Tuesday, May 9, 2017

የአማራው ብሔር በኢትዮጵያዊነቱ በአህያ ተመፈናጣጥ አውጥቶን የጄት አብራሪ እና የአይር መንገድ ባለቤት አድርጎናል! የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው

የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው
May 10, 2017
ይድረስ ለመላው የኢትዮጵያ ወጣቱ ትውልድ፥
አትታለል! አማራው አልበደለህም! ሊያጠፋህ በገንዘብ ተገዝቶ በብሔር እየከፋፈልህ ያለው ጸረ አማራው የብሔር ነፃ አዎጭው ቡድን እንጂ አማራ አይደልም። በአንተ ደም፣ አጥንት እና ሕይወት የእሱ ልጆች ተንደላቀው  በእንግሊዝ ኦክስ ፎርድ; በአሜሪካን ሳይቀር ተምሮ ብዙም ሃብት ተጉዞለት በየባንኩ ስለተቀመጠለት መከራን፣ እረሃብ እና ጥማት መታረዝና ችግር የሚባል እንዳያየው በዶላር ተጠቅልሎ ይገኛል።

አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ወላይታ፣ አኙዋክ፣ ዶርዜ፣ ከምባታ፣ ሐዲያ፣ እናም ሌላውም ብሔር ነኝ እያልክ እራስህን ሳታታልልኢትዮጵያዊ ነኝብለህ ተሰባሰብህ ታገል፣ አንድ ሁን። አንድ ሆነህ በኢትዮጵያዊነትህ ከዳር እስከዳር ኢትዮጵያን፤ለሉዓላዊነትህና ለኢትዮጵያዊነት ኩራትህን ለማስመለስና ለመጠበቅ ስትል  ጎሰኛነትን አስወግደህ በቁጥጥርህ ስር አግባት። የብሔርን አጥር ክልል ብጥስጥሱን አውጥተህ ካላቃጠልከው አገርህ በአደገኛ ሁኔታ መጓዝዋን ትቀጥላለች።ስለሆነም ኢትዮጵያ ዛሬውኑ ትጠራሃለች!

ከዚህ በታች የሚታዩት ፎቶግራፎች የተወሰዱት በእጄ ከሚገኘው 1990 የኢትዮጵያን የአየር መንገድ በይፋ እንድጎበኝ በተደረገ ጊዜ ከኢትዮጵያ የአየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ካፕቴን መሃመድ እጅ በይፋ በአየር መንገዱ ስም ካበረከቱልኝ ስጦታዎች መሃል ከአንዱ መጽሃፍ ነው። አላማውም የኢትዮጵያ የአየር መንገድን ባገኘሁት መድረክ ሁሉ ታሪኩን በኩራት እንዳስተዋውቅ ነበር።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመርያው የአፍሪካ ተወላጆች አየር መንገድ ነው።


እዚህ ፎቶግራፍ ላይ የሚታየቱት አማራው የብሔር ልዩነት ሳያደርግ እንደውም ታሪክ እንዳስቀመጠው የትምህርቱ እድል ከተሰጣቸው ማንነት ሲታይ በብዛት አማራው ሳይሆን ሌላውን ብሔር ነበር እድል በመስጠት ቅድሚያ ተጠቃሚ ያደረገው ትግሪኛ ተናጋሪውን ጭምር ነበር ከባሕር መላሽ (ኤርትራን) አካቶ።

ከእኛ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አልፎ ተርፎ የአማራው ማንቃት እና ጥረቱ ሌሎቹን የአፍሪካ ትወላጆች ለምሳሌ እንደ ካሜሩን ኤር (ካሜር) ጋና ኤርወይስ፣ ኬኒያ ኤርወይስ እና ናይጄሪያ ኤርወይስ በጊዜው ሌሎቹንም የጄት አብራሪ አድርጓቸዋል። እነ ካፕቴን ቤሎ ካሜር አዲስ አበባ የነበሩ የካምሩን ዲፕሎማቲክ ልጆች የካሜሩን አየር መንገድ ድንቅ ካፕቴኖች የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ውጤቶች ናቸው። የኒልሰን ማንዴላም ኩራት ይሄው አየር መንገዳችን እና አብራሪዎቹ መሆናቸውን መዘንጋት አይኖርብንም። ማንዴላም ወደ ኢትዮጵያ መጀመርያ የገቡት በኢትዮጵያ የአየር መንገድ እና በኢትዮጵያውያን ካፕቴን እና ኮፓይለት በመንገደኛ ኤርፕሌን ከለንደን አዲስ አበባ አብርረዋቸው መሆኑ እዚህ ላይ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ማራው ኩራትን እና እራስን ቀና አድርጎ መሄድን እንጂ ያስተማረው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዝቅተኛነትን አላስተማረውም። ወንጀል የለበትም። ወንጀለኛ ወያኔ ብቻ ነው። አማራው ዛሬ የባዕዳን ተላላኪ ለሆነው ወያኔ ትልቅነትን ነበር ያስተማረው።

ሃቅ እና ውለታ በክህደት ሊጠፋ አይችልም። አማራው አንድም ቀን ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን በድሎ አያውቅም። ወንጀሉ ሕዝቡን ከኋላ ቀርነት እንዲወጣ ባጭር ጊዜ ጥረት አድርጎ ከጦርነት ማግስት ኢትዮጵያን የማልማት ሕልሙን በአጤ ምኒልክ መንግስት ጊዜ ጀመሮ ትምህርት ቤት በመክፈት እና ባቡር በማስገባት፤ ትልቅ ልማትን፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የባቡር ሀዲድ በመዘርጋት፤ ባቡሩ በሚያልፍበባቸው ቦታዎች ሰፋፊ የንግድ ከተማዎችን እንዳስፋፋው ሁሉ፤ በአጤ ኃይለስላሴም ጊዜ በተመሳሳይ ጣሊያን አባርሮ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙም ሳይቆይ ወዲያው ወደ የትምህርት ገበታ ተመጋቢ ነው ያደረጉት። አማራው ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብሔር የማይስተካከል ትልቅ እድገትን ለኢትዮጵያ እና ለመላው ሕዝቧቻ እየሰጠ ያስተማረው ብዙ ነው።
ሕዝብን እናቱ እና አባቱ ሳያስተምሩት በግ እና ፍየል፣ በሬ እና ላም፣ ዶሮ እና ግመል ብሎም ፈረስ አግድ እየተባለ የሚደብቁትን ነበር ወደ ትምህርት ገበታ በማቅረብ በቀን ሶስት አራት ጊዜ እየበላ ንጽህናው ተጠብቆለት ጤንነቱን በመንከባከብ ተምሮ ለራሱ እና ለቤተሰቡ ደራሽ የተደረገው (ያውም ወደ ሁለተኛ ደረጃ እና ዩኒቨርሲቲ የሚማሩትን ጎሳ ሳይለይ የኪስ ገንዘብ እየተከፈለው አንደነበር ታሪክ መዝግቦታል) ዛሬ ያ ዕድል በምን ዕደሉ ያግኘው!? ለዚህ ምስክሩ እራሱ በዘመናዊ ትምህርት እውቀትን የቀሰመው በመላ ዓለም የተበተነው ምሁሩ ክፍል ነው። ታዲያ የአማራው ውለታ ብዙ ሆኖ እያለ  ወደ ኋላ አስቀረን እራሱን ብቻ ጠቅሟል፤ ለጎሳው በማዳላት በድሎህ ነበር እየተባለ በፋሺስት ጣሊያን ወራሪዎች ዘመን የተጀመረው ተኪስ የወጣ የጠላት ዘመቻ መበራከቱ አገርን ከመጉዳት አልፎ ፤ሥልጣን መወጣጪያ ምክንያት ከመሆን እና እርባና ቢስ ውንጀላው ራስን በትንሽነት ከማስገመት በቀር  የአማራውን ትልቅነትና ለአገሩ የዋለው አምላክ በማሕደሩ የዘገበውን የአማራ አገራዊ ውለታ ምንም ታምር አይቀንሰውም።

እያንዳንዱ አገር ውስጥ አልሚ ብሄር ወይም ብሄሮች እና መሪዎቻቸው ባደረጉት የልማት አስተዋጽዖ ይታወቃሉ። አማራው ሌላውን ትቼ ለዛሬ የተነሳሁበት ላይ ብቻ ባተኩር ዘመናዊ እውቀትን እንደ ዶርዜው የጥበብ የሃገር ልብስ ባለቤት ሲያደርገን እንደኖረው፡ ዛሬ በኢትዮጵያ አገራችን ትልቅ የእውቀት ጥበብን በደማችን መጀመርያ ስለወጋን ስለ አማራው እና አመራሩ ባለውለታነት በማስቀመጥ ስለሌሎቹም ቀጥዬ በተከታታይ ከአማራው ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን አገራቸውን ስላለሟት በግልጽ በማስረጃ ጭምር በማቅረብ ነፃ አውጪነን በሚል ለወጣቱ ትውልድ ውሸት እያጎረሱት ግራ ላጋቡት ወጣት ኢትዮጵያዊ መነሻ መረጃ ይሆነው ዘንድ፡ እያንዳንዱን በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ ኢትዮጵያዊ ተብሎ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያደርጋትን የተለያየ ባሕል እና ቋንቋ አንድነት ድምር ባለቤት በአንድነት እና በግሉ ለአገሩ ኢትዮጵያ ያበረከተውን የልማት እና ንቃት አዳዲስ ስልጣኔ እና ነባሩን በማገናዘብ ለወጣቱ ትውልድ አካፍላለሁ።


አሜሪካንን ብንወሰድ ዛሬ አሜሪካን እያበደረች እንጂ በነጻ ትምህርት አትሰጠም፣ በዩንቨርስቲዎቿ ለዜጎችዋ አትሰጠም። ለእኔ እንጂ ለእኛ የሚል መሪ እና የመንግስት አስተዳደር ባለመሆኑ በአሜሪካን ያለው ተማሪው ጎበዝ እንኳን ቢሆን አብዛኛው ተማሪ በባችለር ደረጃ ያቆማል፣ ትምህርቱን በገንዘብ ችግር እና እዳ ላለማብዛት በማሰብ። ጥቂቱ የነፃ ትምህርት በጣም ጎበዝ ስለሆነ ብቻ ተብሎ ቢሰጠውም ስኮላርሽፕ ሃቁ ግን አብዛኛው አሜሪካን መማር እየቻለ እንዳይማር ይደረጋል።

ኢትዮጵያ ግንእኛበሚል የሚያምኑ ማለትም እኛ ኢትዮጵያውያን በሚል ለኢትዮጵያውያን የሚያስበው የአማራው አመራር መጀመርያ የፊደል ትምህርት አስፋፍቶ ሴቱንም ወንዱንም በማስተማር ከዛም ዘመናዊ የትምህርት ቤት በመስራት ገና ከጣሊያን ጦርነት እና ቁስል ሳያገግም ወገኑ ከሁሉም አብራክ ኢትዮጵያዊ የተወለደውን ወጣት በጊዜው ከአውሮፓውያን እኩል ለማስቀመጥ በጥበብ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃን ትምህርት ቤት በመክፈት እያስተማረ ቀጥሎም ብዙም ሳይቆይ የኮሌጆች እና የዩንቨርስቲዎች ባለቤት አደረገው ወጣቱን እና ኢትዮጵያን ሐገሩን። ይሄንን አይነት አስተዋጽዎ ለማበርከት እና ለማልማት አገርን እና የሕዝቧን አይምሮ እኛየሚል የኢትዮጵያዊነትን ደም የተወጋ መሪ እና ሕዝብ ያስፈልጋል። በመሆኑም ጥቂቶቹን በስም ለማስቅመጥ አማራው ይሄንን በተግባር በማስረጃ አስረክቧል; ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ። ለመጥቀስ ያህል በጥቂቱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፡ አዲስ አበባ። የሕንጻ ኮሌጅ አዲስ አበባ። ተግባረ እድ፣ አዲስ አበባ፣ የመከላከያ ትምህርት ቤቶችን አስመክቲ ደግሞ የፓሊስ አባዲና ኮሌጅ አዲስ አበባ። የሐረር የጦር አካዳሚ፣ ሐረር። ሆለታ የጦር ትምህርት ቤት፣ ሆለታ ወዘተ.. ዛሬ ወያኔ ወደ ሥልጣን መጥቶ አንዳንዶቹን መጠሪያ ስያሜአቸው ለውጦ በእራሱ ታጋዮች ስም ይጥራቸው እንጂ ዛሬ ወያኔም እየተገለገለባቸው ያሉት እነዚህ ተቋማት መካድ የማይቻል ህያው ቋሚ ምስክሮች ናቸው።

የጅማ ዩንቨርስቲጂማ። የባህር ዳር ዩንቨርስቲባህር ዳር። አስመራ ዩንቨርሲቲ በግሪጎሪያን አቆጣጠር 1958 አስመራኤርትራ። አሁን ግን ኢሳይያስ በውስጥ በተፈጠረው የፓለቲካ ቀውስ የዘጋው ማለት ነው። እንግዲህ በአማራው አመራር ዘመን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ አስተምሯል። ይሄውም ኢሳያስ አፈወርቅን፣ ለገሰ ዜናዊን እና ሌንጮ ለታ በሚል የሚታወቀው ውነተኛ ስሙ ዮሐንስን ያስተማሩ ተቋማት ናቸው።
ኢትዮጵያ በሃቀኛ ልጆችዋ ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!
ከአክብሮት ጋር።
የኢትዮጵያወርቅ (የሐረርወርቅ) ጋሻው።
ዘብሄረ አንድ ኢትዮጵያ።
ከዚህ በታች ያለውን በጎግል የምታገኙት መረጃ ነው።
Historical Background
Jimma University College of Agriculture and Veterinary Medicine (JUCAVM) was established in 1952 as Jimma Agricultural Technical School (JATS) following the agreement signed between the United States of America and the Imperial Ethiopian Government under the joint affiliation of Ethiopian Ministry of Education (MoE) and the Oklahoma State University (former Oklahoma Agricultural and Mechanical College) for the period between 1952 and 1956. From 1956 to 1968, the school was jointly administered under the Ethiopian Ministry of Agriculture (MoA) and the Oklahoma State University. Following the termination of the agreement with the Oklahoma State University, the school was under the exclusive administration of the Ethiopian MoA for the period 1968 to 1979 and it was renamed as Jimma Institute of Agriculture (JIA). From 1979 to 1990, the institute was under the administration of Commission for Higher Education and the naming was once again tailored to Jimma Junior College of Agriculture (JJCA).
ባሕር ዳር ዩንቨርስትይ፡ በግሪጎሪያን አቆጣጠር 1963 ጀምሮ። http://www.bdu.edu.et/
(Thanks Yeharerwerk Gashaw- posted at Ethiopian Semay)