Monday, November 27, 2023

በዕብሪታቸው ለውርደት የተዳረጉት በ5000 ዘመናችን ታይቶ የማያውቅ የትግራይ ፋሺሰቶች አስደማሚው መጨረሻቸው The Fascists of Tigray, who were humiliated by their arrogance, have never been seen in 5000 years. ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/27/2023

 

በዕብሪታቸው ለውርደት የተዳረጉት በ5000 ዘመናችን ታይቶ የማያውቅ የትግራይ ፋሺሰቶች አስደማሚው መጨረሻቸው

The Fascists of Tigray, who were humiliated by their arrogance, have never been seen in 5000 years of our history

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

11/27/2023

ፋሺስቶች ዕብሪተኞች ናቸው ፤በዛው ልክ አወዳደቃቸው አያምርም። ጣሊያኖች የሞሶሊኒ የመጨረሻው ውድቀቱ “ሓምሌ 5” ብለው ይጠሩታል። የትግሬ ፋሺሰት መሪዎች መጨረሻ ኢትዮጵያውያን ምን ብለው እንደሚጠሩት እስካሁን ድረስ ስም አልሰጡትም። ሁለተኛ ዙር ስለሚኖር እስከዛው እንታገስ።

 ትግሬዎች ኢትዮጵያን ከመጥላታቸው የተነሳ ቅኝ ገዢዎችን ያንበረከከች ገናናዋ ኢትዮጵያን 27 አመት በአፓርታይድ አስተዳዳር አምበርክከው ግጠው አዋርደው ባህልዋን እንዲበላሽ አድርገው ፤ ሁሉም ስለ ወያኔ ትግሬ እንዲዘምር አስገድደው ፤ ባሕር በርዋን ዘግተው አሁን ላላው ተረኛ ኦሮሙማው ቡድን አስረክበው ወደ ትግራ ሸሹ።

በዕብሪት ተወጥረው ስለነበር፡ የትግራይን ሕዝብ ህይወት ሲጠብቅና\ በገንዘብና በሞራል ሲረዳ የነበረው የሰሜን ዕዝ ሲባል የነበረው 70% ቱ የኢትዮጵያ ወታደር በተለያዩ ማዘናጊያ ሴራ አዘናግተው በመጨፍጨፍ “ጀነሳይዳል ወንጀል” ፈጽመው ወደ ትግራይ በረሃዎች ሸሽተው እነሆ በዚህ ቪዲዮ እንደምታዩት በታሪካችን አይተነው የማይታወቅ ልብ ወለድ የሚመስል ግን እውነተኛ የውርደት ትዕይንት እንድናይ ሆነ።

ወያኔዎች ዕብሪተኞች ናቸው። ዕብሪቱ ወደ ሕዝቡም ተሻግሮ ለነሱም ለአማራዎችና አፋሮችም ጭምር ችግር አምጥቷል። ወያኔዎች ብዙ ነውር ፈጽመዋል። ነውርን ለመግለጽ እና ለመለካት በጣም ከባድ ቢሆንም ፤ነውራቸው ሞልቶ የፈሰሰ ነው። እንደ ኢንጂኔር እምብዛ ታደስ እንዳይሆኑ ከወያኔ ሰይፍ ሸሽተው አዲስ አበባና በየቦታው ያሉት ጥቂት ኢትዮጵያውያን ትግሬዎችን አይመለከትም።

በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱት የተማረኩት የወያኔ መሪዎችና ቁልፍ አባሎቻቸው ሲያዙ  ውጭ አገር በምቾት ግፋ በለው ሲሉ የነበሩት ምን ተሰምቷችሁ ነበር እናውቃለን። ውጭ አገር በምቾት የሚኖሩ የትግሬ ምሁራን ውርደትን እንደ አሸናፊነት አድርገው ሲስሉት ሰምተናል።  ከነሱ ይልቅ እኛ ለነሱ አፈርንላቸው።  ይህንን ውርደት ከማረም ይለቅ ዛሬም “በቅልጥማችን” የሚሉ ምሁራኖቻቻው እየገኑ መጥተዋል። ይህንን ለማድመጥ “ዩ ኤም ዲ“  እየተባለ የሚጠራው ካናዳ ያለው ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ የሚያዘጋጀው ሚዲያ እየተጋበዙ የሚያቀርቧቸው እንግዶቹ የሕክምና ዶክተሮች ሳይቀሩ የሚሰነዝርዋቸው አደገኛ አገር አፍራሽ ንግግሮች ለሁለተኛ ዙር ውርደት የሚጋብዙ ናቸው።

 “በጡንጫችን መተማመን አለበን” ይላሉ። ዛሬም ትንናትም መፈክራቸው ‘ጡንቻ ነው”።  << ወይ አማራው ወይ እኛ አንደኛችን መጥፋት አለብን፤ካልሆነ መኖር አንችልም>> እያሉ  ሳደምጥ የትግራይ ሕዝብ መጻኢ ዕድል የለመለመች አገረ ትግራይ ለመመስረት <<አማራ መጥፋት አለበት>> የሚለው ይዘውት ከመጡት የወያኔ ማኒፌስቶ ዛሬም ህያው ነው።

ይህ ዕብሪት የትግራይን ማሕበረሰብ ለሁለተኛ ዙር መከራ እያጠመዱለት መሆኑን ሳደምጣቸው እኔን የሚያስጨንቀኝ ነገር ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በነዚህ ዕብሪተኞች ዕብሪት የተነሳ በዚህ ጦርነ ብቻ ሁለት ቤተሰብ አጥቻለሁ። የነዚህ ምሁራን ትግሬዎች ውይይት ሳደምጥ “እኛም በድለናል ሳይሆን ሁሌም 500 አመት ወደ ሗላ በመሄድ ተበድለናል የሚል ማቆሚያ የታጣለት “የቪክቲማይዘሽን” ትርክት ዛሬም ያለ ነውር ቀጥለውበታል።

 ፋሺሰቶች ውርደትንና ሞትን ምን ያህል እንደሚደፍሩት ይገርመኛል፤፡ “ዩ ኤም ዲ የተባለው ሚዲያ አድምጡ: ብዙ አክራሪ ትግሬዎችና ኦነጐችን ታደምጣላችሁ“። ባለፈው ሰሞን ድንገት ዩ ቲብ ገብቼ ሳደምጥ ዶ/ር ገብረሚካል ገ/መስቀል (ሓኪም ውጭ አገር የሚኖር) ሃይሉ ከበደ (ትግራይ ውስጥ የሚኖር- በጣም አደገኛ ጽንፈኛ ጸረ አማራ- << አንደኛችን መጥፋት አለብን>> የሚለው) ፤ ክብሮም በርሃ የታላቅዋ ትግራይ (ባይቶና ፓርቲ መሪ) እና ወደ ላ ተመልካች ጸረ ምኒሊክና አማራ ጸረ ኢትዮጵያ ፋሺሰት ቀውሰኛ ተገንጣይ) እንዲሁም ውጭ አገር የሚኖር በጸረ አማራነቱ የታወቀው ድሬዳዋ ያደገው አድዋዊው መርስኤ ኪዳነ (ለግንጠላ የሚሰራ ፋሺሰት)። እነዚህ ሁሉ ሳደምጥ በዚህ ቪዲዮ ያየነው የዘመናችን ዕብሪትና ውጤቱ እንደገና ከአሁን በኋላ እንዳይከሰት እሰጋለሃለሁ።

  ትግራይ ውስጥ ሁለት የማያባራ ግጭት ይካሄዳል ፡ <<እርስ በርስ>> (የኛ የትግሬዎች  ዝንተ ባሕሪ <ዕብሪት> ባሕላችን ስለሆነ)።  እንዲሁም ታላቅዋን ትግራይ ለመመስረት የሚከሰት አደገኛ ጦርነት። በተለይ የለኛው ግጭት እውን የሚሆነው ተገንጣይ ክንፎች፧ በሕግ እንዲንቀሳቀሱ አብይ አሕመድ ሆን ብሎ ስለፈቀደላቸው እንቅስቃሴው ያንን ዕድል፣በመጠቀም ወደ ዘንዶነት አድገው ከፍተኛ ብጥብጥ ያመጣሉ። ይህ የሚከሰተው ወልቃይትና ራያ ለመንጠቅ በሚያደርጉት ጦርነት ይሆናል።ቦታውም የፈለጉት ለግንጣላ አላማ ስለሆነ::

ይህንን ስገነዘብ በውጭም በውስጥም ያሉት ተገንጣይ ትግሬዎች አብይ አሕመድ እየሰጣቸው ያለው <<ኦክሲጅን>> በመጠቀም ሁለተኛ ዙር የዕብሪት፤ የዕልቂትና የሓፍረት ትዕይንት እየመጣ እንደሆነ ይታየኛል

በዕብሪታቸው ለውርደት የተዳረጉት በ5000 ዘመናችን ታይቶ የማያውቅ የትግራይ ፋሺሰቶች አስደማሚው መጨረሻ ይደገም ይሆን?

ጌታቸው ረዳ  - የሚከተለው ቪዲዮ ይመልከቱ