Sunday, March 8, 2020

የትግል ፎርማሊቲው መለወጥ አለበት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) 1/8/2020 (6/2912)


የትግል ፎርማሊቲው መለወጥ አለበት!
ጌታቸው ረዳ
 (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)
1/8/2020  (6/2912)

በቅድሚያ ለእስክንድር ነጋ ድጋፌ ዛሬም ጠንካራ ነው። የባልደራስ ፓርቲ ከ “መ. ኢ አ . ድ” ጋር ግምባር መፍጠሩ ሰሞኑን በዜና ሰምቻለሁ። በኔ አስተያየት እጅግ የሠለጠነ ፖለቲካ ስልት ነው። አንዳንድ ደናቁርት እስክንድር ከብሔሩ ጋር ግምባር ፈጠረ እያሉ ለማጣጣል ሲሞክሩ ከዚያም አልፈው እስክንድር የሰብኣዊ መብት ዕውቀት እንጂ የፖለቲካ ዕውቀት የለውም ሲሉ አስቂኝ የሆነ የጠላ ቤቶች ንቃተ ትምህርት ሲተነትኑ በዩቱብ አድምጬኣቸዋለሁ።

እስክንድር ነጋ በትግሬዎች “ፋሺስታዋ ሥርወመንግሥት”  ያሳለፋቸው የእስርና የድብደባ የመከራ አመታት ትተን ዛሬም ወያኔ ወደ መቀሌ ካፈገፈገ በላ እረፍት አላገኝም፡ በከፋ መልኩ እያዋከቡት ነው። ወያኔን ተክቶ ወደ ሥልጣን የወጣው የ16ኛው ክ/ዘመን ‘የኦሮሙማ ህዳሴ’ የጋላዎቹ ፋሺሰታዊ ሥርወ-መንግሥት መሪ ከሆነው “በአብይ አሕመድ” ትዕዛዝ በእስክንድር ነጋ እና የባልዴራስ አማራርና አባላቱ ላይ የሰነዘረው የ22 ወራት “ግልፅ ጦርነት” ስንመለክት እስክንድር ነጋ እየተሻገረበት ያለው አስቸጋሪ ፈተና በታሪካችን ጉልህ ሥፍራ ተቀምጦ ለታሪክ ምስጋና በወረቅ ብዕር ይጻፍለታል። ከባልደራስነት ሲቪክ ማሕበር ወደ ፖለቲካ ድርጅት እንዲለወጥ እኛ ፈቅደን የተስማማንበትን አካሄድ ለምን እስክንድር ወደ ፖለቲካ እራሱን ለወጠ ብለው የሚጮሁ እንቁራሪቶች ተበራክተዋል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲል ባለቤቱና ልጁን አሜሪካን አገር ትቶ የተራመደበት አስቸጋሪ መስዋእትነት መረዳት ያልቻለ ደንቆሮ ማሕበረሰብ በእስክንድር ላይ ዘለፋ የሚሰነዝር ይህ ደንቆሮ ማሕበረሰብ ለመጪው 3000 አመታት “የኦሮሙማ ፋሺስቶች እየተፈራረቁ ቢገዙት ምን ያስገርማል?”።

እጅግ የሚገርመኝ ደግሞ የ16ኛው ክ/ዘመን የጋላዎቹ ወረራ ተመልሶ ዛሬ “በኦሮሙማ” ስም በዚህ በዛሬው ትውልድ የተከሰተው ‘አክራሪ የጎሳና ሃይማኖታዊ የመንጋ መንግሥት’ ገና ምርጫ ሳይደርግ “እኛ ኦሮሞዎች” ለ3000 አመት እንገዛቹለን (የአብይ አሕመድ የውጭ ጉዳይና የፖለቲካ አማካሪው ዘረኛው ሌንጮ ባቲ በግልጽ ሚዲያ ላይ ወጥቶ እንደተናገረው) ብለው በዛቱት መሰረት ኦሮሞዎቹ ኢትዮጵያን ለመግዛት ካልሆነም “ለማፍረስ” ባሰፈሰፉበት ወቅት የፖለቲካ ተቃዋሚዎች “ሕብርት ሳይፈጥሩ” በምርጫ ወቅት በተናጠል ይህንን ‘ፋሺሰታዊ ኦሮሙማው የበረሃ መንጋ’ እናሸንፋለን ብለው መነሳታቸው ስንመለከት ዛሬም ተቃዋሚዎቹ ከነበሩበት ባሰባቸው እንጂ አልተሻላቸውም። ስለዚህ እስክንድር ከመሰለው ድርጅት ጋር ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅኑ ጋር ግምባር መፍጠሩ በጣም የሚደገፍ እርምጃ ነው።እነ ልደቱ አያሌውና እና ይልቃል ጌትነት ከእስክንድር ነጋ እና መኢአድ ጋር ግምባር መፍጠር ይጠበቅባቸዋል። ሌሎቹም እንዲሁ ከነዚህ ጋር ጥምርት በማድረግ አንድ አገራዊ ፓርቲ መመስረት አለባቸው እላለሁ።

እዚህ ያልጠቀስኳቸው “ፓን-ኢትዮጵያኒስቶች” ካሉም እንዲሁ በጋራ በማበር ግምባር ፈጥረው ይህንን ሥልጣን የተቆጣተረው ኦሮሙማው ፋሺሰት ስብስብ እና ለ27 አመት በዝርፍያና ወንጀል የተጨማለቁት ተመሳሳይ ፋሺሰቶችን በድምጽ መቅጣትና ሥርዓቱን መለወጥ ይቻላል። ይህ ካላደረጉ በየቦታው ያሰፈሰፉ የሃይማኖትና የጎሳ ፋሺስት አክራሪዎች  ምኒሊክ ቤተመንግሥት የተቆጣጠረው አብይ አሕመድ የተባለው “የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ” (እራሱ “ነኝ” ብሎ ነግሮናል፡በየቦታውም ኢሳያስን እየወከለ ንግግር ያደርጋል) አንድነት ፈጥረው አገሪቷን ወደ ባሰ አቅጣጫ ስለሚወስዷት ይህ አዲስ ስልት መከተል አለባቸው። ካሁን በፊት ተሞክሮ ያልሰራውን የተናጠል መወራጨት ዛሬ ተመሳሳይ ነገር መድግም ፍጹም ጸረ አገራዊነት ነው።

ይህ መንግሥት ለመጣል ትንሽ ገፋ ማድረግ ነው የሚለው የቆየ “ኢጎ” (ግትር) ቋንቋ አይሰራም። ይህ ሥርዓት በወንጀለኞችና በሌቦች የተዋቀረ ከላይ እስከታች ሞልቶ የተጠቀጠቀ የታጠቀ ቡድን ለ27 አመት በሃይማኖት አክራሪዎችና በጣም በርካታ በሆኑ የጎሳ አክራሪዎች የተገነባ ከመሆኑ አልፎ የታጠቁ የጎሳ ጦር ሃይሎች በእጁ የያዘ ስለሆነ በተናጠል የሚዋዥቀው ተቃዋሚ ወደ “መነጋገሪያ ሚዲያ” ብቅ ተብሎ ባንድ ጀምበር ሳይደራጁና ውህደት ሳይኖር የሚገፋ ቡድን ኣይደለም። ስለሆነም ኢትዮጵያዊ መንግሥት ለመገንባት ተቃዋሚው በጨኸት ማዕበል ብቻ ሳይወሰን “አገር ለማዳን” ሲባል የራሳቸውን ዛር (ኢጎ) ዋጥ አድርገው ባንድ ግምባር ቅንጅት ፈጥረው “ባንድ ድምፅ መስጫ ሳጥን” ሕዝቡ ድምጽ እንዲሰጣቸውና ነፃነት እንዲታወጅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

 የማለርያ/የወባ/ በሽታ መድሃኒት “ፕሮቶዞው” ከተለማመደው ‘ፈውስነቱ’ አይሰራም፡ ተቃዋሚ ድርጅቶች የተናጠል ትግል የማድረጋቸው አባዜ ገዢው መደብ ለ27 አመት ተለማምዶት ስለነበር ከመንበሩ አላነቃነቀውም (ከአብይ አሕመድ የንቀት ንግግር ማስተዋል አለባቸው)። የጦቢያው ጸሓፊ የሱፍ (ሓሰን ዑመር አብደላ) “ዳንከራው ሲለወጥ እስክስታውም መለወጥ አበት” እንዳለው ሁሉ እኔም የትግል ፎርማሊቲው መለወጥ አለበት እላለሁ።አሁን ያለው አደገኛ “ኦሮሙማው ንጉሥ” እንደ ድሮ ጠግኖ ጠጋግኖ የሚሄድ ሳይሆን “በሰበሩን ቦታ ሰበርናቸው፤ ከአለኛ ፈቃድ እዚህ አይመጡም” የሚል “በኬኛ” ፖለቲካ የሚጓዝ፤ ቆመኛ እና ሥልጣን አግበስባሽ፤ በጣም አደገኛ ንጉሥ ስለሆነ “ፎረሙላው” ኢትዮጵያዊ ኮምፐነንቶች” ከሆኑት ቡድኖች ጋር ግምባር ፈጥሮ የትግል ፍልሚያው ባልታየ ወኔ ይህንን ንጉሥ ካላስወገዱት አሁን ካየነው የ23 ወራት ሥርዓተ አልባ የመከራና የብጥብጥ ዘመን በከፋ መልኩ የሚቀጥል ሲሆን፡ ያውም እንዳለፈው ለ27 አመት ሳይሆን እነሱ በግልጽ በሚዲያ እንደነገሩን ለ3ሺ አመት ይቀጥላል።
      አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)