የወያኔዎች እና የኦነግ አብይ አሕመድ የ33 አመት ኢትዮጵያ ይህንን ትመስላለች! እንኳን እንኳን ቀረችብኝ!
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay
11/22/24
ባሕሉን በጣጥሰው አንዲህ ያለ አስደንግጭና አሳፋሪ ማሕበረሰብ አፍርተው ኢትዮጵያን አሳደግን ሲሉን፤ ይህ ሕዝብ ታግለን ነፃ ብናወጣውስ የባሕል ወረራ የተፈጸመበት ማንነቱን የረሳ እንዲህ ያለ ሕዝብ ያጋግማል ተብሎ ይታሰባል?!
ይህ የባሕል ወረራ እንዲደረግብን የታቀደው በጣሊያን ወረራ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በ14ኛው በ16ኛው ፤ በ18ኘው በ19ኛው እና በመለስ ዜናዊ እና አብይ አሕመድ በገዝዋት ኢትዮጵያ የቀጠለ ነው።
ለምሳሌ በትንሹ ራስ አሊ ዘመነ መንግሥት በኛ አቆጣጠር በ1822 ወይንም 1821 ዓ.ም አካባቢ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ነበር የተባለው የእንግሊዝ የታሪክ ምሁርና የፓርላማ አባል የነበረው “ሎርድ ቶማስ ባቢነግቶነ ማካውላይ” (Thomas Babington Macaulay) ስለ ጉብኝቱ አስመልክቶ በፈረንጆች 1827 ዓ.ም (በኛው ዘመ አቆጣጠር ለፓርለማው ጉባኤ የተናገረው የማይረሳ አደገኛ ንግግሩ እያመረቀዘ መጥቶ በትግሬዎችና ኦሮሞ ፖለቲከኞች ማዳበሪያ አግኝቶ እነሆ ዛሬ በ33 አመት ውስጥ በቪዲዮው የምታዩት ማንንቱን ጥሎ የባሕል ወረራ የተፈጸመበት ማሕበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ ዐይኑን አፍጦ ለማየት በቅተናል።
ቪዲዮውን ለማየት ከመሽቀዳደማችሁ በፊት እንዴት እንዲህ ሊከሰት እንደቻለ “ሎርድ ቶማስ ባቢነግቶነ ማካውላይ” (Thomas Babington Macaulay) ንግግር እነሆ፦
<< አፍሪካን ከጫፍ እስከጫፍ በስፋት የተዘረጋው ይህ ክ/ዓለም ሁሉንም ተዘዋውሬ አይቻለሁ። አንድም ሌባም ሆነ ለማኝ ሰው አላየሁም፤ በዚህች ሀገር (አትዮጵያ ማለቱ
ነው) ያየሁት ሃብት እና እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የሞራል እሴቶች ከቶውንም የትም አላየሁም ። እንደዚያ ያለ ማሕበረሰብ አከርካሪን
ሰብሮ ለማስገበር መንፈሳዊ እና ባህላዊ ቅርሶቿ በዘዴ እንዲሰበሩ
ካለደርግን በስተቀር ይህችን ሀገር እንቆጣጠራታለን ማለት ዘበት
ነው። ይህንን ለማድረግ አሮጌውን እና ጥንታዊውን የትምህርት ስርዓቷንና ባህሏን ሁሉ በእንግሊዝ ባሕልና በአንግሊዛዊ የትምሕርት ስርዓት እንዲተካ ሀሳብ
አቀርባለሁ ፣ ምክንያቱም አፍሪካውያን የውጭ ባሕል ሁሉ ስልጡን ነው ብለው እንዲያምኑ ከተደረገ የራሳቸው የሆነውን ባሕልና
ትምሕርት ንቀው ከጣሉት ሌላው ከራሳቸው የሚበልጥ ነው ብለው ስለሚቀበሉት፣
ለራሳቸው ያላቸውን ግምት በመቀነስ፣ የአፍ መፍቻ ባህላቸውንና ራሳቸው የሚገልጹበት ሃገራዊ ማንተቻውን ሁሉ ያጣሉ። በዚያ ጊዜ እኛ የምንፈልገውን ይሆናሉ፣ በእውነት የበታችና ተጨቋኝ የሆነ ህዝብ
ይሆናሉ>>
እ.ኤ.አ. የካቲት 2 ቀን 1835 የሎርድ ማካውላይ የእንግሊዝ ፓርላማ ከተናገረው ጠቅለል ብሎ ላንባቢ በቀላሊ እንደገባው አድርጌ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት። እንግዲህ በዚህ መልክ ኢትዮጵያ በ33 አመት ውስጥ ከጥንት ተያይዘው የመጡ ክቡር ባሕሎቻችን በጥበብ እንዲፈርሱ ከተደረጉ በኋላ ራሳችንን የምንገልጽባቸው ሃገራዊ ማንነተቻን በቸልተኛነት አስነጥቀን ወራሪዎች የሚፈልጉትን ሆነንላቸው። እነሆ ባስነዋሪ ባሕል ተዘፍቀናል። ይህንን ስዕለ ድምፅ እንድታዩና የ33 አመት ዕድገትን ሥልጣኔ ምን ውስጥ እንደዘፈቀን ይህንን እንድታዩ እጋብዛለሁ። አሁን አሁን ሳየው እንኳን እንዲህ ያለቺው ኢትዮጵያ ሄዶ ማየት ቀረቺብኝ ብያለሁ !
ሴቶችን ጠልፈው ልጅ እያስወለዱ የተወለዱትን ልጆች ይሸጣሉ
https://youtu.be/iO4HZCT8Fno?si=KZhDJcS9NkElQgFp