ባሕር ዳር ከተማ ከአንድ አመት በፊት አንዲት ህፃን ተደፍራ ተገድላለች በሚል በከሳሽና በተከሳሽ ወገን ያለው ክርክር
ጣልቃ የገባው “የመንጋ ፍትሕ” እየተለመደ የመጣው የኢትዮጵያዊያን አዲስ ባሕል!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
9/1/2024
ዜናው በሚሊዮን ሲጨፈጨፍና ሲፈናቀል የነበረው የአማራው ማሕበረሰብ የዓለም ዜናዎች ከዘገቡት ይልቅ በዚች ምስኪን ሕጻን የደረሰው ግድያ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይወሰን በዓለም ሚዲያዎች ላይ ደርሶ ሲነገር ሰምተናል። ለዚህ ደግሞ ምክንያት አለው። ለልጅትዋ እንደጮተጮኸው ለመቶዎች ህጻናት አንገታቸው እየተቀላ እርጉዞች ሆዳቸው እተቀደደ የተረገዙት ሕፃናት በቢላዋ ታርደው በሞቱት እናቶች አፍ ላይ ስጋቸው አንዲጎርሱት ሲደረግ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ በመንጋ የሚጮኸው ጫኺ አልጨኸላቸውም። ስለዚህም አማራው በዓለም ዜና ጀሮ አልተሰጠውምና በዚህ ትዝብት እንለፈው።
ልጅትዋ ተደፍራለች ብሎ የባሕር ዳር ፍርድቤት በተከሳሹ ላይ በርካታ አመታት እስር ፈርዶበታል። የተከሳሽ ወገኖች ደግሞ ፍርዱና የተከሄደበት የምርምራ ሂደት ከሕግ ውጭ የተካሄደና ከሳሹ የተጠቀሰው ወንጀል አልፈጸመም ብለው የዓለምና የፈጣሪ እንዲሁም የአገሪቱ ሕግ በሰጠው የይግባኝ መብት ተጠቅመው ይግባኝ ጠይቀው ፍትሕ አንዲሰጣቸው ወደ አዲስ አባባ መጥተው ክርክር ለማድረግ ሲመጡ መንጋው ጣልቃ ገብቶ ጭራሽ የሕግ ምሁር ሆኖ የተከሳሹን የመደመጥ መብቱን መነፈግ አንዳለበትና መገደል እንዳለበት ወስኗል።
ሕግ አዋቂ ነኝ የሚለው መንጋው “በፌስቡክ እና በይትዩብ ጫካ” ውስጥ ተወሽቆ <ጃንግል ጃስቲስ> ተብሎ የሚታወቀው ዓለም ያወገዘው በናይጀሪያ በካሜሩን በኬኒያ በኡጋንዳ እና በርካታ ባልሰለጠኑ ማሕበረሰቦች ዘንድ የሚታየው አሰቃቂ “የሞብ ፍትሕ” (የመንጋ ፍትሕ) ዩቱብ መስተዋት ላይ ቆሞ በሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ ሴትና ወንድ በተከሳሹ ላይ የሞት ፍርድ ፈርዶ የይግባኝ መብቱንም እንዲነፈግ እየጮኸ (በአካል ባገኘው ሥጋውን ተልትየ ለጅብ ነበር የማሰጣው ስትል የሰማሗት ልጅ አለች፤ (የናጄሪያው “ጃንግል ጃስቲስ ባሕሪ ማለት ነው) ይገኛሉ።
ብዙዎቹ እንዲሁ ተከሳሹ ሕግ ፈቅዶለት በዋስ ቢወጣ የናይጀሪያን “ሞብ ጃስቲስ” ይፈጽሙበት እንደነበር
ጥርጥር የለውም።
ተከሳሹ “ወንጀሉን አልፈጸምኩም” አንደገና ክሴን በአገሪቱ ጠ/ፍርድቤትና ከዚያም አልሆን ካለ በሰበር ችሎት ፍትሕ እንዳገኝ ይግባኝ ብሎ በተከራከረው የተከሳሽ ወገኖች ማስረጃችን አንደገና ይኼው ብለው ሰሞኑን ወደ <<ጋዜጠኛ ተ/ሃይማኖት አዳነ (እግረኛ ሚዲያ>> ቀርበው ጋዜጠኛውም ባሕር ዳር ድረስ በመሄድ ጋዜጣዊ ሙያውና “የሞብ ጃስቲስ” እየደረሰባቸው ያለው የተከሳሹ ወገኖችን ለማድመጥ ቦታው ድረስ ሄዶ ያጣራው ዘገባ እንኳን መንጋው በጋዜጠኛነት የተቀመጠው ሳይቀር ሐመር ሚዲያ የተባለ ዘረኛም (መስከረም አበራን በጋዜጠኛነት ሲጠይቃት የነበረ ልጅ ነው) የእግረኛ ሚዲያ አዘጋጅ ተ/ሃይማኖት አዳነን <<ሕጻን ሄቨንን እና ተክለሃይማኖት አዳነን ምን አገናኛቸው>> (በዚህ ስልክ ደውላችሁ ምን አገናኛቸው ስትል ምን ማለትህ ነው ብላችሁ ዘረኛው የሐመር ጋዜጠኛውን እስኪ ጠይቁት 251 939 46 58 99)>> በማለት ጋዜጠኛው በመሰለው መንገድ ዘገባው ለመስራት ወደ ባሕር ዳር በመሄዱ ይህ ዘረኛ ጋዜጠኛ “ከሟቿ ህፃን ጋር ምን አገናኛቸው? ሲል ይጠይቃል። በጣም አስገራሚ የሆነ ትውልድ ነው እንደ አሸን የፈላው።
አንድ ተጠርጣሪ
ባንድ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ ስለተወሰነበት ተከሳሽም ይሆን ቤተሰቡ ጥፋተኛ አይደለም ብለው ካመኑበት የፈለጋቸው የመከራከያም
ሆነ መልስ መስጠት መብታቸው ሲሆን ተከሳሹም ሆነ ቤተሰቡ ለሚሰጡት መልስ በቂ ነው በቂ አይደለም፤ተገቢ ነው፤ተገቢ አይደለም የማለት መብቱ የከፍተኛ
ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አንጂ የመንጋው መብት አይደለም። መንጋው ማድረግ የነበረበት የመጨረሻው ፍትሕ እስኪሰማ
ድረስ ፍትሕ ላለማበላሸት በጥሞና መጠበቅ
ነበረበት።
ያ ግን አልሆነም: ምክንያቱም አሁን የበቀለው የኢትዮጵያ አዲስ ማሕበረሰብ ሳያጣራ የሚቀበል፤ብዙዎቹ ካፍንጫቸው የማይርቅ እይታ ያለው ፤ ስሜታዊ፤ ኢትዮጵያዊያን ዓድዋ ላይ ጣሊያንን አላሸነፉትም የተሸነፈው እንደ ዕድል ነው የሚል የኢትጵያን ሕዝብ አርበኛነት የሚክዱ ፤ ቅኝ ገዢ አይገዛኝም ባይነቱን የሚያንኳስሱ፤ ጦረኛነቱንና አልበገሬነቱን የሚያንኳስሱ ኢትዮጵያን የሚጠሉ የኦሮሞና የኤርትራ ባንዳዎች የሰበኩዋቸው በወቅቱ የተዘገቡት ዘገባዎች ማንበብ የማይችሉና ያላነበቡ አፋቸው የሚከፍቱ ማፈሪያ መንጋዎች የተራቡበት ማሕበረሰብ መሆኑን፤ ግብረሰዶማዊና ፍናፍንታዊ ወንዴላ የተበራከተበት፤ ለመጣው አሸርጋጅ፤ አጨብጫቢ ፤ ክፉ ፤ ዋሾ ፤ “ንክ” ፤ አልቃሻ ፤ ተሳዳቢ፤ ዘራፊ ፤ የተጠርጣሪን የመከራከር መብት (ፍትሕ) የሚነፍግ መንጋ ነው።
የሕግ መጽሐፍት ስትፈትሹ “የመንጋ ፍትሕ” (ጃንግል-ጀስቲስ) “ጋንጋዊ/መንጋዊ”
ነው። በመንጋ የሚጮሕ ጅብ ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊው መንጋ “በዩቱብ “ጫካ” ተደብቆ ሕግ የሚጥስ “ዘረኛና” “ቦዘኔ” ማሕበረሰብ እየሆነ”
እየሆነ መምጣቱ ለናንተ አልታይ ብሎአችሁ ከሆነ አላውቅም እንጂ ለኔ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ይታየኛል።
መንጋ ሕግን የሚጥስ ባሕሪ አለው ስል ምን ማለት ነው?
እስኪ እንመርምረው። መንጋው ተጠርጣሪን የሚነፍገው የትኛውን መብቱ ነው? ሦስት ጥሰቶችን እናያለን።
የመጀመሪያው ጥሰት-
‘መንጋው በቁጣ ስለሚነሳሳ’ ተጠርጣሪው የመጨረሻውን ፍትሕ ሳያይ አንዲገደል ይወስንና ፕሮፓጋንዳ ይነዛል ፤ በአካል
ካገኘውም ካላይ ሴትዮዋ ስትል እንደሰማኋት ደብድቦ ቦጫጭቆ
ይገድለዋል።
ሁለተኛው ጥሰት-
ሕዝብ እንዲገለገልበት የመሰረተው ሕግ የታችኞቹ ፍርድ ቤቶች ጥፋተኛ ነው ብለው ቢፈርዱበትም፤ ጥፋተኛ ተብሎ የሚጠራው እስከ መጨረሻ እርከን ካለው ፍርድ ቤት ጥፋተኝነቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ንፁህ ሆኖ የመጠራት መብቱን መንጋው በጭሖትና በማስፈራራት እንዲጣስና እንዳይሰማ ያደርጋል፡ (ባለሥልጣናትም ሆነ የፍትሕ አባላትን ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፤ (ፖለቲካ የሰራቺበት አበበች አዳኔንም ልብ ይለዋል) (አሜሪካ ውስጥ ጁሪ የሚባሉት የተከሳሽና ከሳሽ የመጨረሻ ፍርድ ለመበየን ከሕዝብ የተውጣጡ 12 ፈራጆችም መንጋው ሲያሰራጨው የነበረው ጩኸት ዜና ሰምተው ከቆዩ በሚሰጡት ፍርድ ላይ ተጽእኖ ስለሚያሳድር፡ ይህንን ለመከላከል አሜሪካ ውስጥ “ጁረር” ሲመረጥ ስለ ጉዳዩ ምንም ዜናም ሆነ እውቀት እንዳልነበረው ለማረጋገጥ ነው ምርመራ የሚደረገው)። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው “የመንጋ ፍትሕ” ተከሳሽ ንጹሕ ይሁን አይሁን በመንጋ ምህረት ላይ ከወደቀ በሕግ የተመሰረተ ፍርድ እንደሚሰጠው ዓይነት ፍትህ የማግኘት መብት አይሰጠውም።
ሦስተኛው ጥሰት
ችላ ሊባል ወይም ሊታለፍ የሚችል መብት ሙሉ መልስ የመስጠት እና ራስን የመከላከል መብት ነው። ሆኖም በመንጋ ማሕበረሰብ ውስጥ ተከሳሽ የቱንም ያህል አሳማኝ እና ትክክለኛ ቢሆንም በተከሳሹ በኩል የሚሰጠውን ማብራሪያ ለማዳመጥ፣ በጥንቃቄ መዝኖ ሊቀበል አይፈልግም።
ድርጊቱ የተፈጸመው በውሻ፤ በሰው፤ በዘር፤ በሃይማኖት ወዘተ.. ወዘተ…
ወዘተ…. ሲሆን ልክ እንደ ህጻንዋ መንጋው ውስጥም ሕጻናት ልጆች ስላልዋቸው በራሳቸው ሕጻን የደረሰ መስሎ ስለሚያያይዙት ልክ እንደ
ድሮው ጨዋው ኢትዮጵያዊያን ወላጆቻችን ድርጊቱ የፈጸመው ተከሳሽ “ሕግና ሓጢያቱ ያዋጣው” ብሎ ለሕግ ከመተው ይልቅ በስሜት ተነሳስተው
(ፕረጂዲስ ይሉታል የስነ ልቦና ጠበብት) በተከሳሹ ላይ ይፈርዳሉ (ጭራሽ ሊሰሙት አይፈልጉም፤የመናገር መብቱን ዝግ እንዲሆን ከፍተኛ
ጩኸት ያሰማሉ!)።
አሜሪካ ውስጥ
ብዙ ሰዎች በዘረኛ ፖሊሶችና በሐሰተኛ መስካሪዎች የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሲሰቃዩ ቆይተው “ከ 30 40 አመት” በሗላ አዲስ ምርምራ
ተከፍቶ ይግባኝ ተብሎ
በፈሮንዚክና በዲ ኤን ኤ ምርምራ ተጣርቶ አድራጊው ሌላ ሆኖ ተገኝቶ ብዙ ሰዎች ከተወነጀሉበት ነጻ እየሆኑ
አይተናል። ኢትዮጵያ ውስጥም በሥርዓቱ የታሰሩ ሰዎች ያለ ስማቸውና ወንጀላቸው እየተወንጀሉ “ይሰቀል፤ ይሰቀል” ሲባልላቸው የነበሩ
ብዙ ሰዎች በምሳሌ ማቅረብ ይቻላል።
ስለዚህ ተከሳሹ ፍትሕ አንዲያገኝ በሚጥርበት ወቅት የሕግ ምሁራን መስለው የመንጋ ፍትሕ በመስጠት በከሳሽና በተከሳሽ መሃል ገብተው ፍትሕ የሚያበላሹ “መንጋዎች” የመብዛቱ ጉዳይ ለፖለቲካውም ለፍትሑም ለማሕበረሰባዊ ሰላማዊ ግንኙነትም አስጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ፈራጅ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም። ክርስትያኖች ከሆናችሁ (ብዙዎቹ የመንጋው ብዛት ክርስትያኖች ይመስሉኛል) “አትፍረድ፤ ይፈረድብሃል” የሚለው የክርሰትያኖች ቅዱስ-ሕግ አያምኑበትም። በመንጋ መጓዝ ፤ በመንጋ ማጨብጨብ ፤ በመንጋ ማውገዝ ፤ በመንጋ ማወደስ ፤ መሳደብ፤ አንደ ከብት በመንጋ የመነዳት አዲስ ባሕል ይቁም! የግል ነፃነታችሁ ለመንጋ አሳልፋችሁ አትስጡ።
ጌታቸው ረዳ