክሰስ ዝግጅት ተጠናቀቀ
ኣንደኛ ከኣቶ ኣስገደ መኖርያ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ፍርድ ቤት ውጭ ወደ ቀዳማይ ወያኔ ፖሊስ ጣብያ ሄደው በዋና ኢንስፔክተር ሙሉ ብርሃን ካሕሳይ እንዲመረመር።ሁለተኛ በቀዳማይ ወያኔ ኣቃቢ ሕግ ክስ ተመስርቶ በዚሁ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተደረገ። ለምን እዛው ተመሰረተ? ሌላ ግዜ በስፊው እመለስበታለሁ፡፡ግን ደግሞ ይህ ጥያቄ የኔ ብቻ ኣይደለም፡፡ የሁሉም ሕግ ባለሞያ ነው፡፡
 የክሱ ሴራ በጠበቃ ማሩ /ስላሴ ከተቀናበረ ክሱ ለፖሊስ እንዲስጥ ማሩ በስተጀርባ ሆኖ እንዲያማክር ተባለ፡፡ ምክንያቱም ወንጀሉ የሚከራከረው ኣቃቢ ሕግ ስለሆነ፡፡ ከመጀመርያው ግን ለኣስገደ ክብር ላለመስጠት ጠበቃ ለሆነ ኣስፈላጊ ገንዘብ እንከፍላለን ተባለ፡፡ ይቺ ኣገር ጥቂት ተጠቃሚዎች የሚፈነጥዙባት ለጭቁኖች የጠበበች ሆነች በእነ ኣሜሪካዊው ዜጋ ብስራት ኣማረ፡፡ ይቺ ኣገር ከውጭ ለመጡ የሰፋች በኣገር ውስጥ ለሚኖረው ግን የጠበበች ሆነች፡፡ በቃ!!
           በመጨረሻ ኣቶ ኣስገ ምን ሆኑ ?
መጀመርያ ኣንድ ቀን 3ሰዓት ኣከባቢ ከፖሊስ ስልክ ይደወላል
ማን ነህ ?
፦ከፖሊስ ጣብያ ቀዳማይ ወያነ ነው፤ዋና ኢንስፔክተር ሙሉ ብርሃን ካሕሳይ
፦ምን ነበር?
፦በወንጀል ስለተከሰሱ ወደ ጣብያችን ይምጡና የምርመራ ቃላቸው ይስጡ (ሃይለ ቃል በተሞላበት)
፦ታዲያ እኔ ወንጀል ኣልሰራሁም እንጂ ካላችሁ በቃል ትእዛዝ ኣልመጣም መጥርያ ወረቀት ኣምጡ በግ ኣይደለሁም
፦በክብር ራስህ ካልመጣህ እኛ በምንፈልገው እርምጃ እንወስድሃለን
ሀ፦ከሕግ ውጭ የምታደርገው ኣይኖርም፡፡ ቢኖርም ውጤቱ መጥፎ ነው (ስልኩን ተዘጋ)
ከኣንድ ሳምንት 5/11/2003 . ከጥዋቱ 130 ቀኑ የፀደይን ፆም ጨርሰን የፆም መፍቻ የሃዋርያት በኣል ነው፡፡ እኔም ጥዋት ተነሰቼ ለፆም መፍቻ ትንሽ ፍየል ብጤ ኣርጄ ከጨረስኩ ፆማችን ልንፈታ ቁርሳችን ልንበላ ስንዘጋጅ በራችን ተንኳኳ፡፡ እኔም ከግቢ ውስጥ ቆይቼ ከነ ፒጃማየ ከፈትኩት ሰውየው በደርግ ጊዜ ፖሊስ የነበረ ኣሁን ምሊሺያ የሆነ ኣቶ ተካ ነው፡፡ ሰላም ምን ነበር? ስለው ለስራ ጉዳይ ነው የመጣነው አለኝ። ራቅ ብለው ሁለት ወጣት ወንድችና ኣንድ የቀበሌ ሴት ቆሞዋል፡፡ ለምስክርነት ነውመስለኛል የቆሙት፡፡ከሩቅ 3 ፖሊሶች ቆሞዋል ወዲያው ኣንዴ ፖሊስ ሮጦ መጣና ኣቶ ኣስገደ ወደ ጣብያችን ለምርመራ ይፈለጋሉ እና እንሂድ ኣለኝ፡፡ መጥርያ ኣላችሁ ኣልኩት፡፡ የለንም ኣለኝ፡፡ በኣከባቢ እኔ የማውቀው ሰው ኣልነበረም እና እሺ ብየ ሰዎች ወደ ኣሉበት 25 ሜትር ኣከባቢ ወሰዴኳቸው፡፡ ምስክሮች ከያዝኩ በሉ ያለ መጥርያ ኣሌሄድም እናንተ ሰዎች ስሙሉኝ ያለ ፍርድ ቤት መጥርያ ታሰር ይለኛል የፈለጉትን እርምጃ ውሰዱ እንጂ ኣሌሄድም ኣልኳቸው፡፡ ሰዎቹም እንዴ ለምን ያለ ፍርድ ቤት መጥርያ ይታሰራሉ? ኣልዋቸው፡፡ ረዳት ሳጅን /መድህን /ኣረጋይ የተባለ ፖሊስ የመጥርያ ወረቀት በኪሱ ደብቆ ቆይቶ መጥርያ ኣለን እንካ ብሎ ሰጠኝ፡፡ ለምን ደበቀው? መልስ ያስፈልገዋል።
ከዛ ቁርስ ስላልበላን ቁርስ ለመብላት ፍቀዱልኝ ኣልኳቸው፤ ፈቀዱልኝ ።ቁርስ በልቼ በፖሊስ ታጅቤ ፖሊስ ጣብያ ሄዴኩኝ፡፡ 60 ኣመት እዴሜየ በፖሊስ ታጅቤ ኣላውቅም፣ 17 ዓመት ታግየ ወደ ስልጣን ያመጣሁት የኢሕዴግ መንግስት በማይረባ ነገር ተጠርጥረሃል ብሎ ሲያንገላታኝ ማየት ያሳዝናል።ደግሞ እኮ የሚገርመው ሕገ መንግስታዊ መብቴ ተጠቅሜ በፃፍኩዋቸው የታሪክ መጻሕፍቶቼ ምክንያት ነው፡፡
                        ፓሊስ ጣብያ ከደረስንስ በኋላ?
ሻለቃ ሙለ ብርሃን ቢሮው ውስጥ ኣስገባኝና ሲናገርቆጣ ቆጣ” ይላል፡፡ ያጣጥለኝም ጀመር ወዲያውኑ ከሳሽህ ብስራት ኣማረ ነው፤የከሰሰህ ደግሞ
1ኛ ያገረሸበት ታሪክ ኣርእስት ያለው ብስራት አማረን የሚሰድብ ፅሁፍ በትነሃል፡፡
2ኛ በጋህዲ ቁጥር 3 ያለው በብዙ ነጥብ፣ በዚህ-በዚህ ይለኝ ጀመር፡፡
                   እኔም ያቀረብኩለት ጥያቄ፡
ክሱ ይህ ከሆነ መፅሓፈ የታተመው በሰሜን ወረዳ ነው ቤቴ ቀበሌየ ቀጠናየ እዛው ነው ለምን እዚህ እጠየቃለሁ? ስለው ሻለቃው ይሄ ጥያቄ ልታነሳ ኣትችልም፡፡ መንግስት በፈለገው ጊዜና ቦታ ሊመረምርህም ሉያስርህም ይችሊል፡ ቃልህ ስጥ! ባትሰጥ እኛ የምንከተለው ኣሰራር ኣሁን እምቢ ልትል ትችላለህ! አለኝ ትእቢት በተሞላው ኣነጋገር፡፡እኔም ግፊቱ ወዴት እንደሚያመራ ስለተረዳሁት በትእግስት ቃሌን ሰጠሁ፡፡ ከሁለት ሰኣት እስከ ኣስር ሰዓት ታስሬ ዋልኩ 1030 ላይ 3000 ብር ዋስ ተለቀቅኩ፡፡
ከእስር ከተፈታሁ የተሰጠኝ የመፍቻ ወረቀት ከምትኖርበት ወደ ሌላ ቦታ ስትንቀሳቀስ ፌርድ ቤት ኣስታውቀህ ተንቀሳቀስ የሚል ነው፡፡ ይህ ማለት ግዞት ነው? የቁም እሱር መሆን ነው? መልሱ ለሕግ ባለሞያዎች ልተው፡፡
ሂደቱ ከካይ እንደተዘረዘረ ሆኖ በመጨረሻ ግን የሆነ ኣንባቢና ትእዝብት የምትሰጡበት በኣገር ውስጥም ይሁን በደያስፖራ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ኣሉኝ፡፡

1. ኣቶ ብስራት ኣማረ ለኣቶ ኣስገደና ለጋህዲ መጽሐፍ ቁ.3 ሊከስ የቻለው በራሱ ተነሳሽነት ወይስ በስተጀርባ ግፊት የሚያደርግለት ሃይል ኣለ? ለምንስ?

2. ኣቶ ብስራት ኣማረ በጋህዲ የሰፈሩ ታሪኮች ለምን ብቻውን አሳሰበው? ብስራት አማረ ኣቶ ኣስገደን በመክሰስ በህወሓት መሪዎች ጠቀሜታ ያገኝ ይሆን?
3. ብስራት የመሰረተው ክስ(ወደ ፖሊስ ያቀረበው) አስገደን በመክሰስ እጅ መንሺያ ለማድረግ ከሁሉም የኢሕዴግ መሪዎች ያስታርቀኝ ይሆናል ብሉ ይሆን?
4. ብስራት ኣማረ በአዲስ ኣበባ እና በመቐለ ከኣቶ ስብሓት ነጋ፣ ኣቶ ፀጋይ በርሄ፣ ዘኣማኑኤል ለገሰ፣ / ገብርኤል እና ሌሎችም ይገናኝ ነበር፡፡ ክሱ ሲጠነስሰው
በራሱ ብቸኛ አነሳሺነት ነው ወይስ እነሱ ጋር ተማክሮ ነው የጠነሰሰው ?

              የብስራት ክስ ኣላማ
1. እውን መብቱን ለማስከበር ሲል ነው?
2. ማንን ለማስደሰት ይሆን? የኢሕአዴግን መሬዎችን ለማስደሰት?
3. የኣረናን መድረክ ለማዳከም?
4. ለህወሓት ታሪክ በመቆርቆር?
5. ኣስገደንመክስስ ከተፈለገ በሚኖርበት ቀበሌ ፖሊስ ጣቢያ ክሱን ከመመስረት ይልቅ ለምን ክሱን በሌላ ወረዳ እንዲመሰረት ተፈለገ?
6. ብስራት ወደ አሜሪካ ፈርጥጦ የፖለቲካ ጥገኝነት ሲጠይቅ እውን ከህወሓት    የኢሕኣዴግ ፖለቲካ በመቃወም ነበር?
7.ወደ ኣሜሪካ ጥገኝነት ጠይቆ ሲቀናው ለምን ወደ ትዮጵያ ተመለሰ?
8. በኣሜሪካ እየኖረ  የህወሓት ኢሕኣዴግ አመራሮችን መጥፎ ባሕሪ እና አምባገነንነት ኣንድ ባንድ በብዙሃን መገናኛ ያዋርዳቸው ነበር፡፡ ተመልሶ ኣዲስ ኣበባ ሲመጣ ሲሰደቡ የነበሩ መሪዎች በኣውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለው መኪና መድበው ያንሸራሽሩት ነበር። ለምን?
9. የኣቶ ብስራት መመላለስ ወደ ቀድሞ የደህንነትና የእስር ቤት ሃሊፉነታቸው የመመከስ ፍላጎት ይኑራቸው ይሁን?
10. በአሜሪካ ኣገርና በኣገር ውስጥ ባላቸው ሃብት በኣዲስ ኣበባና ሌሎች ቦታዎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍሊጎት ይኖራቸው ይሆንና ሁኔታዎች ማመቻቸት ይሆን?
11. ያሁሉ ፍላጎታቸው ለሟሟላት ከኢሕኣዴግ ከፍተኛ ባለ ስልጣኖች መልካም ግንኙነት መኖር የግድ ይላል።ከነዚህስ መልካም ግንኙነት ኣላቸው?
12. ኣቶ ብስራት ዜግነታቸው ኣሜሪካዊ ሆነው የህወሓት ባለስጣኖች በስተጀርባቸው ከሌሉበት በቀጥታ መጥተው ኢትዮጵያዊን ዜጋ ሊከሱ ይችላሉ ? መልሱ ከሕግ ባለሞያዎች እና ለኣቶ ብስራት እተወዋለሁ።
13. የህውሓት ባለስልጣኖች ኣቶ ብስራት ሲንቀሳቀሱ የሚያደርጉላቸው እንክብካቤ ከምን የመነጨ ይሆን?
14. ኣቶ ብስራትህወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት ጋር እንዴት ታረቁ? ድሮውኑስ  ጠብ ነበራቸው?

     ጥሪ
1. ባገርም በውጭም ኣገርም ያላችሁ ወገኖቼ በኣቶ ብስራት ተመስርቶብኝ ያለው ክስ ከኣቶ ብስራት ኣማረ በስተጀርባ እኔን ለማጥቃት የተሰለፈ ሃይል ስላለ ይህ ሴራ በሕግ ለማክሸፍ የፍርዱ ጠበቆች ስለሚያስፈልጉኝ
1. በማንኛውም ተፅእኖ የማይምበረከክ ጠበቃ በነፃ እንዱያግዘኝ
2. በፖሊስ ምርመራ በቀረበብኝ ነጥቦች ምስክሮች ያስፈልጉኛል የሚል ኣስተሳሰብ ስላለኝ ለምስክሮች ማጓጓዣ ኣበል ገንዘብ ስለሚያስፈልግ
3. በነፃ ጠበቃ ካልተገኘ ገንዘብ ተከፍሎት ለጉዳየ ጥብቅና የሚቆምልኝ ስለሚያስፈልገኝ የገንዘብ ደጋፍ ስለሚያስፈልገኝ ሁላችሁም ለፍትህ የቆማችሁ በያላችሁበት ስጋፍ እንድታደርጉልኝ ጥሪየን ኣቀርባለሁ፡፡

ከኣቶ ኣስገደ /ስሊሴ /ሚካኤል
መቐለ ሰሜን ወረዳ
ቀበሌ 06