Monday, September 2, 2019

The Ethiopian Version of the Beast (666) – የኢትዮጵያው ዐውሬ (666) - “ሰባተኛው ንጉሥ” ትንቢቱ ደረሰ (ከአዲ አበባ) posted at Ethio Semay


The Ethiopian Version of the Beast (666) –
የኢትዮጵያው ዐውሬ (666) - “ሰባተኛው ንጉሥ”
ትንቢቱ ደረሰ (ከአዲ አበባ)
posted at Ethio Semay

ባለፈው ሰሞን “ትንቢትን በሤራና በግድያ ማስቀረት አይቻልም!” በሚል ርዕስ አንዲት መጣጥፍ ለየድረገፆች መላኬና አንዳንዶች መለጠፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በራሳቸው ምክንያት አላወጡትም፡፡ ወደ ምክንያታቸው ገብቼ በከንቱ መዳከርን አልወደድኩም፡፡ የምልከውን አወጡ አላወጡ ለኔ አይደለም፤ እኔ አልጠቀምም/ አልጎዳምም፡፡ ይህ ነው ብዬ በውል የማላውቀው ኃይል ከልጅነቴ ጀምሮ ላለፉት 30 ዓመታት ሲያስጮኸኝ ሰንብቷል፡፡ ብዙዎቹ የምላቸው ነገሮች በገሃድ ታይተዋል፡፡ እኔን “እንዲህ ነኝ/አይደለሁም” እያልኩ አይደለም፡፡ የማይታወቅ ሰው ምንም ቢል ደግሞ ሰሚ የለውምና ጉራ አይከጅለውም፡፡  

ዛሬ ጧት ዐውሬው በእሥራኤል ሀገር የተደረገለትን ሁለት ዓይነት አቀባበል በዩቲዩብ አየሁ፡፡ ውድ ኢትዮ-እሥራኤላውያን በነፃነት በሚኖሩባት ሁለተኛ ሀገራቸው እሥራኤል ውስጥ ለዚህ መሠሪ ዐውሬ ያደረጉት አቀባበል እንደ አንድ የሀገር መሪ ነኝ ባይ እጅግ አሣፋሪ ነው፡፡ እርሱ ግን አራት ኪሎን የያዘበት የተለዬ ዓላማ ስላለው ሀፍረትን አያውቅም፡፡ መለስንና አቢይን የመሳሰሉ ሰዎች ለተለዬ አጋንንታዊ ተልእኮ ሥልጣን ስለሚይዙ ዐይናቸውን በጨው አጥበው በሚያከናውኗቸው ፀያፍ ተግባሮቻቸው ከመኩራት ይልቅ አያፍሩም፡፡ እኔ ያን ከዚህ ማስታወሻ ግርጌ አንዱን አድራሻ ያስቀመጥኩትን ጽሑፍ ካወጣሁ ከአንድ ሣምንት በኋላ ዩቲዩብ ስጎረጉር የአባ አምሐ ሥላሤን ማስጠንቀቂያ አገኘሁና አዳመጥኩት፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከኔው ጽሑፍ ጋር በብዙ ነገሩ ይመሳሰላል፡፡ ፈጣሪ ሲፈልግ ድንጋይንም ዛፍና ቅጠልንም ያናግራልና እኛ በኑሮ ዘይቤም ሆነ በመኖሪያ ቦታ የምንለያይ ሰዎች የምናስላልፈው መልእክት መመሳሰል ለነገር መሆኑን ለመጠቆም ይህችን አጭር አስተያየት ዛሬ ሰነዘርኩ፡፡

መጥምቁ ዮሐንስ ሰሚ ባያገኝም “መንግሥተ ሰማይ ቀርባለችና ንስሃ ግቡ” እያለ በበረሃ ይዘዋወር ነበር፡፡ እኔ ኃጢኣተኛውና ዓለማዊው ግለሰብ ደግሞ የታየኝን ተናገርኩ፤ እናገራለሁም፡፡ 

የዮሐንስ ራዕይ ላይ የተጠቀሰው ዐውሬ አንድ ብቻ አይመስለኝም፡፡ በየሀገራቱና በየዘመናቱ የሚመጣና ራሱን እንደአሜባ የሚያበዛም ይመስለኛል፡፡ በዚህ ዘመን ይህ አቢይ የሚባል የጭቃ እሾህ የዐውሬው ምትክ ሆኖ እያገለገለ እንደሆነ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ (በፊት ልዝብ ሰይጣን ነበር አሁን ግን ለይቶለት ዲያብሎስን በኢትዮጵያ ተክቷል!)
የአባ አምሐየስን የትንቢት ቃል ለማዳመጥ የፈለገ  


“ትንቢትን በሤራና በግድያ ማስቀረት አይቻልም!” የሚለውን ጽሑፍ ማንበብ የሚፈልግ ይህን ማስወንጨፊያ መንካትና ከኢትዮፎረም ድረገጽ ማንበብ ይችላል፡፡  Welkait website 


- ይቺን ገጽ ለመሙላት ብቻ ጥቂት ነገር ልበል፡- በአሁኑ ወቅት የሚሾሙ ሰዎችን ተመልከቱ፡፡ አብዛኞቹና ወሳኝ ቦታ ላይ የሚመደቡት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ በኦሮሞነታቸው ላይ ሃይማኖታቸው ፕሮቴስታንት ነው፡፡ ወይም ኢ-ሃይማኖታውያን(atheists)፡፡ ጥቂቶች ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ተሹዋሚዎች በዕድሜ ፌዴራላዊያን ናቸው - ማለትም በዕድሜ ያልገፉ ወጣቶችና ጎልማሦች ናቸው - በፌዘኛ ፌዴራሊዝም ዘመን ተኮትኩተው ያደጉ፡፡ ብዙዎቹ አቢይ የሚያውቃቸውና በካድሬነት ወያኔን ያገለገሉ ናቸው፡፡ ግለ ታሪካቸው ደግሞ በሹመታቸው ላይ አንድም ተፅዕኖ የለውም - ሙልጭ ያሉ ሌቦች ወይም ገዳዮች መሆናቸው ከሹመት አያግዳቸውም - ብቻ የከይሲው ወዳጆችና ደንገጡሮች ይሁኑ፡፡ በዕድሜ በአማካይ ከ25 እስ 45 ግፋ ቢል እስከ 50 ይሆናሉ፡፡ ብዙዎቹ ሹመኞች ራስ ወዳድና ማኅደራቸው በ”ፋወል” የተሞላ አጭበርባሪዎች ናቸው - በሀሰት ዲግሪዎች የተምበሸበሹ  ከርሳሞች፡፡ ሆዳምነቱንና ከሃዲነቱን በግልጽ ካላስመሰከረ በስተቀር ኦርቶዶክስና አማራ በምንም መንገድ አይሾምም፡፡ በቅርብ የሚለይላት ገደል አፋፍ ላይ የምትገኘው የአቢይ ኢትዮጵያ ይህች ናት፡፡
Posted at Ethio Semay
ትንቢትን በሤራና በግድያ ማስቀረት አይቻልም!
ትንቢቱ ደረሰ (ከአዲስ አበባ)
የባህር ዳሩን የአማራ ባለሥልጣናት ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሄኖክ የሽጥላ በዩቲዩብ ያቀረበውን ሀተታ ተከታተልኩ፡፡ እነአቢይና ወያኔዎች ይህን ግድያ ማቀነባበራቸውን በፊትም የምንጠረጥረው ነገር ነው፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተገለጸው የአማራ ጠላቶች እጅግ ከመብዛታቸውም በተጨማሪ አንዳንድ ወፍዘራሾችከናካቴው የለምየሚሉትን ይህን ጎሣ በማጥፋት ረገድ ሁሉም ይተባበራሉእነሱ ራሳቸው የማይስማሙና እንደዐይጥና ድመት አጥፊና ጠፊ ሆነውም ቢሆንቤንዚንና እሳት ሆነውም ቢሆን በአማራ ላይ ያላቸው አቋም ግን አንድ ነውይህንን የኢትዮጵያ አለኝታ ነገድ ከሥሩ መንግሎ ማጥፋት፡ትልቅ ምክንያትም አላቸውእርሱ ወደ ሥልጣን ከመጣ እንደልባቸው የሚዘባነኑበት በሙስናና በዘረፋ የሚገኝ የሀገር ሀብት፣ ለየደናቁርት የጎሣ አባሎቻቸው እንደገና ዳቦ እንዳፈተታቸው የሚያቃርጡት የይስሙላው የፌዴራል ሥልጣን አይኖርም፤ወርቃማ ጊዚያችን ይህች ናት!” ብለው ስለሚያምኑ ይህን የኳስ አበደች ዘመን በፍቅር ይወዱታልበዚህ ዘመን የሚመጣባቸውን ሁሉ ግም ለግም እየተረዳዱአንድ ሰውና አንድ ጥይትእስኪቀራቸው ይዋጉታል፡፡ ለዚህም ነውበህገ መንግሥታችን አንደራደርምበሚል እንደ አሠርቱ ትዕዛዛት ጉያቸው ውስጥ ወትፈው ያን ከሽንት ቤት ወረቀትነት ያነሰ ዋጋ ያለውን ሕወሓታዊ ሠነድ ጣዖታዊ ቤተ መቅደሳቸው ውስጥ አኑረው የሚፎክሩበት፡፡
-     
-    አማራ ካልጠፋላቸው ዕንቅልፍ የሚባል በዐይናቸው አይዞርም፡፡ እነዚህ የአማራ ጠላቶች የትግራይ ወያኔዎችና የኦሮሞ ኦነጋውያን ናቸው፡፡ እነዚህን የሚያሰማሩ የአዲሱ ዓለም ሥርዓት አዋላጅ የሆኑት ኢሉሚናቲዎችም መዘንጋት የለባቸውም (The so called Illuminati who are by now at the(ir) peak to form the New World Order after destroying nearly 80% of the world’s population….)፡፡ እነዚህን ፍናፍንት ዜጎች በአማራ ጠላትነት እያነሳሱና እያደራጁ፣ በበጀትና በዘመናዊ ጦር መሣሪያም እያጠናከሩ፣ ዘመናዊ የሣተላይት መረጃ እየመገቡ በኢትዮጵያ ላይ ጃዝ ብለው ይለቋቸዋል፡፡ ይህም ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ የፈዘዝነውም ሆነ የተበታተንነው ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ አንድ ያልሆነውም ሆነ በትንሹም በትልቁም የምንንነታረከው ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ብዙ ሆነን ሳለ ጥቂት የሆንነው፣ ኃያል ሆነን ሳለ ደካማ የሆንነው፣ ሀብታም ሆነን ሳለ ድሃ የሆንነው፣ አንበሣ ሆነን ሳለ ከዝንጀሮም ያነስነው ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ይህን ካልኩ ዘንዳ የትንቢቱን ፍጻሜ ልንገርህ፡፡ የምታውቁትን ነገር እንደአዲስ በመቁጠርያበጠው ይፈንዳበሚል ብሂል ቆዳየን አላዋድድም፡፡ እውነቱ ግን ይሄው ነው፡፡ ጠላቶችም መከራቸውን የሚያዩትና ከዳር እዳር ኅብረት ፈጥረው አማራንና የአማራን ብቸኛ መመኪያ ኢትዮጵያን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚራወጡት የመጨረሻውን ትንቢት እነሱም ስለሚያውቁና ያንን የማይቀር ትንቢት የቀለበሱ መስሏቸው ነው፡፡ ይህን እያስገመገመ በመምጣት ላይ የሚገኝን ገሃድ እውነት መናገር ድፍረት ሊመስል ይችላል፡፡ ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡
-     
-    አማራ ማንሠራራቱ ዕንቅልፍ እንደነሳቸው ገልጸናል፡፡ እነአሣምነው እየተጓዙበት የነበረው ሀገርን የመፍጠር እንቅስቃሴ እነአቢይንና አክራሪ ኦሮሞዎችን፣ አክራሪ ትግሬዎችን፣ ከየጎሣው ያሉ ሆዳምና ነቀዝ ዜጎችን በጠቅላላው ዕረፍት ነስቷቸው ነበር፡፡ ስለዚህም ያንን ግልጽ የግድያ ዘመቻ ካላንዳች ይሉኝታና ሀፍረት በመፈንቅለ መንግሥት ሰበብ ማካሄድ ነበረባቸውዓለም አቀፍ ማኅበረሰብየምንለው የኢሉሚናቲዎች ጭምብልም ከጎናቸው ስለሆነ ማንንም አይፈሩም፤ አያፍሩምም፡፡የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገርይባላል፡፡ እነአቢይ የሚገድሉትን ሁሉ ከገደሉና መረጃ ካጠፉ በኋላ ያን ከእውነት የራቀ ነገር መደስኮራቸው በሕዝብ ንቃተ ኅሊና ላይ ጢባጢቤ ከመጫወታቸውም በላይ የነሱን ማይማዊ ዕብሪት አጉልቶ ያሳያል፡፡ አክራሪ ኦሮሞዎች በከሚሴና በቤንሻንጉል ጉሙዝ በኩል ሊሠሩት ያቀዱትንና የጀመሩትንም አማራን በጎጥና በሸንተረር የመከፋፈል እንዲሁም በሳል አመራር የማሳጣት እንቅስቃሴ እነአሣምነው ቀድመው ነቅተውባቸው ሊያከሽፉባቸው በመነሳታቸው በአማራ ልሂቃንና አመራሮች ላይ ሁሉ ውርጅብኝ ወረደ፡፡ መሆን ስለነበረበት ነው የሆነው ብለን በአርምሞ እንቀበለዋለን፡፡ አንድ መሆን ያለበት ነገር ደግሞ ይዘገያል እንጂ ከመሆን አይዘልም፡፡ አሁን እንደምንሰማው በአክራሪ ወያኔዎችና ኦህዲድ/ኦነጎች የተጠነሰሰ ዘመቻዘመቻ ቅንጸላይባል ነበር፡፡
-     
-    ቅንጸላ ምን ማለት እንደሆነ በውል አላውቀውም፡፡እንደሚመስለኝ ግንማምከን፣ ማስቀረት፣ መቀምጠል፣ ማጉደል፣ ማክሸፍ…” ሳይሆን አይቀርም፡፡ የአማራን ትንሣኤ ለማስተጓጎልና እስከወዲያኛው ለመቅበር የተደረገ ሙከራ እንደሆነ ወዲያና ወዲህ ከሚያቅነዘንዛቸው ዕረፍት ያጣ ተግባራቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡ አሁን አሁንማ ይሠሩትን አጥተዋል፡፡
-   
ይህ አማራን የማጥፋት ሁለገብ ዘመቻ በነአቢይ አህመድ ይመራ እንጂ አንዳንድ ሆዳም የብአዴን አባላትም የጥፋት ዘመቻውን መተባበራቸው የታወቀ ነው፡፡ ዱሮውንም ሆዳም ፍቅር አያውቅም፡፡ ሆዳም ሚስቱንም፣ ልጁንም፣ አባቱንም፣ እናቱንም ለገንዘብና ለጥቅም አሳልፎ ይሸጣል፡፡ ይሁዳ ጌታውን 30 አላድ እንደሸጠ ሁሉ የባሰበት ሆዳም አማራም አማራን አይሸጥም ተብሎ አይታሰብም፡፡ የአማራ መከራ የበዛው የራሱ ልጆች ሳይቀሩ ከታሪካዊው ጠላቶቹ ጋር በመተባበር ለከርሳቸው ሲሉ ስለሸጡት ነው፡፡ ያለ ነው፡፡ ወደፊትም ይህን መሰሉ አስቀያሚ ክህደትና ሽርሙጥና አይቀርም፡፡ ዋጋቸው ግን በሠፈሩት ቁና ልክ ይሠፈራል፡፡ እንጂ ለክህደት ለክህደትማ እነክፍሌ ወዳጆንና ገነት ዘውዴን ማን ይረሳቸዋል?
-     
-    ዘመቻ ቅንጸላ ያደረገውን አድርጎ ለጊዜው የተሣካ ይመስላል፡፡ በዚያም ምክንያት በአማራው አካባቢ አሁን ለጊዜው መፍዘዝ ይታያል፡፡ ግን በዚህ መልክ አይቀጥልም፡፡ ምክንያቱም ትንቢቱ ደርሷልና፡፡ ንግርት ቢዘገይ እንጂ አይቀርም፡፡
ይህ ነው ትንቢቱ፡፡ መጀመሪያ ከሰሜን የመጡ አንበጦች ኢትዮጵያን እንደተምች ይወሯታል፡፡ ወርረውም እስከ አጥንቷ ይግጧታል፡፡ መሣሪያ ከትከሻቸው የማይወርድ እረኞች በሽምብራ ዛፍ ሥር ተቀምጠው ጠማማ ፍርድን ይሰጣሉ፡፡ እህል በሸሃኔ ይሠፈራል፡፡ ቀጣና ይበዛል፡፡ ርሀብና መከራ ይናኛል፡፡ ትልቅ ሰው ይዋረዳል፤ ትንሽ ሰው ይከበራል፡፡ በመጨረሻቸው ግን እነዚያ ጉዶች እንደጢስ በንነው፣ እንደጤዛ ረግፈው ይጠፋሉ፡፡ ይህን አሁን አይደለም እኛ የምንለው፡፡ ከልጅነታችን ጀምሮ 50 እና 60ዎቹ ዕድሜ የምንገኝ ሁሉ የምናውቀው የቅርብ ዘመን ትውስታ ነው፡፡
-   
ቀጥሎ ፊጋ ከብቶች ባዶውን በረት ይወርሳሉ፡፡ ለተወሰነ ጊዜም ባዶ ያገኙትን በረት እውነት መስሏቸው እምቡር እምቡር ይሉበታል፡፡ ዕውቀትና ጥበብ ባለፈበት መንገድ ያላለፉ የለዬላቸው ነፈዞች ናቸው፡፡ መሪያቸው ሃይማኖት የለውም፡፡ አለው ቢባልም ማስመሰያ እንጂ ከአንጀት አይደለም፡፡ ዕድሜው ከሦስት ዓመታት አያልፍም፡፡ የነሱም የመጨረሻ ዕጣ ልክ እንደአንበጣዎቹ ይሆንና ባላሰቡትና ባልጠበቁት ሁኔታ አከርካሪያቸውን ተመትተው ወደ ታሪክ ትቢያነት ይለወጣሉ፡፡ ያንን ጊዜ አንተ ወይም አንቺና እኔ ላናየው ብንችልም የማይቀር ስለመሆኑ ግን የዮዲትና የግራኝ አህመድ ወይም የመንግሥቱና የመለስ karmic መጻሕፍት ምሥክሮቼ ናቸው፡፡ ይህ እውነት መሃላ የማያሻው አጠቃላይ እውነት ነው፡፡
-     
-    በመጨረሻው መጨረሻ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ተጠራርተውና ኃይላቸውን አስተባብረው ኢትዮጵያን ይረከባሉ፡፡ በነሱም የኢትዮጵያ የቀድሞ ክብር ይመለሳል፡፡ ያም ጊዜ እጅግ ቀርቧል፡፡ይህን እውነት መናገር ማንንም አይጎዳም፤ ለማንምም የሥጋት መንስኤ ሊሆን አይችልም፡፡ እንዲያውም የምሥራች ነው፡፡ ለወፍ አራሾች ግን መርዶ ነው፡፡ (ባይገርምህ እናትና ልጅም ተገናኝተው ጥጃዋ ከእህትና ወንድሞቿ ጋር የእናቷን ጡት የምትጠባበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ምን ያስቅሃል?)
-     
-    እነዚህ የአሁኖቹ ከንቱዎችና ጌቶቻቸው ወያኔዎች ግን ትልቅ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ የነሱን የዓመታት መርዝ ለመንቀል ብዙ ትግልን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ሕዝብ መስዋዕት ይሆናል፡፡ የደም ጎርፍ የማናመልጠው ዕዳችን ይሆናል፡፡ለኃጥኣን የመጣ ለፃድቃን ይተርፋልእንዲሉ ነውና ብዙ አሣር ያገኘናል፡፡ መስዋዕቱን ለመቀነስ እንዲቻል (ትንቢትን ማስቀረት ባይቻልም) ወደ ፈጣሪ ተመልሰን በፆምና በጸሎት ብዙ መድከም ይኖርብናል፡፡ ኢትዮጵያ ቃል የተገባላት ምድር ናት፡፡ ጠላቶቿ ቀበርናት ሲሉ አፈሯን አራግፋ የምትነሣ፣ ገደልናት ሲሉ የምትድን ልዩ ሀገር እንደሆነች በተደጋጋሚ አስመስክራለች፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ብዙ ዕልቂት ቢኖርም ከህመሟ ተፈውሳ በሚተርፏት ጥቂት ዜጎች ልዕልናዋን እንደገና ታስከብራለች፡፡ አራሙቻዎችም ተጠራርገው የጨለማው ንጉሥ ግዛት ወደሆነው ወደ መጡበት መቀመቅ ይወርዳሉ፡፡
-     
-    በየከተሞች የሚታየው የሴቴኒዝም እምነትም በነፃነታችን ቶሎ አለመምጣት ላይ የበኩሉን ጽላሎት ማሳረፉ አይቀርም፡፡ ከጥግ እስከጥግ የቆሸሸውና በዘረኝነት፣ በሙስናና በድንቁርና የተበከለው ቤተ መንግሥታችን ብቻ አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያንንና የእምነት ቤቶችን በጥቅሉ ሰይጣን ስለተቆጣጠራቸው እውነተኛ እረኞች የሉንም፡፡ ሰይጣን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስያንን ጨምሮ የእስክንድርያዋንና የኢትዮጵያዋን ኦርቶዶክስ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተቆጣጥሯል፡፡ ልጅ እየወለደ በድብቅና አንዳንዴም ልክ እንቫቲካኑ 15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ ሊቀ ጳጳስ (ፖፕ ሮድሪጎ) በማንአለብኝነት በግልጽ የሚያሳድግ ፓትርያርክና ጳጳስ ባለባት ሀገራችን ውስጥ የእግዚአብሔር በረከትና ጥበቃ በቀላሉ ይገኛል ማለት ቀልድ ነው፡፡ በዚህ ዘመን መዳን ከባድ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና በደል እየተሠራ እያለ አንድም የሃይማኖት አባት በግልጽ ወጥቶ አይቃወምም፤ ቂጡ ላይ ቁስል ያለበት ውሻ እንደልቡ አይጮህም፤ ፈስ ያለበትም ዝላይ አይችልም፡፡አባቶቻችን በጠባያቸው ሰይጣናዊነት የተነሣ ፀጋ እግዚአብሔር ጎድሏቸዋልና በጎቻቸውን ተኩላና ቀበሮ ሲቦተራርፍ፣ ሀገርን ማንም ወስላታና ወለፈንዴ ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ሲጫወትባት ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምክንያቱም በሆነ ነገር አፋቸው ተሸብቧል፡፡ ለነፍሳቸው ያደሩ እንደነ አቡነ ጴጥሮስ ያሉ አባቶች ሞታቸው ሰማዕትነት እንጂ ተራ ዓለማዊ የሥጋ ሞት እንዳልሆነ ስለሚረዱ እውነትን መስክረው በጥይት ተደብድበው ሞተዋል፡፡ አሁን ግን የምዕመናንንና የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ማሠሪያ ገንዘብ እየዘረፉ፣ በዘረኝነት አሮንቃ እየዳከሩና በሴሰኝነት የወሲብ ንዳድ እየነፈሩ ስለነፍስና ስለሀገር ማሰብ የማይቻል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን በቅርጽ እንጂ በይዘት የለችምየምለው ሀሰት ቢሆን ጌታ ይፍረድብኝ (ባይባልም አንዳንዶችን ደስ እንዲላቸው ግዴለም ልበለው)፡፡ ድንጋይ ይክባሉ እንጂ አእምሮ ላይ የሚሠሩት አንዳችም ነገር የለም፤ የነሱ የራሳቸው አእምሮም ባዶ ቀፎ ነው፡፡ አብዛኛው ካህንና ደብተራ ዐይኑ የሚጎለጎለው፣ መረዋ ድምጹ የሚጎላው፣ ቅኔውና ወረብ ሽብሸባው የሚሠምረው ገንዘብ ላይ ነው፡፡ ከሁለት ሰዓት የዐውደ ምሕረት ስብከት ውስጥ 30 እና 40 ደቂቃው ብቻ በተግባር ለማይተረጎም ሃይማኖታዊ ቃል የሚውል ሆኖ ሌላው ገንዘብ ስጡ ላይ ነውመስጠት ብቻውን ያጸድቅ ይመስል፡፡ብዙ አየንአለች አሉ ቦለቅያ፡፡
-    እንግዲህ እውነቱ እንዲህ ነው፡፡ ሴቴኒዝምን እንዋጋ፡፡ ዝርዝሩን መናገር ለቀባሪ ማርዳት ነው( Romans 1:18-32, Leviticus 20:13, 1 Corinthians 6:9-10, 1 Timothy. 1:9-10)፡፡ ነገር ግን ይህ የጨለማ ዘመን በቶሎ እንዲነጋ ለማድረግ የእውነት ዘገርን እንጨብጥ፡፡ ከላይ እስከታች የሠፈነውን ሙስና እንዋጋ፡፡ በመደበኛ ገቢያን መኖርን እንለማመድ፡፡ በልጆች አእምሮ ላይ ብዙ እንሥራ፡፡ እንደሀገርም እንደሕዝብም እየጠፋን ነውና ከተሳሳተ መንገድ በቶሎ እንመለስ፡፡ ከሰሞነኛ ቅሌታችን ብጠቅስ ለምሣሌፈተናን እየሠረቅንና በመምህራን እያሠራን መልስ በመበተን ትውልድን ከማደደብ በላይ ምን ወንጀል አለ? በምግብና በልብስ እንዲሁም በሌሎች የንግድ ዕቃዎች የሚሠራውን ፌክና አሻጥር አናንሳው፡፡ የጀሦና የሴጋቱራን እንጀራ፣ የቀይ ሸክላ በርበሬንና የሞራ ቅቤን መመገብ ለምደን ሰው መሆን ቢያቅተን በርግጥም አይፈረደብንም፡፡ የምንገርም ሆነናል እኮ …. ሀገርና ሕዝብ 30 ዓመታት ውስጥ ብቻ መጥፋት የሚችሉ ተራ ነገሮች ናቸው ማለት ነው?
ከነአቢይ አህመድ የሕይወት መመርያ ቀጣዩን ለአብነት ያህል እንመልከት፡-
-     
-    Politics has nothing in common with moral. The ruler who is governed by the moral is not a skilled politician, and is therefore unstable on his throne. He who wishes to rule must have recourse to both cunning and to make believe. Great national qualities, like frankness and honesty, are vices in politics, for they bring down rulers from their thrones more effectively and more certainly than the most powerful enemy. (Source: Secret Societies and their Power in the 20th Century, by Jan Van Helsing)
-     
-    ለዚህ ነው የሁሉም ችግር ማስወገጃ መንገዳቸው ውቃው ሆኖ የቀረው፡፡ ሰው ሰው የማይሸት ፖለቲካና ሃይማኖት፣ ከምክንያት ይልቅ ከራስ ወዳድነትና ከስግብግብነት ጋር የተቆራኘ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተራክቦ ገጥሞን ወደ ሮቦትነት እየተለወጥን ነውና ጨርሰን ሳንጠፋ እንምከር፤ እንነጋገር፤ ለዚሁ ጉዳይ መድረኮችም ይዘጋጁ፡፡ የኑሮ ውድነቱንም ለማብረድ ወደ ሰውነት እንመለስ፡፡ ሰውነት እጅጉን ርቆናል፤ ናፍቆናልም፡፡

Ethio Semay