Wednesday, November 1, 2023

ይድረስ ለአርበኛ ዘመነ ካሤና መሰል “ታጋዮች”ና ታጋዮች! ብሥራት ደረሰ Posted at Ethiopian Semay blogspot

 

ይድረስ ለአርበኛ ዘመነ ካሤና መሰልታጋዮች ታጋዮች!

 

ብሥራት ደረሰ

Posted at Ethiopian Semay blogspot

11/1/23

ምንም ነገር የመጻፍ ፍላጎት የለኝም፡፡ ጊዜው ሀገራችን ልትወለድ ምጥ የበዛበት በመሆኑ ከመጻፍ ይልቅ የነገሮችን አካሄድ በጥሞና የመከታተያ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ላለፉት አራት አሠርት ዓመታት ገደማ ብዙ ብለናል፡፡ አሁን በክፉም ሆነ በደግ የገነኑ ሰዎች ወደ መድረክ ከመዝለቃቸው ብዙ ዓመታት አስቀድመን ስለሀገራችን መፃዒ ሁኔታ ሣይቀር ጥቂት የማንባል ወገኖች ብዙብለናል፡፡ ከጮህንበት ውስጥ አብዛኛው በተግባር ታይቶ የሀገር ትንሣኤው ብቻ ይቀራል፡፡  ይህ ነባራዊ ክስተት ደግሞ በቅርቡ እውን ይሆናል፡፡ የሀገር ጠላቶችም ግብዓተ መሬታቸው ይፈጸማል – ዓለም እያዬ!!

በዚህን አስቸጋሪ ወቅት ነው እንግዲህ ዝም ማለት ያላስቻለኝ ነገር የተፈጠረው፡፡ ነገሩ ትናንት ማታ ነው፡፡ አንድ ሚዲያ ስከታተለል ታጋይ አርበኛ ዘመነ ካሤ ሲናገር ሰማሁና ሙሉውን አዳመጥኩት፡፡ ጥሩ ንግግር ነው፡፡ ነገር ግን የእስክንድርን ስም ሲያነሳ “ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ” ብሎ እንደቀላል ነገር ሲናገር ስሜቴ ተረበሸ፡፡ እኔ ዘመነን ብሆን “አርበኛ ፋኖ እስክንድር ነጋ” እል ነበር – “አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ፣ ታላቁ እስክንድር…” የሚለው ቀርቶበት አሁን በተሠማራበት የትግል መስመሩ ቢጠራ ማንም አይጎዳም፤ መከባበር ደግሞ ከቤት ይጀምራል፡፡ “ከአነጋገር ይፈረዳል፣ ከአያያዝ ይቀደዳል” እንዲሉ መላ ሕይወቱን ለሀገሩ የገበረን ሰው በዚህ መልክ አሳንሶ መጥራት ለኔ የሸተተኝ ነገር አለ – ጋ ዜ ጠኛ   መ ባሉ   አይደለም ማነሱ   ግን  እስክንድር  በረሃ የወረደው  የፋኖን  ውሎና ውሎና  አዳር  ለመዘገብ  ሣይሆን  ለትግል  እንደመሆኑ  ጋዜጠኛ  ተብሎ  መጠራቱ  ለነገር  እንጂ  ለበጎ  አልመስልህ  አለኝ ፡፡ እርግጥ ነው እስኬው ጋዜጠኛ ነበር፡፡ አሁን ግን አይደለም፡፡ እንዳልኩት  አሁን ሌላ ነው፡፡ የፋኖ አደራጅና ትልቅ ሥራ በመሥራት ላይ የሚገኝ ሁለመናውን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ የሰጠ እንደማንኛውም የፋኖ አባል ሁሉ ውድ ልጃችን ነው፡፡ ጋዜጠኛ መባል ከነበረበት በፊት ነው፡፡ አሁን ግን ይህን ዕንቁ ሰው ወደ ዱሮውና  አሁን  ወደማይሠራበት  የጋዜጠኝነት ሙያ መመለስ ውስጠ ወይራው አልገባኝም፡፡ ለምን?

 የኢትዮጵያ ትንሣኤ ብዙ አሣር እንዳለበት ይገባኛል፡፡ በአንድ ጎራ ባሉ ወገኖች ግን ይህ አሣር መቀነስ አለበት፡፡ ካለፈው ተሞክሯችን መማር አለብን፡፡ እዬዬም ሲደላ ነው፡፡ አማራንና ኢትዮጵያን ክፉኛ እየጎዳት ያለው ይሄ የኢጎ ጉዳይ ነው – ራስን ከፍ አድርጎ የመገመትና ለሌሎች ዝቅተኛ ግምት የመስጠት አባዜ ክፉኛ እያወከን ይገኛል፡፡ ብዙ ሚሊዮን አማራን በነፍሰ ሥጋው እየተጫወተበት ያለው አስጠሊታ ነገር የድል ሽሚያና የሥልጣን ፍቅር ነው፡፡ በዚህ ረገድ አማራ አልታደለም፡፡ ብዛቱና ዕውቀት ጥበቡ እያለው በትንሾች እንደክርስቶስ የሚወገረው የራሱ ልጆች አልስማማ ብለው እርስ በርስ ስለሚናናቁና እንደጅብ ስለሚዘራጠጡ ነው፡፡ መጥፎ ጠባይ፡፡ ካላስወገድነው  ይጨርሰናል፡፡

አራት ኪሎ የሚችለው አንድ ሰው ነው፡፡ 15 ሚሊዮን ፋኖ ቢኖር ሁሉም አራት ኪሎ አይገባም፡፡ 100 ሽህ የፋኖ መሪ ቢኖር ሁሉም ያቺን የምታሳብድና የምታቃዥ ወንበር አይዝም፡፡ በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም የሚባለው አለነገር አይደለም፡፡ በረሃ እያለ በአልደፈርም ባይነት የሚኩነሰነስና በብዙ  አጃቢ የሚቆነን ሰው አራት ኪሎ ቢገባ ምን ሊያሳየን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት  አይከብድምና ከዚህ ዓይነቱ መጥፎ ጠባይ እንድትርቁ ምክራችን የሚያስፈልጋችሁ ወገኖቻችንን ከአሁኑ እንመክራለን፡፡ ሰው ዐይን ውስጥ አትግቡ፡፡ ትሁት ሁኑ፡፡ ትኅትናችሁ ወደላይ ያውጣችሁ፡፡ ላዩን ከፈለጋች ሁ ደግሞ ታቹን ምረጡ፡፡ ከመጽሐፍ  ቅዱስና  ከክርስቶስ  ትኅትናን ተማሩ፡፡

አሁን ደግሞ የወቅቱ ትኩረት የወንበር ጉዳይ ሳይሆን የኅልውና ጉዳይ ነው፡፡ መጀመሪያ የመቀመጫየን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ አማራ በመሆኑ ምክንያት ተወልዶ እንዳያድግ ጽንስ ከሆድ እየተቀደደ ወጥቶ  አንገቱ በቢላ በሚቀረደድበት ሰዓት፣ አማራ ቆሞ ብቻ ሳይሆን ታሞ ተኝቶም መኖር እንዳይችል ከያለበት በአክራሪ  ኦሮሞ እየታደነ በሚታጨድበት ወቅት፣ የአማራ ምድር የሚባለው ሳይቀር በኦህዲድ መከላከያ ተወርሮ ዜጎች ቀን ከሌት እየታጨዱ በሚገኙበት ዘመን፣ አዲስ አበባ መግባት ለአማራ ህልም በሆነበት ሁኔታ፣ የአማራ ቤትና ሰውነት በተረኛ ዘረኞች እየፈራረሰና አማራ ሎተሪ አዙሮ ወይም ዘበኝነት ተቀጥሮ እንኳን መኖር ባልተፈቀደለት ወቅት… እንዲህ ዓይነት ቅንጡ የሥልጣን መራኮት ከአሁኑ ሲታይ በርግጥም የአማራው መረገም ሥር የሰደደ እንደሆነ መረዳት አይከብድም፡፡

ስለዚህ እባክህን ዘመነ ሆይ! እባካ ችሁን ዘመነዎች ሆይ! መጀመሪያ በየቀኑ ለምንታረደው ዜጎች ቅድሚያ ስጡ፡፡ የሥልጣን አራራውና ሽኩቻው ይደርሳል፡፡ ሀገር ሲኖር ለሚደርስ ነገር ጠላቶች እስኪስቁባችሁ ሳይቀር አትወዛገቡ፡፡ አማራን አማራ እንዲህ እየጠለፈው የትም አይደረስም፡፡ ከተሳሳትኩ  ይቅርታ፡፡

ሁሉም ነገር እንደሚጠራ ግን  አሳምሬ   አውቃለሁ፡፡ አማራዊነት እንደሚያሸንፍ ዘመነ ጫካ ከመግባቱ በፊት ብዙ ተጮሆበታል፡፡ የሚያበሳጨኝ ግን በዚህን ወቅት እንኳን ከብአዴን ተምሮ አማራነትንና ኢትዮጵያዊነትን ከማስቀደም ይልቅ የግል የሥልጣን፣  የዝናና የጥቅም ፍላጎትን በማስቀደም ለትዝብት በሚዳርግ ሁኔታ የሚሠራው የጭቡና  የሸር  ሥራ ነው፡፡ ይገርማል፡፡ ፋኖን እግዚአብሔር ከውስጥም ከውጭም ደባና  ተንኮል  ይጠብቀው፡፡ 

 

በመጨረሻም እንዲህ ልበልና ልጨርስ፡፡ በምንም ምክንያት ይሁን በምን አማራን ሊከፋፍልና ለኦሮሙማው የዘር ፍጂት ዳርጎ ሁሉንም አማራ ተራ በተራ ለማስፈጀት የሚንቀሳቀስ ሆዳም አማራ የእነፕሮፌሰር አሥራትና የእነአሣምነው ጽጌ ዐፅም እሾህ ሆኖ ይውጋው፡፡ የአማራን ኅልውና ለግል ጥቅም የሚሸጥ አስመሳይና የውስጥ ባንዳ ሁሉ  ዘር አይውጣለት፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡