Dear Readers;
I want all of you to visit Ethioforum.com and read on Hayelom Araya’s death on the commentary page and see for yourself how the ESAT TV (executive member) and EMF chief editor allowing Tigrayan people to be insulted by psychopathic individuals while he crossed the word I use (fool) in response to the same person use the same word (fool) while Kinfu Assefa allowed the word “fool” to be used to insult Tigrayans. I will have a full follow up on this next week, stay tune.
A message to all Tigrayans; (from Ethiopian semay Editor)
As you know well, we are challenging the bad system of TPLF not our people. But, there are few Ethiopian journalists like Kinfu Assefa the Ex member of the Army during the Derg currently living in Amsterdam/Holland and his associates may be Dawit Kebede also a former Derg Army.( my apology if he is not EMF’s associate at this time- he has to come out and tell us he is not in EMF website as associate editor) who are in the business of bias journalism against Tigrayans. So you know now, based on the two time recent evidence I showed you, shows that there are bias and racist journalist in the opposition that they hate Tigrayans not Meles or TPLF or no body. That was their intention, their intention is by any means using EPLF/OLF supporters acting as Ethiopians allowed to insult Tigrayans to be down graded on EMF. And we Tigrayans and other Ethiopian patriots will not allow that! we have to stick together when bias journalist like Kinfu and his friends target us when it comes against ourselves and our people in the name of politics.
There is no point of me to expose TPLF when it insult the Amhara population, and not fair if I shut my mouth when journalists conspired with racist individuals to insult Tigrayan population to be insulted. We have all kind of enemies inside us, masquerading as political opposition and opposition media.
To see the page/font with a wider range, please press the key Ctrl and + sign. To view the page/font with a narrow range, please press the key CTRL and _ sign.
ላይ የሚታየው የወያኔ ገበና ማህደር አዲሱ መጽሐፍ ለመግዛት $30.00 ዶላር ሲሆን ይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፍ ደግሞ $25.00 ወይንም ሓይካማ የሚለው የትግርኛ መጽሐፌ ደግሞ $15.00 ዶላር ብትልኩ መጽሐፎቹን ማግኘት ትችላላችሁ።Getachew Reda P. O.Box 2219 San Jsoe, CA 95109 getachre@aol.com Phone (408) 561 4836
ባለፈው ሰሞን “የሻዕቢያ ገበና እና ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚ ድርጅቶች” ክፍል ሁለት አቀርብላችኋለሁ ብየ ነበር። ሆኖም ለዛሬ እሱን በመዝለል በሚቀጥለው ሰሞን እንደማቀርብላችሁ ቃል እየገባሁ፤ የዚያን ትችት ክፍለ ጊዜ አሁን የተቀራመተው ፋታ ያልሰጠኝ በቅርቡ “ሲያትል የተካሄደው “ፊረስት ታይም ኢትዮጵያንሰ ፎረም” (ባማርኛ ፈልጌ ስላጣሁ ርዐስሱን በሰየሙት ስም ተጠቅሜአለሁ) በሚል የተካሄደው ስብሰባ ውሸትና ስድብ ሲስተጋባ ዝም ማለት አላስቻለኝም እና እሱን ለዛሬ እንመለከት። ትችቱ ረዘም ስለሚል ከወዲሁ ትዕግስታችሁን እጠይቃለሁ።
በዚህ የመምህሬ የሟቹ የፕሮፌሰር ዓለሜ እሸቴን (ነብስ ይማር!) አባባል ለእነ ግንቦት 7ና መሰሎቹ ባዶነት መገለጪያ የመግቢያ ጥቅስ ልጥቀስ እና ይዤአችሁ ልግባ።
“For some time now this OLF stand has been supported by "well-intentioned" and "patriarchal gurus (with or without hidden agendas) calling for the unity of ETHIOPIAN OPPOSITION PARTIES to topple the Woyane. A rotten apple, plus a rotten apple, plus a rotten apple ---you may continue adding up - will never produce a good healthy apple” (Aleme Eshete (source –“Oromo NefTeNga- When The OLF Political sky Gets Darker. Response to Dr. Ghelawedos Araia. By Getachew Reda September 18, 2003) http://www.geocities.ws/oromosociety/Oromo_and_Nafthenya.html
ይህ ጉባኤ ከሌሎቹ ካሁን በፊት የተደረጉ ኦነግና መሰሎቹ የጨመረ ስብሰባ ውሸትን በማስተጋባት የተለየ እንኳ ባይሆን ለየት ያደረገው ነገር ቢኖር “የኦሮሞ ጥያቄ አንድነት ሃይሎች ነን የሚሉ "ኦነግ ተገንጣይ ነው" እያሉ ለሕዝብ የዋሹት ውሸት እንጂ ኦነግ በውኑም በሕልሙም አልሞበትም፤ አስቦበትም፤ ጽፎትም፤ተናግሮበትም አያውቅም” የሚለውን አስበርጋጊ ደማቅ ውሸት እና እንዲሁም የግንቦት 7 ጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ የሆነው ፊልድ ማርሻል ጀኔራል ዶ/ር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስያትል ስብሰባ አዳራሽ ባነነበበው የጽሑፍ መልዕክት፤ በመመርኮዝ እተቻለሁ።
ብርሃኑ ነጋ
ስለ አንድነት ድርጅቶች እንዲህ ሲል ያጣጥላቸዋል።
“በተግባር የሌሉ; "የቃላት" አንድነት ሃይሎች እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ ክፈሎች ቢሰድቡንም እኛ እንደ ግንቦት 7 መልስ ላለመስጠት በሰለጠነ ፖለቲካ ለመጓዝ ከወሰንን ቆይተናል የተቀራችሁትም ሆነ እነሱ በዚህ ስልታችን እንዲጓዙ ጥሪ እናቀርባለን ሲል ይቆይና ደቂቃ ሳይሞላው እኛን ኦባማን ከተሳደቡት ጽንፈኛ /አልትራ ወግ አጥባቂ/ እና ያበዱ ውሾች ከሚባሉት ነብሰ ገዳዮች ከጆን በርች ሶሳይቲ” ቡድኖች ጋር በማያያዝ የሰደብንን ስድብ ሳዳምጥ ነው “ውሸታሞቹን ስንት ጊዜ እግዚሐር ይማራችሁ እንበላቸው” በማለት ልተችበት የፈለግኩት።
ሰውየው በዚያው ስድብ አልተወሰነም።
"ባንድነት ስም የሚያቅራሩ መፈክር አሰሚዎች እና ፎካሪዎች ነብሳቸውን የምትዳስስ አስፈሪ ነገር አጠገባቸው ስትደርስ አገር ጥለው በመሄድ የመጨረሻዋ ጥይት አንጐነጫለን ያሏትን ሳይጐነጩ እየፈረጠጡ ወደ ውጭ የሄዱ ብዙ ናቸው። መንግሥቱን ጨምሮ!" በማለት አገር ጥሎ; ድምበር ተሻግሮ; ፈርጥጦ የመጣው ጋዜጠኛም ሆነ የፖለቲካ መሪ እና ያገር መሪ ሁሉ ፈርጣጮች ሲላቸው:- አገር ወዳዱ እና ቆራጡ ጀኔራል ብርሃኑ ነጋ ግን አገር ውስጥ ሆኖ እሱን ለመፈተሽ የመጣቺውን "ጥይት" አክሽፎ ፈርሃትን አንበርክኮ "በረከት ስሞንን" ሳይማጠን አሁንም “ፍንፍኔ” ውስጥ "አካኪ ዘራፍ! የነጌ ልጅ! እያለ በመታገል እንዳለ በማስመሰል “ፈርጣጮች” ሲል የተመጻደቀበትን ስድብ ጨምሮ እንመለከት።
በኦነግ ልጀምር።
ኦነጐች እና ወያኔዎች ያጣላቸው መሰረታዊ ነገር እንደምታውቁት ኦነግ “የኦሮሞ ጥያቄ የኮሎኒ ጥያቄ ነው ያለ ቅድመ ኩነት መገንጠል እችላለሁ” ሲል ወያኔ እና ሻዕቢያ ያወጡት ባለ 66 ገጽ ማኒፌስቶ ደግሞ ‘የኦሮሞ ጥያቄ አንደ ማንኛውም የናሽናል/ብሔር ጥያቄ እስከ መገንጠል ድረስ ነው” በሚል ነው የተጨቃጨቁትና ወደ መተናነቅ የደረሱት። አሁን ኦነግ እነ ብርሃኑ ነጋን እየኰበኰበ ወያኔ የጋራ ጠላት ነውና አብረን እንምታ ሲለው; ብርሃኑ ተመልሶ የማይጨው ውርደታችን እየነገረን “ኦነግ የ100 ዓመቷ ቄሳራዊት ኢትዮጵያ ያስቆጣቺው ልጅ ስለሆነ “ናልኝ ሟሙሽ” እያላችሁ አስገቡት” ብሎናል። ሃብል ባንገቱ ያጠለቀ በሞቀ አልጋ የሚተኛ ክራባት አሳሪ ;በአዳራሽ “የአበባ ጉዝጓዝ” የለመደ ሽምቅ ተዋጊ አውሮጳና አሜሪካ ለመሸገ ነጻ አውጪ "የሟሙሽየ" "እፍ እፍ" ስልት ያታልለዋል ወይ አያታልለውም አብረን በሂደት እንመለከተዋለን።
አረጋዊ በርሔን/እና ሁለቱ የሻዕቢያ መንግሥት በVolunatry/በጐ ፈቃደኝነት ለሻዕቢያ ስራ አስፈጻሚነት ደጀ ጠኚዎች (ግንቦት7 እና ኦነግን) የጨመረ የስያትል ስብሰባ ከተካኼደ በኋላ “በኢትዮ-ሚዲያ” ድረገጽ ላይ ከስያትል ከአንድ “ግዕዝ ተናጋሪ” ኦነግ የተለፈፈው የውሸት ዕልልታ ጽሑፍ ጨምሮ ኢትዮ-ሚዲያ አዘጋጅ አብርሃ በላይ የለጠፈውና ያጋነነው ደማቅ ውሸት እንዲሀም እራሱ የኦነግ ጸሐፊ ነኝ የሚል “አሚን ጃንዳይ” ያስተላለፈውን ሃሰት ሁሉ እንመለክታለን።ወይ ትጉዱ! ይኼ ትግሬ ደግሞ ምን አመጣብን እንዳትሉ “የፊልድ መርሻሉ”ንግግርን ነው የማስደምጣችሁ። አትቸኩሉብኝ የፈጠራ አይደለም።
ኢትዮጵያን ላለመጥራት ተጠይፏት “ያቺ አገር” እያሌ አስሬ ሲጠራት ኢትዮጵያ አይደለሁም ወይንም ነኝ ለማለት እና ላለማለት ተቸግሮ ዳር ዳሩን ሲዞር የዘላበደውን የኦነጉን ፀሐፊ ንግግር እንጀምር። “የኦነግ አጀንዳ መገንጠልን ነው ብሎ ማሳነስ አይገባም።” “የኦሮሞ ሕዝብ ከትግሬው ከአማራው…እንደዚህ አይነት አገር (ኢትዮጵያ) የምትባል አገር እንመስርት ብሎ የተፈራረመበት ወቅት የለም።”
እሰኪ እዩት ይህ ቅዠት ምን ይባላል? ኦነግ በዓለም ውስጥ ያልታየ አገራዊ ምስረታ “ፌርማ” የሚለው ከየት አንዳመጣው አይገርማችሁም። አሜሪካ እንግሊዝ ጣሊያን ሩሲያ ቻይና….ሀሉም እየተፋጀ እየተጋባ እየተገበያየ ነው አገር የመሰረተው በፌርማ እንዳልሆነ እየታወቀ።ኦነግ በዚህ በተመራመረ ዘመን “አገርን” የሚያክል የፈጣሪ ትልቅ አገራዊ ምስጢር እረስቶት ልክ እንደ ባልና ሚስት “ በጋብቻ ፌርማ” አገር እንደማይቀና እና እንደማይመሳሰል እየታወቀ ኢትዮጵያ ስትመሰረት “የቤት ህንፃ” ይመስል ‘ፌርማ” ሚባል ነገር አልነበረም; ካለ ደግሞ አሳዩን ሲለን “ኦነግ” በግብዝ መሪዎች የተሞላ ብቻ ሳይሆን ድርጅቱ ጭራሽኑ የባሰበት በሽተኛ መሆነን ተረዱልኝ።
ነገሩ “ግንጠላ” የምትለዋን ቃላት በዘዴ በማምለጥ ('ሰታብሊሽመትን' ተክቷታል) ሲሞክር ኦሮሞ ያለው ከቦታው “ኦሮሚያ ሪፑብሊክ” ውስጥ ነው፤ የተፈራረምንበት አገራዊ ምስረታ የለም: ስለዚህ ከማን ነው የምንገነጠለው በማለት በዘዴ ለመሸወድ ፈልጐ ነው። “የኦሮሞ (ህዝብ) ያለው በቄዬው ነው፤ ታዲያ (የኦሮሞ ህዘብ ) ማንን ወረረ? የማን አገር ወሰደ?” እንግዲህ ኦሮሞ ያለው ከቄየው ነው! ከማን ነው የሚገነጠለው?" ሲል አድማጮቹ ሳይገባቸው ይሁን አውቀውት ጭብጨባውን አቀለጡት። ኦነግ ሲታመም አብረው የሚታመሙ ክፍሎች አሉ ማለት ነው። ቁንጪ ሓሚሙ ቁማል ተሓጒሙ (ትግርኛው) “ቁንጫ ታሞ ቅማል ዋግምት ገባ” (መሰለኝ ትርጉሙ)።
ልክ የነጋሶ ጊዳዳ ድርጅት አዲስ አበባ ውስጥ በቅርቡ ጋዜጠኞች “ስለ ግንጠላ አስመልከቶ ”በአንደነት ግምባር ውስጥ የተካተቱ የብሔር ድርጅቶች መገንጠልን ያካተቱ ወይንም በመገንጠልን እንደ መብት በፕሮራማቸው ያሰፈሩ እና የሚያምኑ አሁንም ካሉ ሲጠየቅ; በድርጅታችን ውስጥ “እስከ መገንጠል የሚያምኑ አሉ፤ ቢሆንም ‘ለማስገንጠል እንታገላለን” ከሚለው ይለያያል። አዎ ላለማለት በዘዴ ለመሸሽ ሲል የቃላት ጨዋታ ውስጥ እንደገባው ማለት ነው። የኦነጉ አማን ጀናዳይ ይሁን ነጋሶ ጊዳዳም ብቻ ሳይሆን በቃላት ጨዋታ የሚሸውዱ ብርሃኑ ነጋ “ባላጋራ” “ጠላት” ምናምን እያሉ ቃላት ጨዋታ ውስጥ እንደሚገባው ዓይነት ማለት ነው። የዶከተር ጌታቸው በጋሻው እማ አይወራ “ኦነግ ነጻ ኦሮሚያን እመሠርታለሁ ሲል ሰምቼ አላውቅም” (see Allula አሉላ አባ ነጋ ፓል ቶክ ሩም http://www.abugidainfo.com/amharic/?p=6954 ),
ትዝ ይላችኋል የድሮው የዶክተር በየነ ጴጥሮስ የሕዝብ ግንኙነት የዛሬው የግንቦቱ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ኤፈሬም ማዴቦ የተባለው ሰው ስለ ኦሮሞ ነጻ አውጪ ትርጉም ሲነግረን? በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር እና የኦሮሞ ነፃነት ግምባር ልዩነት የማይገባቸው ደንቆሮዎች አሉ፡ብሎናል ኤፍሬም ማዴቦ የቃላት ስንጠቃ ውስጥ ሲገባ። እንደ እኔ የገረመው ወዳጄ አቶ ጊዜው ደረሰ “አዘለም አሉ አቀፈ ሁሉም ተሸከመ ነው” ብሎ የአማርኛውን አጠቃቀም ዘይቤ አስተማረው። ልክ አንዳርጋቸው ጽጌ የጻፈው ዘረኛው “የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” ስለሚለው መጽሐፉ ተጠይቆ ዘረኛ መጽሐፍ መሆኑን ለመሸፋፈን ሲመክር “መጽሐፍም ነው ለማለት አይቻልም። ያው ትንሽ ገጽ ያላት መጽሐፍ ብጤ ነች….” ይላል። ሰዎቹ ጥፋታቸውን ላለማረም ይቅርታ ተሳስተናል ማለት ዳግቷቸው ላለማመን እንዴት እንዴት ዙርያ ጥምጥም ዳር ዳሩን እንደሚሸሹ ማየት ያሳዝናል።“አንተ ነጋዴ እያላችሁ ለምን ትሳደባለችሁ ገበያ ከደመቀ ምን ደኅና አለ።” መጽሐፈ ጨዋታ ገጽ 20 (አሁንም ወዳጄ የላከልኝ ግሩም መጽሐፍ ካገኘሁት)::
ወደ አሚን ጃንዳይ ንግግር ልቀጥል
“ ስለዚህ የኦሮሞ ጥያቄ አሳንሶ ወደ መገንጠል ጥያቄ ለመውሰድ የሚፈልጉ ቡድኖች ወይንም ሕዝቦች የኦሮሞን ሕዝብ ችግር መፍትሔ ላለመስጠት የተደረገ መከራ/ዱለታ ነው እንጂ የኦሮሞ ነፃ አውጪ የኦሮሞ ሕዝብ (ኦሮሚያ ሪፐብሊክ የሚባል አገር ለመመስረት እታገላለሁ ብሎ አያውቅም) ይገንጠል ብሎ አንድም ቀንም አልተናገረም የጻፉትም እስከነመረጃቸው መምጣት ይችላሉ።” ይላል አሚን ጀንዳይ (የኦሮሞ ነፃ አውጪ ዋና ጸሐፊ/ “የኦሮሞ ነፃነት ግምባር” ብየ በአቶ ኤፍሬም ማዴቦ አጠራር ልጠቀም 'እንዳይቆጣ') ልብ በሉ። የኦነግ ጥያቄ የመገንጠል ጥያቄ መሆኑን ባንዴራው እያውለበለበ 40 ዓመት የዋሸውን ውሸት ግጥም አድርጐ ክዷል።ይህ አባባል ፖለቲካውን ያልገባቸው እና የኦነግ ውሸታም እና ዳር ዳር ሩጫ ባሕሪ ያላወቁ ሰዎች “መገንጠል ጠይቆ አያውቅም” ሲላችሁ ኦሮሞዎች የሚኖሩት በተፈጠሩበት ስታብሊሽድ በሆነው “ኦሮሚያ ሪፑብሊክ” በምትባለዋ ኦሮሞ የሚባል ሰው ሁሉ የትም ይኑር የትም በሚኖርበት አገርና ቦታ ሲፈጠር የኖረበት ስለሆነ ከየት ነው የምንገነጠለው እያለው ያለውን አበክራችሁ መመለከት ያስፈልጋል። ስለዚህ የምንገነጠለው ከየት ነው? የሚለው አባባሉ ይግባችሁ። የሚገነጣጠሉት በኦሮሞ መሬት /ድምበር “ዙርያ የከበቡትን ጎሳዎች ባዲሲቷ ሪፑብሊክ ስፋት/ስታብሊሽመንት የሚጋረዱት ናቸው እንዳይገናኙ የሚጋረዱት/የሚገነጣጠሉት እንጂ ትልቁ ሰፊው አሮሚያ አይደለም የሚገነጠለው/ የሚጋረደው ማለቱ ነው (ከሁሉም ጋር መገናኘት ይችላል ማለቱ ነው)። ይኼ በጣም ወንጀል ነው።
ሳይታወቀው ሸወድኩኝ ብሎ ያመለጠቺው አንዲት ሐረግ ቱክረቴን የሳበቺውን ግን ልግለጽ። እንዲህ ይላል “ስለዚህ የኦሮሞ ጥያቄ አሳንሶ ወደ መገንጠል ጥያቄ ለመወሰድ የሚፈልጉ በድኖች ወይንም ሕዝቦች የኦሮሞን ሕዝብ ችግር መፍትሔ ላለመስጠት የተደረገ መከራ/ዱለታ ነው። ይላል።”
“ናተንስያ ንሓመተን” (የራሷን ለአማቿ )“የማየን ወደ አባዬ” አድርጎ ተወቃሾቹ “እኛ" ተገንጣዩ ከግንጠላው አጀንዳ ከተገንጣይነት “ነፃ” ለማድረግ መሞከሩ አስገራሚ ይሁን እንጂ፡ የመገንጠል ጥያቄ በፖለቲካ ስነ አስተዳደር ችግር እንደ መፍትሄ ከተወሰደ የመጨረሻው “አተላ” መሆኑን ብዙ ዓመት ስንናገረው “ግንጠላ መፍትሄ አይሆንም” ስንል ብዙ ሰዎች እኛኑን “ነፍጠኞች” እና “የነፍጠኛ አመለካከት” ነው እያሉን ነበር (ተመጻዳቂው ኦነግ እራሱ ጨምሮ)። ዋናው የመገንጠል አቀንቃኙ “አሚን ጀንዳይ”
መገንጠልን ለኦሮሞ ሕዝብ እንደ መፍትሔ የሚያቀርቡ “የሚያሳንስ” “ትንንሽ ሰዎች የሚያነሱት “የወራዶች” ጥያቄ/አጀንዳ’ መሆኑን ይሄው አውቆም ሳይውቅም ብቻ ያንን አስረግጦ በማመን “ነፍጠኛ” ከመበል ነፃ አውጥቶናል:: “ወፊርካ እቶ” ይላል ትግሬ “ውለህ በሰላም ግባ” እንደ ማለት።
ተገንጣዮች አይደለንም! መገንጠል “የደደቦች አጀንዳ” ነው ብሎ ኦነግ አለ፤ ብንላችሁ አታምኑንም ነበር።ደግነቱ በራሱ ወንበር አዘጋጆች ድረገጽ ውስጥ መነገሩን በጀን። ያ እንዳለ ሆኖ፤ ሚስተር አማን ጃንዳይ ስለ ተናገረው “ኦሮሞ በቀዬው ውስጥ ነው እየኖረ ያለው ማንም ሰው/ጐሳ መሬት አልወረረም/ወርሮ አያውቅም” እና “ኦነግ የኦሮሞ ሕዝብ ይገንጠል ብሎ/ኦሮሚያ ሪፐብሊክ ለመመስረት እንድም አጀንዳ አቀንቅኖ አያውቅም” ያለውን ውሸት ስታሸት ከግማቱ ብርታት የተነሳ ሽቅብ ይላሃል። ትግሬዎች እንዲህ ዓይነት ደማቅ ውሸት ሲሰሙ ብቻ ሳይሆን እያወቀም ቢሆን ሆን ብሎ ሁኔታውን ለመመዝመዝ መስመሩን የሚያጣምም ውሸታሙን “ለኽባጥ” ይሉታል። ማለትም “አቋመ ቢስ/እዚህም እዛም የሚረግጥ ጦጣ” “በሁለት እግር ሁለት ዛፍ ባንዴ ለመውጣት የሚሞክር” ማለት ነው። ግልጽ ለማድረግ “ካብ ኪሒዱ ዝርታዕ አሚኑ ዝካታዕ” ማለት ነው። “ክዶ ከመረታት አምኖ የሚሟገትና የሚሸነፍ ሰው ክብር አለው” ማለት ነው።
ኦነግ በአጀንዳው ውስጥ የመገንጠልን ጥያቄ በፍጹም አንስቶ አያወቅም ብሎ ከሚናገር “ደማቅ ውሸታም” ይልቅ የመገንጠልን ጥያቄ አቅርበናል ነገር ግን አሁንም አቋማችን እንዳለ ነው ወይንም አሁን ትተናል ብለው የሚሟገቱኝን አቋማቸው ግልጽ ያደረጉ ኦነግያኖች አከብራለሁ። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ምን እንደሚፈልጉ ግልጽ ነው። ኦነግ የመገንጠል አጀንዳ አልነበረውም የለውም /አልጻፈም/ አልተናገረም/መዝገበን ፈትሾ መገንጠል ነገር አይገኝበትም/ ልገንጠል ብሎ አልጻፈም…ወዘተ የሚል የደመቀ ውሸት እና አራዳነት የሚያስተጋባ ግለሰብ ግን በጣም አታላይ፤ ሆን ብሎ የታዳሚውና ያታዛቢውን ሕሊና ዝቅ አድርጎ በመመለክት አድማጮቹን “ሞኞች” ብሎ የሚሳለቅ ሰው ነው።
ካገር ቤት እየሸሹ ለብዙ ዘመናት የጫካ ህይወት በመጥላት እነኚህ የኦሮሞ ነፃ አውጪ መሪዎች ነን የሚሉን በኦሮሞ ስም የሚነግዱ ቁጥር ስፍር የሌላቸው በአውሮጳ እና አሜሪካ የሚኖሩ "መሪዎች" በጣቶቻቸው ቀለበት ባንገታቸው ሃብል በትላልቅ አልማዝ እና ወርቅ አሸብርቀው ውድ የሆኑ መኪኖች እየነዱ እና ውድ በሆኑ ቤቶች እየኖሩ ህይታቸው የሚገፉ እነኚህ “የውሸት ሽምቅ ተዋጊዎች” (ቫኒላ ጉሬላ) ነው የሚባሉት? ካልተሳሳትኩ? ሳይሆን የሚገርሙኝ እነሱን ሚከተሉ አባሎቻቸውን በጣም አዝንላቸዋለሁ።
ከወራት በፊት የአርሊነግተን ስብሰባ ውስጥ ብርሃኑ ነጋ እና አዲሱ “የኦነግ ጸናጽል” ደ/ር ጌታቸው በጋሻው ሆነው ስለ ኦነግ ማንነት ሲዋሹን፡ ዜግነቴ ኦሮሞ ነው የሚል አንድ ወጣት “ዕድሜ ለኦነግ “ኦሮሞ ነኝ” ብየ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ቆሜ ደፍሬ እንድናገር ስላደረገኝ ኦነግ ምስጋና ይግባውና “ቅንጅት” አንድ ባሕል ፤አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ቋንቋ፤አንድ አገር የሚለውን አጀንዳው አሁን ደግሞ ግንቦት 7 በፕሮግራሙ ሊደግመው ይሆን? ይህን በሚመለከት ምንድነው አቋማችሁ?” ብሎ ብርሃኑን የጠየቀው ትዝ አለኝ::
(የኦነግ አባሎች እንዴት በውሸት ቅስቀሳ እንደሚወናበዱ ለማሳየት ምሳሌ ልስጣችሁ ብየ ነው)።
ጠያቂው እንዲህ ብሎ ሲጠይቅ፡ ብርሃኑ ነጋ አንጀቴን ያኔ አራሰኝ (ከዚያ ሁለ የብርሃኑ ነጋ ሙጃና አራሙቻ የሞላው አቅማዳ ውሸቱ ማለቴ ነው)። ብርሃኑ ነጋ እንዲህ አለው፡ ‘አንተ በየትኛው የቅንጅት አጀንዳ ነው እንዲህ ዓይነት የተዛባ መረጃ ያገኘኸው? አንተ ነበርክ አዲስ አበባ? እኔ ነበርኩ አንተ አልነበርከም የኔ ወንድም! እንዲህ ብሎ ነገር አንድም ቅንጅት ፕሮግራመ ላይ አታገኘኘም። ቅንጅት በሌላው ነገር ማማት ትችል ይሆናል እንጂ “በስቱፒዲቲ” ልተከሰው አትችልም። አልተባለም። የት አንዳገኘኸው እና ማን እንደነገረህ ልትነግረኝ ትችላለህ? ብርሃኑ ነጋ ዝርዘር ፕሮግራሙ አጠር አድርጐ ሲጠቅስለት ...” “ኦነግየው” ቆማ ሳታስበው ጐርፍ የወሰዳት ጥጃ መስሎ “ሰመም” (ሲንሳፈፍ) ሲል አይቼው፡ - ያኔ ብርሃኑን እውነት “በመናገሩ አመሰገንኩት”።
እነኘጂ የመሳሰሉ የዋህ ተከታዮቻቸውን እየዋሹ ነው ኦነጎች እስከ ዛሬ 40 ዓመት የበሰበሱት።
መሪዎቹ በጎረቤት አገር ኬኒያም ሆነ ኡጋንዳ አሜሪካም ሆነ አውሮጳ እየኖሩ ለምን ጫካ ይዛችሁን አትኼዱም ብለው ጠይቀዋቸው አያውቁም። ምክንያቱም ተከታዮቻቸውም ሙቀቱ ለምደውታልና ብርዱ ጥማቱ የኦሮሞ እረኛ የምስኪኑ ገበሬ ልጅ እንዲቀምስላቸው ስለሚፈልጉ እነሱም “ኦሮሚያ ኦሮሚያ ሪፑብሊክ” እያሉ ሃምበርገር እየገመጡ “ራፕ-ሚዩዚክ” እያደመጡ አብረው በውሸት ዓለም ተዘፍቀዋልና የሚገርም አይደለም። እውነቴን ነው የምነግራችሁ! ነፃ አውጪ አውሮጳ እና አሜሪካ አገር ውስጥ ምን ሥራ አለው?
እነኚህ የዋህ የኦነግ ከበሮ መቺዎች ብቻ ሳይሆኑ የአሚንን “ደማቃ ውሸት” በጭብጨባ ሲክቡ የነበሩት እነ አብርሃ በላይ (ኢትዮ ሚዲያ እና ስማቸው አሁን ለጊዜው ለመጥቀስ ያልፈለግኳቸው በይደር የያዝኳቸው የድሮ የወያኔ አባሎች) በድረገጹ ላይ የለጠፈው ደማቅ ውሸት እስኪ እንብቡትና ተወያዩበት እነሆ፦
“Amin Jundi: secessionism has never been the agenda of the Oromo people Ethiomedia | November 17, 2011” SEATTLE - Amin Jundi, Secretary of the Oromo Liberation Front (OLF), said reducing the quest of the Oromo people for democracy and justice to "secessionism" was unfair since "secessionism" has never been the agenda of the Oromo people nor of the OLF. Impressive in presenting his ideas both in Oromiffa and Amharic languages, the articulate Amin Jundi brightened the mood of the audience that has for a long time been forced to portray the OLF as a separatist group. Aregawi Berhe of UEDF and Berhanu Nega of Ginbot 7 also dwelt at length how to consolidate the opposition camp and move on to dislodging the tyrannical regime of Meles Zenawi.”
ልዘርዝረውና እንወያይ። አብርሃ በላይ- አሚን ጀንዳይ የዋሸውን ውሸት ምን ሲል እንዳደመቀለት እነሆ “, the articulate Amin Jundi brightened the mood of the audience that has for a long time been forced to portray the OLF as a separatist group.” እንግዲህ ኦነግ ሳይሆን እኛ ነን በአድማጩ ሕሊና ውስጥ “ኦነግ የመገንጠል አጀንዳ ያለው” ብለን “ያልዋለበትን ያላለመውን፤ያለ ስሙ እና ያለ ዓለማው በመስጠት” ዋሽተን ለብዙ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳስተን እንዲያምን በማድረግ ኦነግን በአድማጭ ሕሊና ተገንጣይ ነው በማለት እንዲጠላ ያደረግነው ሲል እኛኑን ወንጅሎናል። ያውም (ሃዝ ቢን ፎርስድ) የምትለዋን ሀረግ ንከስዋትና “the audience that has for a long time been forced to portray the OLF as a separatist group”
አብርሃ በላይ የተቀበለው እና ያደመቀው ውሸት አሚን ያለውን በማድመቅ ብቻ ሳይሆን እሱም አምኖበት “ውንጀላው/accusation” አርቲኩለት” እንደሆነ ነው የገለጸው። ጃንዳይም እንዲህ ሲል ይወነጅለናል፡
“የኦሮሞ ጥያቄ ወደ መገንጠል ጥያቄ ለመወሰድ የሚፈልጉ በድኖች ወይንም ሕዝቦች የኦሮሞን ሕዝብ ችግር መፍትሔ ላለመስጠት የተደረገ መከራ/ዱለታ ነው እንጂ የኦሮሞ ነፃ አውጪ (ኦሮሚያው ሪፓብሊክ የሚባል አገር ለመመስረት እታገላለሀ ብሎ አያውቅም) ይገንጠል ብሎ አንድም ቀንም አልተናገረም የጻፉትም እስከነ መረጃቸው ማምጣት ይችላሉ።”
መዝገቡን ላቅርብ እነሆ፡
The Oromo Liberation Front (OLF) is a political organization established in 1973 by Oromo nationalists to lead the national liberation struggle of the Oromo people against the Abyssinian colonial rule.( OLF USA Office P.O.Box- 73247 Washington, DC 20056SA-USA-Phone #: (206) 462-5477 Ext. 202-Fax #: (202) 332-7011) አሁንም ተለጥፎ በፕሮገራሙ የሚነበበው ሕያው መመሪያው አንደሆነ ማረጋገጥ ከድረ ገጹ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
አልቀየረም።
-MAP OF OROMIYA REPUBLIC – shows- MORE THAN HALF OF ETHIOPIAN TERRITORY EXTENDING TO ABAI IN THE NORTH AND HARAR IN THE EAST. Capital sity of Ormia Republic – Finfine (እንደ ላይኛው)።
እንግዲህ በዚህ ፕሮግራም ስትመለከቱ
The aim of the Oromo struggle led by the OLF is only to gain back our country that was taken away from us by force. It is not, in any way, against the rights of any other people. (OLF USA Office P.O.Box- 73247 Washington, DC 20056SA-USA-Phone #: (206) 462-5477 Ext. 202-Fax #: (202) 332-7011)
ይህ የሚለው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት ፕሮግራም እና በድረ ገጹ ተለጥፎ ዛሬም የሚታይ ነው። ብዙ በኦነግ የሚጠሩ ኦ ኤል ኤፎች አሉ። ታዲያ ማንኛቸውን ኦነግ እንመን? ሁሉም በኦነግ ነው የሚጠሩት። መልከአ ምድሩ “ሪፑብሊክ ኦፈ ኦሮሚያ” ይላል “ስፋቱ ሦስት አራተኛ ያገሪቱ የቆዳ ስፋት በካርታው አስቀምጦታል” ታዲያ መጠሪያቸው “ኦ ኤል ኤፍ” (ኦነግ) ፕሮግራማቸው አንድ ሰንደቃላማቸው አንድ ጽሑፋቸው “ላቲን” እና “ሁሉም “ዜግነታችን ኦሮሚያ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለም፤ለ ኢትዮጵያ ባዕድ ነን” ብለው ራሳቸው የሚገልጹ ከኣእላፍ ኦነጐች ማንን ለይተን “አይደለንም ሲሉን ኢትጵያዊያን ናቸሁ እንበል?” (ናችሁ ካልን ደግሞ “ሰስድብ አለ፤ ኦሮሞ አንጂ ኢትጵያ አየደለሁም” ብሎ እስኪ በቃህ ይሰድብሃል።
ታዲያ እንዴት መገንጠልን፤ የኢትዮጵያ አንደነትና አገር ማፈራረስን አያቀነቅንም ማለት ይቻላል? የ ኦነጉ ጸሓፊ “አማን ጃንዳይ” ኦ ኤል ኤፍ አገር ለመገንጠል አልተነሳም አላለም ፤አልጻፈም ይላል። ፕሮግራሙ ግን ከላይ ያነባችሁት ነው። ታዲያ ከዚህ የባሰ የደመቀ ውሸት አለ? ይሄ ነው ደማቅ ውሸት የምላችሁ። ደማቅ ውሸት ደግነቱ እንደ ባውዛ (ሓዊ ለይቲ (በትግርኛ) አማርኛ “አጭበርባሪ ብርሃን” ልበለው) ደምቆ ይቆይና በጨለማ ዓይንን ያስደሰተ አጭበርባሪ መብራት በደቂቃዎች ራሱን በልቶ ከድቶህ ይጠፋል። ዓይንህ ተጭበርብሮ ጭለማ ውስጥ ተውጠህ ቁጭ!
እውነት እኛ ነን ሕዝቡን ኦነግ የመገንጠል አላማ አለው ብለው በፕሮግራሙ እንደ መመሪያው ያሰፈርንለት? አብርሃ በላይ “ፖርትረይ” ሲል ምን ማለቱ ነው። ያልሆነውን ሆነ ብለው ሚናገሩ መላት ነው። እኛ በገዛ አጀንዳው ውሸታሞች ሆነን ኦነግ አውነተኛ ሲባል፤ “ዘበን ያ ግርመቢጥስ ማይ ንዓቐብ” (!?) ግርምቢጠኛ ጊዜ ከላይ ወደ ታች መዝነቡን ትቶ ከታች ወደ ላይ ሲዘንብ ይህ ተገላቢጦሽ ዘመን ምን እንበለው?”
ፖለቲካ ለማሳመን አንዳንድ ቅመም መቀመም የታየ የተለመደ ብልሃት ነው። ነገር ግን ራስህ ፈስተህ ፈሳሽብኝ እሳ ምነው? ስትላት ለዚህ ውሸት ምን የሚባል ስም ይውጣለት? ለዚህ ነው ባለፈው ሰሞን ትችቴ ውስጥ ተቃዋሚ ነን የሚለት ድረገፃች አብዛኛዎቻቸው ወገንተኞች ብቻ ሳይሆኑ ውሸትን እያደመቁ ሕዝብን እያሳሳቱ ነው፡ ያልኩት ከላይ በኢትዮ ሚዲያ አብርሃ በላይ የተለጠፈው ውሸታሞችን “አርቲኩሌት” “አስተዋይ/ብልህ” እያለ ያለውን “የፖለቲካ ደላላነት” (ሎቢ) አስተውሉት ። የኦነጉ “አሚን” ኦነግ ልገንጠል ብሎ በአጀንዳው ጽፎም ተናግሮም አያውቅም ብሎ ዑውር ውሸት ሲዋሽ ሰው ምን ይለኛል ብሎ “ትንሽ ሃፍረት’ አልተሰማውም። ምክንያቱም የውሸት በሸተኞች ሲዋሹ እየዋሹ እንደሆነ አይታወቃቸውም እና ልዩ የሕሊና ሕክምና ያስፈልጋቸዋል። የሰከረ ሰው “ሰክራሃል” ስትለው አንተነን ተመልሶ “ውሸታም አልሰከርኩም” እንደሚለህ ሁሉ ማለት እኮ ነው።ከውሸታሙ ይልቅ ውሸቱን የሚያደምቁለት በሁለተኛ ደረጃ የታመሙ አዳማቂ በሽተኞችን ስንት ጊዜ “ይማራችህ” እንበላቸው? “ወትሩ ሕሙም ክንደይ ጊዜ ይብጻሕ? “ለረዢም ዓመታት የታመመን በሽተኛ በደረስከው ቁጥር ስንቴ “ እግዚሔር ይማርህ” ማለት ይቻላል?” ይላል የትግሬ ሰው። እውነትም ስንት ጊዜ ይማራችሁ እንበላቸው?
የገረመኝ ነገር ደግሞ አማን ደረቱን ነፍቶ ኦነግ ሰው አልገደልም፤ ምንንም ህዝብ አልበደለም ይላል። በግድያ መሳተፉን መረጃውን ይመልከቱ
አሁን ወደ ብርሃኑ ነጋ እናምራ።
ብርሃኑ ራሱን በውሸት ሲያሞካሽና ሲክብ “ቢሰድቡንም አንሳደብም” ሲል ይቈይና በሰከንድ የተናገረውን ስልጡን ንግግሩን ጥሎ ወደ ፋራ ፖለቲካው ወደ “ሰድብ” ይገባል። እራሱ ፈርጥጦ እንዳልፈረጠጠ ሁሉ ሌላውን ፈሪ እና ፈርጣጭ ሲል ጭብጨባ ተለግሶለታል። መረጃው እንሆ።
“ራሳቸውን በቃላት “የአንድነት ሃይሎች” እያሉ ራሳቸውን የሚጠሩ ሃይሎች ድርጊታቸው የአንድነት ጠላትን ሚያጠናክር እንደሆነ ልንነግራቸው ይገባል። ግንቦት 7 ከማንኛቸውም ድርጅቶች ግምባር ቀደም “የተግባር ድርጅት” ነው ብየ በድፍረትና በሙሉ ልብ ለመናገር እችላለሁ (ሞቅ ያለ የተለመደው የበሽተኞቹ የጭብጨባ ሱስ ይደመጣል) ። ግንቦት 7 በአንድነት ጥያቄ ያለው ተግባር እና ተግባራዊ እንቅስቃሴ በ ግቡ ለመጠየቅ የሚሞክሩ ሃይሎች እዚህ አሜሪካን አገር “የፕረዚዳንት ኦባማን ዜግነት ከሚጠይቁ አክራሪ የፖለቲካ ሰዎች “የደበርዘር ሙቭመንት” ከሚሉት ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር አለ።….
…አይገባውም ብለው ከሚንቁት ሕዝብ መሃል ጊዜያዊ ድጋፍ ለማግኘት ብቻ ሲባል የሚነሱ “ኦባማ”እንዳለው ‘የፖለቲከ ማስመሳያ ቀልድ ጊዜ ወይም “ፖለቲካል ሲሊሲዝም” ገላጮች ብቻ ነው። ከማንም ጸረ ወያኔ ከሆኑ ኢትዮጵያዊ ሃይሎች “ምንም ዓይነት ያመለካከት ልዩነት ይኑረን” ከነዚህ ሃይሎች ጋር “አላስፈላጊ እንካ ስላንትያ”ላለመግባት ድርጅታችን ከተቋቋመ ጀምሮ በተግባር እየፈጸመ ያለውን ውሳኔ አሁንም እያከበረ እንደ ሚቀጥል ይህም ለወደፊቱ አስፈላጊ አወንታዊ የስነ ልቦናዊ ድባብ ስለሚፈጥር ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች የምር እንዲወስዱትና ከልብ እንዲተገብሩት በአጽንኦት እጠይቃለሁ። አመሰግናለሁ” ብርሃኑ ነጋ። Dr. Berhanu Nega's speech on Ginbot 7 and Ethiopian Unity http://youtu.be/B8Ytx8e2cW4)
“ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፍቅር በምን ይለካል? ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መፈክር ከሚያወርዱት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው የመጨረሻዋን ጥይት ተጐንጭተው ቃላቸው በተግባር ፈጽመው አለፉት? መንግሥቱን ጨምሮ! (ብርሃኑ ነጋ ከሲያትል ንግግሩ የተገኘ) ምንጩን ለማየት ዩ ቱብ ገብታችሁ (Dr. Berhanu Nega's speech on Ginbot 7 and Ethiopian Unity http://youtu.be/B8Ytx8e2cW4) አድምጡ።
ለመሆኑ ግንቦት 7 መልስ ላለመስጠት በሰለጠነ ፖለቲካ ለመጓዝ ከወሰንን ቆይተናል የተቀራችሀትም ሆነ እነሱ በዚህ ስልታችን እንዲጓዙ ጥሪ እናቀርባለን ሲል ይቆይና ደቂቃ ሳይሞላው እኛን ከኦባማ ጽንፈኛ /አልትራ ወግ አጥባቂ እና ያበዱ ውሾች ከሚባሉት ነብሰ ገዳዮች ከጆን በርች ሶሳይቲ” ጋር በማያያዝ የሰደብንን ስድብ እሱ ከሚለው “ምንም ዓይነት ያመለካከት ልዩነት ይኑረን” ከነዚህ ሃይሎች ጋር “አላስፈላጊ እንካ ስላንትያ” ላለመግባት ድርጅታችን ከተቋቋመ ጀምሮ በተግባር እየፈጸመ ያለውን ውሳኔ አሁንም እያከበረ እንደ ሚቀጥል ይህም ለወደፊቱ አስፈላጊ አወንታዊ የስነ ልቦናዊ ድባብ ስለሚፈጥር ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች የምር እንዲወስዱትና ከልብ እንዲተገብሩት በአጽንኦት እጠይቃለሁ።” ከሚለው ንግግሩ በምኑ ሊጣጣም ይችላል? ፈረንጅ ሲጨንቀው “ካን ሳም ዋን ሐልፕ!” ይላል። ወገኖቼ እንዲህ ዓይነት ዘለፋ እራሱን ከሚያመጻድቅ ግለሰብ ሲደመጥ ነውር የሚለው ሰው ታጣ? አሁን እሱን ብንሰድበው እኛ እንዴት ልንወቀስ እንችላለን? ልታስረዱኝ ትችላላችሁ? “ዛኣኽለን ጥሒነን በዓለ ማርያም ይብላ” (የሚበቃትን ፈጭታ በዓለ ማርያም ነው ይብቃኝ” ትላለች ይባላል። የሚበቃውን ሰድብ ተሳድቦ ‘ላለመሳደብ ቃል ገብተናል” ይላል። ወይ ትጉዱ!
ብርሃኑ እየለጠፈብን ያለው የስድብ ስም “ጃን/ጆን በርች ሶሳይቲ/ሙቭመነት” እኮ በጣም አክራሪ፤ ነብስ ግድያ ውስጥ የሚሳተፍ፤ አገሮች ውስጥ ጣልቃ እየገባ አንድነትን የሚያውክ “ስም የታጣለት እግዚሃር የተጣላው ቀኝ አክራሪ እንቅስቃሴ ቡድን ነው”። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ በተለይ በቀዝቃዛው ጦርነት መባቻ ላይ የተመሰረተ የዘረኞች እንቅስቃሴ እና አፍሪካ ውስጥ ኰንጐ (ፓትሪስ ሉቡምበ ወቅት) አንጐላ፤ሞዛምቢክ …ኒካራጉዋ…. እና በመሳሰሉት “ሶሻሊዝም” መስረተዋል በሚባሉት አገሮች ወይንም የሶሻሊስት መርህ ይከተላል በሚባል አገር ጣልቃ በመግባት ወይንም ሶሻሊሰት አመለካከት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸው ታዋቂ ግለሰብ/መሪ (ኬነዲ- ኦባማ) የመሳሰሉት ሰዎች መጥፎ ተግባርና ስም በመስጠት የታወቀ ነው።
ይህ የተጠቀሰው ቀኝ አክራሪ ድርጅቱ የኦባማን የማንነት ዘር የጠየቀበት ምክንያት እኮ ዘረኛ ቡድን መሆኑን ቢታወቅም “ኦባማ” ጥቁር በመሆኑ ወይንም አፍሪካዊ ደም ስላለበት ሳይሆን “ሶሻሊስት/ኮሚኒስት” ነው ብሎ ስለመደበው ነው። ሶሻሊዝም ከነ ስሙ ከሰማ “ከጥቁር ቆዳነት” በላይ ሶሻሊዝምን የጠላል። እና ጠለፋ ውስጥ ይገባል። ይህ ድርጅት በጣም አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ 'ከብላክ ዋተር' የባሰ ቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ መሆኑ አንዳንዶቹ ይናገራሉ። ድሮ ሲኣይ ኤ በገባበት አገር ድርጅቱ ግምባር ቀደም ሚና ተሳታፊነት ነበረው። “ኪሊንግ ሆፕ” የሚለው መጽሐፍ ስታነቡ ይህ ጽንፈኛ (አልተራ ኮንሰርቫቲቭ) ድርጅት የሰራው የወንጀል እንቅስቃሴ አጸያፊ ነው። ታዲያ ብርሃኑ በዛው ድርጅት ስም ነው ያንድነት ሃይሉን ሲያትል ንግግሩ ውስጥ ሲዘልፍ የተደመጠው። እንዴት የዚህ ሰው “አታካራ ውስጥ እንካ ስላንትያ” ውስጥ አንገባም እያለ እንዲህ አይነት ስም እየለጠፈ የምር ጥሪ ነው ተብሎ ሰው ሊያምነው ይችላል? ለመሆኑ አማካሪዎቹ ምን እየበሉ ኖሮው ነው ይህ ጽሑፍ ሲያዘጋጅ ዝም ብለው የለቀቁት? የነ አብርሃ በላይ “ፈረስት ኢትዮጵያን ፎረም” “ተናጋሪ አርቲኩሌቶች” ይኼንን ይመስላሉ። እንግዲህ የመጪዋን ኢት ጵያ “ጋዜጠኞቻችን፤ መሪዎቻችን” ምን እንደሚመስሉ ካሁኑኑ የምናይበት ምልከት የሰጠን አጋጣሚ ነው።
አስገራሚው ደግሞ የሚከተለውን ተመልከቱልኝ። ብርሃኑ ነጋ እንዲህ ይላል፦
“ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፍቅር በምን ይለካል? ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መፈክር ከሚያወርዱት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው የመጨረሻዋን ጥይት ተጐንጭተው ቃላቸው በተግባር ፈጽመው አለፉት? መንግሥቱን ጨምሮ! “ ብርሃኑ ነጋ ከሲያትል ንግግሩ የተገኘ።
እግዚሔር ውለታውን ይክፈለው እና ቴክሳስ የሚኖር ጥሩ ወዳጄ ትናንት የማይገኙ መጽሐፍቶች በፖስታ ልኰልኝ “መጽሐፈ ጨዋታ፤መንፈሳዊ” የሚለው መጽሐፍ ስመለከት በገጽ 12 እንዲህ ይላል “ሥጋም ፍራቱን እጅግ አበዛው ከታረደ በኋላ ምን ያንቀጠቅጠዋል፤ምንስ ያንበደብደዋል?”ይላል። በግ/ፍየል ከታረደ በኋላ ስጋው ሲርገበገብ ሲንቀጠቀጥ አይታችኋል አይደል? ትርጉሙ ይግባችሁ።
ብርሃኑ ታዲያ እንኳን ታርዶ ገና ለገና “ኦመታለሁ፤ይይዙኛል” ብሎ ምንም ሳይነኩት ከእስር ሲለቁት እግሬ አውጪኝ ብሎ ሕዝቡን አጣብቂኝ አስገብቶ፤ያለ መሪ አስቀርቶ፤ ሜዳ ላይ ጥሎት፤ ፈርጥጦ ለትምህርት ወደ ውጭ አገር መጥቶ “ተራራ ላይ ውጥተህ ተፈላሰፍ በለውኛል” ብሎ መራራዋን ሞት እና ጥይት አንዳትቀድመው አገር ጥሎ ቀድሟት መውጣቱን ዘነግቶት “መንግሥቱን” ፈርጣጭ ብሎ ዓለም ሙሉ እያደመጠው በሌላ ሰው ሲሳለቅ ምን ዓይነት ደፋር ሰው እንደሆነ ይገርመኛል። እንኳን ብርሃኑ ነጋ ባለ ጦር ባለ ታንክ፤ባለ ኮማንዶ ነብስ ጠባቂ ያለው መለስ ዜናዊ ሳይቀር “ፍርሐት” ወርሮት እንደ ነበር ጥቅምት 2003/ኦክቶበር 2010 ቮልዩም 11 ቁጥር/ናምበር 21 “ፍርሓት” የሚለው ዘ ሐበሻ ጋዜጣ ላይ በእውቁ ኢንቬስቲጌቲቭ ጋዜጠኛ ኢየሩሳሌም አርአያ የተጻፈውን ስታነብቡ ለካ “ፍርሃት” ክፉ ነው፡ የማይጐበኘው ሰው የለም ትላለህ። ፍርሐት የማይበግረው ሰው ግን የግንቦቱ ጠቅላይ ጦር አዛዥ እና አዋጊው ጀኔራል ብርሃኑ ነጋ ብቻ ናቸው።
ለመሆኑ ኰለኔሉ ሲፈረጥጡ እኮ እንደ ብርሃኑ “ተራራ ላይ ወጥተው የፍልስፍና ትምህርት ለመማር” እንኳ ባይሆን እሳቸውም የራሳቸው የሰጡት ምክንያት አለ። ለመፈርጠጣቸው ምክንያት፤ ፈረጠጥኩ አላሉም: “ካገሬ ለመሰሰድ ምክንያት ለጉብኘት ለአስቸኳይ የስራ ስብሰባ ኬኒያ መኼድ ስለነበረብኝ፤ እንደኼድኩኝ ተቀናቃኞቼ መፈንቅለ መንግሥት አደረጉብኝ። ኬኒያውያኖችም ከዱኝ፡ ስለዚህ ለጊዜው ዚምባበዌ አመራሁ።” ነው ያሉት። ሁልም ፈርጣጭ የየራሱ የራስ መጠምጠሚያ መሸፈኛ “ሻሽ/መንዲል” አለው። ከብዲ ይጹሮ! ብኽድኑ! ትላለች አንዲት ትግርኛ የምትሞከር ኢትዮጵያዊት አገር ወደዳድ ሲገርማት (ሆድ ይቻለው/ይሸከመው! ተከድኖ ይብሰል!) ማለቷ ነው።
ስለዚህ ኰለኔሉም ሞት ሳትቀድማቸው ቀድመዋት ሲፈረጥጡ “ፈረጠጥኩ” አላሉም። የሰጡት ምክንያት የራሳቸው ምክንያት ሲሰጡን ፤ የግንቦት 7ቱ የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ እና ዶከተር ፕሮፌሰር ፈልድ ማርሻል ጀኔራል ብርሃኑ ነጋ ደግሞ የወያኔ “ዊፕ/ጅራፍ” ቀምሶ ስላማያውቅ ‘እስር ቤት ውስጥ ሌሎች ሲገረፉ” (ስዬ አበርሃን “የምን እሪታ የምን ጅራፍ ነው የሚጮኸው ብሎ ደንግጦ መጠየቁን አስታውሱት መጽሐፉ ላይ) ሰምቶ ሞት ላለመጐንጨት ተደናግጦ ያላደረገውን ወንጀል “አዎ ፈጽሜአለሁ” ብሎ “ፈርሞ” ሲወጣ “ወያኔዎች ሰውን ሲገረፉ የሰማው የብርሃኑ “ቂጥ” በፍርሃት ተምበድብዶ ሲንቀጠቀጥ የወያኔዎቹ ጅራፍ “ጀኔራሉ” ቂጥ ላይ ከማረፏ በፊት ሲፈረጥጥም ለመፈርጠጡ የሰጠን ሽፋን “ባይ ኤኒ ሚንስ -ከትግሉ ቀደም ብሎ መቀጠል ያለብኝ ኤክስቴንሽን ትምሕርት የመቀጠል እቅድ ስለነበረ መውጣት ነበረብኝ” አለን እንጂ “ፈረጠጥኩ እኮ አላለም። ማን ፈረጠጥኩ እንዳለ ብርሃኑ ነጋ ብቻውን መፈርጠጡን ይመን? ሞኝህን ፈልግ አለ ያማራ ሰው!
ታዲያ ብርሃኑ ነጋ ““ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፍቅር በምን ይለካል? ብሎ ይጠይቅና “ስለ ኢትዮጵያ አንድነት መፈክር ከሚያወርዱት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው የመጨረሻዋን ጥይት ተጐንጭተው ቃላቸው በተግባር ፈጽመው ያለፉት? መንግሥቱን ጨምሮ!” (በርሃኑ ነጋ)
እያለ እራሱ ከፈርጣጮቹ አንዱ ትልቁ ጉሬዛ ሆኖ እያለ ሌሎቹን “ፈርጣጮች” እያሉ ሲመጻደቅ እና ጥያቄ ሲያቀርብ “ምሕረት የውርድ” (ምሕረቱን ያውርድ) ከማለት ምን እንበል?
መንግሥቱ አስመራ መሄድ አይችሉም፤ ሽምቅ ተዋጊ ማሰማራትና መምራት አይፈቀድላቸውም። ብርሃኑ ግን አስመራ መሄድ ይችላል፤ ጫካ መሄድ ይችላል።ጫካ መሄዷን ግን አልወደዳትም። ምክንያቱም መራራዋን ጽዋ መጐንጨት ያልለመደች ፈርጣጭ ነብስ “ወያኔ ጐማ እግሩ” ጫካ ውስጥ “ጦሽ” ብሎ ድንገት ቢመጣበት “አድነኝ ብሎ የሚማጸነው ጓደኛው በረከት ስሞን” እንደ ማያገኘው ያውቃል እና ነው! ወይ እኚህ መንግሥቱ ፈርጣጭ ሁሉ የእንጨት ፈለጣ ተማሪ መለማመጃ አደረጋቸው። ወይ አለመታደል! ያረጀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል፡ የሚባለው ለካ እንደዚህ ነው።
ባንድነት ሃይሎች ላይ የስድብ ውርጅብኝ ማውረዱ የብርሃኑ ስድብ የገዛ እናቴ ንግግር አስታወሰኝ። እቤታችን ውስጥ የጠላ ንግድ ስለሚጠመቅ፤ እናቴ ሲነሽጣት ለደምበኞቻችን አለፍ አለፍ ብላ “ምን የመሰለ አምቧሻ” ትጋግራለች። ታዲያ እኔ እና ወንድሞቼ እህቶች ክፉ አመል ነበረን። ከተጋገረው ትኩስ ዳቦ ሰው ፊት ቆርሳ ስትሰጠን “የተባረክን ልጆች” እንድንባል “ደህና ጠገቤአለሁ፤ ለእንግዶቹ ይሁን”እንላትና ሰዎቹ ያሳድጋችሁ! ብሩካን ልጆች! ብለው ምርቃን ከሰጡን በኋላ፡ እናቴ ወዲያ ወዲህ ስትል እኛ ዞር ብለን ሳታውቅ ተደብቀን ዳቦው ሰፌድ ውስጥ ከተደበቀበት ወደ ኩሽና/ማዕድ ቤት በመግባት በግምጃ/ነጠላ የተከደነውን ትልልቅ ዳቦ እየወጣን እየገባን “ቆርመም” እያደረግን እየገመጥን፤ ሙሉ የነበረው ዳቦ “አይጥ” የበላው ይመስል ተቆርምሞ እናቴ ዳቦውን ለሰዎች ለማደል ስትከፍተው “ክብ ቅርጹ ጠፍቶ” ተቆርምሞ ስታገኘው “አንታ ታይ ወሪዱና? ዋይ! ናይ ሰብ አናፁ እውንዶ ይገጥመካ! ታይ ማዓቱ ደቀይ?! ( ወይ ጉድ! ምን ጉድ ነው! የሰው አይጥም ለካ አለ እባካች ? ትል እና ፤እኛ እንዳደረግነው ስለምታውቅ እንደነቃችብን ለማሳወቅ ስትል እኛን እያየች “ቆርማሚ ጐጐ ከፉእ አመል” ትላለች። “ዳቦ መቆርመምን የሚመስል ለማስጣል የሚያዳግት ኩፉ ሱሰኛ አመል ከቶ የለም” ማለቷ ነው። ስለሆነም የነኚህ ፖለቲከኞች ውሸትና የአድማቂዎቻቸው አመል ፈውስ ያለው አይመስልም። ስንት ጊዜ ይማራችሀ እንበላቸው?
አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com (Ethiopian Semay) getachre@aol.com