Wednesday, July 17, 2024

የኅብረት ምስል የሌለው ቅዠት ውሰጥ የገባው የአማራ ብሔረተኛነት! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay


የኅብረት ምስል የሌለው ቅዠት ውሰጥ የገባው የአማራ ብሔረተኛነት!

ጌታቸው ረዳ 

Ethiopian Semay

ዛሬ ስለ አማራና ትግሬ ጽንፈኛ ብሔረተኛነት በመጠኑ እንመለከታለን፡፡ ፋኖ በጎጠኛነት ሕመም እየተበጠበጠ ነው፡፡ እባካችሁ የፋኖ አለመጣጣም አታባብሱት አትተቹ የሚሉ ቀና ሰዎችና የሚዲያ ሰዎች አድምጫለሁ፡፡ መስመራቸው ቀና ነው፤ ግን ጽንፍኞችና የኅብረት አፈንጋጮችን ግን መሰምራዊ ተክለ ሰውነታቸውን (የጎጃሙ ዘመነ ካሴ ከእስክንድር ጋር  አይዲኦሎጂ ልዩነት አለኝ ሰለሚለው <<ምናልባትም ጎጃሜ የሚመራው የሃገረ አማራ ምስረታ (?)>> መተቸቱ ትግሉ ጥራት እንዲኖሮው ይረዳል (ለምሳሌ የጎጃሙ ማርሸት ጸሃየ የመሰለ እጅግ አደገኛ አጨበርባሪ ወጣት ከአለቃው ዘመነ ጋር አብሮ መተቸት  ያሰፈለጋል)፡፡

ዘመነ ካሴ ስለ አማራ አንድነት ሲዲሰኩር እንጂ በተግባር ሲፈተሽ ሙሾ ነው፡፡ የደብረማረቆሰ ወጣቶች ሰብስቦአማራ! አማራ! ! አማራ!.” እያለ ሲጠራቸው ምነው ድምጻችሁ ዝቅ አለ? እያለ በአማራነታቸው እንዲኮሩ ሲያጽናናቸው ሰለ አንድነት የተናገረውን

ላስታወሳችሁ፤ እንዲህ ይላል፤

<< ከተከበብንበት ከበባ ሰብረን ስንወጣ ፤በጋራ እንስራ ሲባል ስንጀምርና በመካከላችን ያለው ስንጥቅ ሊደፈን ሲመስላቸው አብይ በፈጥነት ብርሃኑ ነጋን ወደ ባሕርዳር ላከው፡፡ አልተሳካም! አልተሳካም! (ወጣቱ ይደገም እያለ ጮኽ)፡፡ ሲነኩኝ አልወድም ፤ምክንቱም አማራ ነኝ!>> አማራዎች ነን ሰው እንወዳለን በፍቅር ከመጡ አማራዎች ሰለሆንን ልብሳቸውንም ቢሆን አጥበን መሰጠት እንችላለን በፀብ ከመጡ ግን  ሱሪያቸው ላይ እናሸናቸዋለን>>፡፡

ይላል ዘመነ፡፡ 3 ነጥቦች አነሳለሁ፡፡ 2ኛው ልጀምር፡

 (2) ሲነኩኝ አልወድም ፤ምክንቱም አማራ ነኝ!>> የላል፡፡ ሲነኩት ማንም ፍጡር (እንሥሣም ሲነካኩት አይወድም) ለአማራ ብቻ የተሰጠ ባሕሪ አይደለም (የዘመነ አባባል ለራሱ እና ለጥቂት አርበኞች እንጂ ውርደትን እንደ ባህል የሚቀበል የዛሬ ኢትዮጵያዊውን ወጣት አማራን አይመለከትም፡፡ ሲነኩት የማይጥመው የድሮው ኢትዮጵያዊ አማራ የታየ ባሕሪ ነው) ዘመነ እንደ ግለሰብ ያንን የአትንኩኝ ኢትዮጵያዊነት ባሕሪ  ይላበሳል ብየ ባምንም በእርሱ እድሜ ያሉት ወያነ ክመጣ ጀምሮ (36 አመት) ያለው ኢትዮጵያዊ ወጣት ግን ውርደት ተከናናቢና ቀልድ እያሳመረ፤ ጫት እየቃመ፤ ተመችቶት ተገዝቶ ለጥ ብሎ የሚተኛማፍርያ ነው፡፡በዚህ ጉዳይ ዘመነ ካሴ አሁን ካለው ወጣት በደፋርነቱ እመሰክርለታለሁ፡፡

( 3ኛው) - <<አማራዎች ነን ሰው እንወዳለን በፍቅር ከመጡ አማራዎች ሰለሆንን ልብሳቸውንም ቢሆን አጥበን መሰጠት እንችላለን : በፀብ ከመጡ ግን  ሱሪያቸው ላይ እናሸናቸዋለን>>፡፡

ሰለሚለው በጎነት ግን ለባእድ ካለሆነ በሽምግልናም ይሁን በተነኮል ተከብቦ እጁ ሰጥቶ እስር ገብቶ በነበረበት ወቅት የትግል ወንድሜ ታስሮ ትግሉን መኮላሸት የለበትም ብሎ ሰውነቱ ከስቶ (የዘመነ ተላላኪ የነበረው ስድ አደግ ባለ ማርሸት ፀሃየ እስክንድርን  አንጋሬ ብሎ እስኪዘልፍው ድረስ) ትግሉን ያቀጣጠለለት በፀብ ያልመጣበትን አርበኛው ታላቁ እስክንድርን ግን የጎጃም ምድር ለጎጃሜዎች በሚል ውሰጠ ሴራ (ወያ ኢሕአፓን ትግራይ ምድር እንዳደረገው ጎጠኛነት) ባይተዋርነት እስኪሰማው ድረስ ገፈትሮ ወደ ክፈለሃገርህ ወደ ሸዋ ሂድ ብሎ ገፈተረው፡፡ ወሎም ሊቆይ አልፈለገም (መገመት ትችላላችሁ) አየሩ መደሩ ሁሉ ጎጥ፤ ጎጥ ስለሸተተው፡ ሰለሆነም ወደ ተወለድ ቦታው "ሸዋ" መጣ፡፡ ይህ ነው በቃ! በታላቁ እስክንድር የዘመነ ጎጠኛ ጎጃሜነት እርምጃውን ነው በጣሙኑ አንጀቴን ያቃጠለው!!

ወደ አንደኛው (1) በተግባር የማይተረጎም ስለ አንድነት  ንግግሩን እንመልከት፤

<<ከተከበብንበት ከበባ ሰብረን ስንወጣ ፤በጋራ እንስራ ሲባል ስንጀምርና በመካከላችን ያለው ስንጥቅ ሊደፈን ሲመስላቸው አብይ በፈጥነት ብርሃኑ ነጋን ባሕርዳር ላከው፡፡ አልተሳካም! አልተሳካም!>> ይላል፡፡

<<<<ከተከበብንበት ከበባ ሰብረን እንውጣ ፤በጋራ እንስራ ብሎ ያለውንና እስክንድርና መሰል የትግል ወንድሞቹ ትግሉ ባንድ የተቀናጀ እዝ እንምራው ማለት ሲጀምሩ የሸሸውና መሪነቱ ለኛ ከልተሰጠ የአዲዮሎጂ ልዩነት አለን ብሎ ካንድነቱ የሸሸ ማን ነው? እራሱ በጥራቃው ዘመነ ሆኖ ተገኝ፡፡

ጎጃሜዎች የተዋጣላቸው የሊቃውንት ምድር እንጂ የተናጋሪዎች ምድር አይደለም፡ ዘመነ ግን እንደ ወሎ አማራዎቹ ጎጃሜ ሆኖ እነሱን የሚያስገነዳ ጥሩ የተዋጣለት ማራኪ ተናጋሪ ነው፡፡ ችግሩ አንድነት ሲባል በተግባር ግን የመንግሥቱ ሃይለማርያም ቃል ልዋስናሙሾ ነው!”

በዚህ የሚጥማችሁና የማይጥማችሁ ሰለምትኖሩ፤ ትግሬ ነህና በኛ ጉዳይ አያገባህም ስትሉኝ 25 አመት ያደከማቸሁኝ ዛሬም በለመደባችሁ ዘረኛ ባሕሪያችሁ ብትቃጠሉም ካልደፈረሰ አይጠራምነውና መቻል ነው)፡፡

ያም ሆኖ አማራዎቹ በባሕሪ ትግሬዎች በቀየሱላቸው ጎዳና እየተራመዱ ይመስላሉ፡፡ የትግሬዎች ፋሺዝም ለዘመናት የተቸንበት ስለሆነ ብዙ አልሄድበትም አንድ አዲሰ አሰገራሚ ክስተት ግን ከታች በማስረጃ ሰነድ እናያለን፡፡

  ሰለ አማራው ሳልተች እስኪ ይስተካከል ይሆን እያልኩ እሰካሁን ታግሸው የነበረው የአማራው ብሔረተኛ መናገር መጀመር የግድ ሆኖብኛል፡፡ ቢጎመዘዛችሁም እውነታው የአማራ ብሔረተኛነት ወደ ፋሺዝም እየተንደረደረ ነው(if not already) ነውና አጢኑት፡፡

ትግሬዎችን ያየሁበት ለብዙ አመታት ያጠናሁት/ትዝብት አማራው ላይየትሬዎችን ፋሺዝም ለመወዳደር ቡቃያውእየበቀለ እያየሁ ነው፡፡ይህ ደግሞ ጸረ አማራዎችን እያስደሰተና እየተቀባበሉት ነው፡፡ ወይኔዎችና ኦሮሙማ ኦነጎች ፋኖን በመደገፍ ወደ ብሔረተኛነት እንዲገቡ ድጋፍ እየሰጡ ነው፡፡ ለምን? ኢትዮጵያን የመገነጣጠል አመቺው ጎዳና ሰለሆነላቸው፡፡ ቢሆንም፤ መረን ሳይለቅ እንደ ትግሬዎቹ ከመሆናችሁ በፊት መስመራችሁን አስተካክሉና አማራውን ባንድነት ታደጉት ለማለት ወቅቱ አሁን ነው፡፡ ሰዎች ቢተችዋቸሁ ለምን ተተችን የሚል አንስታችሁ ትችቱን ለምን እንደተሰነዘረ ማጣራት አለባችሁ፡፡  

እዚህ ትችት ውስጥ አማራውን ስተች የምትቁነጠነጡ ትኖራላችሁ (እርግጠኛ ነኝ) ማውቅ ያለባችሁ እኔ የተገኘሁበት ማኅበረሰብ ትግራይ ለዘመናት ስተች ሰታንጨበጭቡልኝ የነበራችሁ አሁን የናንተ ወገን የሆነው አማራ ስተች እንደምትጮሁብኝ አውቃለሁ (ካሁን በፊት አይቻችሃለሁና) እየመረራችሁም ቢሆን ድከመታቸሁን ዋጡ፡፡

ለብዙ አመታት አማራ ከደረሰበት ጥቃት ለመከላከል ጫካ መግባት እንዳለበት ከማናቸውም ጸሃፊዎቸና ተቺዎች በፊት ስጽፍና ስመክር ነበር (ተከታታዮቼ ታሰታወሱኛላቸሁ) አለመታደል አማራ በማንነቱ እየተገደለና እየተዋረደ እያለ ወጣቱና ምሁሩ አማራ ግን የሰው ተቺዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆኖው ግማሹ የወያኔ ደጋፊ በመሆን የወያኔ እሳት ማሞቂያ ምድጃ ሲሆን፤ እንደ እነ ዘመነ ካሴ የመሳስሉ ደግሞ የጸረ አማራዎቹ የእነ ኤፍሬም ማዴቦ ቃል አቀባይና ተላላኪ ሆኖ አማራውን ሲያሰድብ ነበር፡፡

ብሔረተኛነት አደጋ አለው፡፡ የአማራው ትግል የጠበቅነውና የመከርናቸውም በተለይ አማራውን በመምከር ግምባር ቀደም የነበርነው እኔና ወዳጄ / አሰፋ ነጋሽ አማራው የብሔረተኛነት ትግል እንዲያካሂድ ሳይሆን የወያኔ እና  የኦሮሙማው አቀንቃኝ የፋሺስቱ አብይ አሕመድና መሰል ኦነጎች እያደረሱት ያሉትን ጭፍጨፋ፤ አድልዎ ግፍና በደልን ማስቆምና ማስቆም ነበር እንጂ፡ አማራው እንደ ትግራይ በጠባብ ብሔረተኛነት ገመድ ራሱን እየጎተተ እርስ በርስ እንዲዘላለፍና እንዲገዳደል አልነበረም፡፡ ሆኖም አሁን አማራ ፋኖ አመራር ውስጥ እና በየማሕበራዊ መገናኛ መስመሮች የሚነገሩና የሚሰነዘሩ ቅሰቀሳዎችና ቃላቶች እያየነው ያለው የፋሺዝም ባሕሪ አቆጥቁጦ መታየት መጀመሩ ነው፡፡

ይህንን ላለመቀበል ያዳገታቸሁ ካላችሁ ተቀበሉ ስንላቸው ሲስያሰቸግሩን የነበሩት ትግሬዎችና ኤርትራኖች መጨረሻቸው ሲያዩ ምን እንደሆኑ መመልከት ነው፡፡ 

የጎጃሙ ተበጥራቂ  ዓለም የሸለመው እስክንድር ነጋን የመሰለ ከላሲክ (ኦሪታዊ) ኢትዮያዊ ከጎጃም ገፍትሮ ወደ ትውልድ ክፍለሃገሩ ወደ ሸዋ እንዲጠለል ሲያደረገው ቢያንስ ቀና አማራዎች ይቃወማሉ ብየ ስጠብቅጭጭነበር ያሉት፡፡ የህ አደገኛ ወጣት ደንቃራ ፋሺስታዊና ትምክሕታዊ ባህሪ እየተላበሰ መምጣቱ ክሚሰነዝራቸው ቃላቶች ለብዙ ወቅት ብታዘበውም ምናልባት አማራዎቹ ራሳቸው ያርሙት ይሆናል ስል ምንም አላየሁም፡፡ አሁን ብሶበት ኢትዮጵያዊው ማንዴላችንን እስክንድርን ለማሰኮንመን በመጣር ትግሉ አማራን ማዳን ሳይሆንጎጃማዊ ብሔርተኛነትንማቀንቀን ቀዳሚ መንገድ ተጠርጎ አያየነ ነው፡፡

ያለህን ይመስልሃል ተበልተህ አልቀሃል የተባለው ካልገባችሁ ትግሬዎች በገሃድ ከኢትዮጵያ ከተገነጠሉ 6 አመታቸው ተገንጠለዋል እያልኩ ብዙ ብያለሁ፤ ያመነኝ ፖለቲከኛ ተንታኝና ሚዲያ የለም፡፡ በዚህ ወቅት አማራው ምን ለመሆን እየጣረ እንደሆነ አልገባኝም፡፡

ትግሬዎች አሁን ያሉበት ሁኔታ እንደ ኤርትራኖች አመች ወቅት ሲያገኙ ተገንጥለው አገር ለመመስረት ነው እየተዘጋጁ ያሉት (ወልቃይትና ራያ ለዚያ ግብ ነው እየሞቱለት ያሉት)፡፡

በዙዎቹ ኢትዮጵያና ምንሊክን እየሰደቡ አዲሰ አበባ ቁጭ ብለው ኢትዮጵያን ጠላታችን ነች የሚሉ እንደ እነ ጮርቃው መዘክር አባዲና (አከሱማዊ) የታሪክ መምህር የሆነው የሳልሳይ ወያኔ መሃንዲስ ጽንፈኛው ተሰፋኪሮስ (እንደርታዊ) ወዘተ፣የመሳሰሉ የአገሪቱን ወተት እየጠቡ ደሞዝና ምቾት እየሰጠቻቸው ስዋን ተመልሰው ለማፍረስ ስይተኙ የሚያድሩ አደገኛ የትግራይ ፋሺስቶች አዲሰ አበባ ወሰጥ አሉ፡፡ አማራዎች ደግሞ በጎጥ ይራኮታሉ፡፡

እድሜ ለኦሮሙማው ፋሺስቱ አብይ አሕመድ ትግራይ ወሰጥም መላው የወያ አመራርና ጀሌ ለትግራይ ግንጠላ እየሰራ ሙሉ ደሞዝና መኪና ተስጥቶአቸው ለመጻኢት ሃገራቸው በአገራችን ሃብት እየገነቡ ነው፡፡ ሠራዊቱን በመጨፈጨፋና በመግደል ሲሳተፉ የነበሩት መምህራንም ሆኑ ሃኪሞችና ሠራተኞች ጫካ ሆነው (TDF ተብለው) ሰው ሲገድሉ የነበሩበትን አንድ/ሁለት አመታትና ወራቶች (ባክ ፐይ / back pay) ተቆጥሮላቸውየተከማቸ ደሞዝእዲከፈላቸው ተደርጓል፡፡ (ሲገድልዋት የነበሩትን ደሞዝ የምትከፍልና የምታስጠልል የምትገርም አገር ማለት አገራችን ኢትዮጵያ ነች) አሁንም የምትሰደብበትና ሰለ ግንጠላ የሚደሰኮርባቸው ቲቪና ራዲዮጣቢያዎች ደሞዝ እየከፈለቻቸው ትገኛለች (አናረኪና መሪ አልባ አገር ማለት ይህ ነው)፡፡ 

ትግራይ ውሰጥ ለምልክትም ለማሞኝትም ቢሆን  የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አንዲትም ብጫቂ ሰንደቅ አላማ የትም ሰትውለበለብ አታዩም፡፡

የተገነጠሉት ፋሺስታዊ ቀሳውስቶችና ጳጳሳት ተብየዎችም፤ የኢትዮጵያ ብር፤ ባንክ፤ ቴለፎን፤ መገናኛና ነዳጅ እየተገለገሉ ኢትዮጵያ አገራችን አይደለቺም ብለው ክደተዋታል፡፡ የምትገርም መሪ ያጣች አገር !

 እንዳውም ሰሞኑን ለትግራይ ቀሳወሰቶችና ጳጳሳት (ተብየዎች) መገንጠል ያመቻቸላቸው አደገኛው አጭበርባሪውና ወንጀለኛው በጌታቸው ረዳ ሥር የሚታዘዘው የአክሱም አሰተዳደር የሕዝብ ግንኙነት /ቤትጎንደር ላይ 4 ቢሊዮን ብር የቅዱስ ያሬድ ገዳምለማሰራት የታቀደው እቅድ በመቃወም በትግርኛ ያወጣው መግለጫ ወደ አማርኛ ልተርጉምላችሁና ፋሺዝም ተንሰራፍቶ አገር እየሆነ እንደሆነ ላሳያቸሁና ትግሬ የሁሉም ነገር ፈጣሪና የአከሱም መስራች ሃይማኖትና ገዳማት ፈቃጅና ከልካይ ፤ብቸኛ ባለቤት ነኝ ሲል የአማራው ፋሺዝም ደግሞ ያንን ባሕሪ ተመሳሳይነት እየደገመው እንደሆነ ከታች ሁለቱም ጽንፈኛ አማራዎችና ጽንፈኛ ትግሬይዎቹ የሚዘምሩትና የሚደሰኩሩት ተመሳሳይነት አሳይቼ እደመደማለሁ፡፡

ልጥቀስ፡

ትግርኛ

<<Axum town communications affairs office

ዘይናትካ ጉሕለት ደው ይበል!!

ሎሚ አብ ጎንደር 4 ቢሊዮን ብር ገዳም ቅዱስ ያሬድ  ኢሉ ኽህነፅ አማራ ኮምኒኬሽን አውፂእዎ ዘሎ ዜና ዝቀፀለ  ኣካል ናይቲ ዝነበረ ናይ ህዝቢ ትግራይ መንነትን ታሪኽን ስርቂ  ዝተለመደ ስለዝኾነ እዚ ዘይናትካ ዘይምልከተካ ናይ መንነት ጉሕለት ፍፁም ተቀባልነት ሰለዘየብሉ ማሕበረሰብ ዓለም ብጋንኡ ኽፈልጦ ኽንሰርሕ ይግባእ!!

ሓበሬታን ርክብን ከተማ ኣኽሱም

7 ሓምለ 2016 / ኣኽሱም>>

ወደ አማርኛ  ልተርጉምላችሁ

Axum town communications affairs office

የራስ ያልሆነ የኔ ነው የሚል ሌብነት የቁም!!

ዛሬ ጎንደር ላይ 4 ቢሊዮን ብር የቅዱሰ ያሬድ ገዳም ለማስራት የአማራ ኮሚዩኒከሽን ቢሮ አውጥቶት ያለው ዜና የሚያሳየን ቀደም ብለው ማራዎች ሲያደርጉት የነበረው የቆየ ስርቆታቸው ታሪካችንን የመሰረቅ ልምድ ስለሆነ ለትግራይ ብቻ የተፈጠረ የራሳችን የሆነው ቅዱስ ሬድ፤ አማራ የራሱ ያልሆነውን የማንነት ስርቆት እየፈጸመ ያለው ፍጹም ተቀባይነት ሰለሌለው የዓለም ማሕበረሰብ በትኩሱ እንዲያውቀው ማድረግ ይገባናል፡፡

የአክሱም ከተማ የመረጃና የመገናኛ / ቤት 7 ሐምሌ 2016 / አከሱም)>> ይላል የመግለጫው ዋና ይዘት ሲተነተን ፡፡

ከላይ ያነበባችሁት ከሶረያኖችና ከግብጽ የተቀዳው የገዳማትና የቤክርስትያናትን የማሳነጽ ልምድ ገዳማትና ቤክርስትያናትን ማነጽ ለትግሬ ብቻ እንደተፈቀደና እንደፈለሰፉት አድርጎ በመቃዠት አከሱሞች አላስቀምጥ አላስቆም ሲሉት ያሬድ አከሱም ለቅቆ ወደ ጎንደር በመሄድ ሲያሰተምርበትና አንዳንድ የቅድስና ትምሕርቶችን የፈጠረበት  ቅዱስ ገላው በቅዱስ መሬት የተቀበረበትን መሬት ጎንደር ለቅዱስነቱ ማስታወሻ ገዳም መስራቱን በመቃወም ሁሉም ነገር የኔ ( ኦሮሞዎችም የግብጽ ፒራሚድም ኬኛ ) እንደሚሉት ሁሉ  ናዚያዊ የትግሬ ድንቁርና ደግሞ ትግራይ ውስጥ የተቀበሩት ሶርያውያኖች (ተስዓቱ ቀዱሳን) ገዳም ሲኖራቸው ቅዱስ ያሬድ በገዛ አገሩ ገላው የተቀበረበት (ይተሰወረበት) ጎንደር አፈር ላይ መታሰብያ ገዳም አይሰራም  ካለ ትግሬ በቀር ኦርቶዶከስ  የለም፤ ክትግሬ በቀር ማንም ክርስትያናዊ ሕዝብ የቅዱሳን መታሰቢያ ቤተ ጸሎት እንዳይሰራ የሚያዝ ይፋ የሆነ በአከሱም ከተማ ሕዝብ ሥም  መግለጫ ሲወጣ ትግሬ ፋሺስቶች ድንቁርና እና ትምክሕት አሰገራሚ “Collective narcissism” (የጋራ እብደት) ስንመለከት፡ በዚህ ትይዩ አማራው ደግሞ የትግራይን ፋሺዝም እየተላበሰ መምጣቱን ላሳያቸሁ፡፡

 ጥንተ አከሱም ምስራ  ከአገር በፊት አገር የሆንን፤ የዳ'ማኣት ባላሻራ  የአክሱም ዙፋን አልጋ ወራሽ  ቅድመ-ዓለም መንግሥት ወጣኝ  ቅድመ-ዓለም ጥበብ ጠንሳሽ ... ወዘተ... የሚል ሁሉም የኛ ( ኬኛ ) ሲዘምሩት ያለ ሰቀቀን በየሚዲያው ሲያሰተጋቡት፤በየ አዳራሹ የንግግር መክፈቻ ሆኖ መስማት ፋሺዝም አማራ ውስጥ ባጭር ወቅት እንዳቆጠቆጠ ላሳያችሁና ልሰናበት፡፡

አማራዊ ፋሺስታዊነት የተላበሰ መዝሙር ደግሞ እንዲህ ይላል፡

ዐማራ ነን፤ ዐምሐራ ነን!

የዳ'ማኣት ባላሻራ፣

የአክሱም ዙፋን አልጋ ወራሽ፣

ቅድመ-ዓለም መንግሥት ወጣኝ

ቅድመ-ዓለም ጥበብ ጠንሳሽ፤

ዐማራ ነን ሥልጡን ሕዝቦች

የሐ፣ ሮሐን የተጠበብን

ሐውልት ያቆምን መቅደስ ያነጽን፣

ድንጋይ ፈልጠን ዐለት ጠርበን።

*

የጊዮን ባለጸጎች፣

የቤተ ዐማራ ባለ 'ርስቶች፣

ከአገር በፊት አገር የሆንን፣

የኢትዮጵያ መሥራች ሕዝቦች

ዐማራ ነን ነባር ሕዝቦች፣

ባለ ታሪክ ባለ ገድል፣

ጊዜ አቅንቶን የማንበድል፣

ዘመን ገፍቶን የማንጎድል። (2x)

*

በተፈጥሮ ኩል የደመቅን

የውብ ሕዝቦች ቤተ-ተውኔት፣

ዐማራ ነን ለጋስ ሕዝቦች፣

በፍቅር የኖርን በቼርነት፤

በእምነት በግብር የታነጽን

ፍትሐዊ ፍርድ አዋቂ

በአበው ቁና ግፍ ሰፋሪ፣

በአበው ስሪት ደም አድራቂ

ዐማራ ነን ነባር ሕዝቦች

ባለ ታሪክ ባለ ገድል፣

ጊዜ አቅንቶን የማንበድል፣

ዘመን ገፍቶን የማንጎድል።

*

እንደ ንብ አብረን የታተርን፣

እንደ አንበሳ የተከባበርን፤

ጊዜ አቅንቶን የማንበድል፣

ዘመን ገፍቶን የማንጎድል።

*

በተፈጥሮ ኩል የደመቅን

የውብ ሕዝቦች ቤተ-ተውኔት፣

ዐማራ ነን ለጋስ ሕዝቦች፣

በፍቅር የኖርን በቼርነት፤

በእምነት በግብር የታነጽን

ፍትሐዊ ፍርድ አዋቂ

በአበው ቁና ግፍ ሰፋሪ፣

በአበው ስሪት ደም አድራቂ

ዐማራ ነን ነባር ሕዝቦች

ባለ ታሪክ ባለ ገድል፣

ጊዜ አቅንቶን የማንበድል፣

ዘመን ገፍቶን የማንጎድል።

*

እንደ ንብ አብረን የታተርን፣

እንደ አንበሳ የተከባበርን፤///>>

የኅብረት ምስል የሌለው ቅዠት ውሰጥ የገባው የአማራ ብሔረተኛነት እውን እንደ ንብ አብሮ እየታተረ፣ እንደ አንበሳ እየተከባበረ ነውን? መልሱ ላንባቢዎች ልተው፡፡

በሰላም እንሰንብት!

ጌታቸው ረዳ