Monday, October 11, 2021

የፖለቲካ ልሂቃን በጅምላ እንዲቀብሩ ጥሪ ስለማቅረብ አስፈላጊነት ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) Ethio Semay October 12/2021

 

 

የፖለቲካ ልሂቃን በጅምላ እንዲቀብሩ ጥሪ ስለማቅረብ አስፈላጊነት

ጌታቸው ረዳ

(ኢትዮ ሰማይ)  Ethio Semay

October 12/2021


ፎቶግራፍ ጌታቸው ረዳ (ከሆስፒታል ምሜ ከወጣሁ በሳምንቱ) የሕግ ምሁር እና ጋዜጠኛ አበበ  ገላው እና ጃዋር መሓመድ ናቸው።

ከአራት አመት በፊት አንድ የጎዳና ላይ የሚኖር ናይጄሪያዊ ወጣት፤ ለናይጄሪያ ለማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮችመጥፎ አመራሮች እና ሊሂቃንንተጠያቂ ያደረገበት ቪዲዮ በአገሪቱ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭተው አይተናል። በእሱ አስተያየት ንቅዘትን ለመዋጋት እና የአገሪቱን አቅም ለመክፈት የሚረዳውን የአገሪቱን የፖለቲካ ልሂቃን በጅምላ እንዲቀብሩ ጥሪ የአቀረበበት ጥሪ ነበር።

የእሱ አመለካከት በአፍሪካ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ስለ መሪዎቻቸው ያላቸውን ውስጣዊ እና የተደበቀ ስሜት ያስተጋባ እውነታ ነበር። ይህ ስሜትና ፍላጎትም በአገራችንም 30 አመት የቀጠለ ስሜት ነው።

ናይጄሪያኖቹ የሚሰቃዩት ሥልጣን ላይ ባሉ እና ባለ ሥልጣኖችን የሚያባልጉ የምጣኔ ሃብት ንቅዘት አራማጆች ነው የሚከስሰው። የእኛ ስቃይ ግን ንቅዘትም/ሌብነት (ኮራፕሽን) ብቻ ሳይሆን ሕዝባችን በውስጥ ቅኝ ግዛት ቀንበር 30 አመት እየተሰቃየን ያለንበት፤ እጅግ አሳዛኝ እውነታ ለስቃያችን ለየት ያደርገዋል።

አገራችን 27 አመትበትግሬዎች የውስጥ ቅኝ ግዛትሥር ነበረች። ዛሬም የሥልጣን ተጋሪዎች በሆኑ ኦሮሞዎች በአብይ አሕመድ መሪነት በኦሮሙማ አጀንዳ የተቀረጸው የውስጥ ቅኝ ግዛትበመላ አገሪቱ የዘር ጭፍጨፋ፤ አመጽየዋይታ ድምጽና መፈናቀል በከፋ መልኩ እንዲቀጥል አድርጎታል።

የውስጥ ቅኝ ግዛት ምንነት ያልገባችሁ ሰዎች ስለምትኖሩ በመጽሐፍ መልክ ለመስራት እያሰብኩ ስለሆነ እስከዚያው ድረስ ትንሽ ልበል። ውስጣዊ ቅኝ ግዛት የአንድ ሀገር ነገድ በቁጥር አነሳም ይሁን አብዝሃአንዱን ሌላኛውንለማስገበርለምጣኔ ሃብት ወይንም ለሥልጣን ስግብግብነት ሲል ሥልጣን ይዞ ያንን አጀንዳው ለማሳካት የሚጠቀምበት በጉልበት የሚፈጸምሄጀመኒ” (ሥልቀጣ/ሬፕ/) ነው።

 ሥልጣን የተቆጣጠረውአውራ-ቡድን የማኅበራዊ ተቋማትን በማጭበርበር የተቃጣባቸው የነገዶች መብት በማፈን እና የማኅበረሰቦቻቸውን ጥቅሞች ሙሉ በሙሉ እንዳያገኙ ይነፍጋቸዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ወዳጄ ይነጋል አንድ የጻፋት ነገር ታወሰቺኝ። 83 . ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ በወያኔ ሬዲዮ የትግርኛ ፕሮግራም ስለትግራይ ሕዝብ በወያኔ ሥልጣን መያዝ ተጠቃሚነት የተጠየቀ አንድ ትግሬ ባለሥልጣንየመጀመሪያው ጠቀሜታሥነ ልቦናዊ ነው ፡፡የኔ ሰው ሥልጣን ያዘልኝብሎ ማሰቡ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ይላል።

የኔ ሰው ሥልጣን ያዘ/ሥልጣን ላይ ነውየሚለው ተጠቃሚ ባይሆንም የስነልቦና ልዕልናዘውድ ያስደፋል በሌላ መልኩ ይህ ልዕልና በሌሎች ነገዶች ላይ የመንፈስ ስብራት የበታችነት ስሜት እንዲሰፍን ያደርጋል።

 ትግሬዎችም ሆኑ ኦሮሞዎች በተቀሩት ላይ በየተራ የፈጸሙት የስልቀጣ አሰራር እንዲያ ነበር። ያንን የትግሬዎች ዘመን ለዛሬው ኦሮሙማው አብይ እንዳንሸጋጋር ነበር ወዳጄይነጋል በላቸው” ‘የእስካሁኑ በቃችሁ ብሎ ለሌላ ውርጅብኝ አይዳርገን፡፡ ጸሎት መያዝ አሁን ነው።ያለውን ሁሌም አልረሳውም። ጸሎት ስላልያዝን ይሆን ሌላ ውርጅብኝ ሊደርስብን የቻለው? የሚል ጥያቄም በአማኞች ሕሊና ዘንድ ያሰጭራል።

በትግሬዎች አገዛዝ ዘመን ትግሬዎች እጅግ ተንደላቅቀው እንደነበር አንድ ምሳሌ ላቅርብ እና ወደ ኦሮሞዎቹም አንዲህ አሳያለሁ።

በዘመነ ትግሬዎች ትግሬዎች የነበራቸው ቦታ ወዳጄ ይነጋል ያጋጠመው ገጠመኝ ብዙ ቢሆኑም አንዱን እንዲህ ይጠቅሰዋል።

እውነት ብትመር ብትጎመዝዝም ምርጫ በምናጣበት ወቅት ዶሮ ማታ ብለን መጨለጥ ይገባናል፡፡ እንዲህ ስናደርግ አንድም ከተጣባን ኮሶ እንሽራለን አሊያም ሌላ አማራጭ እንፈልግና ከህመማችን እንፈወሳለን፤ እየተዝረጠረጥን መኖር ግን አይገባንም፡፡ ይልና በማያያዝም እንዲህ ይላል፤፡

‘’በጣም የሳበኝ አንዱ ፈረንጅ የትግሬውን አገዛዝ “Internal Colonialism” ሲል የገለጸው ነው፡፡ እኛም እንዳቅሚቲ ከዚህ አልፈን ይህን ሥርዓት ጥቁሮች በጥቁሮች ወንድሞቻቸው ላይ የጣሉት አፓርታይድ እንደሆነ በተደጋጋሚ ጮኸናልጊዜው አልደረሰ ሆኖ ሰሚ ጠፋ እንጂ፡፡ ዘመኑ ሲብትማ ሣሩ ቅጠሉ ጆሮም አንደበትም አለውየወር ተረኛን የድል ብሥራት ዜና ለዱር ለገደሉ ለማወጅ፡፡ አዲስ የቅኝ ግዛት ዓይነት ነው የገጠመን፡፡

አዲስ የአፓርታይድ ዓይነት ነው የተጣለብን፡፡ የዚህ ጭራቃዊ ቅኝ አገዛዝና አፓርታይድ የመጨረሻ ውጤት የሚሆነው የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እንጂ ከሦርያ የበለጠ ዕልቂት ነው፡፡

ያለንበት አገዛዝ የትግሬ ቅኝ ገዢ አገዛዝ ነው፡፡ ይህን ማስተባበል አንድም የሞትን ዕድሜ ወድዶ ማራዘም ነው፡፡ አንድም መዋሸት ነው፡፡ አንድም ጭልጥ ያለ አድርባይነት ነው፡፡ ሀገሪቱ ከግርጌ እስከ ራስጌ በትግሬ ወያኔ ተቀፍድዳ ኤሎሄ እያለች ሳለትግሬ እየገዛን አይደለም፤ ትግሬዎች አልተጠቀሙምብሎ መወሽከት ታሪክ ይቅር የማይለው የለየለት እብለት ነው፡፡ እንዲህ የሚሉ ወገኖች ግና በርግጥ ዐይንና ጆሮ ይኖራቸው ይሆን? ለምን አዲስ አበባ አይመጡምና የመንግሥት ተብዬውን የወያኔ መናኸሪያ ጓዳከተፈቀደላቸውአይጎበኙም? ካለ በሗላ

አባይን በጭልፋ ዓይነት ነው፤ የትኛው የመንግሥት ቤት ነው ከወያኔ ቀጥተኛ ቁጥጥር ነፃ የሆነና በሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚተዳደር? -ትግራውያን ሠራተኞች የወያኔ ባርያና ሽቁጥቁጥ ሎሌዎች አይደሉም እንዴ? በሁሉም መሥሪያ ቤት እንደልቡ የሚዘባነነው ማን ነው? ማነው አዛዥ ናዛዥ? ይህን የፈጠጠ እውነት ማየት የማያስችል ምን ዓይነት ደምባራነት ነው? (በአንድ የመንግሥት – (“የመንግሥትስል እንዴት እንደሚቀፈኝ ብታዩ) – የጦር ሆስፒታል አንድ ወቅት ስታከም እንደታዘብኩት ፈረቃቸው ደርሶ የተቀያየሩት ዘጠኙም የክፍሉ ሐኪሞችና ነርሶች ከጽዳቶቹ ጭምር ትግሬዎች ናቸው (ግን ገራገርና ጥሩዎች ናቸው) – ይህ ምን ዓይነት አጋጣሚ ይሆን?

ይህን የማፊያ ሥርዓት ላይገባው የራስን ክብር አዋርዶ በውሸት ለማባበል መሞከር መናኛነት ይመስለኛልወይንም በአንዳች አእምሯዊ ግርዶሽ መሸፈን ነው፡፡

ይላል ይነጋል በላቸው።

አሁን ደግሞ እስኪ ወደ ተረኞቹ ኦሮሞዎች እንመለክት

አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ) በአንድ ትችቱ በዚህ ፌስቡኬ ላይ ጠቅሼው ከነበረው ልጥቀስ። እንዲህ ይላል፤

ኪራይ ቤቶች ከዘበኛ እስከ ዋና ማናጀር አክራሪ ኦሮሞ ነው አሉ የወረሰው - የይስሙላውን የመጣያ ዓይነት ሹመት ትተን፡፡ በዚያም ምክንያት የኪራይ ቤቶች ንብረት የሆኑ የመንግሥት ቤቶች ለኦሮሞ ሀብታሞች ባወጡ እየተቸበቸቡ ነው፡፡ ድንቁ ደያስ የተባለው የዲግሪ ወፍጮ ባለቤት ከኪራይ ቤቶች የወሰደውን አንድ ቤት እንዴት አድርጎ እንዳሳመረው ራሴ አይቻለሁ፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ እንዳለች በቄሮ ቅርጫ እንደጉንዳን ተወርራለች፡፡ አሁን ያልከበረ ኦሮሞ መቼም አይከብርም የተባለ ይመስላል።

 

አዲስ አበባ አሥር የትራፊክ ፖሊሶችን ሰብሰብ ብለው ካየህ አሥሩም ኦሮሞ ለመሆናቸው ብዙም አትጠራጠር፡፡ አሥር የመንገድ ላይ ፖሊሶችን ካየህ ቢያንስ ዘጠኙ ኦሮሞ ስለመሆናቸው ጥርጣሬ አይግባህ፡፡ አሥር የአሥር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ታላላቅና ወሳኝ ባለሥልጣናት ሰብሰብ ብለው ቡና ሲጠጡ ብታይ አሥሩም ኦሮሞ መሆናቸውን ለማወቅ ማንንም መጠየቅ አይጠበቅብህም፡፡ የአሥራ ምናምኑን ክፍለ ከተማ ዋና ዋና ባለሥልጣናት ብታይ ከኦሮሞ ውጭ አይሆኑም፤ ወረዳና ቀበሌዎችንማ ተዋቸው፡፡ የመከላከያን አሥር ዋና ዋና ባለሥልጣናት ድንገት ሻይ ሲጠጡ ብታይ ከኦሮምኛ ውጪ ሲናገሩ የመስማት ዕድል የለህም፡፡ ወያኔ ሞትኩ አትበል፤ ዐይኗን ባይኗ አይታና ራሷን ተክታ ነው ፍግም ያለችው፡፡ እነዚህም እንደፈጣሪያቸው ፍግም እስኪሉ ጉድ እያሳዩን ነው፡፡ ምን አለፋህ አቢይ እላይ ሆኖኢትዮጵያ የጋራ ናትይልሃል ከሥር ግን በእርሱ ዕውቅናና ሽፋን ሰጪነት ለአንድ የቀን ጅብ ተሰጥተን የትህነግን ዘመን እየናፈቅን ነው፡፡ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይመሰገንምየሚባለው እውነት ነው፡፡በይሉኝታቢስነት ከወያኔ የሚበልጥ የለምበሚል ብዙ ጊዜ እከራከርና እጽፍም ነበር፡፡የባሰ አለ አገርህን አትልቀቅነው ወንድሜ፡፡

ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ የሀገራችን ነጋዴዎችና ባለሥልጣናት እንደዚህ ናቸው - የቀን ጅቦች፡፡ እነዚህ ፈርሰው ካልተሰሩ ሀገር አትኖረንም፡፡ አንድ ሰው በቃኝን ካላወቀ ደግሞ ሀገርንና ሕዝብን ተወውና ሚስቱንም ልጁንም አባትና እናቱንም ከመሸጥ ወይም ለዲያብሎስ ጭዳነት ከመገበር አይመለስም፡ ስለ ኦሮሞዎች የሰለቀጡት የሥልጣን ስልቀጣ እንዲያ አሳይቶናል።

መበስበሱ በፖለቲካ ሰንሰለቱ ውስጥ ወደ ተመረጡ እና ወደ ተሾሙ የመንግሥት ባለሥልጣናት - ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጀምሮ። የብቃት እና የውስጥ ዴሞክራሲን ግምት ውስጥ ሳያስገባ የመንግ ገንዘብ ነክ የመባከን እና የእምነት አባቶች የሚሾሙትና የሚመርቁትስ ማንን ነው። የመንግሥት ጉዳዮች እና ገንዘቦች እንዴት እንደሚተዳደሩ ለሕዝብ አይገለጽም። ስለዚህ  በ30 አመት የታየው ምርጫም ፋሺስቶች እና ወንጀለኘፐች እንዲሁም ሌቦችን እና ዋሾቸን ሥልጣን ላይ የሚያስቀምጥ ቀጠፊዎች የሚነጥቁት ትዕይንት ነው።። በዋናነት ሊሂቁም ፖለቲከኞችም የበሰበሱ መንጋዎች ስብስቦች ናቸው። የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ርዕዮተ ዓለምን የሚደግፉ መስለው ይናገሩ እንጂ መንግስታት/መሪዎች/ ሲቀየሩ እነሱም አብረው ይደመራሉ። ቱና በእውነቱ ምንም የሚለወጥ ነገር የለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ሲያስፈጽሙና እየፈጸሙ ያሉ ሊሂቃን የመንፈስ ሞት ሞተው በቁም ሞተዋል እና ምድሩን ከሚያጠነቡት ይልቅ በጅምላ እንዲቀበሩና አገሪቱ ጤናማ አየር እንዲተነፍስ ጥሪ ማቅረብ ወቅታዊ ነው የምለው ለዚህ ነው። አንዳንዶቹ ሕገመንግሥቱን አንቃወማለን ሲሉ ከርመው ለፋሺሰቶቹ ሕገ መንግት ታዛዥነታቸው በምሃላ አረጋግጠው ፓርላማ / የሞት ሞታቸው አየንላቸው። እስርቤት ያሉትን እነ እስክንድርን ጋር አነጻጽርዋቸው እና የመንፈስ ሞት እና የመንፈስ ጥንካሬ ልዩነቱን እዩልኝ።

ለብዙ አመት ስቃወመው የነበረው አንድ እዚህ ውጭ አገር ኗሪ የሆነ ምሁር ተብየ ግለሰብ ስለጻፈው የምሁር መንፈስ ሞት ምን እንደሚመስል እኔ እና ወዳጄ አብረን ስለዚህ ምሁር ቀደም ብለን የተቸንበትን ላሳያችሁና ልደምድም።

ዶክተር አቢይ አመድ 3 ዓመት በዓለ ሢመት (ባለፈው ሰሞን የተደረገውሢመትሳይሆን አምና ስላከበረው ነው እያወራሁ ያለሁት) ሊያከብር ጉድ ጉዱ መጧጧፉን በሚዲያ እየሰማን ነው፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ አሳፋሪነቱን ማስረዳት እችላለሁ፡፡ የዚህ ሰውዬ ነገር እጅጉን የሚደነቅ ነው፡፡ የከበቡትም አሻንጉሊቶች እንጂ ሰዎች አይመስሉኝም፡፡

“We are blessed to have a fair and gracious foreman during this transition from chaos to order. The last three difficult years, Dr. Abiy Ahmed has proven he is a born leader. No one would have predicted such a beautiful flower to bloom from Woyane’s toxic garden.”

“The sun is rising over Ethiopia.” (Yilma Bekele)

ልተርጉመው ይሆን? እስኪ ልሞክረው፡-

ከዚህ ካለንበት ሥርዓት አልበኝነት ወደ ሥርዓታዊ ሀገራዊ ኑባሬ ሊያሸጋግረን የሚችል ዶክተር አቢይን የመሰለ ፍትኅ ዐዋቂና ግርማ ሞገሱ የሚያርድ አሻጋሪ ማግኘታችን በውነቱ መባረክ ነው፡፡ ያለፉት ሦስት አስቸጋሪ ዓመታት ዶክተር አቢይ ሙሤያዊ አሻጋሪነቱን አረጋግጠውልናል፡፡ እንዲህ ዓይነት በውብ አበባ ሊመሰል የሚችል ድንቅ ዜጋ በወያኔ መርዛማ ማሕጸን ውስጥ ሊፈጠር ይችላል ብሎ ቀድሞ የገመተ ሰው አልነበረም፡፡

በኢትዮጵያ ፀሐይ እየወጣች ነው” (ይልማ በቀለ)

እንደዚህ ያሉ ምሁራን ያሉባት አገር አምባገነኖች እንዴት ሊወገዱ ይችላሉ? በምን ቢገለጹ ይገልጻቸዋል? አብይ አሕመድ በሚያስተዳድረውክልልእናድርጅትበአማራ ማሕበረሰብ ላይ እየደረሰበት ያለው የዘር ግድያ እና መፈናቀል እነዚህ ምሁራን የሚመለከቱትሙሤያዊ ሽግግርበማለት የተረጉሙታል። እነዚህ ምሁራን የመንፈስ ሞት ከሞቱ ቆይተዋል እናፈርሰው ካልተሰሩ ሀገር አትኖረንም፡፡ ለዚህ ነው ናይጄሪያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥም የፖለቲካ ልሂቃን የመንፈስ ሞት ስለሞቱ በጅምላ እንዲቀበሩ ጥሪ የማቀርበው። ካልሆነ በአህጉሪቱ ያሉ አብዛኛዎቹ መሪዎች በኃይለኛ እና በፓራክያል (አባታዊ) አማልክት  እና ጎድ ፋዘርአባቶች ቁጥጥር ሥር  የተጋለጡ እንደሆኑ ይቀጥላሉ።

ሼር በማድረግ ሕዝቡን አስተምሩተሩ። መረጃ ከጥይት ባሩድ በላይ ነው።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ