Monday, April 17, 2017

ጥያቄ ለኢሕአፓ

      ከአዘጋጁ ማስታወሻ፤-  
ጥያቄ ለኢሕአፓ               
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) 4/17/2017
Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay)
Getachew Reda Editor Ethiopian Semay
ዛሬ የምንመለከተው ለኢሕአፓ አመራሮች፤ ለድረገጽ ተቋማቶቻቸው እና ለተከታዮች አጭር ጥያቄና አስተያየት ነው። ባለፈው ወር እኔን በእጅጉ በአግራሞት ያስደነገጠኝ እና እጅግ ያስገረመኝ ኢሕአፓ ስለ ኢትዮጵያ፤ ስለ አማራ፤ስለ አጼ ምኒልክ፤ስለ ሶማሌ፤ ስለ ኦጋዴን….ወዘተርፈ ያተተበት የቆየ የድርጅቱ ሰነድ ነው የተባለ  “እስኪ ዶሴው ይውጣ! የማን? የኢሕአፓ” በሚል በአቻምየለህ ታምሩ የቀረበ ለኢሕአፓ መሪዎችና ተከታዮች እንዲሁም ደጋፊዎች እጅግ ፈታኝ የሆነ ሰነድ በተከታታይ ቀርቧል። ይህ ሰነድ እስካሁን ድረስ ከኢሕአፓ መሪዎችም ሆነ ከተከታዮች መልስ ያላገኘ ነው። እኔ በበኩሌ እንዲህ ያለ ሰነድ ለሕዝብ ይፋ ሲሆን እውነት ነው፤ ይርታ፤ ወይንም ውሸት ነው፤ እንዲህ ነው…፤ ተብሎ መልስ መሰጠት ነበረበት። እስካሁን ድረስ መልስ አላገም።

ዋለልኝ መኮንን ተችተሃል ተብየ በኢሕአፓ ጀሌዎች ያልተሰደብኩት ስድብ አልነበረም። አሲምባ በሚባለው የኢሕአፓ ድረገጽም “አሲምባ” ጽሁፎቼ ለሕዝብ እንዳይስተናገዱ እስከማገድ ድረስ የደረሰ ብቻ ሳይሆን ስለ እኔ ካርቱን ለጥፎብኛል። በዚህም ጸብ እንደፈጠርን የሚታወቅ ነው። ዛሬ ከዋለልኝ በባሰ “ኢትዮጵያን ፤አማራን፤ ታሪኩን፤አንድነቷን፤ሚኒሊክን…. የሚዘልፍ ሰነድ የኢሕአፓ ነው ተብሎ ይፋ ሲወጣ፤ ኢሕአፓዎች “አፋቸው ሲዘጉ” ማስተዋል ለኔ በጣም ከማስገረሙ በላይ አስደንግጦኛል።

አቻምየለህ በ 6 ተከታታይ ምዕራፎች (ሁሉንም ማግኘት ባልችልም አንዳንዱን ተመልክቼቻቸዋለሁ) በወጣው ሰነድ ላይ አንድ ባንድ፤ነጥብ በነጥብ አንዲት መስምር ሳይዘሉ የተጠቀሱት ክሶች ኢሕአፓ መልስ ካልሰጠበት ኢሕአፓ እንደተቀበለው አድርገን እንወስደዋለን (ኢሕአፓ ስንል ሁሉም “ዲ”/አንጃ የሚባለውም ሆነ ዋናው ኢሕአፓም ሆነ የሚመለከታቸው ሁሉ መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል)። መልስ ካልሰጡበት “ዋለልኝ መኮንን አትንኩብን” እያሉ “ማሃይሞች” ሲሉን እና ሲዘልፉን የነበሩት የኢሕአፓ “ሊቃውንቶች” ካሁን ወዲያ “ከኔ ወዲያ ስለ ኢትዮጵያ ለአሳር፤ ዋለልኝን አትተቹ… ወዘተ” የሚለው መስመራቸው “የኢሕአፓ ሊቅነት” ከባድ ፈተና ውስጥ ገብቷል እና መልስ እንዲሰጡበት እንጠብቃለን። ለምን ጠየቅከን ተብየ በድጋሜ አንደማልዘፍ ተስፋ አደርጋለሁ።  አሎ! አሎ! ሃሎ! ሃሎ! ይሰማል?

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) Getachew Reda (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com