ኢትዮጵያዊ አማራ እና ንጹህ አማራ እኛና እነሱ
የዘመነ ካሴ የፋሺስት ፍረጃ
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Semay 7/20/2024
ዘመነ ካሴ ከታላቁ የናዚ መሪ ሂትለር የቀሰማቸው ባሕሪዎች አሉ፡፡ ሂትለር ሕዝብ ያንቀሳቀሰበትን ስልት እንዲህ የላል፡፡
"ብዙሃኑ ሕዝብ ከትንሽዋ እውነት ይልቅ ግነት ላገኘ ለትልቅ ውሸት በቀላሉ
ሰለባ ይሆናሉ።" የላል፡፡
ዘመነ ይህንን ስልት በመከተል ትልልቅ
ውሸቶችን በመዋሸት ብዙ ስዎች የውሸቱ ሰለባዎች ሆነው እያየሁ ነው፡፡ እንደ ሙስሎኒ እየተለጠጠ ደረቱን ነፍቶ ፤እንደ ሂትለር ቃላቶች
እየደረደረ የዋሁን ሲያስከትል ታዝቤ አለሁ፡፡
በእጅ ጽሑፍ የተጻፈው ለእስክንድር
ነጋ የጻፈው የዘመነ ካሴ የልተቆነጠጠ ፤ ሞገደኛ ፤ ዘረኛ መግለጫው ሰምታችሁ ይሆናል፡፡ የሚድያ ባለቤቶች እንደመሆናችን መጠን መዘገብና መተንተን የግድ ስለ እሚል ለመነሻ እዚህ ልጥቀስ፦
መግለጫው እንዲህ ይላል፡፟
<<(ግጭታችን) የዓለሙና
የከበደ የሁለት ሰዎች ግጭት አይደለም፡፡ይህ የርዕዮተ ዓለም ግጭት ነው፡፡ የሌባና ፖሊስ ትንቅንቅ ነው፡፡ የትውልዱን ትግልና ድል ሊሰርቁ ጭምብል ለብሰው ማጅራት መምቻ ቆመጥ ታጥቀው በጠራራ ፀሐይ
በመጡ ሌቦችና የትውልዱን ደምና አብዮት ሰለሚጠብቁ ፖሊሶች
መካከል ያለ ግብግብ ነው፡፡
ይህ ይሉኝታቸውን በሸጡ ያልዘሩትን አጫዶችና አብዮቱን በ30
ዲናር አንሸጥም ባሉ የሕዝብ ልጆች መሃከል እየተደረገ ያለ ትንቅንቅ ነው፡፡ የዘመነ እና የእስክንድር የሁለት ሰዎች ጸብ አይደለም፡፡
ዘመነ የወንደሞቹን ደም ለገበያ አወጥቶ በሊትር የሚሸጥ ከሃዲ አይደለም፡፡ በሕልሜ የመጡብኝ አሁን ነው፡፡አሁንማ ተነቃቃን እኮ፡…
እሰከንድር ሲያምሰን ከርሞ ነገ ሽሉክ ይላል፡፡ያኔ እንተዛዘባለን፡፡ የሚደብረው የምንታዘበው የራሳችን ወንድሞችን ነው፡፡
ወንድምን መታዘብ ትልቅ ሕመም አለው፡፡አንዳንዱ ወንድሞቻችን በጨለማ ሄዱ ፤ አዝነናል፡፡>>
(በእጅ ከተጻፈ ጽሑፍ)
ይህ የዘመነ ከትላንት በስትያ ያስተላለፈው “ዘረኛና ነውር የተሞላበት መግለጫው” በዝርዝር እንሄድበታለን፡፡
በመጨረሻ ጽሑፉ ልጀምር፡፟
<<ወንድምን መታዘብ ትልቅ ሕመም አለው፡፡አንዳንዱ
ወንድሞቻችን በጨለማ ሄዱ አዝነናል፡፡>>
የሚለው የሄሊኮፕተር አብራሪው ሲታሰር ሲፈታ አብሮ የታሰረና የተሰቃየ ፤ ሲደበቅ አበሮት የተደበቀ ፤ የቅርብ መስጢር አማካሪውና ጓዱ የነበረው የዘመነ ቃል አቀባይ የማርሸት ጸሃየ የእናት እህት ልጅ የሆነው ካፕቴን ማስረሻ ሰጤን ነው፡፡ የራሱን ፋኖ ያደራጀ ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ ዘመነን አልመርጥም ብሎ እስክንድርን ለመሪነት ድመጽ በመሰጠቱ ነው፡፡ (ወንድሞቻችን ከዱን የሚለው ኡኡታው)፡፡
ከላይ እንዳነበባችሁት እኛና እነሱ፤ እኔ ንጹህ አማራ እስክንድር ግን አማራ መስሎ ጭምብል በመልበስ የአማራዎችን የኛን የንጹሃን አማራዎችን ትግል ለመጥለፍ የተቀላቀለን አማራ ያልሆነ ሰው ነው፡ ሲል የፋሺስቶች ፍረጃ ውስጥ ገብቷል፡፡ ይህ ደግሞ መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ ሲሆን እስክንድር ግን አማራ ሰላልሆነ ጭምብል በመልበስ መነሻው አማራ ቢሆንም መዳረሻየ ግን ኢትዮጵያ ናት ሲል “የርእዮተ አለም አመለካከት ልዩነት አለን” እያለ የገለጸው ፡ ልክ እኛ ወያኔ የምንቃወም መዳረሻችንና መነሻችን ኢትዮጰያ ስንል የነበርን ትግሬዎች “ሸዋውያን ተጋሩ” የሸዋ ትግሬዎች እንደሚሉን ሁሉ ፤ የጽንፈኛ ፋሺስት ብሔረተኛነት አቀንቃኙ ዘመነ ደግሞ እስክንድር አማራ ሳይሆን አማራ መስሎ የአማራነት ጭምብል የለበሰ “የኢትዮጵያ አማራ” ማለቱ ነው ( የኛ ያልሆነ ፤ ጭምብል የለበሰ “ጸጉረ ለወጥ”) ማለቱ ነው፡፡
የእብደቱ ብልግና ማሳያ አመባገነን ፋሺስታዊነቱ ደግሞ በሚገርም አፈራረጅ
እራሱን የአማራ ሕዝብ ፖሊስ አድርጎ ሲሾም እስክንድር ነጋ ደግሞ “ማጅራት መቺ ሌባ” በማለት በጸያፍ ቃል ዘልፎታል፡፡
እንግዲህ ይላል ዘመነ <<ይህ የሌባና የፖሊስ ትንቅንቅ ነው፡፡ቆመጥ ታጥቆ በጠራራ ፀሐይ የመጣ ሌባ>> ሲል በስድ መላሱ እስክንድርን
እንዲህ በወረደ ቃል ይዘልፈዋል፡፡ (ጨርቁን የጣለ ንክ ማለት ይህ ነው!! በቃ)
እራሱን ጉልበተኛ ድመት እስክንድርን
ደግሞ ደካማ ዓይጥ አድርጎ በመሳል “ትግሉ
የአይጥና የድመት ነው (በፖሊሰና
በማጅራት መቺ)” አሁንማ ተነቃቃን እኮ በማለት ደካማው እስክንድርን በ “ዲገላው ድመት” (በፖሊሱ ዘመነ ) ተይዞ እንደሚበላ/እንደሚዋጥ ተዝቶበታል፡፡
ይህ የሚያመላክተው የዘመነ ፋሺታዊ
ባሕሪ ነው፡፡ ፋሺስቶች አስተሳሰብን ሳይሆን “ወንድነትን” ( በጡንቻ/masculinity) እኔ የዓለም ፖሊስ ነኝ በሚል ትምክሕት ተቃዋሚያቸውን በደካማ አይጥነት አስቀምጠው ማስወገድ እንድሚቻል፣ ከመግለጫው
መረዳት ትችላላችሁ፡፡ ዛቻ እና አመፅ በማመንጨት ሥልጣኑንና ሃይልነቱ በመግለጽ ታዛቢው ዓለም ፤ ተከታዮቹና ተቃውሚዎቹ እንዲያውቁለት
የፈልጋል። ብዙ ጊዜ፣ ፋሺስቶች ይህንን የድመትና አይጥ (የፖሊስና የሌባ) ስእል የሚጠቀሙበት ምክንያት ይፋ የወጡ ተቃዋሚዎቹም ሆኑ በተቃውሞ ለመምጣት የሚዳዱ አዳዲሶች ካሉ ለማስደንገጥ ነው፡፡
የድመቶች ሁሉ አለቃ ሆኖ’ አድፈጦ ገርበብ ብሎ
የሚያገኘውን መዝጊያ ሸልኮ ገብቶ ጫጩቶችን በመንጠቅ፤ የተሰቀለ ቋንጣ ወይንም ለምሳ የተዘጋጀ ሥጋ ድስት እየከፈተ ነጥቆ የሚሮጥ
፤ ቆርቆሮ ጣራ ላይ ውጥቶ ቆርቆሮውን እየቧጠጠ በከፈተኛ አስፈሪ ጩኸት በመጮህ ትንንሽ ድመቶች (ኪትን) እና አይጦችን ሁሉ መጣሁባችሁ እያለ የተኛውንም
ሰው አካቢውን የሚረብሽ የሚፈሩትና እንዲረበሹ የሚያደርግ የድመቶች ሁሉ አውራ ሞገደኛ ድመት << ሓኽሊ ድሙ>> እንለዋለን
በትግርኛ፤ አማርኛው “ዲገላ ድመት”
ይመሰለኛል፡፡የዘመነ የዲገላ ድመት መጣሁብህ ያልታረመ ባሕሪ ምልክት ነው፡፡
ከዚሀ ባሻገር ዘመነ በመግለጫው
ዘመነ የአማራ ትግል እንዳይሸጥ ተከላካይ
፤እስክንድር ደግሞ የአማራ ትግል ለመጥለፍ ከአማራ ጠላቶች የተላከ ፤ ትግሉን በ30 ዲናር ለመሸጥ የመጣ “ይሁዳ” ፤ የጠላት ተላላኪ በማለት ፈርጆታል፡፡ ይህ
ልጅ ነው እንግዲህ እንደ ሙሶሉኒ ደረቱንና አንገቱን አሳብጦ የሰው ክብር በመዘርጠጥ አማራ ነፃ ሊያወጣ “ብቸኛ ፖሊሰ” ነኝ የሚለው፡፡
ለመሆኑ እኛ የማናውቃቸው የአማራ ጠላቶች
እነማን ናቸው? በወዳጄ ዳግማዊ ጉዱ ካሳ ዝርዝሮች ልጥቀስ
እንዲህ ይላል፤
የዐማራ ጠላቶች በስም ይታወቃሉ፡፡ የተወሰኑትን አሁን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በክፋት ደረጃቸው ቅደም ተከተል ስለመጥቀሴ እጠራጠራለሁና ደረጃ ውስጥ አልገባም፡፡
1. ኢሕዲን - ብአዴን - አዴፓ፡፡
2- ሕወሓት -
3-
. ሻዕቢያ -
4-
ኦነግ - ኦህዲድ - ኦሮሙማ፡፡
5- ግብጽና ልጆቿ፡፡
6- ምዕራባውያን - በአሜሪካን መንግሥት የሚመራው….. ፤
7- የኑሮ ውድነት፡፡
በማለት ዳግማዊ ጉዱ ካሳ አምና የነገረንን
የአማራ ጠላቶች ሰፊውን ዝርዝር እንድታዩ ለጥፌው ከነበረው ነው እንድታሰታወሱ የለጠፍኩት፡፡ ታዲያ ከነዚህ ውስጥ በየትኞቹ ረድፎች ከተጠቀሱት የዘመነ የአማራ ጠላቶች ነው
እሰክንድር ተልእኮ ተሰጥቶት ተበሎ ጭምብል ለብሶ ጫካ በመግባት “በንጹህ
አማራው ዘመነ” መግለጫ “ኢትዮጵያዊ አማራው እሰከንድርን”
“ወንድሙን ለመሸጥ የመጣ ይሁዳ”
ብሎ በይሁዳነት የገለጸው!?
ነፍጥ የታጠቁ እንዲህ ያሉ ፋሺቶች
ሰውን በመወንጀል “የማያዳግም እርምጃ”
የሚሉት የፋሺት መፈክሮች በመጠቀም ሰው ባልዋለበት ድርጊት በማጠልሸት ታጋዮችን የሚፈጁበት መክንያት በዚህ መንገድ ነው፡፡
“እስክንድር አማራ አይደለም” ሰለሆነም
ትግሉን አኮላሸቶ ሹልክ ብሎ
እንደ አመሉ ወደ መዳረሻው ወደ “ኢትዮጵያው” ይህዳል፡፡ ይላል ዘመነ፡፡
ባለፈው ወር ዘመነ ውንጀላውን እስክንድር ላይ
እንዲህ ያለውን ላስታውሳችሁ፦
“(አብይ አሕመድ) በጦር ሜዳ ስናሸንፈው በካድሬ አዲስ ቀሰቀሳ አፈር ልሶ ሊነሳ መጣ”
ካድሬ እያለ ያለው እስክንድርን ነው፡፡ እስክንድርን የአብይ ተላላኪና
ካድሬ ቅጥረኛ ነው ሲል ሳያፍር ወንጅሎታል፡፡ ዘመነ ሰውን ሲወነጅል ማስረጃ ሳይኖሮው ነው፡፡ የበረሃ ሽምቅ ተዋጊ ፋሺቶችና ኮሚኒስቶች ተቃውሚያቸውን መወንጀል የባሕሪ
መለያቸው (trade mark) ነው፡፡
ይህ የተናገረበት ወቅት ባለፈው ጊዜ አዲሰ አበባ ያለው የአሜሪካን አምባሲ ተወካይ ስለ ድርድር አንስቶ ስላቀረበው ሃሳብ ፤ እስክድር ለBBC ያደረገው ቃለ ምልልስ ተጥይቆ ሲመልስ “አሁን አንድ ሰላልሆንን ለድርድር አይመችም ፤ ፋኖዎች
አንድ ስንሆን ከማንም ጋር መደራደር ይቻላል፤ ድርድር የትግሉ አንዱ ሂደት ነው” ፡ ሲል መልስ በመስጠቱ ነው ‘ልቡ ያበጠበት የጎጃሙ
‘’ዲገላው ዘመነ” ምላሽ ድግሞ፤
እንዲሀ ይላል፡
<<ገድለን ከቀበርነው እብድ ጋር (የአብይ ኦሮሙማ መንግሥት ማለቱ ነው)ማን ይደራደራል፤ ሥልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ለአማራ አስረከቦ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዜጎቻ ያስረክብ” ሲል ዘመነ በዚህ መልክ እስክንድርን
“በካድሬነት ከሰሰው፡፡
አብይ አሕመድ ሥልጣኑን (*ምኒሊክ ቤተ መንግሥት አራት ኪሎና መናልባትም አዲሰ አበባ*ሙሉ ለሙሉ ለአማራ (ብቻ) አስረክቦ “ኢትዮጵያ” የምትባል በዘመነ 'ችሮታ' (ለገስና) ከአማራ ጡንቻ የቀረቺዋን ኢትዮጵያ ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ነን ለምንል ለነ እሰክንድር ነጋና ለመሳሰልነው ለኛ ለዜጎቿ ማስረከብ” አለበት፡ የላል፡፡ ሥልጣን ተረካቢውና ፈቃጅና አከፋፋይ በንጹህ አማራነቱ የሚመካው ቻንስለር ዘመነ ካሴ ነው፡፡
በሚገርም ሁኔታ ግን የራሱ ቃል አቀባይ ማርሸት
ጸሃየ የተባለ ልጅ ደግሞ “ድርድርን አንቃወምም” ሲል እስክንድርን በመደገፍ ተናግሯል፡፡ ባንድ ድርጅት ሁለት ምላስ!
ዘመነ ካሴ ብቻ አይደለም አማራ ፋኖ እዝ
በሸዋ የሚባለው አሰግድ የተባለ “ዘረኛ” ደግሞ እስክንድርን “አማራ በመምሰል” የአማራን ታላላቅ
ድርጅቶችን በማፈራረስ የአማራን ትግል የማስጠለፍ ‘ሴራ አዘል’ ቀጥሎበታል ይላል፡፡
ከሁሉ የገረመኝ ደግሞ “የተጎዱ አማራዎችን በመጎብኘት” ጋዜጠኛ መአዛ መሐመድ የተባለች ቅሌታም ‘ሰብአዊ በጎ ሥራ በመስራት አድናቆት አግኝታ የነበረቺው’ እዚህ አሜሪካ በስደት ላይ ያለቺው ጋዜጠኛ መአዛ መሐመድ ሲያቀብጣት ከዘረኞቹ ከእነ ዘመነ ካሴና አሰግድ ጋር በመወገን ክብርዋን ዝቅ ለማድረግ እዚህ ቅሌት ውስጥ በመግባት በምታዘጋጀው የሮሃ ሚዲያ ላይ ለወገነችላቸው ለዘረኞቹ
ቡደኖች የፕሮፓጋንዳ መስኮት በመሆን እስክንድር አማራ አይደለም የሚለው “ኮማንደር አሰግድ” የተባለ የደሮ ባሕር ሃይል አባል የነበረ” ቆይቶም ወያነ በመሰረተው ሰራዊት የነበረ (የሚባልለት) ፤ “የአማራ
ፋኖ እዝ በሸዋ” በሚል ያስተላለፈውን ዘረኛና የሃሰት ውንጀላ በሮሃ ሚዲያዋ ሰታስደምጠን ፤ የመሪዋ የአሰግድ ፈለግ በመከተል እስክንድርን
አቶ እያለች ፤
<<የአማራ ሕዝቦች አንድነት
ድርጀትን አማራ መስሎ
ሰርጎ በመገባት ያፈራረስ፡፡ እንዲሁም አማራ መሰል ድረጀቶችን በማቋቋም እውነተኛ የሕዝብ ድርጅት በማፈራረስ
ተጠምዶ የነበረና ዛሬም የአማራ ፋኖ ይሕልውና ትግልን ቁማር ለማስያዝ ከጠላት
ተልእኮ ይዞ የመጣ አስቦበት እየተንቀሳቀሰ ነው>> ሲል <<የአማራ ፋኖ እዝ በሸዋ>> አቶ እስክንድር ነጋን ወቅሷል፡ በማለት መግለጫውን ያነበበቺው “ቅሌታማዋ” መአዛ
መሕመድ የስራ ባልደረባዋ የነበረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አቶ
እያለች በማሳነስ (የሃሰት ውንጀላውን ደግሞ በማሳነስ ወቀሳ ትለዋለች)
በመቀጠል
<< አማራ መስሎ ሰርጎ በመግባት>> <<“ፍጹም “አማራ” በመምሰል>> የሚሉትን የፋሺቶች ቃላት በመጠቀም ልክ እንደ ዘመነ ካሴን አባባል “አሰግድ” የተባለው ናዚ ያንን ቃል በመቅዳት እየሰማን ያለነው “እስክንድር አማራዊ የደም ንጽህና የሌለው የኛ ያልሆነ ፤ እኛን መሰሎ ትግሉን ለመጥለፍ የተቀላቀል “ባእድ” ነው>> ሲል ይወነጅለዋል፡፡
በዚህ መልክ ብሔርተኝነትን የሚያስረዳን
ምንድን ነው?
ብሔርተኞች በተፈጥሯቸው የራሳቸው ካልሆኑ
ብሔሮች ውጭ "ሌሎች" ግለሰቦችን - ባእድ ነው በሚል እንዲመለከቱዋቸው የሚያደርግ አስተሳሰብ ነው፡፡የናዚዎች
መነሻ ኣልፋ እና ኦሜጋቸው “መነሻቸው የኛ የሚሉት ነገድና ዘር ሲሆን መዳረሻቸውም ያንኑ ነገድና ዘር
ነው፡፡ መነሻችን ትግራይ መዳረሻችን ትግራይ፤ መነሻችን አማራ መዳረሻችን አማራ፤ በማለት ልክ ሯጮች (አትልቶች) የሚሰመርላችው የመነሻ መስመርና የሚጨርሱት መድረሻቸው መሰመር ከተሰመረላቸው መነሻና
መድረሻ ውጭ መሻገር እንድማይችሉ ሁሉ ዘመነ ካሴና አጋሮቹ “መነሻቸው አማራ መደረሻቸው አማራ ነው” ከዚያ ወጭ ስለ አገራቸው ኢትይዮጵያ የሚጨነቁና የሚመለከታቸው እኛን
የመሰሉና እስክንድር የመሰሉት የኢትዮጵያ ዜጎችን ብቻ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡
ከላይ ዘመነ ራሱ እንደገለጸው “አብይ አሕመድ ሥልጣኑን ለአማራ አስረክቦ የተቀረቺው
ኢትዮጵያ ደግሞ ለዜጎቸዋ ኢትዮጵያዊያን ያስረክብ” ሲል ተናግሯል፡፡ ለዚሀ ነው ብሔርተኞች ኢትዮጵያን መዳረሻቸው የማያደርጉዋት፡፡
የየትም አገር ብሔርትኞች መዳረሻቸውና መነሻቸው ንፁህ የደም ጥራታቸውን የሚለኩበት ሚዛን ከመጡበት ዘርና ነገድ ሚዛን
ነው፡፡ እኔ ፖሊሰ ፤ እሱ ቆመጥ የያዘ ማጅራት መቺ ፤ ሌባ ፤ እኔ ድመት እሱ አይጥ ፤ ኢትዮጵያዊ አማራ እና ንጹህ አማራ ፤ እኛና እነሱ የዘመነ ካሴ የፋሺስት ፍረጃ ይህን ይመሰላል፡፡
ሰሞኑን ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ስናወራ የነገረኝን ልጥቀስና ልሰናበት፡፡
አስተዋይ የቀድሞ አማራዎች መሳሌ እንዲህ የላል <<ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ አይጥፋ” ይላሉ አማራ አባቶቻችን ብሎኛል፡፡ ፍሬ ነገሩ የክፉ ቀን ወዳጅህ ስትጣላውም እንኳ ግብረገብ በተሞላው ቃላት መሰናበት ባትችል እንኳ ፤ ኋላ የሚፀፅትህንና የሚያራርቅህን አብሮ ሲኖሩ የተካፈልካቸው መስጢሮችን ለሌላ ሰው ክመዘክዘክና ከሚያስቆጭ ከሚያስተዛዝብ የስድብ ቃል መቆጠብ በሞራልም በሃይማኖትም በሕግም፤ በባሕል ሚዛን ላይ የሚለካ
ጨዋነትን ያለመርሳት መምረጥ አለብን ማለት ነው፡፡ ይላል የስነ አእመሮ ሐኪም ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ከአምስተርዳም ሆላንድ፡፡
ሰላም ሁኑ!
ጌታቸው ረዳ