Saturday, October 10, 2020

ድንቁርና የተባለ የአብይ አሕመድ ሸቀጥ ዲሲ ውስጥ ለገበያ ቀርቦ ሲታይ ዋለ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) የድንቁርና ሱሰኛነት Saturday, October 10, 2020

 

ድንቁርና የተባለ የአብይ አሕመድ ሸቀጥ ዲሲ ውስጥ ለገበያ ቀርቦ ሲታይ ዋለ

ጌታቸው ረዳ

(Ethiopian Semay)

የድንቁርና ሱሰኛነት

Saturday, October 10, 2020



ድንቁርና ማለት ምን ማለት ነው? የሚል ብትጠየቁ ዘርፈ ብዙ ተርጉም ያለው ቢሆንም ድንቁርና ማለት በራሳችን ላይ የምንጭነው ራስን በራስ የማታለያ ባሕሪ ነው።

ድንቁርናን ለመሸጥ የድንቁርና ጣዕም ያጣጣሙ ደንቆሮ ቸርቻሪዎች መፈለግ የግድ ነው። እነዚህ የድንቁርና ሸመተኞችና ቸርቻሪዎች አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ዛሬ ቅዳሜ October 10, 2020 የአብይ አሕመድን የድንቁርናን ጣዕም በጭፈራ ሲገልጹ  በቪዲዮ አይተናቸዋል።

 በሚገርም ሁኔታ ደግሞ የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች የሆኑትን የሻዕቢያ ባለሠልጣናትን አድናቂ የሆነው አሳዛኙ “የታሪክ ይፍረደን ዘፋኙ!?” “የዛሬው የአቢቹ አድናቂ” “ባለሁለት ምላሱ በአዝማሪው በሻምበል በላይነህ” አጫፋሪነት የታጅበው የድንቁርና ሸቀጣቸውን “በስዕለ ድምጽ” ያሰራጩትን የድጋፍ ሰልፋቸውን አይቼ ተገረምኩኝ።

ትዕይንቱ ያስታወሰኝ ወደ ግንቦት 7 ወደ ሗላ ከጥቂት አመታት በፊት ወደ እነ ብርሃኑ ነጋ እና ንአምን ዘለቀ የሻዕቢያ ባንዴራ እያውለበለቡ ሲያስቁንና ሲያበሽቁን የነበረውን አሳፋሪው የሻዕብያና የግንቦት 7 ጥምረት ሲያደርጉት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በትዝታ እንዳስታውስ አደረገኝ። እዚህ ሰልፍም የተደገመው ያው ሻዕቢያ በማያገባው አገር ገብቶ ደምጽ ሲያስተጋባ ከውስጥ በጥምረት የተቀናጀ ሰልፍ እንደሆነ የሚያሳየው ባንዴራቸው አብሮ ከኢትዮጵያ ባንዴራ ጎን እኩል ሲውለበለብ ማየት በአገሩ ውስጥ ያልፈቀደውን መብትና ትዕይነተ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ሊፈተፍት የፈቀደው ማን ነው የሚል ትልቅ ጥያቄና ስጋት የሚጭር ነው።

 አብይ አሕመድ መሪያችን ነው የሚለው የ2013  ለገበያ ቀርበው ድንቁርና ‘ያውም ሆን ተብሎ’ ‘ድንቁርናን መታገሱ’ (ዊልፉል ኢግኖራንስ) በሕግ መጠየቅ የሚገባቸው እነ አብይ አሕመድ የመሳሰሉ ግዙፋን ወንጀለኞችን ወንጀላቸው እንዲረሳና እንዲቀጥሉበት ማበረታታት ነው። የድንቁርና ቸርቻሪዎች ሚሊዮኖች በርሃብ በታረዙባት አገር እና በሃይማኖታቸውና በነገዳቸው እየደረሰባቸው ያለውን ዓለም ያወቀው ዕልቂት እየተካሄደባት ባለቺው ኢትዮጵያ ያውም በስደት አገር በመሃል አሜሪካ ውስጥ በሙዚቃ እየታጀቡ አደባበይ ለላይ አሳፋሪ ደስታቸውን በሙዚቃ ጭፈራ ሲያስተጋቡ ማየት ሆን ብለው እያዩ ያሉትን ዕልቂት ላለማየት ወስነው በተጠለሉባት አሜሪካ ምድር እንዲህ ያለ የጥጋብ ጭፈራ ውስጥ ገብተው ማየት ሆን ብለው ራሳቸውን እውነትን ከመማር ተቆጥበዋል።

 ይህም  በሕግ ዓይን deliberate disregard of the facts” እያዩ እና እየሰሙ ሰምተው እንዳልሰሙና አይተው እንዳላዩ በሞራልም በሕግና በታሪክ ያስቀጣል (ሕግ ቢኖር)።  

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የችለማ ዘመን የኢትዮጵያውያኖች ጭፍጨፋ ርሃብና ስደት ከመጤፍ ባይቆጥሩትም፡ እዚህ አሜሪካ በቫይረስ በሸታ ደስታዋን በተነጠቀቺውና ስራ በታጣባት ምድር ዋሺንግተን እና አካባቢዋ እየኖሩ እንዲህ ያለ የጥጋብ ጭፈራ ማንጸባረቅ ካሁን በፊት እንዳየናቸው ሁሉ የነዚህም እንዲሁ የፍትሕ ትርጉም ፤ የአገር ትርጉም ከጠላት ባንዴራ ጋር አብሮ መጨፈር እጅግ ዘግናኝ መሆኑን ለደነቆሩ ሰዎች ለማስረዳት ከባድ ነው።

ዋና ተልዕኮአቸው ልክ እንደመሪያቸው አብይ አሕመድና ልክ እንደ ተባባሪያቸው ሻዕቢያ “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ ፤ ራሳቸውን በጥልቅ የድንቁርና ባሕር ውስጥ እየዋኙ ፤ድሉዥን ውስጥ ገብተው’ የማይዳሰሰውን በመዳሰስ ላይ ናቸው። በሃዘን ድባብ በተወረረች አገር ኢትዮጵያ ላይ ጭፈራ የሚጨፍሩ እንዲህ ያሉ ጨፋሪዎች ሲያዩ ወላጆቻችን ትግሬዎች  “ጨርቁ ዝደርበየ ዕቡድ” (ጨርቁን የጣለ ዕብድ) ይሉታል።

አብይን ለመክሰስ በር የተዘጋባትን “ፍትሕ” ፤ ድምጽዋን ለማፈን የተነሳው ዋሺንገተን የተበሰበው “የብዝሃነት ድንቁርና” የሚነገረን ነገር  ‘አገራችን ውስጥ ለ29 አመት የዘለቀ የወንጀለኞች ሥርዓት ዛሬ ሥልጣኑን ላለመልቀቅና በወንጀል እንዳይጠየቅ የሚያደርጉት ጥረት ፤ በጉራጌው ፤ በጋሞውና በክርስትያኖች ህይወት ጥቃት እንዲፈጽሙ ለማድረግ መሪያችን ነው የሚሉትን አበይ አሕመድ ድሮ በሕቡእ የጥፋት ሃይሎች አባል ሆኖ (በሁለት አለም ሰላይነቱ) ሲያደራጅና ምስጢር ሲያቀብላቸው የነበሩትን ነብሰገዳዮች ጓዶቹ ከውጭ አገሮች ወደ አገር ውስጥ ያለ ምንም ውል እንዲገቡ በመፍቀድ፤  የሰለጠኑ የመንግሥት ወታደሮች ጠባቂ መድቦላቸው ዳግም ወንጀል እንዲፈጽሙ በማድረግ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች እንደ እንሰሳ ታርደው የዘርና የሃይማኖት ፍጅት እንዲከናወን ያደረገው ተጠያቂው መሪያቸውን ለመከላከል ነው።  

የአባ ጂፋር አድናቂው “የበሻሻው ንጉሥ አብይ አሕመድን” በመደገፍ በሻዕቢያ ባንዴራና ሁለት ዓይነት ይዘት ያላቸው የኢትዮጵያ ባንዴራ በያዙ ኢትዮጵያውያን እና በሻዕቢያ ኤርትራኖች ጭፈራ እየጨፈሩ ከንቱ ዝላይ ቢደረግም ውሎ አድሮ አብይ አሕመድ ከወንጀል ተጠያቂነት ሊደብቁት ከቶ አይቻላቸውም።  “በደንቁርና ሱሰኞች” እውነታዎች ችላ ቢባሉም  መኖራቸው አያቆሙም!

አመሰግናለሁ።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)