Tuesday, January 13, 2015

ጋዜጠኛው ሲሳይ አገና እንደ ካድሬም እንደ ጋዜጠኛም! ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ብሎግ አዘጋጅ)


ጋዜጠኛው ሲሳይ አገና እንደ ካድሬም እንደ ጋዜጠኛም!
ጌታቸው ረዳ (የ Ethiopian Semay ብሎግ አዘጋጅ)
Sisay Agena” ESAT News Anchor and Ginbot 7 propagandis.
Berhanu Negga” Ginbot 7 leader who wants to destroy Ethiopia using Democracy for secessionist purpose.

Ephrem Madebo of Ginbot 7 at Eritrean Festival Okaland CA telling his audience Eritrea as David and weak Ethiopia as Goliath or Golliad


ወይ ቅለት! ይላል ትግሬ፡ ወይ “ቅሌት ማለት” ነው ባማርኛው። ሕብር ራዲዮ በተባለው ከ “ቬጋስ” ከኢሳቱ ጋዜጠኛ ከመቶ አለቃ ሲሳይ አገና ጋር ዛሬ ያደረገው ቃለ ምልልስ ዘሐበሻ ላይ ተለጥፎ አንብቤአለሁ።  የመቶአለቃ ሲሳይ አገና ስለ ኤርትራ በጎ አድራጊነት እና ስለ ፋሺስቱ ሻዕቢያ መልአካዊ ተክለሰውነት እንዲከናነብ ለኢትዮጵያዊያን መለፈፉ እንደ የግንቦት 7 ካድሬነቱ የሚጠበቅ ቢሆንም “ቅሌት ነው”። ሲሳይ በዛው በፋሺስቱ ሻዕቢያ ተይዘው ደብዛቸው የጠፋው ኢትዮጵያዊያን እንደ እነ “ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ” የመሳሰሉ በርካታ ዜጎቻችንን ሕዝባችን እንዳያውቀው  እነ ተሸመ ተንኰሉን እንደ ማካካሻ እያደረገ በምሳሌ እየጠቀሰ ስለ ሻዕቢያ መልአካዊነት ሊሰብከን መስማቱ ከግንቦት 7 ጋዜጠኛ እና እሱ ከሚያጃጅላቸው ለጀሌ አድማጮቹ የሚጠበቅ ካልሆነ ሻዕቢያን ከጅምሩ እስከ አሁን ድረስ ለምናውቅ ተንክትክተን ሊያስቀን ከመሞከሩ በቀር የሚፈይደው የለም።

በጣም የሚገርመው ደግሞ የኢሳት ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ሰዎች በየመን ሰንዓ አንዳርጋቸው ከታፈነ በሗላም ወደ ኤርትራ ሲተላለፉበት እንደነበር ሲገልጽ ለወያኔ ጥሩ መረጃ እያቀበለው መሆኑን ልብ ያለው አይመስልም። በዚህ ትችቴ ለሚፈጠረው ነገር ይህ ትችቴን አስታውሱ። 

አስገራሚው ደግሞ በብዙ ሚሊዮን ብር የሚደገፍ የወያኔ የስለላ መዋቅሩ አገር ውስጥ እንጂ ውጭ አገር የለውም ብሎ ሲያናንቅ ከሱዳን ጀምሮ ምስራቅ አፍሪቃ ያሉት አገሮች በሙሉ በወያኔ የስለላ መረብ የተያዘ መሆኑን ጋዜጠኛው ሲሳይ ወያኔን ያወቀው አልመሰለኝም።: 

በዛው ቅሌት ስለመ ኤርትራ በጎ ባሕሪ ሲያወራ ‘ታደሰ ሙሉነህ’ መፈንቅለ መንግስት ሲያደርግ በተያያዘ መያዙ አንዳርጋቸው አንደቀላበደው ሲሳይም ፋሸስቷን ኤርትራን ለማሳመር ሲል ከንግግሩ ሌላ የውሸት ታሪክ እንዳይጨመርብት ሰግቼ ነበር። ደግነቱ የሕብር ጋዜጠኛ ስለ እነ ታደሰ ሙሉነህ ጉዳይም ሆነ ግንቦት 7 ስላፈናቸው እና አሁንም በኤርትራ ገራፊ ቡድን ተይዘው እየተሰቃዩ ያሉትን እና ደብዛቸው የጠፉትን ለሲሳይ ሊያነሳለት አልቻለም። ያው ሚዲያዎቹ እንደ “ላሞች” እየተላለሱ መኖራቸው አዲስ አልሆነኝም እና የሚጠበቅ ነው። እኛ ግን ማንሳታችን ከቶ የሚቆም አይሆንም።
ለመሆኑ፤ አርበኞች ግምባር ለ18 ዓመት ኤርትራ ውስጥ ሲመሽግ የመቶ አለቃ ሲሳይ አገና እንደሚቦተልከው “ተቃዋሚዎች አንድ ስላልሆኑ ነበር” አንዲት ትንሽር ገጠር በቁጥጥር ስር አድርጎ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንኳን መፍጠር ያልቻሉት? ለአንድነታቸው መደፍረስ እና እርስ በርስ መተማማት ኤርትራ ውስጥ የመሸጉት ወይስ ኢሳያስና ካድሬዎቹ ጣልቃ እየገቡ ሿሚዎች እና ሻሪዎች ሆነው ለ18 አመት ሙሉ በዛው “ዶርማንት” በዶለዘ ጉዞ  “ሙትም ህሉዊም” የሆኑት?  ወይስ እንደ አንዳርጋቸው አባባል “ሰነፎች” ስለሆኑ? ወይስ ግንቦት 7 ወደ ኤርትራ ምድር ባለመቀላቀሉ ነበር የሕብረታቸው ችግር? ሲሳይ እራሱን ወይስ ጀሌዎቹን፤ ወይስ እኛን? ለማን ነው እየሰበከ ያለው? 

እንድያው ለነገሩ አልን እንጂ “አርበኞች ግምባር የሚባል ጦር በሕይውት  የለም፤! ስለ አርበኞች ግምባር ዜናም ኢሳት አንዳይዘግብ ይደረጋል” ብሎ የሲሳይ አለቃ ክቡርነታቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በምስጢር የተቀዳው አውዲዮ ለሕዝብ ይፋ የሆነውን ስናስታውስ አሁን ግንቦት 7 ወደ ኤርትራ ዘልቆ ብርሃኑ ይህንን ከተናገረ ከአንድ አመት በሗላ “ሕይወት” የተዘራለትን አርበኞች ግምባር  ሲሳይም ሆነ የሕብረ ጋዜጠኛው ሊያነሱት አልቻሉም/አልፈለጉም። እነ ብርሃኑ ለእነሱ ካልተስማማቸው አርበኞች የሚባል የለም ይላሉ ሲያመቻቸው ደግም በሻዕቢያው አገልጋዩ ‘በመሃይሙ’ ማአዛው ጌጡ የሚመራው አርበኞች ግንባር የሚባል ‘አገር አድን’ ጦር ከግንቦት 7 ጋር ውሕደት መፍጠሩን ይነግሩናል።

 ጋዜጠኞቹ በፖለቲካ አለቆቻቸው የሚንዛዛ ንግግራቸውን ለምንድነው የሚደብቁላቸው? ጋዜጠኛ ምን ማለት ነው? ግንቦት 7ም ይሁን ማንም ድረጅት በሚሰራው የፖለቲካ እና የጦር አንቅስቃሴ እኛንም አንደ ኢትዮጵያዊያን የሚነካ ስለሆነ ለትችታችን መልስ ከመስጠት ይልቅ እንደ ሰሲሳይ የመሳሰሉ ግለሰዎች ትችታችነን በሌላ መልክ ጠምዝው ሊተረጉሙት ይሞክራሉ። ሲሳይ ስለ ጉንቦት 7 የሚተቹን እያዋረደ ሲተች፤ ግንቦት 7ን የሚተቹ ግን መብት የላቸውም ይለናል። አስገራሚው ደግሞ ተቺዎቹ በሁለት ይከፍላቸዋል። እኛስ ሲሳይ እና ግንቦት 7 ለሁለት ከፍልን መተቸት አንችልም?  ወይ ትዕቢት!

ዘሃበሻ የተባለው እና መሳይ ድረገጾችም ሕዝብ የመነጋጋር መብት አለው ይሉ እና እንደዜጎች ስንተቻቸው ትችታችንን ያፍኑታል/አይለጥፉትም። ለምን እንደሚፈሩ አይገባኝም። ታዲያ ከወያኔ ሚዲያ በምን ተሻሉ?

 ኢትዮጵያን ከወያኔ ነፃ የሚያወጣው አሜሪካ በምቹ አልጋ ላይ እንቅልፉን በምቾት እየለጠጠ እየኖረ ያለው (ምንም እንኳ ወኪሉ የጥምረት መሪ ነኝ እያለ በጐን የግንቦት 7 እና የኢሳት ቲቪ/ራዲዮ ፊታውራሪው ንአምን ዘለቀ ኤርትራ ለመኖር ወስኛለሁ ብሎ ከመሄዱ በፊት ወሬው ቢያናፍሰውና አሁንም ኤርትራ አንዳለ እና በውሕደቱ አዳራሽ ፎቶው ያየነው ቢሆንም) 18 አመት ኤርትራ ውስጥ አለ የለም እየተባለ የበሰበሰው የብርሃኑ ነጋ እና የመአዛው ጌጡ ጦር ከኤርትራ ገስግሶ ሕዝቡን ከወያኔ የሚያላቅቁት ወይስ “በምርጫ እገነጠላለሁ የሚል ካለ ዲሞክራሲ ነው እና መገንጠል ይችላል” ብሎ ግንቦት 7 የሚመራበት የግንጠላ አይዲኦሎጂው?

ይህ አሁን ስለ ሰካራሙ ኢሳያስ አፈወርቂ ፋሺስታዊ እና ‘ፓራያ’ አስተዳደር በጎ ተክለሰውነት እየቀባው ያለው  የመቶ አለቃ ሲሳይ አገና  እና መሰሎቹ ስለ የሲሳይ፤ያንዳርጋቸው፤የኤፍሬም ማዴቦ ስለ ኤርትራ በጐ አሳቢነት እና “ለኢትዮጵያ ሞዴል/አርአያነት” መስበኩ ካሁን በፊት እነዚህ ሰዎችን የሚመስሉ ግለሰዎች Ethiopia: anatomy of a traditional polity በሚለው መጽሐፍ በሴረኛውና ጸረ ኢትዮጵያው ግሪካዊው (?) ጆን ማርካኪስ የጎነጐነልንን ሦሰቱ ሴራዎች አንብቡ። እንደ እነዚህ ያሉ “ሑልኩሳት” (ትግርኛ) ልክስክስ/ውሸታም (?) (አማርኛ) አይተናል። እነዚህ የመሳሰሉትን ግለሰዎች የማርካኪስ መጽሐፍ ሴራ 1 ሴራ 2….እያለ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሴራውን ሲተነትነው ለሁለተኛው ዙር ሴራ እግንቦት 7 እና ጋዜጠኞቹ  “ምቹ አንደሆኑ” ታያላችሁ። (ከአንድ አመት በፊት እነ ኢሳቶችም ያ ጸረ ኢትዮጵያ  “ማርካኪስ” ቃለ መጠይቅ አድርገውለት ሲዘባርቅ ነበር።) ያ የመቶ አመት ብሎ የሚጠራው ኢሳያስ አፈወርቂ ሴራም በሳልሕ ሳቤ ስም ታነቡታላችሁ።

ማርካኪስ ያስቀመጠው ኢትዮ ያን የማጣጣልና የማፍረስ የቤት ሥራ፤ እና ሴራ የግንቦት 7 የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ባንዳው ኤፍሬም ማዴቦ በቃሉ ሲናገር ሻዕቢያ ፌስቲቫል ኦክላንድ ካሊፎርኒያ ድረስ ሄዶ አማራውን አንገት የማስደፋት የሚለውን “ሦስተኛው የሥራ ቤት/ሆም ዎርክ/ የሚለው የጆን ማርካኪስ ሴራ ለኤርትራኖች እንዴት ከሽኖ አቅርቦ ሳያመነታ አማራ እና ዋሺንግቶን ራዲዮ ውስጥ ያሉትን 14 ክፍለሃገር የሚለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን የሚያስተላልፉትን “ራዲየ ጣቢያዎች” ኤክስትሪሚስት/ የነፍጠኛ ረዝራዦች እያለ እንዴት አንደዘለፋቸው እና፤ ኤክስሪሞቹንም በቁጥጥር አድርገንላችሗል፤“ግድ የላችሁም”  ሲላቸው ሞቅ ያለ ጭብጨባ ሲለገስለት ሞቅ አለውና ኤርትራን “ባለ ወንጭፉ “ዳዊት” ኢትዮጵያን በዳዊት የተንበረከከቺው “ጎልያድ” እያለ “የኢትዮጵያ ታላቅነት ባዶ እና ምንም ዋጋ የለውም” እያለ የኤርትራ እና የማርካኪስን የሥራ ቤት የወጠወጠው  (የከሸነውን) የግንቦት 7 ፖሊሲ እና ሴራ ይፋ ያደረገውን ጋዘዜጠኛው ሲሳይ የረሳነው ይመስለዋል።

 የግንቦት 7 ፖሊሲ በኤርትራ የሚከተለውም ዘርዝሯል። ድርጅቱ ግን ፖሊሲ እና መመሪያ የለኝም ይላል። ኤፍሬም ማዴቦ ግን አሁን የተናገርኩት ግንቦት 7 ወክዬ  የመጣሁ እንደመሆኔ መጠን ንግግሬ የኔ እና የድርጅቴ እምነት ነው ሲል ተናግሯል። ታዲያ ሲሳይ አገና “ግንቦት7” መሬት ላይ ወርዶ አመርቂ ስራ እየሰራ ነው የሚለንን ፕሮፓጋንዳው “ኤፍሬም ማዴቦ” የነገረንን ፖሊሲው ለመተግበር አንደሆነ ሲሳይ ማንን ነው ለማሞኘት እየጣረው ያለው? ሲሳይ የሚናገረው ያውቃል? የግኖበት 7 ፖሊሲ ምን እንደሆነ ሲሳይ ሊነግረን ይችላል?  

እነዚህ ናቸው በሲሳይ ምላስ “መሬት ላይ ወርደው ስራ የሚሰሩ” ሲል ሌሎቻችንን ሲዘልፍ በሕብር ራዲዮ ሲንዘላዘል የሰማነው።

ግንቦት 7 ከመቼው ደረሰለት እና ነው ልቡ አንዲህ ያበጠው እባካችሁ? ይህ ውሕደት ከጠቂት ወራት በሗላ አንደ ዘወትሩ በኢሳያስ ካድሬዎች ቢፈርስ ሲሳይ ምን ይለን ይሆን ደግሞ? መቶ አለቃ ሲሳይ አገና ምነው ፖለቲካው እረስዎ ብቻ የሚከታተሉ መሰለዎት? ይህ ስራ ቤት መሬት ላይ ሲወረድ ማረፊያው የት ይሆን?

መቶ አለቃ ሲሳይ አገና እባክህን እንደ ካድሬ ከመከራከር አንደ ጋዜጠኛ ሆነህ ስለ ስለ የግንቦት 7 መሪዎችህንም አፍራሽ የሴራ እና ስለ አገራችን የሚሰነዝሩትን የንቀት ንግግራቸውን እና ስለ ኤርትራኖች ባሕሪ እና ስለጠፉ ዜጐቻችንም መናገሩንም ጭምር ድፈርበት።ኤርትራኖች አንደሆነ ለግንቦት 7 ሲሉ ዥንጉርጉር ቆዳቸውን ይተውታል ብለህ መስበኩን አቁም።ሞኝህን ፈልግ!

የሰሞኑን ኤርትራ ጉዳይ በዚህ ሰፋ ያለ ትንተና አቀርባለሁ፤ተከታተሉኝ፡
ጌታቸው ረዳ
(ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) getachre@aol.com Ethiopian Semay