Wednesday, January 18, 2023

ልደቱ አያሌው የታሪክ ከሃዲ ባሕረነጋሽና ኢትዮጵያ! ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 1/18/2023

 

ልደቱ አያሌው የታሪክ ከሃዲ ባሕረነጋሽና ኢትዮጵያ!

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

1/18/2023

ልደቱ ክሕደቱ ሲሉት አላምንም ነበር። አሁን አመንኩ። ሰሞኑን ፖለቲከኛው ልደቱ አያሌው “ኤሪሳት” በሚባል ኤርትራዊ ሚዲያ ላይ ተጋብዞ፤ “ኢትዮጵያ” አገራችንን የጎዳ በሴራና (እነሱ እንደሚሉትም “በጉልበት”) የተገነጠለቺው የኤርትራን “ኢ-ሕጋዊ” ግንጣላ የምንቃወም እኔንም ሆነ ጋዜጠኛ ታምራት እና ብዙ  አገር ወዳድ ዜጎችን ጽንፈኞችአክራሪዎች’ እያለ ሲዘልፈን ውሏል።

ስለ ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ገዢነት በተዛባ መልኩ የተሰበከው ወጣት ‘ኤርትራዊ’ ሄኖክ ተኽለ (ቢጫ) የተባለ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል ልደቱን  ይጠይቀዋል።

“ ….. ስለ ኤርትራ ጉዳይ ሲነሳ ሃይለስለሴ “ኤርትራ መሬትዋ እንጂ ሕዝቡ አያስፈልገኝም” ሲል ነበር… ለምሳሌ አንድ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ኢሳያስ ለኛ ትዮጵያዊያን  ባለውለታችን ነው፤ማመስገን ነው ያለብን፤ አገሪቱ አብሶ  የግል ሃገሩ አድረጓታል፤ ከኛ የሚጠበቀው አሁን የወያኔ ጉዳይ ሰንጨርስ ጥርሳችን እየፋቅን አስመራ መግባት ነው” ብሎ  ተናግሯል። ይህ የታምራት ብቻ ሳይሆን የብዙ ፖለቲከኞች ‘ወያኔም፤ አማራም ወዘተ.. አስተሳብ ነው። ይህ አንተ ምን ይሰማሃል? ምን ትላለህ? “

ሲል የጠየቀው በተለይ “ሃይለስለሴ ኤርትራ መሬትዋ እንጂ ሕዝቡ አያስፈልገኝም” ሲል ነበር…” ሲል የተናገረው የሃሰት ውንጀላ ልደቱ ከማስተባበል ይልቅ አንድም ነገር ሳይል ዝም ብሎ እውነቱነቱን አረጋግጦለታል። ይህ የተደጋገመ ውሸት መምህራኖቹ ሲሉት አደመጠ እንጂ አንድም ማስረጃ ንጉሱ የተናገሩት ቃል ወይንም ሰነድ የለም። ልደቱ ግን ታዘብነው። የልደቱ ጉድና መልስ ገና ነው እንዲህ ይላል፦

የልደቱ መልስ

“ መጀመሪያ የማልስማማው አሁን ያልካቸውን ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ወይ? አዎ አሉ።  ጥርጥር የለውም በጣም ጽንፈኛ የሆኑ  አሁን ባልከው በተዛባ መልኩ የሁለቱም አገሮች ግንኙነት የሚተረጉሙ  ሰዎች አሉ። ታምራት የተናገረው መቶ በመቶ አልስማማም፤ እቃወማለሁ። ግን የታምራት ነገራ ሃሳብ የብዙ የፖለቲካ ሃይሎች አስተሳሰብ ነው የሚለው እኔ አልጋራም። አየህ የጎላ ጽንፍ ሃሳብ የሚይዙ ሰዎች በጎላ ይደመጣሉ። ትኩረት ያገኛሉ። ያ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም የሉም። ብዙ ሰው የሚገዛው አስተሳብም አይመሰስለኝም። ጥቂቶች ግን አሉ። ለወደፊትም ይኖራሉ ብየ ነው እማስበው። በሂደት የሚጠፉ ናቸው ይለናል……ልደቱ

 ፤እንዲህ ሲል፡

 < ለምሳሌ ካርታን ስትመለከት ከኤርትራ ውጪ የማየት ፍላጎት አልነበረም። ለኤርትራ አገርም ሆነ መንግሥት እውቅና ለመስጠት ፍላጎት አልነበረም፡ ለተወሰኑ አመታት፤ በጣም የገነገነ “ረዚዝስታንስ ነበር እምታየው”። ያ ሁሉ በሂደት እየተቀየረ በሂደት መጥቷል። ኤርትራን እንደ ነጻ አገር የማየት ጉዳይ እየጠነከረ መጥቷል። የኢትዮጵያ ካርታ እራሱ ከኤርትራ ውጪ የማየት እየተለመደ መጥቷል። ርያሊቱ እንዳውም የመቀበል ሁኔታ እኔ ባለኝ መረጃ እየጠነከረ መምጣቱ ነው የማውቀው። ግን ያም ሆኖ  ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በጣም ጽንፍ የያዘ የኤርትራን ሕዝብ የነጻ አገርንት ሁኔታ እውቅና መስጠት የማይፈልግ ድሮም አሁንም ወደፊትም እውቅና መስጠት የማይፈልግ “በጉልበት” የኢትዮጵያ አካል ሆና እንድትቀጥል የሚፈልጉ ሰዎች አሉ።እነዚህ ትናንት ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ለወደፊቱም ምናልባትም ነገ ይኖራሉ። የነሱበን አስተሳሰብ የሕብረተሰብ አስተሳሰብ አድርጎ መውሰድ ትክክል አይደለም። ከብዙ የፖለቲካ ሃይሎች ግንኙነት አለኝ ይህ አስተሳሰብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየለዘበ የመጣ አስተሳሰብ ነው። ወደ በጎ አቅጣጫ እየሄደ እንጂ እየጠነከረ አልሄደም። የጥቂቶች አስተሳሰብ ነው።

ልደቱ ክሕደቱ በጉልበት የተወሰደው ሉኣላዊ የኢትዮጵያ መሬት (ሕዝቡ አንፈልግም ካለ የራሱ ጉዳይ ነው- የመሬትን የባህር ጠቀሜታ ግን እንጠይቃለን) በጉልበት እንደተወሰደ ሁሉ እኛም አንደ እስራኤላዊያኑ ጠንካራ መሪ ስናገኝ መጀመሪያ በድርድር ካልሆነ ደግሞ በጉልበት ወደ ድርድር እንዲመጡ የምናደርግ መሆናችንን እያጣጣለ ልደቱ ክሕደቱ እንዲህ ይላል፡-

“ማንንም ሕዝብ በጉልበት ኢትዮጵያዊ ለማድረግ አትችልም። ይኸ የ30 አመቱ ኤርትራ ጦርነት አሳይቶናል፤ኦነግ 50 አመት ጦርነት አሳይቶናል፤ አሁንም ከትግራይ ጋር ያለው ጦርነት እያሳየን ነው፤በጉልበት በሃይል አንድነትን ማስጠበቅ አይቻልም፡…..” እያለ የዲሞክራሲው ጌታ ሲበጠረቅ ውሏል።

በዚችኛዋ አንድ ልበልና ወደ ሌላው ሃሳቡ እገባለሁ።

ልደቱ እያለን ያለው “ጉልበት የመጣ ሁሉ ተምበርክክአችሁ ሁሉንም እሺ በሉ ፤ መጨረሻ ሚሰቶቻችሁም፤ መኖርያ ቤቶቻችሁም ጉልበተኞች ሲመጡ ያለ ድርድር ሌላ አማራጭ የላችሁም፤፡ ስለዚህ ለጉልበተኞች ተገዙ፤ ነው እያለ ያለው። የዚህ ከሃዲ ፖለቲከ ሁሌም ውይይት አንጂ ጉልበት አይሰራም ይላል። ይህ ዓለም ያለ ገንዘብና ያለ ጉልበት የሚገባደድ ፍጹም አንዳች እንደሌለ እናውቃለን።

 ኢሳያስ እንዲህ ይላል።፤ “ነጻነታችን በብር ሰሃን አድርጎ የሰጠን ሰው የለም፤ በጉልበታችን ነጻነታችንን አረጋግጠናል”!!!፡ ብሏል አርሱ በጉልበት ያገኘው እኛ በጉልበት የማናስመልሰው ልደቱ ሊነግረን ይችላል? ወይስ ለጉልበተኛ ተገዙ ነው? ለወያኔ ተምበርከኩ እያለ ሽጉጥ ሲታጠቅ እንደነበረ ሁሉ በዚህ ጉዳይም “ተምበርከኩ” እያለን ነው። ለዚህ ነው እንዲህ ያለ ተምበርካኪ ሰው ሥልጣን እንዳይወጣ መከላከል ያለብን። ክሕደቱ “አንድን ነገር ማግኘት የሚቻለው በዲሞክራሲ ነው’ ይላል። ኤርትራ የነጠቀቺውን ወደባችን “በዲሞክራሲ እናገኘዋለን” እያለ ነው። (ምንም አንኳ ክሕደቱ ስለ ባሕር ጉዳዩ ባይሆንም)። ለዚህ ነው ትውልዱ ኤርትራን ያልጨመረ ካርታ ኢትዮጵያዊያን እንዲለማመዱት ካደረጉት አንዱ ልደቱና ባንዳዎቹ ወያኔዎች በሚሰብኩት የ30 አመት ስብከት ተሳክቶላቸዋል። ሆኖም እርበኞች እስከቀጠሉ ድረስ አንድ ቀን ፡ እስራላዊው “ቤን ጉርዮን” አይነት ኢትዮጵያዊ ይወለዳል።

አዎ ልደቱ  ሕዝቡ ያንተን ባንዳዊ አስተምህሮና የባንዳዎቹ የነ አብይ እና ወያኔዎች ትምህርት ተምሮ ማንነታቸውን 30 አመት ሙሉ ለናንተ ፕሮፓጋንዳ ተሰብኮ ሕዝቡ ተምበርካኪ ሆኗል፤ እንኳን ደስ አለህ!። ለዚህ ነው ጉልበት ተው እያልክ ትውልዱ ዛሬ አዲስ አበቤውም ሌላውም ወጣት ቢረግጡት ቢያስሩት ዝም ብሎ እየተምበረከከ እየተገዛ ያለው። ኤርትራ ሁለት የባሕር ወደባችንን ይዛ መኖር ኢትዮጵያ  ሕዝብ ፍላጎት ነው ብሎ ሲሰብክ መስማት ያማል።

ከሃዲው ልደቱ የቀረው ዓሰብ  ዓሰብ የሚሉ “የነፍጠኖች” ቡድኖች ናቸው ማለት ነው የቀረው እንጂ “እነዚህን ትንሽ አክራሪ፤ ጽንፍኛ ሃይሎች” እያለ ዘልፎናል (አክራሪና ጽንፈኛ ማለት “ሽብርተኛ ዘረኛ..” ማለት ነው ።  እኛም “ልደቱ ክሕደቱ” ተብሎ የተሰየመበትን ስም አጽድቀንለታል። እንግዲህ “አላርፍ ያለች ጣት”

ሁሉም ነገር “ዲሞክራሲ” ያመጣልናል የሚለው በቅዠት  ፖለቲካ እየዋኘ ያለው “ልደቱ” እስኪ ስለ ኤርትራ ፌደሬሽንና ኢትዮጵያ አንድ ነገር ልበለው። ልደቱ የምለው ነገር “ያንተን ተምበርካኪነት አይተናል። እኛ ግን ያልተዘጋ ፋይል አለን እና ያ ያልተዘጋ ጉዳታችን በሕግ ወይንም በጉልበት እንዲደመጥ አናደርጋለን” ነው የኛ ስሞታና ቀጣይ የወላጆቻችን እየጮኸ ያለው የደም ድምጽ ላለማራከስ እየታገልን ያለነው።

ስለ ኤርትራ ጉዳይ የተለያዩ አስተያየቶች እና አመለካከቶች ያላቸው ምሁራን እና የታሪክ ምሁራን በሰፊው ጽፈዋል። ምንም እንኳን ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉት ሥራዎች የመገንጠል አራማጆች የሆኑ እና በአብዛኛው ከፕሮፓጋንዳ የማይበልጡ ቢሆኑም፣ ተጨባጭና ሚዛናዊ የሆኑ በጣም ጥሩና ትኩረት የሚሹ ሥራዎችም አሉ። ልደቱ አያሌው በእነሱ በኩል ለመፈተሽ ጊዜ እና ትዕግስት ካለው ፣ ያለፈውን እና የአሁኑን የኤርትራ ችግር ለመረዳት የሚያስችል በቂ ቁሳቁስ አለ። ኤርትራ ዛሬ ያለችበት አዘቅት (ኳግማየር) በ40ዎቹ፣ 50ዎቹ እና 60ዎቹ ውስጥ ከተከሰቱት ሁኔታዎች እና የንቅናቄው አባቶች ካነሷቸው ርዕዮተ ዓለማዊ እምነቶች ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።

የሻዕቢያና  የወያኔ ታሪክ ጸሃፊዎች የኤርትራ የነጻነት ትግል ‘የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት’ የኤርትራ ውጤት እንደሆነ እየነገሩን ነው። ነገር ግን፣ ችግሩ የውጭ ኃይሎች መፈጠር ብቻ ነበር፣ በተለይም የእንግሊዝ፣ የኢጣሊያ እና የአረቡ ዓለም፣ በአገር ውስጥ ቅጥረኞች የተደገሱ ሴራዎች ናቸው። ጉዳዩ የታሪክ፣ የብሔር እና የሃይማኖት ተፈጥሮን በመፍራትና በመጥላት ጭምር ነበር። እንደ አለመታደል ሆኖ የዛሬዎቹ መመራመር የማይፈልጉ በፕሮፐጋንዳ ሰለባነት በዓይነሰውርነት አብዛኛው ኤርትራዊያን የመሬትንና የህዝብን ታሪክ ለመረዳት ምንም አይነት ጥረት ሳያደርጉ በተለይም በ1940ዎቹ እና 50ዎቹ "ቅጥረኞችና አኩራፊዎች”   በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተደገፈውን ፌደሬሽን በማፍረስ ኤርትራ ከቅኝ ግዛት ገዢዋ ኢትዮጵያ እንድትዋሃድ ኢትዮጵያ በጉልበት ቀላቅላታለች ብለዋል።

ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ስትቀላቀል፤ ብዙ ጊዜ  በ"ታጋዮቹ” ታሪክ ፀሃፊዎች  ሲዘገብ ያያነው ጉዳይ የኤርትራ ህዝብ አልወሰነም ይላሉ።  በነፃነት የተካሄደው በኤርትራ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት በመረጣቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት ድምጽ መስጠቱ ሰነዶች ያረጋግጣሉ።

 ፌዴሬሽኑን ፈርሶ ከኢትዮጵያ ጋር ሙሉ ህብረት ለመመስረት ህዳር 14 ቀን 1962. ፌዴሬሽኑን የመፍረስ ጥያቄ ለኤርትራ ምክር ቤት ከመቅረቡ በፊትም ከ68ቱ የፓርላማ አባላት 55 ቱ ማለትም 75% የሚሆኑት መፍረሱን ለመደገፍ ፈርመዋል። . ከአንድ ወር በላይ የፈጀ ሂደት ሲሆን የኤርትራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሞሽን ካነበበ በኋላ በሙሉ ድምጽ ቀርቧል።

የሕግ አውጭው ጉባኤ በመቀጠል ውሳኔውን እንዲያፀድቅ ንጉሠ ነገሥቱን ጠየቀ። "ስለዚህ ፌዴሬሽኑ ከነሙሉ ፋይዳውና አንድምታው በእርግጠኝነት ከዚህ ቅጽበት እንዲወገድ በአንድ ድምፅ ወስነናል፤ ከአሁን በኋላም ከእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ጋር ፍጹም አንድነት እየኖርን እንገኛለን። ይህን የውሳኔ ሃሳብ ለማጽደቅ የተወደደ ሉዓላዊ ገዥ ድምጽ ነው።” ሲሉ የፓርላማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር  ቢትወደድ አስፋሃ ወልደሚካኤል በሦስተኛው የሕግ አውጪ ምክር ቤት ረቡዕ ኅዳር 14 ቀን 1962 ዓ.ም. ንግግራቸው አረጋግጠዋል።

ነገር ግን የመገንጠል አቀንቃኞች የኤርትራ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት በጠመንጃ በኢትዮጵያ ግፊት የፈረሰ ፌዴሬሽን ነው በማለት ውህደቱ ያለ ምክርቤቱ ያለ ፍላጎቱ እንደተገደደ አድርገው ሊያሳምኑን ይፈልጋሉ (ይላል ሌላኘው ኤርትራዊ ምሁር ግርማይ የዕብዮ)

በሚገርም ሁኔታ ከ1955 - 1962 የኤርትራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢትወደድ አስፋሃ ወልደሚካኤል ደግሞ ሁኔታውን ሲገልጹ " ሲጀመር ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን ፌዴሬሽን ጠይቀውም አልጠበቁም ነበር እንኳንስ መረዳት ይቅርና በትልቁ አለም አቀፍ የፖለቲካ ምክንያቶች ከሀያላን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ የወሰኑት - የኤርትራ ፌደሬሽን በተለያዩ አማራጮች መካከል እንደ ስምምነት፣ በሁኔታዎች የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦች ሳይወዱ በግድ ተቀብለውታል፣ የፌዴራል አደረጃጀቱን ተቀብለው ሞክሩት። ሆኖም በሂደት የኤርትራ ህዝብ የማይጠቅም ሆኖ አገኙት። በመሆኑም የኤርትራ ህዝብ በመጨረሻ ውድቅ አድርጎታል። በሕገ መንግሥቱም ሆነ በገዛ ፍቃዳቸው።ከዚያም አብዛኛው የኤርትራ ሕዝብ ለዘለቄታው ሲታገልለት የነበረውን የኢትዮ-ኤርትራን አንድነት መልሰው አስመለሱ።የፌዴሬሽኑን ወደ አንድነት የመቀየር የመጨረሻ ኃላፊነት በእኛ በኤርትራውያን እና ከፈለጋችሁም፣ ከእኔ ጋር ሂደቱን በሃላፊነት የመሩትም ጭምር ወደሚይፈለገው ውሳኔ የወሰንነው ጉዳይ ነው።>> (ቢትወደድ አስፋሃ ወልደሚካኤል)

ከዚያ በላ የሆነው ከ30 አመት በላይ የውህደት ታሪክ የምታውቁት ነው። ኤርትራኖች ከጣሊያን ክፉ የቅኝ አገዛዝ ተላቅቀው ኤርትራኖች ልክ እንደማንኛችንም ተምረው ሃለፊነት ይዘው ነግደው፤ተንደላቅቀው ፈራጅ አዛዥና ናዛዥ ሆነው ኖረዋል።

ይህንን የቢትወደድ አስፍሃ ወልደሚካል ክርክር አውነት መሆኑን በግልጽ ከደገፉት አንዱ ኤርትራዊ ምሁር (ምንም አንኳ በሗላ እንደ እስስት ቢገለበጥም) ዶ/ር አማረ ተኽለ ነው። የዶ/ር አማረ ተኽለ መስመርና ተገለባባጭነት ምሁሩ ኤርትራዊ ግርማይ  የዕብዮ እንዲህ ይላል፡

<< A latter turn coat, Dr Amare Tekle, Chairman of the Eritrean Referendum Commission (1993), in his doctoral dissertation (University of Denver 1964), also agrees with Bitweded Asfaha.  He first explains his position that Eritrea is part of Ethiopia by saying "Was Eritrea part of Ethiopia? Those who argued that Eritrea was never part of Ethiopia are either ignorant of the history of the region or simply want to revise it or, even worse, were simply invoking a milder version of Signor Mussolini’s Fascist thesis about the nature of the Ethiopian state" and regarding the union with Ethiopia he further adds that "Ethiopia should not be criticized for actions related to the dissolution of the federation". >>  (አማረ ተኽለ The Creation of the Ethio-Eritrean Federation: A Case Study in Post War International Relations 1945-1950” Ph. D. dissertation, University of Denver 1964)

ትርጉም፡

<<  የኤርትራ ሪፈረንደም ኮሚሽን ሊቀመንበር (1993) የነበረው ተገለባባጩ ዶ/ር አማረ ተክሌ ፣ለዶክትሬት ዲግሪው (የዴንቨር ዩኒቨርሲቲ 1964) መመረቂያው በጻፈው ቴሲስ (ድርሰት) ከቢትወደድ አስፋሃ ጋር ይስማማል።በመጀመሪያ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ነች የሚለውን አቋሙን ሲያብራራ “ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ነበረች ወይ? ይልና ‘ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል መሆኗን ሲከራከሩ የነበሩት ወይ የቀጣናውን ታሪክ የማያውቁ ደናቁርት ናቸው ወይ ዝም ብለው መከለስ ይፈልጋሉ ወይንም ያብሱታል። ኢትዮጵያ ከፌዴሬሽኑ መፍረስ ጋር በተያያዙ ተግባራት በፍጹም መተቸት የለባትም” ሲል ተናግሯል። (አማረ ተኽለ The Creation of the Ethio-Eritrean Federation: A Case Study in Post War International Relations 1945-1950” Ph. D. dissertation, University of Denver 1964) የኢትዮ-ኤርትራ ፌዴሬሽን አፈጣጠር፡ ከ1945-1950 ከ1945-1950 በድህረ ጦርነት አለም አቀፍ ግንኙነት ላይ የተደረገ የፒኤችዲ መመረቂያ፣ የዴንቨር ዩኒቨርሲቲ 1964)

እንዲህ ያለ ኤርትራዊያን ምሁራን ምስክርነትና መገለባበጥ ስንመለከት ፌደረሺኑን ተቃውመው ወደ ጫካ ገብተው 30 ት የተዋጉት መጨረሻም በወያኔ ትግራይ መሪዎች ፈቃድና ትብብር አሁን ለምናየው ‘ባርያ ለመሆን የታገሉለት ፍሬ አፍርቶ ‘አገር’ እንዲባሉ” ጠመንጃ ያነገቡት ሰዎች ከሕግም ከታሪክም ጭራሽ የማይገጥም ምክንያት አንስተው ነው ጫካ የገቡት።

ለፌደረሺኑ መፍረስ ምክንያት ነበር ቢባል አንኳ መሆን የነበረበት ወደ “ፌደረሺኑ” መመለስ ወይንም ሙሉ ውሕደት ወደ እሚለው የምርጫ ጥያቄ እንጂ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነበርች ስለዚህም አገር ትሁን ወደ እሚል በታሪክም ፌደረሺኑ ሕግ የሚሄድ አይደለም። ይህንን በሚመለከት በግሩም ሕጋዊ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ትንተና አካትቶ የጻፈው በጀርመን አገር የህግ መምህር የሆነው ኤርትራዊው የብረይመን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ዶክተር ተስፋጽዮን መድሃንየ ”Eritrea Dynamics of a National Question” (ሕትመት 1986 በፈረንጅ ዘመን) በሚለው መጽሐፉ ውስጥ Is Eritrea a colony? በሚለው ገጽ 289 ማንበብ ጠቃሚ ነው።

ይሁንና ትግሬዎች ከኤርትራ በላይ ኤርትራኖች ሆነው በትጥቅ ትግሉም በመገንጠሉ በግንጣለው ውሳኔም ግምባር ቀደም ተዋናዮች ሆነው አማሮች 'አድጊ' (በተለዋዋጭነት ኢትዮጵያ ማለት ነው) የኤርትራ እና የኤርትራውያን ቀዳሚ ጠላቶች ናቸው ብለው በመሰየም ኢትዮጵያ ሁለት ሕጋዊ የባሕር  ወደቦችዋን አንድታጣ ተደረገ።

ይህ ሕግ የኛን “የገዢዎቻቸውን” ካርታ ያለካተተ የኮሎኒ (የጣሊያን ካርታ ብቻ መርጠው በመውሰድ የመጨረሻዋ ቅኝ ገዢ የሚልዋትን ኢትዮጵያን ያሰመረቺበትን ካርታ አንኳ ሳያካትት በሴራ የተጎነጎነ የጣሊያን ካርታ ብቻ እንዲዳኝ በማድረግ) መስመር አስምረው  ዓሰብን ምፅዋን በውሰድ፤ ሕዝቡም በሁለት እንዲከፈል አድርገው፤ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኩናማ፤ ትግሬ/ትግርኛ/፤ ዓፋር፤ ሳሆ የተባሉት ነገዶች ምጽ እንዳይሰጡ በማገድ ኤርትራ ውስጥ ያሉትን ብቻ ድምጽ እንዲሰጡ በማስገደድ ግማሽ ወደ ኤርትራ ግማሹ ወደ ኢትዮጵያ ሆነው ቤተሰብና ነገድ ተለያይተው እንዲኖሩ በጉልበት ተገድደዋል።

የኤርትራ ግንጠላ ሕጋዊ አይደለም የምንላቸው በርካታ ምክንያቶች እንዳሉ በተደጋጋሚ የጻፍኩዋቸው ስለሆኑ አሁን ያንን ሰፊ ሰነድ አላቀርብም። ሆኖም እንደ እነ ልደቱ አያሌው የመሳሰሉ ሉአላዊ አገራችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲጣስና ሕግ የጣሰ በጉልበትን በሴራ የተካለለቺው ኤርትራ ተብየዋ “አገር” ሕጋዊ ነች ብለው የሚከራከሩትን  እንደ እነ ልደቱ አያሌው የመሳሰሉ ከሃዲዎች ወደ ሥልጣን መጥተው እንደደገና ኢ ሕጋዊ የኤርትራን መገንጠል “ህጋዊነቱን” ለማጽደቅ ከሴረኞች ጋር ስለሚያብሩ ልደቱን የመሰለ ከሃዲ ወደ ሥልጣን እንዳይወጣና ባንዳነት እንዳይቀጥል ብርቱ ትግል ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።  ልደቱ አገር ቢመራ በፓርላማው ሰገነት ተቀምጦ ልክ እንደ ወያኔዎቹ “እነዚህ ጽንፈኞች/አክራሪ ሃይላት” ነፍጠኖች የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች  እያለ እንደሚዘልፈን አልጠራጠርም።

 በመጨረሻ የምለው ነገር “ኤርትራኖች አብረው ከኛ ጋር መኖር ከፈለጉ ጥሩ፡ ካልፈለጉ ግን ሁለት ባሕር በሴራና በጉልበት የኢትዮጵያን ሕጋዊ መሬትና ሉኣላዊ ምድር “በጥፋት አርክቴክቶች/ቀያሾች” የተሰጣቸው ልአላዊ ንብረታችን እና መሬታችን በሕገ ወይንም በጉልብት ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ እናደርጋለን። ያ የሚሆነው እንደ እነ ልደቱ ክሕደቱ ያሉ የፖለቲካ ተምበርካኪዎችና ባንዳ ሰባኪዎች ሳይሆን ሃገራዊያን ሃርበኛ መሪዎች ወደ ሥልጣን ሲወጡ የሚከሰት ነው። ይህ የወላጆቻችን አደራ እውን እንደሚሆን ይህንን አስለቃሽ የአደራ ድምጽ አደምጡና ልሰናበታችሁ፡

ምፅዋ! ሰዓቱ ለካቲት 9 አጥቢያ ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት ነበር።… በሁሉም አቅጣጫዎች የአብዮታዊ ሠራዊት አባላት በከባድ ጀግንነት ከሻዕቢያ ጋር በጥይት፤በእጅ ቦምብና ላዉንቸር ተጨፋጨፈ። መሬቱ እየነጋ ሲሄድ የምፅዋ ከተማ በአስከሬን ክምር፤በሰዉ ሥጋ ብጥስጣሽና በደም ጎርፍ ጨቅይታለች፡ ድመትና ዉሻ የመረጡትን አስከሬን ይጎትታሉ።አንዳንድ ቦታ ደግሞ የሰዉ እስከሬንና የዉሻ ሬሳ ጎን ለጎን ተኝቷል። በጣም የሚዘገንን ዕልቂት ነበር። የከባድ መሣሪያ ጥይት የቆራረጠዉ ሰዉ አካል በየቦታዉ ዕጣ ያልወጣለት የቅርጫት ሥጋ መደብ መስሏል…አዋጊው ጀኔራል የ6ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ጀኔራል ተሾመ ተሰማ ካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በምፅዋ ከተማ ርዕሲ ምድሪ በተባለ አካባቢ በከባድ መሣሪያ በፈራረሱ ቤቶች ጥግ ሆነዉ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችን እና ባለሌላ ማዕረግተኞችን ሰብስበዉ ንግግር አደረጉ።

<< አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ወድቀዉ ከመዋረድ ሞትን መርጠዉ የራሳቸዉን ሕይወት መቀቅደላ ላይ አጠፉ። እኔ ደግሞ በተራየ ከኢትየጵያ ሕዝብ መንግሥት የተሰጠኝን የጄኔራልነት ማዕረግ ሳላስደፍር ለመንግሥትና ለሕዝብ በገባሁት ቃል ኪዳን መሰረት አስቀድሜ የፈቀደዉን ያህል ተዋግቼና አዋግቼ ሻዕቢያን አራግፌአለሁ። እንደ ጦር መሪም እንደ ተራ ተዋጊም ሁኜ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ይዤ ተፋልሜአለሁ። አሁን ግን ለመጨረሻዋ መስዋዕትነት ህይወቴን ለማጥፋት የቀሩኝ ጥቂት ደቂቃዎች ናቸዉ።… “ጎበዝ ስሙኝ! ይህ አደራ መልዕክቴ ነገ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደርስ ይሆናል። ምናልባት አምላክ ካለ ከእናንተ አንዱ መልዕክቴን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ያደርስ ይሆናል። ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙሃን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለዉም። ይህ ደግሞ ለ ኢትዮጵያ ሀገርና ሕዝቧ ትልቅ አደጋ ነዉ። በቀይ ባሕር በራችን በኩል ብዙዉን ጊዜ ወረራ ፈጽመዉብን በተደጋጋሚ የሳፈርናቸዉና ፊት ለፊት ያልቻሉን ምዕራባዉያን ሀገሮችና ዓረቦች ዛሬ የሻዕቢያን ጊዜያዊ ድል ሰምተዉ ይፈነጥዛሉ። ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነዉንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ፀንቶ የቆየን የባሕር በራችንን በመዝጋት እንዲሁም ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ባሕር አይደለም በማለት በምድር ተወስነን እንድንቀር ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነዉ። “ ይሁን! ምንም ማድረግ አልችልንም። ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጭ ሆኗል። ከሙታን ዓለም መጥቼ ማረጋገጥ ባልችልም የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር አልባ ሆኖ ፤ በኢምፔርያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነማ የአፄ ዮሐንስ የቀይ በሕር ተጋድሎ እና የጀግናዉ ራስ አሉላ አባነጋ አጥንት እንዲሁም የእኔን ጨምሮ የ እበዮታዊ ሠራዊት አባላት አጥንትና ደም የኢትዮ ያን ትዉልድ ሁሉ እሰከዘላለሙ የፋረዳል። ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች መፍለቅያና ገናና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በመሆኑም ጀግናዉ ሕዝቧ ሕዝባዊ የባሕር በሩ በሻዕቢያ ተይዞና የጠላቶቹ መፈንጫ ሆኖ አይኖርም። የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጂ ሻዕቢያ ምፅዋን እንደያዛት ለዘላለሙ አይኖርም”። ጊዜው ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ጠላትን ደምስሶ ምፅዋን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስረክብ እምነቴ የፀና ነዉ።” አሉና ትንፋሽ ዋጡ: የትንሽ ፋታ ወሰዱ።

ከዚያም በወገባቸዉ ታጥቀዉት የነበረዉን ኮልት ሽጉጥ አወጡና የሽጉጡን አፈሙዝ በአፋቸዉ ጎርሰዉ የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጥወቱ 2፡10 ሰዓት ሲሆን ቃታዉን ሳቡት። የሽጉጥ ቶክስ ድምፅ እንደተሰማ ወደ ጀርባቸዉ በቀይባሕር ዉሃ ላይ ወድቀዉ ሰጠሙ። ከጭንቅላታቸዉ የሚፈስ ደም በቀይ ባሕር ዉሃ ላይ ቀልቶ ይታይ ነበር። ወዲያዉም ይህን የጀኔራል ተሾመ ሞት በምስክርነት ቆመዉ ከአዩት መካከል ከ150 የማያንሱ የጦር መኮንኖች ባለሌላ ማዕርጎች በሽጉጥ፤ በእጅ ቦምብና በክላሽ ጠመንጃ ሕይወታቸዉን አጠፉ። >>

ይህ በደም የተላለፈ ያደም ኪዳን አደራ  አለብን!

ጽሑፉን እባካችሁ “ተቀባበሉት” (ሼር) አድርጉት ፤ተምበርካኪዎች እየበረቱብን ነው!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ