Monday, August 1, 2016

ቤተ አማራ ድርጅት የወያኔ ቅዠት ወይስ የሻዕቢያ መልዕክተኛ ጌታቸው ረዳ Editor Ethiopian Semay
ቤተ አማራ ድርጅት የወያኔ ቅዠት ወይስ የሻዕቢያ መልዕክተኛ
ጌታቸው ረዳ Editor Ethiopian Semay
በዚህ ትንተና የተለያዩ ሦስት አበይት  ርዕሶችን እተቻለሁ። “ቤተ አማራ” ድርጅት ስለ እሚባለው እና “ሰኞ ዕለት ስለታየው የጎንደር ሕዝብ ደምፅ”  እና ስለ “የኦሮሞ ሕዝብ ድምፅ” በሚመለከቱ ሁለት ርዕሶች እተነትናለሁ። 

ትናንት ዘሐበሻ ድረገጽ ስጎበኝ፤ “አበሾች ካለ እኛ በስተቀር ሕዝባቸውን የሚያስተምርላቸው የራሳቸው ምሁር ስለሌላቸው “የአማራ ሚዲያዎች”  ካለ እኛ አይሆንላቸውም”። ብናስተምራቸውም ሕዝቡ የሚገባው አይደለም፤ ደደብ ነው። ባስተማርኳቸው ቁጥር እንደውም ድድብናቸው እየባሳበቸው ሄዷል::በእውነት! ባስተማርኳቸው ቁጥር ይብስባቸዋል። እውነት እውነት! ነው የምላችሁ እየባሰባቸው ነው ያለው።”  ሲል በይፋ ለኦሮሞ አድማጮቹ አዳራሽ ውስጥ ሰብስቦ የሚደሶኩረውን “ኢትዮጵያ ኣውት ኦፍ ኦሮሚያ! መፍክሩ እና የገጀራ አብዮተኛ” በመባል የሚታወቀው “የተባረኩ፤ ከክርስትያን ቤተሰብ የተገኙ፤ ቅድስት ክርስተያናዊት አማራ በሆኑ ወላጅ እናቱ” ግፊት የሰንበቴ ትምህርት ሲማር ያደገ ክረስትያኖችን፤ አማራን እና ኢትዮጵያዊያንን የሚጠላ “ጃዋር መሐመድ”ን በየሳምንቱ እየጋበዘ የሚያስሰድብን ሃብታሙ የተባለው “ላስ ቪጋስ” ከተማ ውስጥ ያለው ሕብር ራዲዮ አዘጋጅ ሰሞኑን ደግሞ “አማራ የራሱን መንግሥት” ለመመሥረት ነው የምንታገለው”  የሚል መሰረቱ (ኤርትራ ይሆን?) የት እንደሆነ የማይታወቅ የወያኔ ቅዠት የሚቃዥ በአማራ ስም የሚገዘት ቤተ አማራ የሚባል ድርጅት አዲስ የሻዕቢያ/የወያኔ ፖሊሲ የሚያራምድ የግንጠላ መልዕክተኛ አቅርቦልናል። 

የሕብር ራዲዮ ‘እጅ እጅ’ የሚለው ከጃዋር “እፍ እፍ ፍቅሩን” ባሻገር፤ ቤተ አማራ የተባለ አፍላ “ገንጣይ ድርጅት” እንድናውቀው ማድረጉ ሳላመሰግነው አላልፍም (በዚህ በዚህ ምስጋናየ ልቸረው እሻለሁ)።አስቀድሜ በግልጽ ለብዙ አመታት እኔም ሆንኩኝ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ እንዳስጠነቀቅነው፤ የጎሳ ፖለቲካ በጥንቃቄ ካልተያዘ አደገኛ እና ትንንሽ ሰዎችን የመውለድ እቅም እንዳለው አስጠንቅቀናል።

በጣሊያን፤በጀርመን፤ በመሳሰሉ አገሮች የታዩት “ትንንሽ ሰዎች” አገራቸውን እና ሕዝባቸውን እንዲሁም መላውን ዓለም በምን የጥፋት ጎዳና እንዳሰማሩት አይተናል። በኛ አገር ውስጥ ለበርካታ አመታት  አማራን ከፈጽሞ ጥፋት ለመከላለከል የአማራ ሕዝብ  ደምፅና ወገን እንደዛሬው ባልተበራከተበት ጊዜ፤ “የአማራ ድምፅ ሆነን” የቆምን እኔም ሆነ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ፤ዶ/ር አባባ ፈቃደ እንዲሁም ጥቂቶች ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተጋድሎና ክርክር ያደረግንበት ምክንያት “አማራ”  “ቢጠቃም” ጥቃቱን ለመከላከል የሚያስችለው ድርጅት መመስረት መሆን አለበት እንጂ እንደ ሻዕቢያዎች፤ ወያኔዎችና እንደ ኦኖጎች እንዲሁም እንደ ሶማሌ ኦጋዴኖች” ከኢትዮጵያዊነቱ ተገንጥሎና  ርቆ በመገንጠል ኢትዮጵያን  ለማፍረስ፤  የራሱን መንግሥት” ለመመሥረት ”  ቅዠት ውስጥ መግባት እንደሌለበት አበክረን ግልጽ አድርገናል። በስሜት ተገፋፍቶ በጎሳ ፖለቲካ ተወጥሮና  ተገፍትሮ “የራሱን መንግሥት” ለመመስረት ነው የሚለው እንዲህ ያለ ድርጅት አማራው ሕብረተሰብ እንዲያወግዘው ጥሪ አቀርባለሁ።

 የሩዋንዳንውንም ሆነ የጀርምን እልቂት የጀመረው በጥቂት የጥላቻ “ሞብ” እና በጥላቻ እብሪት የሰከሩ ጎሰኞች መሆኑን ታሪክ ነግሮናል። የመገንጠል ንቅናቄ የሚመነጨው፤  ሌላውን ጎሳ/ሕብረተስብ/ቀለም/ሃይማኖትን በመጥላት ርቆ ለመኖር በሚያልሙ በጥላቻ የሰከሩ “ሞብ ኤሊቶች”/ወረበሎች/  የሚያራምዱት ርዕዮት ነው። አለመታደል ሆኖ ሻዕቢያና ወያኔ ወደ ሕብረተሰባችን እያስሰረጉ በሚያስገብዋቸው “አማርኛ ሚናገሩ ወይንም አማራ አገር የተወለዱ ኤርትራ፤ትግሬ፤ኦሮሞ…  ወዘተ…ወዘተርፈ… ያለባቸው ሰዎችን በማሰማራት፤ የአማራውን ሕጋዊ ጥያቄ አጣምሞ ወደ ሌላ አቅጣጫ በመቀልበስ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የታቀደ ረቂቅ ዘዴ መኖሩን በጥንቃቄ መመርምር ያስፈልጋል።

እንዲህ ያለ የግንጠላ ስራ ለማከናወን፤ ሴረኞቹ የሚመለምሏቸው እና የሚረድዋቸው ሰዎች ሕሊናቸው የተጋጨባቸው፤ በፖለቲካ ያልበሰሉ እና በጥላቻ የሰከሩ ሰዎችን በማፈላለግና በመመልመል የግንጠላ ርዕዮት እንዲያራምዱ ያደራጅዋቸዋል። በኦሮሞ እነ “ጃራ” የመሳሰሉ ክርስትያን እና አማራን የፈጁ የጥላቻና የሃይማኖት አክራሪ ሃይላት የመጀመሪያ ድጋፍ ያገኙ እና የተጠለሉባቸው አገሮች ስትመለከቱ  ለኢትዮጵያ ጥላቻ ያላቸው እንደ ሶማሌ፤የመን፤ ኤርትራ፤ዓረብ አገሮችን…..የመሳሰሉ ነበር። ዛሬም ያ ሴራ አልበረደም።

ጣሊያን ወደ አገራችን ሲገባ መጀመሪያ በኤርትራ ከዚያም ወደ ትግራይ ከዚያም ወደ መሃል አገር ዘልቆ ሰርጎ በመግባት በስርዓቱ ውስጥ ያማረሩ ተቃዋሚ ጎሳዎች፤ግለሰቦች፤ተቋማት (አስልምና ሃይማኖትን ወይንም የስልጣን ሱሰኞችና ባላንጣዎችን) በማፈላለግ መልምሎ ከሥርዓቱ በማስካድ ወደ እሱ ዓላማ ያስሰለፋቸው ሰዎችና ጎሳዎች እንደነበሩ ታሪክ ነግሮናል።

ያ የረቀቀ ሴራ/ሳብበርዥን ዛሬ ወደ አማራዎች እየሰረጸ ገብቶ ስንመለከት አስደንጋጭና አሳሳቢ ነው። የራስን መንግስት ማቋቋም፤ መገንጠል፤አግር ማፈረስ፤ የሚባል አባዜ በሌሎቹ እንጂ በአማራዎች የማይታሰብ የነበረው አሁን “የምዬን እከክ ወደ አባዬ” የጎረቤት እከክ ተጋብቶባቸው አማራዎች ነን የሚሉ “በቤተ አማራ” ድርጅት ተደራጅተው፤አማራን ለማስካድና አገር ለማፍረስ ዬወያኔዎችን ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የሚሯሯጡ “ባንዳዎች” ጠንቅቆ ማስተዋልና ማውገዝ፤ማራቅ አስፈላጊ ነው።
 እንዲህ ያለ የመገንጠል ጥያቄ የሚያቀርቡ ሰዎች የንቃት ደረጃቸው እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ወይንም እንደገለጽኩት የአገር አንድነትና ሉዓላዊነት ምንነት በቅጡ ያልገባቸው ፤ በኤርትራ/ወያኔ የተላኩ የአማራ ሽፋን የለበሱ አሳፋሪ አማራዎች ሕዝቡ እንዲያርቃቸው ከወዲሁ ነቅቶ ካልተነሳ፤ “ዱርየዎች/Mob/ አስሰማርተው፤ የሩዋንዳን እልቂት መሳይ ብጥብጥ እንደሚያስከትሉ ጥርጥር የለውም። ወያኔም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ  ዜጋ “የጎሳ መታወቂያ” ስለሰጠው፤ ዱርየዎች የሩዋንዳን ምሳሌ ተከትለው በመታወቂያው እየለዩ የመገዳደል ሰይጣናዊ ወንጀል በኢትዮጵያ ምድር  እንዲፈጽሙ ያቀደውን መንገድ አመቻችቶላቸዋል።

ቤተ አማራ የተባለው መሰረቱ የማይታወቅ ድርጅት፤ ሕብር ራዲዮ ያስተናገደው ሰው ስም እና ፎቶ ግራፍ በቃለ መጠይቁ ይታያል። የዚህ ሰው ስም “መስፍን ባዘዘው”  ይባላለል፡ በቤተ አማራ ድርጅት ውስጥ ያለው ቦታ ሲገልጽ “የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነትና የድርጅቱ ምክትል ሐላፊ” ነው። የድርጅቱ ማሕተሙንም ስትመለከቱት በሰው ልጅ ግድያ የሚያምኑ፤ ፋሺስት  መንግሥታት፤ ዓረቦች/እና አንዳንድ እስላማዊ አገሮች፤ ሙሶሊኒ፤አሜሪካ፤ስፐየይን፤ በሰይጣን የሚያምኑ የታቱ መተሚያ ድርጅቶች “ጆፌ/አሞራን” በመታወቂያ ማሕተማቸው ይጠቀሙባቸዋል።ለግንነጠላ የተዘጋጀ ድርጅት ይህ ምስል ሲቀም በጣም አስገራሚና አስደንጋጭ ምስል ነው። 

በዚያው ማሕተማቸው ውስጥ በረቂቁ ስትመለከቱት “ሱፐር ማን” የሚጠቀምበት የትምክሕትና የበላይነት፤ዓለምን የመቆጣጠር አባዜ የተጠናወታቸው ድርጅቶች የሚጠቀሙበት ግምባራዊ ጥቅስ/ምልከት ይታያል። ይህ ለምን ሆነ? የድርጅቱ ሰዎች አሞራን ለምን እንደመረጡት አስገራሚ ነው፡፡ 

በዚህ ድርጀትና በቃለ መጠይቁ የተጠቀሱት እጅግ ያልበሰሉ ትንታኔዎች ሌላ ቀን አምለስበታለሁ። ላሁኑ ጊዜ የለንም፤ ወደ ሁለተኛው ትነታናዬ ወደ ወቅታዊው የጎንደር መብረቃዊው  ትዕይንት ልወስዳችሁ ነኝ። ሁለተኛውን ትንታኔዬ ከጨረሳችሁ በሗላ፤ የቤተ አማራ ሕዝብ ግንኙነትና ምክትል ሃላፊ ነኝ የሚለን ሰውዬ ቃለ መጠይቅ ለማድመጥ ከዚህ በታች ያለውን የቪዲዮ መረጃ ይመልከቱ። አስገራሚው ነጥብ ወደ መጨረሻ ገደማ ነው በጥሞና አድምጡት።

Hiber Radio exclusive interview with Bete Amhara Leader, Mesafint Bazezew https://youtu.be/hsn0Z2unFPg
በሁለተኛው ክፍል እንወያይባቸዋለን ያልኳቸው ሦስት ነጥቦች እነሆ።
 ሰኞ ዕለት የጎንደር ሕዝብ መብረቃዊ  ትዕይንት አሳይቶናል።አማራዎች ከራሳቸው አብዮቱታና ብሶት ማስተጋባት አልፈው፤ በጎንደር የኦሮሞ ወንድሞቻችን ግድያ ይቁም ሲሉ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት እና ሰብአዊነት ብሎም አማራዊነት/ርህራሄነት የተላበሰ “አገራዊ መፈክር” አስሰምተዋል። በተጻራሪ ኦሮሞዎች ስለ አማራ መገደልና መጨፍጨፍ አንድም ቀንም ቢሆን ፍጹም “አንስተውትም ፤ አስበውትም፤ ተቆጭተውበትም” አያውቁም።

አማራዎች ስለ ወንድማዊ ፍለጋና ቸርነት፤ አቅርቦነትና መቆርቆር እስከዛሬ ድረስ እየተሰደቡም፤ እየተገደሉም እየተወገዙም እየተወነጀሉም ቢሆን ኤርትራኖች “ወንድሞቻችን ናቸው” በማለት በታወቁ አማራ  መሪዎች (አስራት ወልደየስ) እና በታወቁ አማራ ነባር እና አዳዲስ ወጣት ዘፋኞች በኩል ሳይቀር ወንድማዊ/እህትማዊነታቸውን ሳይገልጹ የቦዘኑበት ወቅት የለም። ይህ ደግሞ የሚያስመሰግን ቢሆንም፤ የዋህነታቸው ሰብአዊነት ባልገባቸው ሰዎች “ከበታችነትና ጉልበት አልባነት” ስሜት የመነጨ አድርገው በመተርጎም የሚሳለቁ ብዙ ጸሐፊዎች አንብቤአለሁ። ‘ዩ ትዩብ’ ሚዲያ ላይ የሚለጠፉ ቪዲዮወችን መመርምር ነው።


አማራዎች ዛሬ ከራሳቸው አልፈው ስለ ኦሮሞዎች በወንድማዊ/እህትማዊ ስሜት ተቆርቁረው ኢትዮጵያዊነትን ሲገልጹ እጅግ ያኮራል። ያ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ስለ የኦሮሞዎች የግለላ/ባንቱስታን/ ስነ ልቦና እና ባሕሪ ያላጠኑና ያልተከታተሉ ብዙ የዋህ ኢትዮጵያዊያን (ውጭ አገር የሚኖሩ የዋህ ተቃወሚዎችና መሰሪ መሪዎቻው በተለይ) ስለ ኦሮሞዎች ከኢትዮጵያዊነት ተስፈንጥሮ መቆማቸውና “ስነ ልቦናቸው መለወጡ” በድፍረት ስከራከር የማይወዱሉኝ የዋሃ ተቃዋሚዎች በርካታ እጅግ በርካታዎች ናቸው። ወንድማችን ሻምበል በላይነህም የኦሮሞዎቹ ፖለቲካ በቅጡ ሳይረዳው፤ ግጥሙን በትከክል ባልይዘውም፤ 

“ከማንም፤ ከማንም፤ ከማንም በፊት ነው፤
 ትግሉን የለሰው የኦሮሞ ልጅ ነው ”

በማለት የገዛ ወገኖቹን የወልቃይቴዎችን ከሃያ አምስት አመት በላይ የለሱትን የአልበገሬነትና የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግላቸውን እረስቶ “የኦሮሞ ኬኛ” መፈክራዊ ንቅናቄ ወደ ኢትዮጵያዊነት አላብሶ በሙዚቃ ዘፍኖላቸዋል። የፖለቲካው ብዥታ የተበራከተበት ተቃዋሚው መከራው ብዙ ነው።  “ግልጽ ግልፁን!!” ይላል የነጻነት ራዲዮ እውቁ ድመጸ መረዋውና ጸሐፊው ጋዜጠኛ “ኢሳያስ ልሳኑ”። ግልፅ በመናገሬ ባትወዱልኝም ችግሩ የናንተ እንጂ የጌታቸው ረዳ የኔ አይደለም።  እንቀጥል፦

የወያኔ “ቡቼዎች” እና “ቡቹየየዎች” ዛሬ ጥዋት በድረገጾቻቸው ያለቀሱትን ልቅሶ ሲያለቅሱ በግልጽ ታንብበዋቸዋላችሁ። ተንሰቅስቆ ማልቀስ የባለ ተራ ነው። አይደለም እንዴ? (ዶ/ር ማንከልክሎት ሃይለስላሴ ናቸው መሰለኝ ‘አይደለም እንዴ? ሲሉ በሚሰጡት ቃለ መጠይቅ ስታደምጡ የሚያምርባቸው) “what goes around comes around” ያለ ማን ነው! አዎ፤ የብዙ ወጣት አማራ እናት ሆድ ሲያለቅስ፤ አማራዎች “ሽንታም አማራ ሲባሉ” የወያኔ “ቡቹየዎች” ሲስቁና ሲሳለቁ ነበር። ዛሬ ትግራይ ያበቀለቻቸው “የሮማ ልጆች”  Roma Boys and the Lazio Irriducibili  ጊዘያቸው ደረሰና “በግነዋል፤ አልቅሰዋል”። Roma Boys and the Lazio Irriducibili  ቃሉ ግራ እንዳይጋበችሁ ሮማ ያበቀለቻቸው በጣም ሞገደኞችና አክራሪ ዘረኞች የሆኑ  ጋንጎች ናቸው። “the Roma Boys and the Lazio Irriducibili are the most violent ultras groups in Italy,.”  ጎንደሬዎች ጠቁሮ የነበረውን ልቤ ዛሬ  በ “ደቂ ሮማ”  መብገን  “ቅቤ አጠጥተውኛል”።

 ዛሬ ጥዋት የተመለከትነው በቪዲዮ ተቀርጾ የተላለፈው ጎንደር ውስጥ የነበረው በፋሺስቶቹ ወያኔዎች እና ቡቹላዎቻቸው ያነጣጠረ “ሕዝባዊ መብረቅና ነጎድጓዳማ ተቃውሞ” ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ፤ አገራዊ ሰንደቃለማ ማውለብለባቸው በታሪክ የሚዘገብ ነው። ሰልፍ ሲወጡ የተለያዩ ቁርጥራጭ ቀለም የተቀቡ ‘መሀረሞችን”  እና “የጎማ ፊኛዎችን/ ባሉኖችን/” በማውለብልብ የሚታወቁ “እስላሞቹ” እና እንደ “ሰማያዊ/ አንድነት ፓርቲ” የመሳሉ ተቃዋሚዎች ከጎንደሬዎች እንደሚማሩ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሁለተኛው ነጥብ ስንዳስስ

 አማራነት ኢትዮጵያዊነት መሆኑን በመፈክራቸው ያሳዩበት ነው። ኦሮሞዎች ወገናቸው የሆነው አማራ ሲጠቃ ለ25 አመት ፤ በጥቃቱ ተዋናዮች ነበሩ ወይንም አማራው ሲጠቃ ምንም ትንፍሽ አላሉም ነበር። ፖለቲካው ወደ ጎን አቆይተን ግልጽ ግልጹን እንነጋገር። ባለፈው December, 20153ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)  /ኦሮሞ ሄጂመኒ” በሚል የኦሮሞዎች በማስተር ፕላን ሰበብ የተቀሰቀሰው “የኦሮሞ ኬኛ” አብዮት እንዲህ ብየ ነበር።

‘’በዚህ ሰሞን የተከሰተው የኦሮሞ ተማሪዎች በፋሺስቱ ወያኔ ላይ እያካሄዱት ያለውን የአንገዛም አምቢተኛነት በወያኔ ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ይሁን እንጂ ከስሩ/ከንጣፉ በታች (ኣንደር ራግ/ ከምንጣፉ/ከንጣፉ በታች) “የሚጨሰው/የሚቦነው የእምቢተኛነት አቧራያነጣጠረውኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችኦሮሞ የሚባል ክልል የባለቤትነት መብት እንደሌላቸውየተንጸባረቀበት እንቅስቃሴ ነው። መፈክሮቻቸውኦሮሚያ የግላችን የኦሮሞዎች ነው!” ይላል። ይህ መፈክር፤- “የግንጠላ ዜግነትፍለጋ ጎልቶ የወጣበት፤ ተገንጣይ ኦሮሞ መሪዎችና ድብቅ ኦሮሞ የግንጠላ አቀንቃኞች በየሚዲያው ወጥተው የአንቀጽ 39 መብትይከበርልን እናየራስን በራስ ማስተዳዳርየነገድ ክልል”/ *የግሩፕ* መብትእንዲከበር የቀሰቀሱበት ትዕይንት፤ በሰልፉ ቀዳሚ የሆነ መፈክር ተንጸባርቋል፤ በኦሮሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጽምጽ ተስተጋብቷል። አማራ ተናጋሪዎች ተገፍትረው ከፎቅ ተወርውረዋል።የተገንጣይ ኦሮሞ ባንዴራዎች ተውለብልቧል። ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ለሽታም አልታየም። ስለተጎዱ ኦሮሞ ሰላማዊ ሰዎች ግን ሀዘኔ እገልጻለሁ። ገዳዮችም ዳኝነት ካለ/የለም እንጂ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።”  ብየ ነበር።


ዛሬ ጎንደር ላይ የታየው ኢትጵያዊነትና በጠባብ የኦሮሞ ብሔረኞች ሊህቃን የተኮሰኮሱ እስካሁን ድረስ የታዩ ተቃውሞዎች ጸረ ወያኔ ይሁኑ እንጂ  ኢትዮጵያዊነት ጭራሽ ለሽታም ተዳስሶ የማይገኝለት  የወያኔ ፌደራል/39ን ይከበር ፤ የኦነግና የጃራ ባንዴራ ይውብለብለብ፤ ወዘተ..ወዘተ..ወዘተ.. የሚሉ ጠባብ ብሔረተኛነትን የሚያቀነቅን፤ ኦነግና ወያኔ እንዲሁም ሻዕቢያ ተማክረው የቀየሱትን የጎሳ ፌደራል ስርዓት ይተግበር ነው የትግላቸው አጠቃላይ ጥሪ። በዚህ አኔ ተቃውሞ አለኝ። ግልጽ ግልጹን እንነጋገር።  ያሳምማችሁ ካላችሁ፤ ችግሩ የኔ ሳይሆን የራሳችሁ ነው።

ኦሮሞወች ለ25 አመት የተሰበኩት የጎሳ ፖለቲካ ማቀንቀን እና የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እንደጠላት መመልከት፤ በአገርም በውጭ አገርም በግልጽ በየስብሳባቸው የሚያሳዩት ነው (እደግመዋለሁ ‘አገርም እዚህ ውጭም’ )። የወዳጄ የነ ሻምበል በላይነህ ማሲንቆ ስለተጮኸላቸው፤ ኦሮሞዎች ከሚያምኑበት ጠባብ ጎሰኛነትና ላቲናዊ ፊደላቸውም ሆነ ከፋሺስታዊ ፌደራሊዘም እምነታቸው አይቀለብሳቸውም። ስለሆነም፤ ጉዞአችን በጥንቃቄ ይሁን። ጎንደር አማራዎች ግን  ስለ ኦሮሞ ወንድሞቻቸው መቆርቆራቸውና በሰላማዊ ድምጻቸው ማስተጋባታቸው፤ የሚመሰገን ኢትዮጵያዊነትና ጨዋ ባሕሪ የተከተለ ስለሆነ፡ ታሪክ በአኩሪ ማሕደር መዝግቦአችሗል። ትግሉ ቀጥሉበት። ኦሮሞችም ከተለያዩ ድርጅቶቻችሁ የተሰጡዋችሁ ፋሺስታዊ  ባንዴራዎችን እና “ፋሺስታዊ ጎሳ ፌደራሊዘምን እና ላቲናዊ ፊደላችሁ” ጥላችሁ “ኢትዮጵያዊ ሰንደቅላማንና፤ ኢትዮጵያዊ ፊደላችሁን’ በማስደምና  ማውለብለብና አገራችሁ  ኢትዮጵያን መውደድ ይጠበቅባችሗል። የመደባበቅ ፖለቲካችሁና እከከኝ ልከክልህ  ከገልቱዎቹ ኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሊሂቃን ዘንድ ይሰራል፤ በኔ ላይ ቦታ የለውም። ግልፅ ግልፁን!

ትግሉ እንዴት ይቀጥል?
 አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን ልንገራችሁ። ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን በደቂቃ ተቀናቃኙን የሚዘርር “አይረን ማይክ” (ብረታዊው ማይክ) ተብሎ የሚታወቅ ቦክሰኛ “ከሆሊ ፊልድ” ጋር ተጋጥሞ ሲሸነፍ፤ ሖሊ ፊልድ የተጠቀመበትን ዘዴ ለጎንደሬዎች የሰነዘረልኝን ሃሳብ ላካፍላችሁ። ሆሊፊልድ ማይክን ባንድ ቡጢ ቀንድብ አይኑ አጠገብ ኩፍኛ ጎድቶታል፡ በዚህ ምክንያት ታይሰን ችግር ገጠመው። ታየስን ያጠራቀመውን የመጨረሻ ጉልበቱ ቢጠቀምም፤ አልሆነልትም። ምክንያቱም ሆሊ ፊልድ የተጠቀመው ዘዴ የሚከተለው ነበር።

ሆሊፊልድ ቅንድቡ ላይ ደጋግሞ በመምታት ታይሰንን እንደሚዘርረው አውቋል። ታዲያ ሆን ብሎ ‘ሆሊ ፊልድ’ ደጋግሞ የሚሰነዝረው ቡጢ ቅንድቡ ላይ ስለነበር፤ ታይሰን ኩፉኛ መድማት ጀመረ። ሳያጋግም “ወዲያውኑ ወዲያውኑ’ ደጋግሞ ሲጠልዘው፤ ዓይኑ በደም ተሸፍኖ ማየት ስላቃተውና ስቃይ ስለበዛበት፤ ‘ታይሰን’ የነበረው አማራጭ፤ ጭንቅ ውስጥ ስለገባ፤ የሆሊ ፊለድን “ጀሮ” “በጥርሱ ነክሶ” ከድብደባው መዳን እንደ አማራጭ ወሰደው።  በቅጽበታዊ ዝረራ በታሪክ ያልታዬ ጀግና የተባለለት ቦክሰኛ ወደ “ጥርስ ንክሻ” ገብቶ ለሆሊ ፊለድ ተምበረከከለት። እጁን ሰጠ። ጊዜ ሚዛኑ! (ጊዜ ሚዛኑ የሚል በቅጽል ስም የሚጠራ ወዳጅ አለኝ፤ ጊዜ ሚዘኑ! እውነትም ጊዜ ሚዛኑ!”

ለሁሉም ጊዜ አለው። አሁንም ጎንድሬዎች/አማሮች ማድረግ ያለባችሁ፤ የተቀጣጠለው “መብረቃዊ አብዮት” ብልጭ ብሎ እንዳይጠፋባችሁ ወደ ነጎድጓድ ዞሮ የኖህ ዶፍ በግፈኞቹ ጫንቃ ላይ እንዲዘንብ ከተፈለገ፤ መንግስታዊ ልብስ የለበሱ Roma Boys እንዲደራጁ ፋታ ሳትሰጡ፤ “ወዲያውኑ፤ወዲያውኑ” ተከታታይ ቡጢ ልክ እንደሆሊ ፊልድ “ወያኔዎች” “በቆሰሉበት ብልታቸው” ደጋግማችሁ መምታት ለድሉ ወሳኝ ስልት ነው። ተቀናቃኝ ሲደክም እና ግራ ሲጋባ፤ ሳይበርድ በትኩሱ መሰንዘር ነው የቡጢ ጥበቡ።

ወያኔዎችና የዓረብ ቡቹሎቹ ሻዕቢያዎች ደርግን የጣሉት “ደርግ” አንድ ድል በተቀዳጀ ሁሉ ተዝናንቶ አንድ ቦታ ላይ ሲቆም” ጠላት ያንን ቸልተኝነት ተጠቅሞ ጊዜ ሳይወስድ ተዋጊዎቹን አደራጅቶ ተመልሶ በመምጣት ሲመቱት “ድሉ” ወደ እነሱ ዞረ። ወያኔዎች፤ አገር ውስጥ  የበቀሉ አደጋኛ “የሮማ ፋሺስቶች” ናቸው።

ወያኔዎች ጫካ እያሉ ሰውን ማፈን የጀምሩት ልምድ አላቸው።፤ ተቃዋሚዎች/ሕዝብ/ግለሰብ ፤ ተዝናንቶ ቁጭ ሲል፤ ሲጨልም፤ ያኔ እያደፈጠ ሲከታተላቸው የነበሩትን ተፈላጊዎቹን እንደ “ዶሮ”  ጭለማን ተገን እያደረገ “ክብሪት” ተብለው በሚጠሩት በጭካኔ እና በነብሰ ገዳይነት የተካፈሉ ማይሞች የተጠራቀመበት፤ደም የጠማቸው “አረመኔዎች” የተጠራቀሙበት ክፍል “በክብሪቶች” እያሳፈነ ወስዶ ያጠፋቸው እንደነበር የምናውቀው ባሕሪያቸው ነው። ዛሬም ጎንደሬዎች የቆሰሉትን “የሮማ ልጆች” ጊዜ ሳትሰጡና በአታላይ ፖለቲካቸው ሳትዘናጉ በቁስላቸው ላይ ደጋግሞ በመምታት እንደ ታይሰን “ማምበርከክ” ወይንም ቢያንስ ለድርድር እንዲቀርቡ ማድረግ አለባችሁ። በትግሉ ላይ የኢትዮጵያ አምላክ ከናንተው ጋር ነው፤ በድል ተወጡ!  ይላል የኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ ፤ጌታቸው ረዳ።
 Ethiopian Semay/  Getachew Reda      getachre@aol.com