Tuesday, June 27, 2023

ይህንን ጥንታዊ ሕዝብ ለምን ከምድረገጽ ሊያጠፉት ፈለጉ? ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/27/23


ይህንን ጥንታዊ ሕዝብ ለምን ከምድረገጽ ሊያጠፉት ፈለጉ?

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/27/23

ከአውሮጳ ስመለስ አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር የሆነ ወዳጄ በአንድ ጽሑፌ ላይ “ወያኔዎችና ኦነጎች እንዲሁም አክራሪ እስላም ኢትዮጵያዊያኖች አሁን እየተከተሉት ያለው የክልል/የቋንቋ/የሃይማኖት/ አስተዳዳር ፋሺሰት ጣሊያን በኢትዮጵያ ስያስተዳዳርበት የነበረው  የተቀዳ አስተዳዳር ነው” የሚለው ባንድ ድረገጽ የጻፍኩትን የቆየ ጽሑፌ ሲመለከተው ግራ ገብቶት “ይህንን አላውቅም ነበር፤ የመጀመሪያ ጆሮየ ነውና ማስረጃውን ላክልኝ” ብሎኝ እኔም በጠየቀኝ መሰረት አማዞን የመጽሐፍት መሸጫ መደብር ጣሊያናዊው “ፕሮፌሰር አልቤርቶ ሰባኪ” (1985) የጻፈውን መጽሐፍ ገዝተህ አንብብ ብየው፤ ያንብበው አያንብበው ባላውቅም ብዙዎቻችሁ ወጣቶች ይህንን መጽሐፍ ስትመለከቱት ወያኔ በሕገመንግሥቱ ያሰፈረው የህንኑ የጣሊያኖች አስተዳዳራዊ ስልት ነበር።

ያ መጽሐፍ የሚነግረን ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ጣሊያን አማራውን ማሕበረሰብ ካላጠፋ ኢትዮጵያን ለረዢም ጊዜ መያዝ እንደማይቻል ይናገራል። ይህ ብቻ ሳይሆን ጀርመኖችም ኢትዮጵያን አፍርሶ የምስራቅ አፍሪካ “ኢምፓየር” ለመዘርጋት መጀመሪያ አገር ዳሳሽ የነበረው “ቄሱ/ፓስተር/”  Rev. Dr.J.Lewis Krapf በወቅቱ በታሪክ ጸሐፍት  “ጋላ” በመባል ሲታወቅ የነበረውን ማሕበረሰብ በፕሮተስታንት ሃይማኖት አስጠምቀህ በመያዝ ጅርመናዊ አምላኪ ማድረግና ሰማቸውን በመሰየም “በላቲን ፊደል” እንዲጽፍ ማድረግና በምፅዋ በኩል አድርጌ በ1836 ወደ ኢትዮጵያ ገብቼ የመጀመሪያው ስልት የተጠቀምኩት መጽሐፍ ቅዱስን ጋልኛን በላቲን እንዲጽፉና እንዲያኑ ማድረግ ነበረብኝ ይህንንም አድርጌአለሁ በማለት “የሃይማኖት ሰባኪ” መስሎ ስብከቱን ሲጀመር፤ የተናገረውን ከመጽሐፉ ልጥቀስ፡- እንዲህ ይላል፡

“ቋንቋቸውን ተማርኩ፤ ይህንንመ ምስራቅ አፍሪካን ለመግዛት ያመቸናል። የሮማው ሚሺኔሪው ቻይናን ስጡንና ኢስያያን የኛ እናደርጋታለን እንዳለው ሁሉ እኛም ጋላን ስጡንና ምሥራቅ አፍሪካን የኛ ትሆናለች” ሲል Rev. Dr.J.Lewis Krapf በራሱ መጽሐፍ Travels, Researchs and Missionary During Eighteen Years Residence in Eastern Africa” (1960) PP.32”

ጥርስዋን መሾል የማታቆመው የዓረብ አገሮች ማሕበራ አባል የሆነቺው አክራሪዋ ሶማሌም ሆነች ከጥንት ጀምሮ ያልተኙብን አረቦችና በዙርያችን የከበቡንን አክራሪ እስላም አገሮች ሁሉም ያተኮሩት ኢትዮጵያን በመገንባት ቀዳሚ ሚና የተጫወተው አማራው ነው (ይህ ታሪክ ከአክሱም ጀምሮ በተለይ በ12ኛው ክ/ዘመን የተነሳው አማራው ንጉሠ ነገሥት ይኩኖ አምላክ እና ልጆቹና የልጅ ልጅ ልጆቹ….የገነቡዋትን ኢትዮጵያና ገድል ለማወቅ “ሰሎሞናውያን” የሚለው በዶ/ር ደረሰ አየናቸው የተጻፈ አዲስ አስገራሚ መጽሐፍ እንድታነቡ እመክራለሁ። ያንን “ሌጋሲ” በመያዝ ነው አማራንና ኦርቶዶክስን ስታጣፋ አብራ ኢትዮጵያም ትርመሰመሳለች ከሚለው የጣሊያን፤ የጀርመን ፤ የእስላምና የአረብ አገሮች ዕቀድና ትንኮሳ መነሻውና ምንጩ።

በሚገርም ሁኔታ ፤ ጣሊያኖች፤ ጀርመኖች፤እንግሊዞችና እስላማዊና ዓረባዊ አገሮች  ከስንት የዘመናት አዝጋሚ ፍትግያና ጦርነት በመጨረሻ እነዚህ በቪዲዮ የምትመለከትዋቸው “ባለሃገር” ጥንታዊ የእግዚአብሔር ልጆችን ለማሰቃየትና ለማጥፋት በከሃዲዎቹ “የትግራይ፤ ኦሮሞ እና በአክራሪ እስላማዊ ሃይላት” ቡችላዎቻቸው በኩል  ከምድሩና ከሰማዩ ከዳመና እና ከአምላካቸው ጋር ሲነጋጋሩ የሚውሉትን እነዚህ ጥንታዊ ባለሃገሮችን ለማጥፋት ወያኔዎች፤ አብይ አሕመድና ኦነጎች እነኚህን የዋህ ገራገር ጥንታዊ ሕዝብ ለምን እንዲህ ያለ ጭካኔ እየፈጸሙ ከምድረገጽ ሊያጠፉዋቸው ፈለጉ? ምን ዓይነትስ አንጀት ቢኖራቸው ነው? የሚለው ለመመለስ ከባድ ነው።

ይህ ሁሉ ልጽፍ ያስቻለኝ፤ ድንገት “You Tube” ላይ ገብቼ አንድ ነገር ስመለከት በምን ምክንያት እንደሆነ በማላውቀው ጫን ስለው አንጀት የሚበሉ የዋህ የጎጃም ባለሃገሮች እስክስታ ስመለከት ቀልቤን ሳቡኝና በነዚህ “እርግቦች” ላይ የተሳለው የጨካኞች ቢላዋ ሳስበው እንባየ አቀረረ።

 እስኪ የነዚህ ጥንታዊ ባለሃገሮች እስክስታ ካለቀ በላ በመጨረሻው የጨዋታው ማሳረጊያ የሰጡትን የአንድ አረጋዊ አባት እሮሮ አድምጡ “ድሃ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ የሚል አስተዳዳሪ ይስጠን” ይላሉ። አሜን!

ጨረስኩ!

 ጌታቸው ረዳ

ካሲናው ጎጃም | አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) | Aschalew Fetene (Ardi) | New Ethiopian Music 2023 (Official Video)

https://youtu.be/dSh0jJXCd_E