Friday, June 22, 2018

መልስ ለአብይ አሕመድ የትግራይ ሕዝብ እና ወያነ አንድ ናቸው ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay


ትኩስ ዜና፤

አባይ ፀሓየ እና በተቀሩት የህወሓት መሪዎች መካካል የመለያየት ፍንጭ ታይቷል። ከውስጥ አዋቂ መረጃው እንዳገኘሁት- አባይ የመጣው ለውጥ መቀላቀል እንዳለባቸው መስመር በመያዙ- አርሱን ለመደብደብ ከቃጡት የአመራር አባሎች ጋር የአካል መተናነቅ (ድብድብ) እንደተደረገ ምንጮቼ ገልጸውልኛል። አባይ የራሱን መስመር እንዲይዝ እና (ዲክለር/በይፋ እንዲያሳውቅ) ከለውጡ ጋር እንዲቀላቀል በውስጥ አዋቂቆቸቻችን ምክር አዘል ልከንለታል። ሆኖም አባይ በተፈጥሮ “አቋመ ቢስ” እንደሆነ ካለፈው ታሪኩ ስለምንረዳ በአቋሙ ጸንቶ ይቀጥላል አይቀጥልም በሂደት የምናየው ይሆናል። ሁኔታው እየተከታተልኩ መረጃው አሳውቃችለሁ።

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


መልስ ለአብይ አሕመድ
የትግራይ ሕዝብ እና ወያነ አንድ ናቸው
ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay

ባለፈው ሰሞን አብይ አሕመድ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አንስቶ የእስራሎችን ቅጅ (የፖቲካ ሞዴል) እንደሚከተል ነግሮናል። ይህ አፍራሽ ፖለቲካ ከሌሎች አገሮች እየቀዳን ካገሪቱ ጋር እያዳበልን በኮሚኒስቶች፤ በካፒታሊሰስቶች (በነፃ ገበያ) ያየነው መከራ ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም። ዛሬ ደግሞ እስራላዊው ቅጂ እተገብራለሁ ብሎ “ልቅ ዲሞክራሲ” ለመፍቀድ “እዛ ያሉ ጥግ ያሉ በጣም ጥቂት…” የሚለው የአብይ ፖለቲካ እያዳመጡ ኢትዮጵያ ውስጥ የግንጠላ ፈቃድ ሊሰጥ ነው፤መሰጠትም አለበት (ሕዝቡ ከመረጠ የሚለው የአብይም ሆነ የመለስ ዜናዊ፤የኦነግ፤ ኦብነግ…) የሚለው የወያኔዎቹ ትከክለኛ ቅጂ  ለመተግበር የቋመጡ በመጥረቢያ እና በገጀራ ነብሰጹሮችን እና ብዙ ነብሳትን ያጠፉ አክራሪ ኦሮሞ ተግንጣዮች እና አክራሪ የሃይማኖት ፖለቲከኞች (ልክ አንደ እስራል ከነሴት ውስጥ እንደተፈቀደላቸው) ወዘተረፈ ወደ አገሪቱ እየተሳበሰቡ ነው። አክራሪዎች ድማጻቸው እንዲያስሰሙ በፓርላማ ወንበር ተፈቀደላቸው አልተፈቀደላቸው ከቶውንም አክራሪ አክራሪ ነው እና ማክረሩን እና ጠምንጃ ማንሳተን የሚቀር አይደለም። ለነገሩ ምስኪን አገር “ገድለህ” “ሰልበህ” እንደልብ የሚዝናኑበት አገር ‘እንደ እምየ ኢትዮጵያ” የት አለም ይገኛል!? ተብሎ ቢጠየቅ የትም፡ የሚል መልስ ታገኛላችሁ።

ሉጓም የሌለው ልቁ ዲሞክራሲ በጉልበት የተቀረጸው 3/4ኛው ኦሮሚያ ተብሎ የተጠቃለለው “አፓርታዩዱ’ ክልል ልገንጠል የሚል ኤሊት ካለም ሜዳውም ፈረሱም ልቅ ነው፤ ግቡ ብሎአቸዋል። የእስራሎቹ ‘ኪነሰት’ እና ኢትዮጵያ አንድ አድርጎ ቅጅ መውሰድ ከተጀመረ እኛም “አገርና ቤተሰብ ለማፍረስ መገንጠል የሚጠይቅ የሞት ፈርድ ይጠብቀዋል” የሚለው የሕንዶች ሕግ የመጠቀም መብታችን ይከበርልን ማለት እንጀምራለን። ለነገሩ ‘ዲሞክራቶቹ’ እስራኤሎች አክራሪ የሃይማኖት አቀንቃኞችን ከነሴት (ፓርላማ) ውስጥ ሆነውም ሆነ ጎደና ላይ የመስበክ መብታቸው ስለፈቀዱላቸው አገሪቱን በጣም አደገኛ ወደ ሆነ የግድያና የቤት ማቃጠል አስፈሪ ሁኔታ እየወስደዋት እንዳሉ ግን የነገረን ሰው የለም። “ኢትዮጵያ/አማራ ኣውት ኦፍ ኦሮሚያ” የሚሉ የጽንፈኛነት መብት የሚጠይቁ ተወዳዳሪዎችም በፓርላማ ወንበር ይፈቀድላቸዋል ተብሏል እና “አዲሱ ልቅ ዲሞክራሲ እስከየት ድረስ እና ‘ጦርነትን የሚያስወግድ ፈውስ‘ ከሆነ ለወደፊቱ በሂደት የምናየው ይሆናል እና አሁን ወደ ርዕሱ እናምራ። እምየ ዲሞክራሲ ስንቱን አስለቀስክ ስንቱን አጃጃልክ! ስንቱንስ ጦርነት አስቆምክ? ስነቶቹን አገር አፈራርሰህ ገነጣጥለህ ወደ ‘ማር እና ወተት ወደ ዲሞክራሲ ሽግግር እንሄዳለን ብለው” ወደ የእርስ በርስ ጦርነት እና ስደትስ ማገድክ? መልሱ አንተው እራስህ መልሰው።

ባለፈው ሰሞን አብይ አሕመድ የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔን መደመር በጠላትነት ማየት ነው ሲል “የፖለቲካ ድርጅቶችን” ከስሷል። እኔ እስከማውቀው ድረስ የትግራይ ሕዝብ እና ህወሓት አንድ ናቸው የሚል እስካሁን ድረስ አንድም መጥቀስ አይቻልም። አንድ ናቸው ብለን የሞገትን ሰዎች እኔ እና በጣም ጥቂት ግለሰቦች ናቸው። ምናልባትም በፖለቲካ ድርጅት ባንፈርጃቸውም ኢሳት የተባለው (የግንቦት 7 አባልነታቸውን ወደ ጎን ትተን) በውስጡ ያያዛቸው ጥቂት ጋዜጠኞች ቀስ እያሉ የኛን መስምር ወደ መደገፍ እየመጡ የነበሩ ግለሰቦች እምደነበሩ እገምታለሁ። ዛሬ ከነፋሱ ጋር ነፍሰው ካልሆኑ ወይንም ተሳስቼ ካልሆነ የኔን መስመር ያራምዱ ነበር ብየ እገምታለሁ። አክቲቪስቶች በመባል የሚታወቁ ትልልቆቹ እንደ እነ ኦባንግ ሜቶ የመሳሰሉ የኔን መስመር ሲደግፍ እንደነበር አስታውሳለሁ። ታማኝ በየነ በሚመለከት የነበረው መስመር ትግሬዎች እና ወያኔ አንድ አይደሉም የሚል በጥናት እና በዘዴ የተቀነባበረ ቪዲዮ ሰሞኑን ሲለቀቅ አይቻለሁ፡ ጊዜ ወስጄ በሌላ ሰነዶች እስክመረምራቸው ድረስ ልተች አልችልም)።

ወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው የምንል ጥቂቶች በሚመለከት ሰሞኑን ዶ/ር አብይ ፓርላማ ውስጥ ተገኝቶ በማይገባ ወንጅሎናል ትክክል አይደለም። እኔ እንደ ትግሬነቴ እኔን አልጠላሁም። ለ27 አመት ሙሉ እንደ ትግሬነቴ ያስጠላኝ ነገር አልነበረም። ምክንያቴንም ገልጫለሁ። ትግሬ በመሆኔ ጭፍን እና አድርባይ መስመር ለማራመድ ስላልፈለግኩ የትግራይ ሕዝብ እና ህወሓት አንድ ናቸው ስል ግን የትግራይ ሕዝብን በጠላትነት መደመር የሚለው የአብይ “ውንጀላ” መመከት የግድ ስለሆነብኝ አባባሉ አልተስማማኝም። ስለዚህም በመስመራችን እንቆማለን። ጭፍን ውንጀላ እና በፖለቲካ መከራከር መለየት አለባቸው።

‘Deceiving the public’ ሕዝብን ማታለል ይቻላል፤ ታሪክም ማታለል ግን ላጭር ጊዜ ብቻ ነው።

ስለ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መነሻ እና አመሰራረት እዚህ አልገልጽም; ከሞከርኩም ‘መጽሐፍ’ ሊሆን ነው። ስለዚህ ባጭሩ ብቻ ነው ልገልጽ የምፈልገው። የትግራይ ወያነ ሦስት ምእራፎችን ተሻግሮ የሦስተኛው ወያኔ (አሁን ያለው) ወያነ እንዴት እንደተሻገረ “የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው የጥላቻ መነሻ ከምን የመነጨ ነው?” በሚለው መጽሐፌ ላይ ምንጩ እና የተሸጋገረበት ሂደት ገልጨለሁ እዛው ይመልከቱ። ዛሬ የማቀርበው የመጀመሪያው መነሻ የሆነው 18ኛው ክ/ዘመን የታየው የትግሬዎች ስሜት ሲሆን በሚቀጥለው ደግሞ ሁለተኛው ወያኔ (1935) ከዚያ ሦስተኛው ወያኔን (1967) አንመለከታላለን።

የትግራይ ሕዝብ የወያኔነት ስሜት ማሳደር የጀመረው የትግሬው ዮሐንስ የሱዳን ድርቡሾን ሲዋጉ መተማ ላይ ተሰውተው በምትካቸው ተመሳሳይ ሃይል የነበራቸው የሸዋው ምኒልክ ቦታቸውን ሲይዙ ነው። ዓይባ በተባለው ተራራ ጫፍ ላይ በሚገኙት ዋሻዎች ውስጥ መሽገው ከምኒልክ ጦር ጋር ሲዋጉ የንጉሡን ወታደሮች ሲጎዱ የነበሩ 7 ብርቱ የገጠር ተዋጊ ወጣቶችን ለማስለቀቅ መድፍ ተተኩሶባቸው እጃቸውን ለመስጠት ቢጠየቁም፤ መጨረሻ ላይ “አንተ ሸዌ እንተዋወቃለን እኮ ንጉሳችን ቢሞት እኛ ልጆቹ  አልሞትንም ‘ግድየለም እንተያያለን” ((፻፴፱-፻፵-(139-140) ዘኒ ከማሁ፤-(የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው? ገጽ 61 ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)   

 በማለት  ሲፎክሩበት የነበረውን ቂም የቋጠረ የትግራይ ገጠር ወጣቶች የትግሬ ብሔረተኛነት ስሜት ከተንጸባረቀበት ጊዜ ጀምሮ፤ ኪዘያም ተከትሎ የታየው የብሔረተኛነት ስሜት የተከሰተው ምዕራፍ ስንመለከትም ተመሳሳይ ስሜት እናያለን።
ታሪኩ እንዲህ ነው፤-

ደጃዝማች መኮንን (ራስ መኮንን- የአፄ ሃይለስላሴ አባት) ጣሊያን አገር ቆይተው በምጽዋ በኩል አድርገው ወደ መቀሌ ሲገቡ የምኒልክ ወታደሮች አጅበዋቸው እንዲመጡ በንጉሡ ታዝዘው ደጃዝማቹ ወደ ትግራይ ድምበር ሲገቡ በክብር ተቀብለው አጅበዋቸው የመጡት የአጋሜ ፤የተምቤን ወዘተ አውራጃ፤ መኳንንት እና ባላባቶች ጋር ሆነው ወደ መቀሌ ከተማ ለመግባት ሲጠጉ የምኒልክ (የሸዋ) ወታደሮች እና ራስ መከንን አጅበዋቸው የመጡት የትግራይ ሠራዊቶች ‘መሰቦ’ በተባለው ዳገት ሲደርሱ በሁለቱ ሠራዎቶች የተፈጠረው ስሜት ማስታወስ ያስፈልጋል።

ምናልባትም መጽሐፌን ያላነበባችሁ አንባቢዎች ስለምትኖሩ በትግሬ ሠራዊቶች ሕሊና የተፈጠረው ስሜት ባጭሩ ላስነብባችሁ፡      

ምኒልክ ሥልጣን በመያዛቸው ምክንያት በአፄ ዮሐንሰ እህት ላይ ያሳደረው ስሜት እንጀመር። በወቅቱ በሕይወት የነበሩት የአፄ ዮሐንስ እህት የሆኑት / ድንቅነሽ የወንድማቸው ዙፋን በሸዋ እጅ በመግባቱ የሚከተለው የቁጭት እና የንቀት ግጥም በትግርኛ ገጠሙ፦ጹሑፉ እንዳይራዘምብኝ ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጐምኩትን ብቻ ላቅርብ፡ እንዲህ ሲሉ ለምኒልክ ገጠሙላቸው፦

እንደምን አለኽ
ንጉሥ ሆይ፤   ንጉሥ ምኒልክ
ያመጡልን ነበር ቅቤ ማር  በትዕዛዝ
ያመጡልን ነበር ላም በሬ  በትዕዛዝ
አልነበሩም ወይ  የዮሐንስ ታዛዥ?
ይታዘዙ ነበር ብለው እጥፍጥፍ
ለጥ ሰጥ ብለው እንዳጎዛው ምንጣፍ?
ዮሐንስ ግን ሲሞት እንደዋዛ ተደብቀው ቆይተው በሽምዛ  ለመሆኑ ዛሬ ምን  አመጣዎት?
ሰተት ብለው ገቡ  ሰው በሌለበት  ቤት?”
በማለት ተቃውሞአቸውን በትግርኛ ግጥም ገልጸዋል።

ምኒልክ 1882 . ወደ ትግራይ ሲመጡ፤ የዮሐንስ ዘሮች የሆኑ መሳፍንቶች እና ተወልጄዎቹ እንዲህ ባለ ተቃውሞ ሲገልጹ፤ ሕዝቡስ ምን ዓይነት ስሜት እና ቅሬታ አንጸባርቆ ነበር? 

አሁን ወደ ዋናው የትግራይ ብሔረተኛነት ስሜት በግልጽ ለመጀመርያ ጊዜ በሕዝቡ ልቦና የተቀረጸበት እና የታየበት ወቅት እወስዳችኋለሁ:: አጼ ዮሐንስ ከሞቱ በኋላ ራስ መንገሻ ዮሐንስ እና የመሳሰሉት የትግራይ ገዢዎችን ከአዲሱ ጉልበተኛ እና ጥበበኛው ንጉሥ ምኒልክ ጋር በፈጠሩት ቅራኔሥልጣኑን ትግራይ ውስጥ ለማቆየት የአካባቢው ገጠሮች ከምኒልክ ሠራዊት ጋር ያካሄዱት መጠነኛ ፍትግያ/ውግያ ሲደረግ የዓይን ምስክር የነበሩይሓ” (ዓድዋ) ውስጥ የተወለዱ የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ደብተራ ፍስሐ ጊዮርጊስ ዓቢየዝጊታሪኽ ኢትዮጵያየሚል 1891 (ኢት. . ) በናፖሊ/ ጣሊያን አገር በእጅ የተጻፈ ባለ 169 ገፅ የትግርኛ መጽሐፍ (16) በጻፉት ውስጥ የመጽሐፉ ምንነት ለማየት እንዲመቻችሁ መጋረጃውን በዚህ ልክፈተው ትግርኛውን ጠቅሼ አማርኛውን ልተርጉምላችሁ።
እነሆ፦

“….ሽዕቱ ገጽ ሸወታይ ጥምት አቢልካ ናብ ገጽ ትግራዋይ ቁልሕ እንተበልካ ዳርጋ ክንዲ ናይ ለይትን ናይ ቀትርን ዚአክል ምፍልላይ ይርኤ ነበረ” ”
(ታሪኽ ኢትዮጵያ ገጽ ፻፴፬ 134) 1891/ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (1899/አውሮጳ ዘመን) ደብተራ ፍስሐ ጊዮርጊስ-ዓብየዝጊናፖሊ/ኢታሊያ) (ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)-17)
 ወደ አማርኛ ሲተረጐም፤

ያኔ የሸዌቹ ገጽታ ተመልክተህ ወደ የትግሬው ሰው ገጽታ ፊትህን ዞር ብለህ ስትመለከት የምትታዘበው የሁለቱ ሰዎች ገጽታ ልዩነት ልክ የቀን ብርሃን እና የሌሊት ጨለማ የገጽታ ልዩነት ይታይ ነበር።” (ታሪኽ ኢትዮጵያ ገጽ ፻፴፬ 134) 1891/ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (1899/አውሮጳ ዘመን) ደብተራ ፍስሐ ጊዮርጊስ-ዓብየዝጊናፖሊ/ኢታሊያ) (ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ከላይ የጠቀስኩት ግልጽ ስዕል ምን ማለት እንደሆነ እና በወቅቱ የታየው የወደፊት መጻኢ ባሕሪው ወዴት እንደሚወስድ እና አሁን ካለው ነባራዊ ክስተት ስታገናዝቡት የወያኔዎች የገጽታ ተማሳሳይ ቅጅ ምንጩያቺኛዋ ወቅትእንደሆነች መገንዘብ ትችላላችሁ።

ከላይ የተመለከትነው ክስተት የታየው ራስ መኮንን የቀ/ሃይለስላሴ አባት ለዲፕሎማሲያዊ ስራ በአፄ ምኒልክ ተልከው ናፖሊ/ከጣሊያን አገር ደርሰው በምፅዋ አድርገው ወደ መቀሌ ከተማ ሲገቡ አጼ ምኒሊክም መቀሌ ከተማ ውስጥ ስለነበሩ ራስ መኮንን ለመቀበል ደራሲው ደብተራ ፍስሃም በግራዝማች ዮሴፍ ስር ስለነበሩ ከሳቸው እና ከነደጃች ስብሐት እና ከመሳሰሉት ከትግራይ መኳንንት ጋር ሆነው ራስ መኮንን ወደ መቀሌ ለማጀብ ወደ ከተማዋ የሚወስደው ቁልቁል መንገድ ሲደርሱ (የመሶቦ ዳገት/ ቁልቁለቱ ማለታቸው ነው) እንዲህ ይላሉ።

ለደጃች ሥዩም ገብተው የነበሩ የተምቤኑ ደጃዝማች ሐጎስ ከሳቸው ጋራ የነበረው ተፈሪ የተባለ ዘመዳቸው አብሯቸው በነበረበት ወቅትሁለት ሰናድርይዞ ወደ ግራዝማች ዮሴፍ በመግባቱአጠፋህልኝብለው ተማጸኑት። ዳኛውም ራስ መኮንን ሆኑ። ያኔ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አፄ ምኒሊክ ናቸው። ተማጓቾች ሁሉ በሙግታቸው ጣልቃ የተሟጋቾቻቸውን አንደበት ስርዓት ለማስያዝ ሲፈልጉዝባን ዮሐንስ! ” (በዮሐንስ አምላክ!) እያሉ ተቸገሩ። ሆኖምበዮሐንስ አምላክእንዳይሉ ዳኛው ራስ መኮንን ሆኑባቸው፤ በሚኒልክ አምላክ እንዳይሉ ደግሞ አዲስ ነገር ሆኖባቸው ከእጅህ ለማማልጥ ሙሉጭልጭ እያለ እንደሚያስቸግርህ ዓሳ በዮሐንስ አምላክ እያሉ ምላሳቸው እያዳለጠባቸው ተቸግረው ነበር። ካፋቸው ሲያመልጣቸው ግን፤ ልክ አንድጎረምሳ ጎበዝጭቃ አዳልጦት ወድቆ ሲነሳ ሰው አይቶት እንደሆንአካባቢው ግራ እና ቀኝ በሐፍረት እንደሚቃኝ ሁሉተሟጋቾቹም ወደ አድማጩ ዞር ዞር እያሉ የሰውን ስሜት በሰቀቀን ሲለኩ ነበር።ፍርዱ ላይ በችሎቱ አካባቢ የነበረው ተሰብሳቢ ሕዝብም እርስ በርሱ በስሜት እየተጠቃቀሰ ይተያይ ነበር። ሁኔታው ሰውን ሁሉ በጣም አቅል የሚያሳጣ ሆነበት። ያችን ችሎት ተሎ ባለቀች እያለ ያልተመኘ አንድም ሰው አልነበረም በውስጡ በብዙ ሃሳቦች ተውጦ ይታይ ነበር።  (ምንጭ ደብተራ ፍስሐ ጊዮርጊስ ዓቢየዝጊ -(ታሪኽ ኢትዮጵያ  ገጽ ፻፴፬ 134) 1891/ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (1899/አውሮጳ ዘመን) ደብተራ ፍስሐ ዓብየዝጊ ናፖሊ/ ኢታሊያ) (“የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው የጥላቻ መነሻ ከምን የመነጨ ነው? ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ደራሲው ይቀጥሉና፤-

አጼ ሚኒልክ ራስ መኮንን ሲቀበሉበሚል ርዕስ ሲተነትኑ (ራስ መኮንን ከናፖሊ ጣሊያን አገር ዲፕሎማሲ ስራ ሰርተው በምፅዋ በኩል ወደ መቀሌ ሲመለሱ-የተደረገላቸው-አቀባበል ማለታቸው-ነው)“አጉላዕ በተባለች ትንሽ መንደር ለአዳር ሰፈራ አድርገን ትንሽ ቆይታ ካደረግን በኋላ በወቅቱ መቀሌ ከተማ ይገኙ ከነበሩት ከአፄ ጋር (ምኒሊክ ጋር) ለመገናኘት ጫን ተባልን። በወቅቱ ራስ መኮንን ከሐረርጌ ወደ ዜላ ከዚያ ወደ ናፖሊ ከዚያ ወደ ምፅዋ፤ ሁሉ መንገላታትና አስቸጋሪ ጉዞ እና ባሕር አቋርጦ በሰላም መመለስ የሸዋ መኳንንትም ሆኑ በእነ ራስ ሐጎስ በኩል ከፍተኛ ደስታ ነበር። ይኼ ደግሞ ግልጽ ነው። ……ወደ መቀሌ የሚያስገባው ቁልቁሉን መንገድ እንደ ጨረስን የአፄው ብዙ ጭፍራ ቆዩን። ደጃዝማች ስብሐት ግን ለራስ መኮንን የሚከተለው ቃል ተናገሯቸው።እኔ ቆየት ብየ እደርሳለሁ፤ እርስዎ ግን ቅድሚያ ይሂዱአሏቸው። ራስ መኮንንምእሺ ደግ ይኹንብለው በሃሰባቸው ተስማሙ። ሰው ግንአይ ተደርበው እንዳይገቡብለው ነው፤ በማለት ተረጎመው። ( ተደርበው እንዳይገቡ ብለው ነው፤ ሲባል - አጃቢ/አሽከር ሆነው ገቡ እንዳይባሉ ማለት ነው በትግሬዎች አባባል)

ቁልቁለቱን ጨርሰን ታች እንደወረድን ወዲያውኑ ከሸዋ ሰራዊት ጋር ዓይን ለዓይን ተያየን።ጸንዓ ደግለእያለሁ ድሮ የማውቀው የአጋሜ የአጉዕዳይ ተወላጅ የሆነው ፊታውራሪ ተስፋይ የተባለ ጎን ለጎን እንጓዝ ነበር እና ወይኔ ወንዱ! ይበለን! ራሳችን ያመጣነው ጣጣ ነው፤ አስታጣቂዎች የነበርነው አሁን ታጣቂዎች ሆንን !አለ። ከዚያ በኋላ ይህ ያዳመጡ ራስ መኮንን ለመሸኘት የተከተሉ እነኮንቲ አንቶኖሊእና ራስን አጅበው እየተጓዙ የነበሩት ትግሬዎች በሞላ ማለትም-ዓጋሜውም፤ አከለጉዛዩም፤ ሐማሴኑ፤ የአሕሳአውም፤ ተምቤንየውም ሁሉ ከሸዋዎቹ ጭፍራዎች ጋር ዓይን ላይን ተገጣጥሞ ሲተያይ ኪፍ አለው።  ስሜቱ ሁሉ ተለዋወጠ። ያኔየሸዌዎቹ ገጽታ ተመልክተህወደየትግሬው ሰው ገጽታ ፊትህን ዞርብለህ ስትመለከት የምትታዘበው የሁለቱ ሰዎች ገጽታ ልዩነት ልክየቀን ብርሃን እና የሌሊት ጨለማ የገጽታ ልዩነትይታይ ነበር…….>>

(ደራሲው የተጠቀሙበት ቃልኪፍየሚል ነው።ኪፍማለት ድመት ወይንም ነብር ጠላት ስታይካንገቷ በላይ ያለው ጸጉርበማቆምበጉብታ ስሜትየጥላቻ እና የመከላከል ገጽታዋ እንደሚለዋወጥ የሚታይ ስሜት ማለት ነው)

<…….የደጃች ሐጎስ አሽከር የነበረ አንድ የተምቤን ሰው ይህ ትርኢት ሲመለከት የአፄ ዮሐንስ ሕልፈት ትዝ ብሎት እንባውዘረፍ አደረገ። እውነት ለመናገር እንኳንየትግራይ የወንዝ ልጅ የሆነየአከለ ጉዛይ እና የሐማሴን ሰው ሁሉ እንባ ተናነቀው። … (ታሪኽ ኢትዮጵያ ገጽ ፻፴፬ 134) 1891/ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 1899/ፈረንጅ ዘመን ደብተራ ፍስሐ ዓብየዝጊ ናፖሊ/ኢታሊያ  በትግርኛ በእጅ ጽሑፍ ተጽፎ ከተገኘ) (“የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው የጥላቻ መነሻ ከምን የመነጨ ነው? ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

“…የትግራይ ሕዝብ ወቅቱ ንፍሮ ቆሎ የሚመገብበት እና በተቅማጥ ወረርሺን በሽታ ሲሰቃይ የነበረበት አስከፊ ወቅት ነበር። በወረራው ወቅትም ብዙ ሰው አልቋል። ወደ ትግራይ መሻገራቸውም ከሸዋ ሰራዊቶች መሃል ያልተደሰቱ ነበሩ።….ትግራይ ጉልበታቸው ሥር ወድቃ ለምና ያመጣቻቸው ይመስል፤ ትግራይን መራገም ጀመሩ።የአማራ ወታደርወደ አጋሜ ከዚያም ወደ አክሱም ሕዝብ እያጠፉ ለመሸጋገር አልሞ ነበርና ፤የአማራ ወታደር ወደ አጋሜ መሻገር አቀበት ሆነበት። ትግራይን መራገም ጀመሩ። ቋንቋውን ሁሉ መስማት አስጠላቸው። ይህ እንደዚህ እያለ የራስ መንገሻ በሰላም እጃቸውን መስጠትደስታሆነ። በወቅቱ ራስ መንገሻ ዮሐንስ እጃቸው ለአፄ ሚኒልክ ሲሰጡ ራስ አሉላ እጄን ለሸዋ አልሰጥም ሲሏቸው ራስ መንገሻ ዮሐንስ ግንሰውና አገር ጠፍቶ እኔ ብቻየን ብቀር ምን ይረባኛል፡ እናንተ ግን የመሰላችሁን ቀጥሉበት እኔ ግን ገቢ ነኝ ብለው እጃቸውን  ሰጡ። “ >

ካሉ በኋላ በ፰መጋቢት፲፰፹፪ (መጋቢት 8/1882) ራስ መንገሻ ወደ ሚኒልክ ሲገቡ መቀሌ ከተማ የተደረገው ስነ ስርዓት በስፋት ከዘረዘሩ በኋላ አስገራሚ ትርኢት ባጭሩ እንዲህ ሲሉ ያሰቀምጡታል፦ 
< “በ፰መጋቢት፲፰፹፪ (መጋቢት 8/1882) ራስ መንገሻ ወደ ምኒልክ ሊገቡ በመዘጋጀት እንዳሉ ከተነገረ በኋላ አጼው ወዲያ ወዲህ ሳትል በጥዋቱ ነገ በየአለቃህ ተሰልፈህ እንድትገኝ ብለው አዋጅ አስነገሩ።

መቀሌ የሚገኙት አጼ ምኒልክ ይህንን ካወጁ በኋላ ጠዋት ጸሐይ ሰትወጣ ሰልፈኛው ከአፄው ደንኳን ጀምሮ በሁለት ረድፍ እንደ ግድግዳ ግራ እና ቀኝ ረዢም ረድፍ በመስራት ይጀምር እና ወደ ታች ራስ ሥዩም ይመጡበታል ወደ ተባለው የተምቤን አቅጣጫ ሲደርስ ወደ አራት እና አምስት ረድፍ ሰልፈኛ ግራ እና ቀኝ በረዢሙ በመሰለፍ ረድፍ ያዘ። በዛው ላይ የራስ መንገሻን መልክ ለማየት እየተጋፋ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ እርስ በርሱ እየተጋፋፋ ነበር። ቀጥሎም ትልልቆቹ ደጃዝማቾች እና ሹሟሙንቶች ወደ ንጉሱ ጃንጥላ ተሰበሰቡ። የንጉሡ ጃንጥላም ተዘረጋ። ከንጉሡ ዱንኳን ጀምሮ በሁለት ረድፍ ግራ እና ቀኝ እንደ ገመድ የተወጠረው የሰልፈኛው ጫፍ የት እንደ ሆነ ለዓይን እስኪያዳግት ድረስ ቀጥ ብሎ በረዢሙ እና በተንጣለለው ሰፊው ሜዳ ወደ ታች የዘለቀው ሰልፈኛ ስትመለከት በግራ እና በቀኝ በተሰለፈው እመሃል ላይ ለራስ መንገሻ ዮሐንስ መምጪያ ክፍት ቦታ ሰርቶ የተንጣለለ የማሳለፊያ ክፍት መንገድ ሰርቷል።

የአማራዎቹ ሠራዊት ብዛት ያኔ ነው ለማየት የተቻለው። ብዛታቸው የመሬት አፈር ያህል ነበር። ከዚያ በኋላ ረፋዱ ላይ ራስ መጡ። ቢያንስ (10,000) የሚሆን ሠራዊት አስከትለው መጡ። እሳቸውን ለመቀበል ግራ እና ቀኝ በተሰለፈው ሰራዊት መሃል ለማሃል ሰንጥቀው በመጓዝ ወደ ንጉሡ ድንኳን ደረሱ። አፄ ምኒልክ ድንቅ ሰው ናቸው እና በብዙ አክብሮት ተቀበሏቸው። መድፍ ተተኰሰ፡ ወዲያውኑ እያንዳንዱ እሳቸውን ለመቀበል የተሰለፈው ሠራዊት በነፍስ ወከፍ የደስታ መግለጫው ጥይት ወደ ሰማይ ተኰሰ። ሰማይ እና ምድር ድብልቅልቁ የወጣ መሰለ። እንዳይጠፉ ታስረው ከነበሩበት በረት ፈረሶች እና በቅሎዎች ማሰሪያቸውን እየነቀሉ እየበረገጉ እንጣጥ እያሉ ሸሹ። በወቅቱ ራስ መንገሻ በአባታቸው (አፄ ዮሐንስ) ሞት ምክንያት ሐዘንተኛ ስለነበሩ በሰልፈኛው መሃል ሰንጥቀው ሲያልፉ የሐዘን ልብስ ለብሰው ነበር የመጡት። ይህንን ሲመለከት ሰው እንዳለ በሙሉ ምርር ብሎ ሐዘን በሐዘን ሆነ።……” “… በወቅቱ ራስ መንገሻ እጃቸው ባይሰጡ ኖሮ ካሁን በፊት ከታየው ውጊያ በከፋ መልኩ ትግራይን ያጠፏት ነበር። ራስ መንገሻ ከመግበታቸው በፊት አፄ ምኒልክ አጋሜ አውራጃን ለማጥፋት ዝግጅት አድርገው ነበር። የአጋሜ አውራጃምከአማራ ጋር ተናንቀን አብረን እንሞታለን እንጂ አይገዛንምብለው ዝግጅት አድርገው በየምሽጉ እና ጉራንጉሩ መዋጊያ ቦታ ይዘው ተዘጋጅተው ነበር። 

ከደጃች ሥዩም በቀር ከሸዋ ጋር የወገኑት እና ያልወገኑት መኳንንት መሃል መጠኑ ያለፈ ጥላቻ በትግሬዎች አርስ በርስ ይንጸባረቅ ነበር። ይህ ጥላቻ የርስ በርስ ጥፋት ማስከተሉን አይቀሬ እና ትርፍ እንደሌለው ከተገነዘቡ በኋላ ሕዝቡ ካለቀ በኋላ ብቻየን ብቀር ምን ትርጉም አለው በማለት፤ እነ ራስ አሉላን የፈቀዳችሁ አድርጉ ብለው እነሱን ትተው ራስ መንገሻ ዮሐንስ እጃቸውን ለመስጠት ነበር የተገደዱት። (ታሪኽ ኢትዮጵያ ገጽ ፻፵፪-/፻፵፬ 142-144) 1899/ፈረንጅ ዘመን አቆጣጠር ደብተራ ፍስሐ ዓብየዝጊ ናፖሊ/ኢታሊያ)-(“የትግራይ ብሔረተኞች በአማራ ላይ ያላቸው የጥላቻ መነሻ ከምን የመነጨ ነው? ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ)

ይህ ሁሉ ሲሆን ይላሉ ደብተራ ፍስሃ ጊዮርጊስ አብየዝጊ እንዲህ ይላሉ፦ 

ሸዋዎቹ እንደርታን እንዳልነበረች አደረጓት። ወንድ የተባለ ሁሉ ይታረድና ይሰለብ ነበር። እንደርታዎቹም በየ ጉራንጉሩና ጫካው እየተሸሸጉ ብዙ ሰው ፈጁባቸው። ሸዌዎቹ ትግራይ የብር (ገምዘብ) ጎተራ ነች  እያሉ ትልልቁ የኪሊአው (ኪሊዔው) ዛፎችን ከሥር እየመነቀሩ ፈነቀሉት።ጊዜ ካላገኙ ግን እሳት ሎኩሶውበት ይኼዱ ነበር። መላ ኢትዮጵያ የሚያከብረው የአብርሃ አጽብሃ ደብር በዘበዙት። ከወረራ የተረፉት እና ከበሽታ የዳኑ ከብቶች በሬ፤ አራስ ላም ባንድ ብር ይሸጥ ነበር። የእህል ሸመታም ጥጋብ ነበር።ልብ ያለው ሰው ስለ ሕለፈተ ትግራይ ብዙ የሚያሳዝን ነበር። አንድ ቀን ማታ መሸት ሸት ሲል  አንድ ናዝራዊ (ሰባኪ) መነኩሴየክርስትያንን ነብስ እንደ ከንቱ ነገር እያጠፋኸው ነው፤ ተጠንቀቅ!’ ሲል ለፈፈ/ አወጀ/ ከዚያም ሰው ሁሉ (የሸዋው ሰራዊት) ተሸበረ፤ ተሰብስቦ እግዚኦ ብሎ ወደ ምሕለላ ገባ። ንጉሡም ይህን ከሰሙ በኋላ በየሰፈሩ ፈረሰኞች እየላኩአንተ ተሰባኪሸዌ ሁላዝም በልእያሉ ዝም አሰኙት። ከዚያም ራስ መንገሻ ሊገቡ ነው የሚል ወሬ ስለሰተማ፤በዛ ሰፈር ደስታ ሆነ። (ዘኒ ከማሁ 137-139)

ሁሉ ሲሆን አጎራባች ያሉ ገጠሮች ተዘመቱ፤ ብዙ ነብስ ተሟሟተ። ምኒሊክን አጅበው የመጡ የጋላ ወታደሮች እንደ አገራቸው ባሕልና ልማድም ወንድ ሴት ሳይሉ ሁሉም አረዱት፤ ትልቅ፤ ትንሽ ወጣት ሁሉንም ሰለቡት። ደጃዝማች ስብሐት ይህንን ሲያስተውሉ፤ ወደ ሚቀጥለው በሁለተኛው ጉዞችን ለመንቀሳቀስ ስንዘጋጅ ንጉሡን እንዲህ ሲሉ ፈቃድ ጠየቁየርስዎ እና የኔ ሰዎች አብረው ቢጓዙ፤ ባለመተዋወቃቸው ምክንያት የርስዎ ሰዎች የኔን ሰዎች  እንዳይጎዱብኝ ፈቀድዎ ከሆነ ራቅ ብየ ወደ ፊት እንድጓዝ ይፍቀዱልኝ፡ ብለው ሲጠይቋቸው፤ንጉሡ ደግ ሰው ነበሩናእሺ ችግር የለውም አድርግብለው ፈቀዱላቸው” (ዘኒ ከማሁ 136)
 
ማጠንጠኛው  

እዚህ ላይ የምንገነዘበው ከደብተራ ፍስሐ የተላለፈው ሰነድ፤ ከመቶ ምናምን አመት በፊት ከወላጆቻችን የተነጠቀው ሥልጣን እና የተደረገው ጭፍጨፋ፤ ዘረፋ፤ ውርደት፤ እንበቀላለን በሚል ነው ወያኔዎችም በማኒፌስቶአቸው <አማራ ብሔር ማሕበረሰባዊ ሰላም አታገኝም> በማለት ጽፈው የጻፉትንም ተግባራዊ በማድረግአማራ የሚባል ዛሬ እየተፈጸመበት ያለው ፍዳወላጆችህ ባደረጉትአንተ ዕዳውን ክፈልበሚል ከላይ የተተወላቸው ሰነድ በመመርኮዝ ቁዘማ ውስጥ በመግባት መነሻቸው አድርገውታል። (እነ ገብረኪዳን ደስታም በመጽሐፋቸው የሚጠቅሱት ብሶት ይህ የጠቀስኩት ታሪካዊ ሰነድ)  ወደ  ኋላ የሄዱበት ስሜት ወላጆቻችን (ነገዳችን) ‘አማራበተባለ ጠላት ስለተዋረደ፤ ያንን ክብር፤ ንግሥና፤ ሥልጣን የተዘረፈው ሃብት፤ የተረገጠው ባሕል ፤ቋንቋ፤ ማንነት ወደ ንቡር ቦታው ለማስቀመጥብድራችንእንመልሳለን በማለት የትግራይ ሊሂቃን “‘ፋሽስቶችየተከተሉት  መንገድ በመከተል በአማራ ላይ ያሳዩት ለጥላቻቸው መነሻ ምክንያት ሆኖ ሕዝቡም አምኖ ከነሱ ይህ ርዕዮትና ግብ ለማሳካት መሪ ሆኖ አራምዶታል የትግራይ ሊሂቁ ክፍል ብቻ ሳይሆን  የትግራይ ሕዝቡም ይህንን ቅስቀሳ አምኖ ተቀብሎታል፤ስለሆነም ወያኔን አቅፎ ደግፎ መግቦ ተከላክሎለት አጅቦ ሞቶለት ታግሏል። በዚህ እንተማመን። የ1936፣ የ1967 ወያኔ እንቅስቃሴዎች የተከተሉዋቸው መፈክሮች “ጸረ ሸዋ” (ሸወቶት- ዘመነ ሸዌ በሚለው የቆየ ብሂል) የሚል የጋራ መፈክር አንግበው አስተጋብተውታል።

እጠቅሳለሁ፦

የትግራይ ህዝብ ለረዢም ዘመን ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተነፍጐ ሲጠላ እና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲደረግበት ቆይቷል። ይህ በደል ጨቋኝዋ የአማራ ብሔር ሆነ ብላ የመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሰራበት የቆየች ሲሆን ፫ሺ ዓመታት የሚያኮራ ታሪክና ባህላችን መመኪያቸውና መፎከሪያቸው ሆኖ ይገኛል። ይህ የታሪክ ስርቆት በአንድ በኩል የአማራው ብሔር መፎከሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትግራይ ህዝብታሪክ እንደሌለውህዝብ እንዲያስቆጥረው የተደረገ የመንግሥት መመሪያ ነው። የትግራይ ሕዝብ ክብሩና መብቱ እስኪመለስለት ድረስ ትግሉ አያቋርጥም። ጨቋኝዋ የአማራ ብሔርም ጭቆናዋ እስካላቆመች ድረስ ሕብረተሰብዓዊ ዕረፍት አታገኝም
 (የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት መግለጫ የካቲት ወር 1968 ..ገጽ 15-16} (ምንጭ የወያኔ ገበና ማህደር ገጽ 21 ደራሲ- ጌታቸው ረዳ)

በዚህ መልክ የትግራይ ሕዝብ
 የትግራይ ሕዝብ ክብሩና መብቱ እስኪመለስለት ድረስ ትግሉ አያቋርጥም።” በሚል መርህ ትግሬዎች ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ስልጣን ተቆጣጥረዋል። ከዮሐንስ የተነጠቀው ስልጣን ወደ ትግራይ መልሶ በማስመጣት ትግሬዎች በበላይነት የሚመሩት እንዳሻቸው የሚያሽከረክሩት አዲስ መንግስት ለመመስረት በቅተዋል (በትግራይ ሕዝብ ግምባር ቀደምተነት ትግል)። ይህ እነ አብይም ሆኑ ተቃዋሚ ተብየዎች አሌ ቡሊትም መስመራችን በሰነድ የተረጋገጠ የጸና ነው። አብይ ለዚህ ደረጃ ያበቁትም ትግሬዎች ስለሆኑ “አገርን የሸጡ ከሃዲ ባንዳዎችን እነ መለስ ዜናዊን” ሳይቀሩ የኔ ጀግኖች” “ወርቆች” ሲል አሞግሶአቸዋል። ይህ ስል አብይን ተቀናቀንክ ብላችሁ ‘በጸረ ትግሬነት የምትከሱኝ“ ‘በትግራይ ሕዝብ ፊት ልዩ ሙገሳ እና ከንቱ ፍቅር ለማግኘት የምትጥሩ ታሪክን እና ሰነድን የምትረግጡ አድርባዮች” እንዳላችሁ ስለማውቅ በዚህ አብይን ተከትላችሁ “ወያኔ እና ትግሬዎች አንድ ናቸው ብሎ በጠላትነት…” የሚለው የአብይ መስመር ተከትላችሁ እኛን በጸረ ትግሬነት ብትከስሱንም “ስድባችሁን” እናከብራለን።

ስለሆነም ከላይ እንደተመለከታችሁት ለትግራይ ሕዝብ በባሕል፤በታሪክ ባለቤትነት፤ በምጣኔ ሃብት እና ስነ መንግሥታዊ አስተዳደር እየተዳከመ መምጣት ወይንም የተጠቀሱ እሴቶችባለቤትነት መነጠቅምክንያትጨቋኝዋ የአማራ-ብሔርእንደሆነች በማያሻማ አገላለጽ አስቀምጦ ሕዝቡን አስተምሮአቸዋል፤ ሕዝቡም ተቀብሎታል። ለዚህም በየአመቱ የትግላቸውን በዓላቸውን ያከብራል (ወየኔ እና የትግራይ ሕዝብ ትግል የራሱ ነው እና)።  ለዚህም ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ ዋነኛ ጠላት አድርጎ መመልክት ያለበትአማራእንደሆነ ካስቀመጠ ላይቀር የአማራው ህልውና ክር እና ድሩ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ስለሚያምን ኢላማ ውስጥ በማስገባትኢትዮጵያንበጠላቻ እይታ መነፅሩ ክብ ወግቷታል። ሕዝቡም ከታች ወደ መደምደሚያ በማስረጃ ኣንደማቀርበው ወያኔ እና ሕዝቡ አንድ መሆኑን ተቀብሎ ቅስቀሳው ተቀብሎታል። እንደ እኔ እና የመሳሰሉ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ትግሬዎች ወያኔ ጋር ቅራኔ የገቡ እንዳሉ አውቃለሁ፡ ያ ግን በቁጥር ኢሚንት ነው።

ለነገሩ የአማራ ጥላቻው ከኢትዮጵያ ጋር አያይዞታልስል ምን ማለቴ ነው? ወደ ዋናው ማኒፌስታቸው ስንመለከት አሁንም የሚጦቁመውጨቋኝዋ ብሔር” (አማራ) ኢትዮጵያ የምትባል አገር የተፈጠረቺውበጨቋኝዋ ብሔር በአማራው ፤በተለይም በሸዋው አማራ በምኒልክ (አንዳርጋቸው ጽጌ የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት በሚለው መጽሐፉ እንዳስቀመጠው ካንድ ቦታ ከተገኙ የሸዋ አማራ መሳፍንቶች ይላል እሱም) እንደሆነ አስቀምጠውታል። ሰለዚህ ኢትዮጵያን የፈጠረ ምኒሊክአማራው እና የአማራ ወታደርየትግራይ ጠላት ስለሆነ የፈጠራት ኢትዮጵያም ከአማራው ባሕል፤ታሪክ (ምንም እንኳ አማራው የራሱ ታሪክም ባሕልም ስለሌለው ከትግራይየተሰረቀባሕልና ታሪክ እያራመደ ነው ብሎ ቢወነጅለውም) ጋር በመያያዙኢትዮጵያየምትባልየጨቋኝዋ ብሔር” (የአማራው) አገር የትግራይ ሕዝብ ከጠላቱ እና ከጨቋኝዋ ብሔር/አገር ለመነጠልአብዮታዊ ትግል” (ወያኔያዊ ትግል) በማካሄድ “…ከባላባታዊ ስርዓትና ኢምፔሪያሊዝም ነፃ የሆነ” “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ማቋቋምእንደሆነ 1968 ያሰራጨው ጽሑፍ አረጋግጦልናል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ሰንደቃላማ አማራዎች የፈጠርዋት ስለሆነች የራሳችን ባንዴራ መፍጠር አለብን ብለው የራሳቸው ባንዴራ ፈጥረዋል። ይህም የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ጥሎ “ድርጅቴ” የሚለው የወየኔን ባንዴራ ተቀብሎ እስካሁን ድረስ በክብር እያውለበለባት ነው። ይህ አብይ ሊክድ ይችላል። እናንተም ልትክዱኝ ትችላላችሁ። ሰነዱ ግን አይክድም።

ስለሆነም “ማኒፌስቶ የካቲት 68” በግልጽ ያስቀመጠው የ1962 ዓ.ም (የማሕበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ ምስረታ) መነሻ የሆነው ምክንያት ሲገልጽ በትግርኛ እንዲህ ይላል። “ፍረ ናይ ቅድሚ 80 ዓመት ውጹዕ ህዝቢ ትግራይ ብዝገበሮ ፍረ ቃልሲ እዩይላል። “ዛሬ ይህ ድርጅት ለመመስረት ያበቃን ምክንያት ጭቁን የትግራይ ሕዝብ የ80 አመት ትግል ያደረገው የትግል ፍሬ ነው። ይህ ደግሞ ከ80 አመት በላይ  አርግዞት የነበረው ጽንስ በ1962 የተወልደ የ 80 ዓመት ጽንስ ልጅ ነው” ይላል። 80 አመት ተጸምሶ የነበረው ጽንስ አዋላጁ ማን ነበር? የሚለው ጥያቄ ስንመልስ ፤ መልሱ “የትግራይ ሕዝብ” የሚል መልስ እሰጣችለሁ። ይህንን ያለመቀበል ግን የናንተው ፈንታ ነው። የ80 አመት ጸንሱ በትግራይ ሕዝብ አቃፊ መጋቢ ተንካባካቢነት እና አዋላጅነት በ1967 አመተ ምሕረት “ወያኔ” የሚባል የትግራይ ሕዝብ ልጅ ተወለደ! ሓቁ ይህ ነው። አድርባዮችም ሆናችሁ አብይም ሆነ ሆነ ሰነዶችን ያለምረመራችሁ ሌሎቻችሁ “ወያኔ እና የትግራይ ሕዝብ ለየብቻቸው ናቸው” የምትሉ ሁሉ “ትንሽ እፈሩ” ብል እንደ ድፍረት እንዳይቆጠርብኝ። የትግራይ ሕዘብ እየተደበደበ በፍርሓት ነው ወያኔን የተከተለው የሚለው ከናንተ በላይ አውቀዋለሁ። አዎ እየተገደለ በግድ ድርጅቱን እንዲከተል ተደርጓል፤ ያ በሌላ ርዕስ እመለስበታለሁ። ወደ እስቶክሆልም ሲንድሮም ታሪክ ሊወስደን ነው። እስርቤት ውስጥ በገመድ የኋላት የፍጢኝ ታስረው ክፉኛ የተሰቃዩት ታጋዮች እንደ እነ ተኽለወይኒ አሰፋ የመሰሉ ታጋዮች ክፉ የወያኔ አምላኪዎች የመሆናቸው ምስጢር እና እየተደበደበ ወያኔን እንዲያመልክ በኋላ የከፋ የወያኔ አምላኪ፤ተዋጊ እና ጠቋሚ ሆኖ ያገለገለ የትግራይ ሕዝብ ለምን እንዲያ ሊሆን ቻለ የሚለው ብዙ ውይይት የሚጠይቅ ነው። አንድነታቸወም ከዚህ በመነሳት ነው። ጀርመኖች፤ጣሊያኖኖች አድርገውታል።   

የትግራይ ሕዝብ በወየኔዎች የተሰጠው ወደ ላ ዘመን መለስ ብሎ የማየት “ትግራይነት እና ስልጣን ባለቤተነት” የተሰጠው ትምህርት ተቀብሏል።

የትግራይ ሕዝብ እና ታጋይ በደስታ ሲጨፍርባት የነበረቺውን ዝነኛ የሆነቺው ከትልቅ እስከ ደቂቅ ሌት ተቀን እየዘፈነ ሲቆዝምባት የነበረቺው ጸረ አማራ ዘፈንን እዚህ ልጠቅስ እፈልጋለሁ። ዛሬም እጅግ ከትግሬዎች ሕሊና የማትወጣ
የትግራይ ሕዝብ እና ታጋይ በደስታ ሲጨፍርባት የነበረቺውን ዝነኛ ጸረ አማራ ዘፈንን እዚህ ልጠቅስ እፈልጋለሁ።

ትግርኛውን ልጥቀስ፤
እንተሸፈንካያ ዘይትሽፈን ሓቀኛ እያ
እንተሓባእካያ ተቐላዒት እያ
ጨቆንትና አምሓሩ ምስ ታሪኽ ፀሐፍቶም
ንዓና  ብሊሎም ታርኽና ጐቢጦም
ኣለው ይምክሑ ብደም ወለድና
ንቃለስ ውፁዓት ክምለስ ቅያና

(“አውነት ልሸፍናት ብትል አትሸፈንም፤ አውነት ልደብቃት ብትልም አትደበቅም፤ ጨቋኞቻችን አማራዎች ከታሪክ ጸሐፍቶቻቸው ጋር ሆነው እኛን አምፀው፤ ይኼው አኩሪ የሆነውን የወላጆቻችንን የትግሬዎች ታሪከ ሰርቀው የወላጆችን የደም ገድል የነሱ አስመስለው ሲሞኩበት እያየን ነውና፤ ጩቁን ትግሬዎች የወላጆቻችን ታሪክ ለማስመለስ ተነሱ እንታገል።”  (በረሃ ውስጥ በዚች ዘፈኑ የታወቀው የህወሓት ዘፋኝ የነበረው ኪዳነማርያም ረዳ)።  (አማርኛ ጥቅስ ይድረስ ለጎጠኛው መምህር ደራሲ ጌታቸው ረዳ - ገጽ 102)

ስለዚህም የትግራይ ብሔረተኞች ከላይ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይበግልጽ እንደተቀመጠው አብዛኛዎቹ የትግራይ ብሔረተኞች ነባር እና ወጣት ምሁራን ከዚህ የህወሓት ቅስቀሳ እና እንደዚሁም ከድሮ ከመሳፍንቶች እና በትዕቢት የተወጠሩ የአካባቢው ባላባቶች ሲያንጸባርቁት የነበረው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ፤ ንጉሳችን ቢሞትእኛ ልጆቹ አልሞትንም፤እንተያያለን የሚለው በዘመነ ምኒልክ ትግራይ ውስጥ ሲያስተጋቡት የነበረውን የወቅቱ የገጠር ጐሰኛ ወጣት ብሔረተኞች ፉከራ ከስንት አመት በኋላበዝግታ ሲከማች ከነበረው የቂም ግምጃ ቤት1935 እና 1967 . ይፋ ሆኖንጉሳችን ቢሞት እኛ ልጆቹ አልሞትንምየሚለው ጸረ አማራ (ጸረ ሸዋ) ጥላቻ የመነጨበት መነሻው ይህ ነው። በዚህ መልክ የትግራይ ሕዝብ ወያኔ ያስተማረውን ጸረ አማራ እና ጸረ ሸዋ መፈክር ተቀብሎ የትግራይ ሕዝብ ጸረ አማራነቱን አንጸባርቋል።

ማስረጃየን ከዚህ በታች ያለውን በሰነድ የተደገፈ ላቅርብ።

ይህ ምስክርነት የተሰጠው ወያኔ በየካቲት 11 1967 ዓ.ም ወደ ደደቢት በረሃ ሲወጣ መስራች ታጋይ የሆኑትን 7ቶቹን ተከትሎ በመሄድ 11ኘው ሰው በመሆን 7ቱን የወያኔ መሪዎች በጦር ስልት ያሰለጠነ እና የወያኔን ታጋዮችን የስልጣና ጣቢያ ሃለፊ በመሆን በጦር ስልጠና ሲያስተምር የነበረው የመጀመሪያው ታጋይ ነው። አስገደ ገብረስለሴ ይባላል። አስገደን ሁሉ የውቀዋል። ወያኔን ተቃውሞ ብዙ በራሱ እና በልጆቹ ላይ ብዙ ፍዳ ደርሶ ብዙ መከራ ያሳለፈ ታጋይ ነው። አሁንም መቀሌ ውስጥ ይኖራል። አስገደ ገብረስላሴ በርካታ የትግርኛ እና አማርኛ መጽሐፈት ጽፏል። በትግርኛ ከጻፋቸው መጽሐፍቶች አንዱ “ጋህዲ” ይባላል። ጋህዲ ማለት “ግልጽ ግልጹን” እንደማለት ነው። አስገደ ስለ ትግራይ ሕዝብ እራሱ ያዋለደው ወያነ’ የተባለው የገዛ ልጁ የቀሰቀሰው ቅስቀሳ ተቀብሎ ‘የትግራይ ሕዝብ ለአማራ ያሳደረው ጥላቻ” (ኤርትራኖች በሻዕብያ ተቀስቅሰው በአማራ ላይ ያሳደሩት ጥላቻም ሆነ ጀርመኖች የናዚዎችን ጸረ አይሁድ ቅስቀሳ ተቀብለው የተንቀሳቀሱባቸው መነሻዎችን ማስታወስ ተገቢ ነው) እንዲህ ይገልጸዋል።

<<ኢህአፓ  በአጋሜ አውራጃ ውስጥ በአሰፈ ሰበያ እና በወረዳ ጉሎ ሞዀዳ በወያነ ትግራይ የጠባብነት ጨረታ አሸናፊነት ተበልጦ ከትግሉ ከወጣ በሗላ።ከዚያ በሗላ የጠባብ ብሔረተኝነት በሽታ በመላዋ ትግራይ እንደ ተላላፊ በሽታ ተስፋፍቶ ወደ ሕዝቡ በመተላለፉ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ፀረ አማራ ተንቀሳቀሰ።”>>
አስገደ /ስላሴ የወያኔ የደደቢት በረሃ ‘ቤዝ” የመጀመሪያ መስራች አንዱ፦ ጋህዲ /2 ገጽ 155  የትግርኛው ቅጂ 2001 .ትርጉም ይድረስ ለጎጠኛው መምህር ደራሲ ጌታቸው ረዳ ገጽ 17-18)

የድርጅቱ መስራች እና የመጀመሪያ የድርጅቱ መሪ እና የሽምቅ ተዋጊው ሃይል ዋና መሪ የነበረው / አረጋዊ በርሔም በጻፈው መጽሐፉ እንዲህ ሲል ነግሮናል።

'' anti-Amhara propaganda was subtly encouraged within the movement.Cultural events, theatrical performances as well as jokes and derogatory remarks were used to disseminate this poisonous attitude..”(163) ይላል። በድርጅቱ ውስጥ ፀረ አምሓራ የሆኑ ፕሮፓጋንዳዎች በረቀቀረ ስልት ሲስተጋባቀጥሉበትሲባል ነበር የድርጅቱ ባህላዊ ዝግጅቶች ሲደረጉ ድራማዎች፤ ትዕይንቶች፤ ቀልድ የያዙ አማራን የሚያንኳስሱ መርዛማ ስድቦች በፕሮፓጋንዳ መልክ እየተለወሱ ቅስቀሳ ይደረጉ ነበር።(Political History of the Tigray Peoeple’s Liberation Front -1975-1991- አረጋዊ በርሐ  )

ይህ ቅስቀሳ በትዕይነት በባህል ዝግጅቶች በቀጣይነት ያለማቋረጥ 17 አመት ብቻ ሳይሆን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮም ቢሆንትምክሕተኛ እና ነፍጠኛ” የሚለው ለአማራ የተሰጠው ቅጥያ ሲከናወኑ የትግራይ ሕዝብ አልተቀበለውም ብሎ የሚል ሰው የጀርመን ሕዝብ እና የና ጀርመኖች ፕሮፓጋንዳዎች ግንኙነት በቅጡ ያልተረዳ ሰው ወይንም የብሔረተኞች ተፈጥሮአዊ ፖለቲካ መነሻ እና ግብ ያልተረዳ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔ የፖለቲካም የታሪክም የማሕበራዊም የትግሉም የደም የአጥንት ግንኙነት አንድ የማያደርጋቸው አንዳችም ምክንያት የለም።
ይቀጥላል……….
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay ድረገጽ አዘጋጅ)