ለጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
(ጌታቸው ረዳ Facebook)
July 22/2019/ሐምሌ16/ 2011
ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay)
(ጌታቸው ረዳ Facebook)
July 22/2019/ሐምሌ16/ 2011
የአንድ ወዳጄ ጽሑፍ በድረገጽ ተለጥፎ አይቼው ወደ “ፌስቡክ” ስለላከኝ እሱን ፍለጋ ፌስ ቡክ ስገባ ምክንያቱ ባልታወቀ በድንገት ዋሺንግተን ውስጥ የሚገኘው የጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል ፌስ ቡክ ውስጥ ከተተኝ።
መግባቴ ላልቀረ ብየ ፌስ ቡካቸውን ስዳስስ “በሥርዓተ አልባው ኦነጋዊው መሪ አብይ አሕመድ ትዕዛዝ” የከፍተኛ ዳኞች ሓላፊ ሆና የተሾመቺው የፍናፍንት (የሌዝቢያን እና ገብረሰዶማዊያን) መብት አከብራለሁ የምትል ከባሕላችን፤ከሃይማኖታችን እና ከመንግሥታዊ ሕግ ውጭ የፍንፍንት መብት ቢከበር አልቃወምም፤ ችግር የለብኝም የምትል ዳኛ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በተጠቀሰው “የጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል” በእንግድነት መጋበዝዋ በሜይ 2019 (ፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር) የተለቀቀው የዚህ ማዕከል ማስታወቂያ ስመለከት እንዴት አንድ የባሕል አስከባሪ እና አሳዳጊ ነኝ የሚል ማዕከል ባሕላችንን ሃይማኖታችንን የሚጻረር
አቋም ያላትን አሳፋሪ ሴት እንዴት እውነት እንዴት፤እንዴት፤ምንዋ ስላማራቸው
በክብር ሊያስተናግድ
የማስታወቂያ ጥሪ አደረገ? የሚል ጥያቄ ጫረብኝ።
በነዚህ የአገራችን ፍናፍንት ላይ ምርምር ያደረጉ አጥኚዎች እንደሚሉት “ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፍናፍንቶች” እጅግ በቀልተኞች እንደሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ይፋ አድርገዋል። ይህ ደግሞ ሌሎች አገሮች ካሉት ፍንፍንቶች በባህሪያቸው የተለዩ በቀልተኞች መሆናቸውን የሚቃወሙዋቸውን በክፋት ለማጥመድ የማይቆፍሩት ሰይጣናዊ ሴራ እንደሌለ የተደረጉው ጥናት ያሳያል።
ይህ እየታወቀ ይህች “የፍንፍንት” መብት ቢከበር አልቃወምም ባይዋ የሕብረተሰባችንን ያፈጠጠ ዓይን የማያስፈራት ‘ገታራ ቅንድብ’ በእዛው አሳፋሪ አቋሟ ታሪክ ዘግቧታል። እንዲህ ያለ አቋም ከየት አገኘሺው ተብላ በጋዜጠኛ ቤቲ (የኤል ቲ ቪ ጋዜጠኛ) ስትጠየቅ “ኢትዮጵያ ውስጥ እያለሁ የፍናፍንቶች መብት ጥያቄ እቃወም ነበር ፡ ነገር ግን አሜሪካ አገር ለትምህርት ሄጄ በነበርኩበት ጊዜ ነው አቋሜን የለወጥኩት” ብላ እርፍ! ወይ አሜረካ!
አያችሁ አሜሪካ እና አውሮጳ እንዲሁም ሩሲያ እየሄዱ የቀሰሙትን ማርክሳዊ ሌኒናዎ ትምህርት እንዲሁም የ666 ቶቹ ቡድን የሚያጠናክረው እና የሚያስፋፋው ‘ የፍናፍንት መብት” ስለ መከበር ትምህርት እየቀሰሙ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ባሕሉን በርዘው አሁን ወዳለንበት የሲኦል አገር አደረግዋት። ይህች ዳኛም “መሃላ ምላ” ፤ለባሕላችን ለሃይማኖታችን ክብር “ቃል ገብታ” የተረከበቺው ከፍተኛ የዳኝነት መንበርም ምንም ሰቀቀን ሳይሰጣት እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት የወጣቶች ሕሊና እና አስተሳሰብ የሚበርዝ በራዥ ንግግር በሚዲያ ማስተላለፍዋ የሚያሳየን የሕዝብ፤የሃይማኖት እና የባሕል አክብሮት እንደሌላት ማሳያ ነው። ኦነጋዊ አናርኪስ መንግሥት ባይሆን ኖሮ ይኼኔ ከሥልጣን ትወገድ ነበር።
ወላጅ እናትዋ ሁለት ሴቶች ግብረስጋ ቢፈጽሙ፤ቢሳሳሙ፤ ሁለት ተባዕት ሰዶማዊ ግብረስጋ ቢፈጽሙ በበኩሌ አልቃወምም ስትል ሰምተዋት ምን ተሰምቷቸው ይሆን? ይህ ጥያቄ ወላጅ እናትዋ ቢጠይቅዋት ለጋዜጠኛዋ የመለሰቺለላትን ዓይነት መልስ ትመልስላቸው ይሆን? የሚገርም ነውረኛ ዘመን!!
ስለ ይህች ዳኛ የመጀመሪያ እውቀቱ የነበረኝ አዲስ አበባ ሲታተም በነበረው ዜጋ መጽሔት ላይ ነው። እኔ በዛው መጽሔት መስከረም ጥቅምት 1994 ቁጥር አንድ ሦስተኛ ዓመት “ብርበራ በሚል አምድ የኔ ጽሑፍ ታትሞ” የእርስዋ ቃለ መጠይቅ ደግሞ “ሰሞኑን ከማን ጋር” በሚለው አምድ ላይ የሁለታችን ታትሞ በወጣበት ወቅት ነው ስለ ሴትዮዋ የሴቶች መብት ጠበቃ መሆንዋን ያወቅኩት። በዛው መስክ በጎ ስራ እንደሰራች እንዳለ ሆኖ በሗላ ወደ አሜሪካ ለትምህርት ሄዳ ጎትታ ያመጣቺው የአቁዋም ለውጥ ግን አነጋጋሪ ነው።
ሌላ ቀርቶ በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው የመብት ረገጣ፤ የኦሮሞ አክራሪ ከንቲባዎች እና ፖሊሶች የዜጎችን መብት እየጣሱ፡ ቤቶቻቸው በቡልዶዘር እያስፈረሱ፤ ህጻናት እርጉዞች፤እመጫቶች እና አዛውንቶች ወደ ጎዳና እየተጣሉ የጐርፍ እና የዝናብ ዶፍ ሲወረድባቸው ምንም ተቃውሞ ያላሳየች ማስቆምም ያልቻለች’ ለዳኝነት የማትመጥን የአፓርታይዱ ሥርዓት ሎሌ ነች። ለዚች ሴት ነው ይህ የጣይቱ ማዕከል ለዚች የአፓርታይድ ሥርዓት አገልጋይ ክብር የሠጠው።
በኋላ ከአንደበትዋ ሳደምጥ ደግሞ “ክፍሌ ወዳጆ” የተባለ የመለስ ዜናዊ አፓርታይድ ሎሌን ስታመሰግን እና እርስዋም በአፓርታይዱ ስርዓት ሕገ መንግሥት እንዴት አንደሚዋቀር ያሳያት ክፍሌ ወዳጆ መሆኑን ስታመሰግነው ሰምቼ “በይ፤በበይ ዞር በይ!” ብያት ነበር። ቆየት ብላ የአሀገሪቱ ከፍተኛ ዳኛ ሆና ስትሾም “በበኩሌ የፍንፍንት” ሴቶች መብት ቢከበር ችግር የለኝም’ ስትል አድምጬኣት ሴትዮዋ ለዛ ቦታ የማትመጥን እንደሆነች አረጋገጠችልን። ዛሬ የጣይቱ ባሕል የሚባል ይህችን ባሕላችንን የማታከብር ዳኛ የአክብሮት እንግዳ ሆና ስትጋበዝ “ጣይቱ የባሕል እና የትምህርት ማዕከል” ጥያቄ ውስጥ አስገብቸዋለሁ። (?!) ወይ ዘመነ አብይ አሕመድ ስንቱን ጉድ አሳይን!
አንድ ጉደ ልጨምርላችሁ እና ላብቃ፦
እርስዋ ብቻ እንዳይመስላችሁ። አንድዋ የቤተመንሥቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቃል አቀባይ “ቢልለኔ ሥዩም” የተባለች ሌላዋ ጉደኛ ደግሞ ዚምባቡዌ አፍሪካ ያደገቺው ወጣት ወንድን “ቢ ኤ ማን” ብለህ “በሦስት አስጠሊታ ቃላት- እንደ መጥራት የመሰለ የመጨረሻ አስጠሊታ መጥፎ ቃላት የለም ብላ ወጣት ወንዶችን የወንድነት ባሕሪ እንዳይዙ የምትኮንን “ጽንፈኛ አንስት/ፌሚኒሰት” ጉዳይ በስዋም ላይ አንድ ልብል።
ይህች ወጣት “ኦነጋዊው አብይ አሕመድ” ፡ ለሥልጣን የሾማት ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ሴትዮም ከስሜ በፊት “ወ/ሮ ወይንም ወ/ት” ብላችሁ አትጥሩኝ ብላ ለዜና ማሰራጫ ደብዳቤ ጽፍ ስትቆጣ ሰምተናል። ይህች “ሴትዮ” ብየ የምልበት ምክንያትም “ሴት ስለምትመስል “ሴት” ከማለት ውጭ ምን ብየ ልጥራት? አንዲት ሄዋን በዓለም አቀፍም ይሁን በኢትዮጵያ አጠራር በወ/ሮ ወይንም በወ/ት ካልተጠራች ምን ብለን እንጥራት? ለምን ያንን አስጠላት? መልሱን አናውቀውም። “አቶ” በሉኝ ብትለን እኮ “አቶ ቢልለኔ ስዩም” ብለን እንጠራት ነበር። ግን እርሱም ግልጽ አላደረገችልንም። እንግዲህ የምስጢሩ እንቆቁልሽ ደብዳቤው ምን ማለት እንደሆነ የሚገባችሁ ይመስለኛል። ወይ አብይ አሕመድ! በአንድ አመት ዕድሜው ውስጥ ከምን እያፈናፈነ እንደሚያገኛቸው አላውቅም
“እየጎተተ” ያላስተዋወቀን
ጉድ የለም።
እምየ ኢትዮጵያ ሆይ! ጉድሽን ሰምተሻል? አንቺ በእናትነትሽ “አንቺ እመየ ኢትዮጵያ” እየተባልሽ የወለድሺያቸው “ሴት ልጆችሽ” ግን “አንቺ” ወይንም ወ/ሮ ወይንም ወ/ት አትበሉን ሲሉ ሰምተሽ ምን ተሰምቶሽ ይሆን? ብርታቱን ይስጥሽ!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ - ጌታቸው ረዳ ፌስ ቡክ)