Thursday, March 19, 2015

ክፍል 2 - በፋሺስትነታቸው የሚኰሩ አስገራሚ ትግሬዎች! ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ

ክፍል 2 - በፋሺስትነታቸው የሚኰሩ አስገራሚ ትግሬዎች!
ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ getachre@aol.com

“……አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚባል አለ። “ሁልጊዜ” በጣቢያው በራፍ አካባቢ “ሁለት” ታጣቂዎች አይጠፉም። ካጠገቡ ሻይ ቤቶች አሉ፡ እዛ ሆኜ ሻይ እየጠጣሁ እንዳለሁኝ፤………..ሞቃታ ጸሐይ ስለነበር ጸሃዩን ለመከላከል ጭንቅላቱ ላይ “ሌዘር ጃኬቱን” ጣል አድርጎ ከፖሊስ ጣቢያው በራፍ በኩል አንድ ሰው ያልፍ ነበር፦ ‘ቁም!’ ብለው ያስቆሙታል። ሁለቱ የህወሃት አባላት ናቸው::  አንዱ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ አንዱ ደግሞ ሽጉጥ ታጥቀዋል። ሲያስቆሙት ጃኬቱን ከጭንቅላቱ ያወርድ እና ይቆማል። በል ወደ እዚህ ‘ና’ እንሂድ ብለው ወደ ሌላ ቦታ ሊመሩት ሲሞክሩ፤ “አልሄድም የሕግ ቦታ እዚህ አለ፤ እዚህ እንግባ” ብሎ እምቢ ይላል።መጓተት ጀመሩ። እነሱ ይጎቱቱታል፤ እሱም ወደ ፖሊስ ጣቢያው ግቢ-ይጎትታቸዋል።……”-ከታሪኩ-የተቀነጨበ።

ባለፈው ክፍል 1 ጽሑፌ የወያኔ ትግሬዎች በትግራይ ሕብረተሰብ ውስጥ ሲፈጽሙት የነበረው ፋሺስታዊ ግፍ በጨረፍታ አይተናል። ያንን ለማንበብ በተመሳሳይ ርዕስ ጉጉል አድርጋችሁ Assimba.org ወይንም Ethiopatriots ወይንም Welkait.com ጉጉል ብታደርጉ ታገኙታላችሁ። ዛሬ ደግሞ ከትግራይ ውጭ በበዴኖ፤በሐረር፤በጋራ ሙለታ (ግራዋ ከተማ)፤በጨለንቆ ወዘተ…እራሳቸው የወያኔ ታጋዮች በቀጥታ በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የፈጸሙት የዘር ማጥፋት ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ በቦታው ከነበሩ የዓይን ምስክሮች ያዩትን እንመለከታለን።
ወያኔዎች 40 አመት ፈጸምን የሚሉት የውሸት “ዲሞክራሲ፤አንድነት፤እና ልማት” የፋሺስቶች ክንዋኔ መሆኑን በተጨባጭ እንመለከታን። ይህ ግፍ ተደጋግሞ ለሕዝብ ካልቀረበ እና ሕዝቡ በራሱ እና በአገሩ የደረሰበትን ፋሺስታዊ ግፍ ካላወቀ፤ የወያኔ የዜና ማሰራጫዎች እና ‘ሌኒን’ “useful idiots” ብሎ በሚጠራቸው ወያኔ “እህት ድርጅቶች” ብሎ አግልግሎታቸውን ለወያኔ የሚሰጡ “ጠቃሚ ጌኞዎች” በሚሰጥዋቸው የአግልጋይነት ትብብሮችና ቅስቀሳዎች ተሞኝቶ እንዳይቀር ይረዳል።

ከላይ እንደተገለጸው ፋሲስት ወያኔ በ1983 ከትግራይ ገስግሶ፤ በለስ ቀንቶት፤ ወደ መሃል እና ወደ ጫፍ አገር በመግባት መላዋን አገሪቱ በጠመንጃ ከተቆጣጠራት በሗላ፤ በመላ አገሪቱ የንብረት ዝርፍያ ከማከናወኑ ሌላ ከትግሬ ሲነሳና ከምስረታው አንስቶ በመመሪያው ውስጥ ያሰፈረው በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ የጥቃት እርምጃ ለማሳካት በአገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በኩል የወሰደውን በዓይነቱ ልዩ የሆነ፤ ከደርግ “የነፃ እርምጃ” ጋር የሚመሳሰል ፋሺስታዊ የዘር ማጥፋት ወንጀሉን እንመልከት።

የዘር ማጥፋት ዒላማ ሰለባ ነው የምለው “የአማራው ሕብረተሰብ” ነው።በሐረር፤በበዴኖ፤በጨለንቆ፤ወዘተ ባንድ ውድቅት ከ300 በላይ አማራዎች በህወሓት ታጣቂ ሰራዊቶች እግለ እገሌ ሳይባል በእግረ መንገዳቸው ሲዘዋወር ያገኙትን የአማራ ነገድ እንደ ጅግራ እያሳደዱ በጥይት የጅምላ ጭፍጨፋ አካሂደውበታል። ለዚህም የዓይን ምስክር የሆኑት በወቅቱ እስፍራው የነበሩ ዛሬ በስደት አገር በቤልጂግ አገር የሚኖሩ የሰብአዊ ድርጅት-ተሟጋች-አባል-የሆኑ፤
መምህር ገበዮህ ደስታ የተባሉ ዜጋ፤ ከሁለት አመት በፊት ከኢሳት የሰብአዊ መብት ክፍል አዘጋጅ ከአቶ ጋሹ ጋር ያካሄዱትን የቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ እንመለከታለን።የጽሑፍ ትርጉም የራሴ።


ይህ ወንጀል ኦነግን እና ኦሆዴድን የሚጨምር ወንጀል ቢሆንም የኦነግም ሆነ የኦሆዴድ ወንጀል እራሱ የቻለ ሌላ ዘገባ ስላለው ለዛሬ ግን የወያኔ ተዋጊ ሰራዊት በቀጥታ የተሳተፉበት የጅምላ ጭፍጨፋ ብቻ እንመለከታለን።
በተለያዩ የወያኔ ድርጅቶም ሆነ፤ የኦሮሞ ነፃ አውጪዎች ነን በሚሉ የተለያዩ ታጣቂ ግምባሮች የተፈጸሙ ወንጀሎች አሉ። በተለያዩ ወቅቶች በተገለጹት ቦታዎች አማራዎችን አንደ ፍየል ቆዳቸው ተገ’ፏል፤ ጡታቸው፤ምላሳቸው፤ እጆቻቸው እና ብልታቸው ተቆርጧል።  ዓይኖቻቸው በአንካሴ ተጎጥጉጦ ወጥቷል። ወዘተ..ወዘተ… ያንን ለዛሬ አንመለከተውም።ከዚህ ቀጥሎ የሚነበበው ቃለ መጠይቅ፤ለጽሑፍ እንዲመች አንዳንድ መስተካክሎች ተደርገውበታል። አሰካኩ ካልሆነ በስተቀር ምስክርነቱ እንዳለ ነው።

ጋሹ (አሳት)፡-
በምን እንጀምር፤ በበዴኖ እንጀምር?

መምህር ገበዮህ ደስታ፡-
ጥሩ። በወቅቱ እኔ የምኖረው ዓለማዮህ ከሚባለው ጓደኛዬ ጋር አሁን በህይወት የለም ተገድሏል፤ ሐረር ከተማ ውስጥ ነበር ስኖር የነበርኩት። በወቅቱ እኔ እና ዓለማዮህ ወደ በዴኖ ሂደን ስለነበር፤ (ግራዋ ማለት ጋራሙለታ ወረዳ ውስጥ ያለች ከተማ ነች)። ከዚያ ወጣ ብሎ “ኢልኰ” የምትባል ቦታ አለች፡በዛች አካባቢ የሚኖሩ አቶ ተስፋማርያም የሚባሉ የጓደኛዬ የነርስ አለማዮህ ወላጅ አባት ነበሩ። በአካባቢው ለረዢም ጊዜ የኖሩ 4 ልጆች የነበሯቸው ኗሪ ናቸው። ከ4 ልጆቻቸው አንዱ ነርስ ሐረር ከተማ ሕይወት ፋና ሆስፒታል ሲሰራ የነበረው ጋደኛዬ አለማዮህ ነው።ከኔ ጋር ቅርብ ጓደኞሞች ነን።

እና በ1983 በተደረገው የሥርዓት ለውጥ ምክንያት ወያኔ አገሪቱን ይቆጣጠረው እንጂ ሐረር የገባው ዘግይቶ በ1984 ዓ.ም ማታ ላይ ነው።  ምክንያቱም እዛ አካባቢ ከፍተኛ ትግል (ረዚስታንስ) ሲካሄድ ስለነበር ነው። እንደሚታወቀው በአካባቢው “ቆፔ ራዲዮ ጣቢያ” በማባል ሲጠራ በነበረው ራዲዮ በኩል፤ አገር ወዳዶች በወቅቱ ከነበሩት የራዲዮኑ ሠራተኞች ጋር ሆነን በመተባባር፤ የመጣውን ጠላት ሕዝቡ እንዳይቀበለው ቅስቀሳ ስናካሂድ ስለበር ነበር እንዳይገቡ ትንሽ ተከላክለናል። በወቅቱ ኦጋዴን ላይ ሰፍሮ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ገሥግሶ ወደ አካባቢው መጥቶ በሩን እንዲዘጋ ወደ በዴኖ እንዳይሻገር ቅስቀሳ ብናደርግም፤ስለዘገዩብን አልተሳካም።ወያኔዎችም ውለው አድረው ገቡ።

ሕዝቡ የተዘጉ የጦር ግምጃ ቤቶችን እየሰበረ እራሱን ማስታጠቅ ጀምሮ በነበረበት ወቅት ወያኔዎች ኗሪዎችን የመዳፈር እርምጃ ዝግተኛ ነበር። ብዙም አልደፈሩትም።ሆኖም ከጊዜ በሗላ ቀስ በቀስ ቁጥጥራቸውን ካደላደሉ በሗላ ፤ መንገድ ላይ ያገኙትን ሁሉ በጥይት መምታት ጀመሩ። የተገደሉትንም አንደ ውሻ ሬሳ “ዋዝ” በሚባሉ የጦር ትላልቅ የጭነት መኪኖች ላይ እየጣሉ ይጭኗቸው ነበር። ጭነው የት አንደሚቀብሯቸው ግን አናውቅም። ሕዝቡ ምን መጣብን ብሎ ተደናገጠ። እኔም ይህንኑ በመስጋት እኔ እና ጓደኛዬ እራሳችንን ለጊዜውም ቢሆን ለማዳን ወደ ግራዋ እንሂድ ብለን ሄድን።
እዛው ሄደን ‘ቆጥ’ ላይ ላሞች በሚያድሩበት በረት ሳር ላይ ከብብን እሳት እያነደድን ውሎ አዳራችንን አድርገን ሁኔታውን በሩቁ ስንከታተል ነበር። ከዚያ ውጭ ወደ ከተማ አንወጣም። ሐረር ከተማ ውስጥም ኦነግ ገብቶ “የገበሬዎች ማሕበር” ህንጻ የሚባል ይመስለኛል፤ እሱን ተቆጣጥረው ቢሮአቸው አድርገውት እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።

ታዲያ እኛ ያለንበት የአቶ ተስፋማርያም ቤት (በዴኖ ውስጥ)ከፍተኛ ስፍራ የሚገኝ ኮረብታማ ቦታ ነው ያለንበት፡ ቁልቁል ስንመለከት “አቶ ከቢራ” የተባሉ የኦሮሞ ነገድ የሆኑ ሦስት ሚሰት ያሏቸው አንደኛዋ ሚስታቸው አማራ ናቸው። እሳቸው ሁለቱ ልጆቻቸውን ይዘው ከከተማው ሸሽተው እየተጣደፉ ወደ እኛው አካባቢ ወደ አቶ ተስፋማርያም መኖሪያ መጡ። እኛ ‘ቆጥ’ ላይ ነን ያለነው። ታዲያ አቶ ከቢራ እየሮጡ መጡ እና ‘ወዳጄ ተስፋማርያም እባክህ እኔን እና ልጆቼን እዚህ ለጊዜው ደብቀን ብለው ሰዎቹ ገፍተው መጥተውብኛል” ብለው ሲጠዩቋቸው። ማናቸው እነኚህ? ብለው ሲጠዩቋቸው’፤ “እነኚሁ ከሰሜን የመጡ ትግሬዎች ናቸው” ብለው የለበሱትን አለባበስ፤ ጸጉራቸው፤ የሚነጋገሩበት ቋንቋ፤ እና የመሳሰሉትን መለያቸውን ለይተው ነው የገለጹት።

እንዲያ ሲሏቸው “አይ ወዳጄ እኔ ጋር ሰዎች አሉኝ፤ እነኚህ ሰዎች አንዲጐዱብኝ አልፈልግም፡ ባይሆን አብሬህ በዚሁ ቁልቁል መንገድ አብሬህ ላዋርድህ ብለው ይዘዋቸው ወደ ታች ወረዱ። ከሰዓት በሗላ ነው ፤በወቅቱ ወያኔዎቹ ፍተሻ ያካሂዳሉ፤ያገኙትን በጥይት ይመታሉ። ኦነጐች አሉ፤ ሆኖም ኦነጎች በየወረዳው ሄደው በስፋት አይፈትሹም፤ ፍተሻ የሚያካሂዱት እነኚያ ወያኔዎች ናቸው። ታዲያ አቶ ከቢራ እና አቶ ተስፋማርያም ቁልቁል መንገዱን ይዘው ሲሄዱ ከከተማው መንገድ ሰዎች ያሰቆሟቸው እና አቶ ከቢራን ገደሏቸው። አቶ ከቢራን የመቷቸው ምክንያት እና ከአካባቢው ሰዎች አንደተረዳነው፤ በታጣቂ ወያኔዎች የተገደሉ “ሬሳዎች” በዓይናቸው ያዩ እና “ሲገደሉም” ከተመለከቱ ሰዎች መካካል ወስጥ አቶ ከቢራ ስለነበሩ፤ ለእማኝነት እንዳይቀርቡ ሲባል ነው።
አቶ ተስፋማርያምም ወደ እኛው በኩል ሲመለሱ፤ልጃቸውን አስቀድመው ልከው ‘ “ከቢራን” ገድለውታል፤ አባዬም እየተከተለን እየመጣ እመንገድ ላይ ነው’ ብሎ ነግሮናል። በመሃሉ አቶ ተስፋማርያም ወደ እኛ እየመጡ ሳሉ እምንገድ ላይ አስቁመው ገደሏቸው።

እኛም ከዚያ ቤት ልቀቁ ተብለን ለደህንንታችን ተብሎ “አደም” ወደ ተባለው ወደ ኦሮሞዎች ቤት ተወሰድን። እሱ ቤት ስንገባ ማንም ወደ ቤቱ የመጣ ሰው አልነበረም። ሆኖም ሁኔታውን ለማየት ብለን እንደ አገሬው አለባበስ ሽርጥ ታጥቀን ሕዝቡ ወደ ተሰበሰበበት ቦታ ሄደን ስንመለከት፤ የተነዛው ወሬ በጣም አስገረሚ ነበር። ምን ይላሉ፤ እሬሳውን ከብበው እየተመለከቱ ላሉ ሰዎች ወያኔዎቹ “ከቢራን የገደለው ተስፋማርያም ነው” ብለው ለሕዝቡ መንገር ጀመሩ።
አቶ ከቢራ በወያኔ ታጣቂ ወታደሮች ተምትተው ሲወደቁም ሆነ አቶ ተስፋማርያምም ያንን ካዩ በሗላ ራሳቸውን ለማዳን ሸሽተው ሲሄዱም በታጣቂዎቹ መገደላቸውን ያዩ እማኞች አሉ። አቶ ተስፋማርም ጠመንጃ የሚባል ነገር አልያዙም ነበር። ባዶ እጃቸውን ነው ልሸኝህ ብለው አብረዋቸው ሄደው ሁለቱም በወያኔዎች የተገደሉት።

አቶ ተስፋማርያምንም ገድለው ሬሳቸውን በሰዎች አሽሸክመው አቶ ከቢራ ሬሳ ካሉበት አብረው አጋደሟቸው። በዛው ሰዓት አደም ቤት ነን ያለነው። ልጃቸው (የተስፋማርያም ልጅ) ጓደኛዬ ዓለማዮህ እኔንም ጭምር ይግደሉኝ ብሎ ተናድዶ  እራሴን እገድላለሁ ብሎ ሲያለቅስ ስለነበር፤ እሱን እያጽናናን ነበርን። እንደውም የአቶ ተስፋማርያም ልጆች በሙሉ የሚናገሩት አሮምኛ ነው። አንደኛዋ ሴት ልጃቸው አማርኛ በደምብ አትችልም።

በማግስቱ ሬሳውን ለማየት ስንሄድ የ9 ሰዎች ሬሳ ከቦታው ተነስቶ ወዴት አንደተወሰደ አይታወቅም፤ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ውስጥ ወያኔዎች ኦነጎችን ለማጥፋት አንደተነሱ ተነገረ። ወዲያውኑ እንቁፍቱ (ገደል) ወደ እሚባለው ገደል ሰዎች ከነ ሕይወታቸው እየተገፈተሩ የተገደሉበት ነው። እዛው ወስጥ ሬሳቸው ተጥሎ ከተገኙት መካካል የነ አቶ ተስፋማርያም እና  የአቶ ከቢራ ሬሳ እጆቻቸውን በፍጢኝ ታስረው ከተገኙት መካካል እነሱ ነበሩበት።
ጋሹ (ኢሳት)፤- ማነው እዛ ገደል ላይ ከነሕይታቸው ከተገፈተሩ ሬሳዎች ላይ አብሮ ወደ ገደል የጣላቸው?
መምህር ገበዮህ ደስታ፤-
እኔ አላውቅም።

ጋሹ (ኢሳት)፤-
ይህ ዘር ማጥፋት ግድያ ወንጀል የጀመረው ማን ነው ይላሉ?

ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው ጀመሪዎቹ። ኦሮሞው አማራው ጉራጌው… አብሮ ለዘመናት የተጋባ የኖረ ፤የተረዳዳ አንድ ሕዝብ ነበር።ክርስትያን እና እስላም የሚጋባበት ሰለማዊ ዘመን ነበር፡ እነሱ ሲገቡ ነው ይህ ሁሉ ግፍ የታየው።ከዚያ በፊት አንዲህ ያለ ጭካኔ ታይቶ ተስምቶ አይታወቅም።ይህ ሁሉ መነሻ የሆነው፤ ድሬዳዋ ላይ ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ) የተባለው ወያኔ ጠ/ሚኒስቴር በነበረበት ወቅት ወደ ድሬዳዋ ሄዶ ባደረገው “ጸረ አማራ ቅስቀሳ ንግግር” ምክንያት ነው የተጀመረው፦

በአንድ የጫት መደብር አዳራሽ ላይ”የባለ ሃብቶች ስብሰባ” በሚል ጉባኤ ጠርቶ ነው “ ሽርጣሞች እያሉ እናንተን ለመግዛት እና ሲጨቁኑዋችሁ የነበሩ ወንዝ ተሻግረው የመጡ አማራዎች አብረዋችሁ ስላሉ እነሱን መንጥራችሁ ዝመቱባቸው” ብሎ “ብእዴን” ወክያለሁ ብሎ በግልጽ ከተናገረ በሗላ ነው አማራን የማጥቃት ዘመቻ የተጀመረ። የሚገርመው ነገር፤ ከየአካባቢው ሽማግሌዎች ተጠርተው ስለነበር፤ “እንዴት እንዲህ ያለ ጸያፍ ንግግር ታደርጋለህ? ብለው በኦሮምኛ ሽማግሌዎቹ ገስጸውታል”። እንዲህ ከተናገሩ መካካል አሁን ስማቸውን ልገልጽ የማልፈልግ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው።

ጋሹ (ኢሳት) …
ወደ ጅምላ ጭፍጨፋው አንሂድ፡

መምህር ገበዮህ ደስታ፦

እንግዲህ አማራ ኦሮሞን ገደለ ብለው ወያኔዎቹ አስወሩ። ከዚያም ኦሮሞውንም አማራውንም ለሁለቱ ወገኖች መሳሪያ አስታጠቁት።

ጋሹ (ኢሳት)
እንዴ! ለምንድነው ሁለቱንም ያስታጠቁዋቸው?

መምህር ገበዮህ ደስታ፤-
የመንቀሳቀሻ ወረቀት ያልያዙ የደርግ ርዝራዦች ያለ ፈቃድ ሲዘዋወሩ ብተገኟቸው “ነፃ እርምጃ” የመውሰድ መብት ተሰጥቷችሗል እና መግደል ትችላላችሁ፤ ብለው ሁለቱንም ወገኖች አስታጠቋቸው።መሳሪያ ሲሰጡ እገሌ አማራ ነው እገሌ ኦሮሞ ነው ብለው አይደለም ያደሉት፡ ዝም ብለው ነው እንደ “ብትር” ለሁሉ ኗሪ ያደሉት።በሗላ ግን መሳሪያው የታደለበት ውስጠ ምስጢር እነግርሃለሁ።

በሗላ ግን ቡርፊያ ጮሌ፤ በበዴኖ እና በመሳሰሉት አካባቢዎች አማራ እና ኦሮሞ፤ ተገዳዳለ እየተባለ ወሬው እየተባዛ ሲስፋፋ የርስ በርስ ጉዳይ የተከሰተበት ጉዳይ አለ። በሗላ የኦነግ ሰራዊቶች እና የአይ ኦ ኤል ኤፍ ሰራዊቶች ‘አማራውን’ ባንድ ሜዳ ሰብስበው የጨፈጨፉት ወንጀል አለ።
በወቅቱ፤ ኦሮሞዎቹ አማራዎችን ስብሰባ አለ እና ‘ኑ’ ብሎ ኦነግ ቢጠራችሁ ‘እንዳትሄዱ’ ብለው እየነገሯቸው ሕይወታቸውን ከሞት ያዳንዋቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ያልሰሙ ግን ወደ ስብሰባው ድረስ ሄደው ወደ እንቅፍቱ (ብዙ እንቅፍቱ/ገደሎች/ አሉ) ገደል ውስጥ ከነ ነብሳቸው ተገፍትረው ተገደለዋል። ከዚያም የአማራዎች ሱቅ እና ንግድ ቤት እየተሰበረ ንብረታቸው ዘረፏቸው። የታገቱ (ሆስተጅ) አማራዎችንም ለማስለቀቅ የምትፈልግ ካለህ $10000 እና $20000 ብር መክፍል አለብህ ተብሎ ይጠየቅ ነበር። ያንንም ከተከፈለ በሗላ ምህረት የለም፤ ይገደላል!

ጋሹ (ኢሳት)፦
አካባቢውን የሚቆጣጠረው ማን ነው? ኦ ኤል ኤፍ/ኦሆዴድ? ማነው?

መምህር ገበዮህ ደስታ፡-
ካልተሳሳትኩ ስሟ “ዳህዋ” (?) እንደዚህ የምትባል መሰልኝ የአንድ የኦ ኤል ኤፍ አባል ባለቤት ነች እሷም ነበረች፤ አንዷም “አይሻ” የምትባል ሴትዮ ነበረች፦ ዳሃቦ (?) መሰሪያ ይዛ ሌሎች ወታደሮችም አብረዋት የሚከተሉዋት ወታደሮች አሉ።እሷ በምትመራው ቡድን እየተዘዋወሩ የአማራ ሱቆችን መዝጊያ እየሰበሩ ምግብ፤ሱካር ፤መከሮኒ ፓስታ ጋዝ ፤ዘይት ወዘተ…..እየዘረፉ በአህያም በሰው ጫንቃም እያስጫኑ ወደ ዳር ገጠር ይወስዱት ነበር።
በሌላ በኩል ደግሞ ወያኔም ግድያውን ያጧጡፋል። ሰው ወደ እንቅፍቱ ገደል ሲጣል መጀመሪያ ምርመራ ላይ ይገረፋል፤ ከዚያ የፍጢኝ ታስሮ ወደ ገደል ይገፈተራል። ይህ የሚያደርገው ወያኔ ነው። ከዚያም በሗላ ኦነግም ተመሳሳይ ድርግት በመፈጸም በአማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል። በዚህ ወንጀል ውስጥ የተገደሉት ሰዎችም የአማራ ወዳጆች ናቸው ተብለው ተገርፈው፤ የተገደሉ ኦሮሞዎችም ጭምር ገደል ውስጥ ተጨምረዋል።በዚህ ወንጀል የተካፈሉ ወንጀለኞች “ወያኔዎች፤ኦነጎች፤ እና ኦሆዴድ’ አይ.ኦ.ኤል.ኤፍ ድርጅቶች ናቸው”።

ጋሹ፦
የኦሮሞ እና የአማራ ጥላቻ አንዲፋፋም በስተጀርባ ሴራውን የጐነጎነው ማን ነው ይላሉ?

መምህር ገበዮህ ደስታ፤-
በወቅቱ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት ኮሎኔል ኪዱ፤ ኮሎኔል ጥላሁን ገሠሠ፤ ከህወሓት፤ ከኦፕዲኦ ደግሞ መገርሳ እና ጣሃ የተባሉ ለዚህም ከላይ ሆኖ ግፋ ሲል የነበረው ታምራት ላይኔ ነው። አማራን ወክለናል ብለው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት “ሰለሞን….. የተባለ የአማራ ነገድ፤ በሗላ የድሬዳዋ አስተዳዳሪ የነበረ በሕመም የሞተ”፤ እና ሌሎች። እነዚህ ሁሉ ሲያስተባብሩ የነበሩ ናቸው። ሐረር ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ ግን ሙሉ በሙሉ የህወሓት አባላት ተጠያቂዎች ናቸው።

ማስታወሻ፦  ጠያቂው(ጋሹ) የተጠያቂውን ‘ግሩም’ ትረካመሃል ላይ በማያስፈልግ ቦታ እያቋረጠ መናኛ ጥያቄዎችን በመጠየቅ መውጣት የነበረባቸው ታሪኮች ነግግራቸውን ባያቋርጠው ብዙ የተደበቁ ምስጢሮች በነገሩን ነበር። ሆኖም ተጠያቂው ስለ ሃረር እንዲነግሩት በተጠየቁት መሰረት እንዲህ ሲሉ ንግግራቸውን ይቀጥላሉ፡-   

ሐረር ውስጥ  ስንመለስ፤ “ሰላም እና መረጋጋት” ተብሎ ሕዝቡ አርፎ በሰላም እየኖረ በነበረበት ሁኔታ፤ የሕዝቡን መሳሪያ እያ’ስፈቱ  በ16 እና 15 አመት ዕድሜ ክልል ያሉትን ወጣቶች ሳይቀር እየጎተቱ መግደል ጀመሩ። ቀበሌ አጥር ሥር የሚያድር ቤት የሌለው ‘’ፍራሽ’ በመስፋት ሲተዳዳር የነበረ ምስኪንም ገደሉት (ያለ ምንም ወንጀል)። ነርስ የነበረው ጓደኛዬ ኣለማዮህም “ሲጋራ ገዝቶ” ወደ ቤቱ ሲመለስ በጥይት ተኩሰው ገደሉት። የጥይቱ ደምጽ ሰምቼ ተደናግጬ ብወጣ አለማዮህ ነው። ሆስፒታል ስንወስደው መንገድ ላይ ሞተብን። ሰለማዊ ሰልፍ ይሳተፋሉ ወዘተ የሚባሉትን እየተፈለጉና እየተጠቆሙ ይገደላሉ።

ጋሹ (ኢሳት)፤-
ነፃ እርምጃ ማለት  ነዋ?

መምህር ገበዮህ፦
አዎ!

በወቅቱ የቀይ መስቀል ተመዝግቤ አባል በመኖሬ፤ ግድያ ሲበዛ  ከቄይ መስቀል መ/ቤት ሠራተኞች ጋር አብሬያቸው ተረዳድተን፤ ሬሳዎችን መቅበር ጀመርን። የወደቁትን ሬሳዎች በቀይ መስቀል ጥቁር ብርድልብስ እየጠቀለልን ወደ ቀይ መስቀል “ቶዮታ” መኪና ጭነን በመቆለል ‘ሚካኤል ቤተክርስትያን” ባቢሌ መውጫ መንገድ አለ፤ እዛው በስተጀርባ የድሮ መቃብር አለ። እዛው ላይም አንድ ትልቅ ሰፊ የመቃብር ጉድጓድ አለ፤እዛው ነው የምንጨምራቸው።  ሰፊ ጉድጓድ አለ ሲባል የነበረው ጉድጓዱን ያየሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ያኔ ነው። አሁንም ምልክት አለው፡ ሬሳቸውን እዛው ውስጥ ነው የምንጨምረው። በአንድ ግማሽ ቀን ውስጥ በከተማው የለቀምናቸው 72 ሬሳዎች እዛው ጉድጓድ ቀብረናል። እኔ እራሴ ሬሳዎቹን ከቀበሩት መካካል አንዱ ነኝ። ጅብ በልቷቸው የተበላሹም እየለቀምን ቀብረናል።

ይህ ቁጥር ከጥዋት ጀምሮ እስከ ግማሽ ቀን ብቻ ነው። ከሰዓት በሗላም የዚያኑ ያህል ቁጥር እየተለቀመ ተቀብረዋል። እኔ ከሰዓት በሗላ እየዞርን መልቀሙን አልቻልኩም፤ አመመኝ ፤አቅለሸለሸኝ፤ አዞረኝ፤ ሰውነቴ ሁሉ አላስችል አለኝ። ሌሎቹ መልቀም ቀጠሉበት። ያኔ ሰውነቴ ሲታወክ ወደ ፋና ህይወት ሆስፒታል ሄጀ ታከምኩኝ፤ የሚጠጣ መድሃኒት ሰጡኝና ወደ ቤቴ ሄድኩኝ። በጣም የሚያሳዝን ትዕይንት ነበር።

እነኚህ ወገኖች ጅብ ከሚበላቸው ለቅመን አንቅበራቸው ብለን ነው በጎ አድራጊ ዜጎች ከቀይ መስቀል ጋር ተባብረን እንዲቀበሩ ያደረግነው። ያውም ሬሳዎቹ እስላም ይሁኑ ክርስትያን ማንም የሚያውቅ የለም። ያንን የደረግነው፤ ሬሳቸው ሜዳ ላይ ተጥሎ በጀብ እየተበላ ስለነበር፤ ክፉ ከማየት ብለን ነው።
አንዳንድ ሰዎች ማንነታቸው ለማወቅ ኪሳቸውን ፈትሸን ስናይ ከነሱ መሃል አንዲት እናቱን ከሚያገኛት $12.00 (አስራ ሁለት ብር) የጡሮታ አበል ሲያስተዳድር የነበረ ወታደር ነው።እስከ ዛሬ ድረስ፤ እናቱ የሆነ ትግሬ መንገድ ላይ ሲያልፍ ካዩ “የልጄን ሬሳ” አትሰጡኝም? መቸ ነው የምትሰጡኝ? ይላሉ። ሽማግሌዋ እናት “ቀለዳምባ” ውስጥ ነው ሚኖሩት። የልጃቸውን 12 የጡሮታ ብሯን ደሞዛቸውን ለማግኘት ሲሄዱ ሽማግሌ ስለሆኑ በእግር መንገድ ስለማይችሉ፤ ታክሲ ተሳፍረው ደርሶ መልስ $2 ብር ይከፍላሉ። የምትቀራቸው $10.00 ነች። አንዳንዴም ደሞዛቸው አልመጣለዎትም ተብለው ሲመልሷቸው ሁለቴ ሲመላለሱ $4.00 ይከፍላሉ፤ $8.00 ትቀራቸዋለች። ሲጨንቃቸው የሰው እጅ ያያሉ፤ እኛም ስንችል አለፍ፤አለፍ ብለን የሆነ ሳንቲም እንጥልላቸዋለን።

ጋሹ፦
ይህ ቀይ ሽብር ነው! ከቀይ ሽብር ሚለይበት ነገር ምንድ ነው?

መምህር ገበዮህ፦
በቀይ ሽብር ጊዜ የነበረው ሁኔታ ባላወቅም ፤ ሰምቻለሁ።ከዚያ የሚለይበት ነገር ያለ አይመስለኝም፤ አንደሰማሁት ከሆነ። ለየት የሚያደርገው ይኸየኛው፤ በጥይት የሚመቱት ሰው ሲኖራቸው፤ ሦስት ሆነው በመምጣት ከቤትህ ያስወጡህ እና፤ እያናገሩህ እንዳለ በጥይት መትተው ይጥሉሃል። ጥለውህ እዛው ይሄዳሉ።

ለምሳሌ፤ ሐረር ውስጥ አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚባል አለ። “ሁልጊዜ” በጣቢያው በር አካባቢ “ሁለት” ፖሊሶች ይቆማሉ። ካጠገቡ ሻይ ቤቶች አሉ፤ እዛ ሆኜ ሻይ እየጠጣሁ እንዳለሁኝ፤ ቀን ነው፤ የታዘብኩት ነገር ልንገርህ። ሞቃታ ጸሐይ ስለነበር፤ ጸሃዩን ለመከላከል ጭንቅላቱ ላይ “ሌዘር ጃኬቱን” ጣል አድርጎ ከፖሊስ ጣቢያው በራፍ በኩል አንድ ሰው ያልፍ ነበር፦ ‘ቁም!’ ብለው ያስቆሙታል። ሁለቱ የህወሃት አባላት አንዱ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ አንዱ ደግሞ ሽጉጥ ታጥቀዋል። ሲያስቆሙት ጃኬቱን ከጭንቅላቱ ያወርድ እና ይቆማል። በል ወደ እዚህ ‘ና’ እንሂድ ብለው ወደ ሌላ ቦታ ሊመሩት ሲሞክሩ፤ “አልሄድም የሕግ ቦታ እዚህ አለ፤ እዚህ እንግባ” ብሎ እምቢ ይላል።መጓተት ጀመሩ። እነሱ ይጎቱቱታል፤ እሱም ወደ ፖሊስ ጣቢያው ግቢ ይጎትታቸዋል።

ለመውሰድ እየቃጡት ያሉት ወደ ወታደራዊ ጽ/ቤታቸው ነው። ጽሕፈት ቤታቸውም ከራስ ሆቴል ፊት ለፊት ነው። እዛው ምርመራ ክፍል አለ፤ ወደ እዛው ከሄድክ፤ትገረፋለህ፤ ከዚያ ትገደላለህ፤ እዛ ከገባህ መውጣት የለም። የህይወትህ ፍጻሜ ነው። ታዲያ ሰውዬው እምቢ ሲላቸው “ሳብ ያደርጉ እና በጥይት ደረቱ ላይ ‘ሦስት’ ጊዜ በጥይት ደብድበው ገደሉት”።ይህ ሲሆን፤ እዛው ያሉ ፖሊሶችም ዝም ብለው ይመለከቱዋቸዋል፤ ማንም የተናገረ ሰው የለም። ከዚያ የራሱን ሌዘር ጃኬት ፊቱ ላይ ሸፍነው ጥለውት ሄዱ።

ሲመቱህ “በሦስት ጥይት” ሆኖ “በጡቶችህ መሃል ደረትህ ላይ ነው የሚተኩሱብህ”። አትድንም። ይህ ሲሆን አፉን ከፍቶ “ለምን” ገደላችሁት ብሎ የሚናገር የለም። ለምን? የምትል ከሆነ ይዘውህ ይሄዳሉ፤ ተገርፈህ አንተም ተመሳሳይ እጣ ታገኛለህ። ከመገደልህ በፊት ግርፍያ የማይቀር ነው፤ ከዚያ ትገደላለህ።” ሲሉ የዓይን እማኙ ምስክርነታቸው ከላይ በተገለጸው መልኩ ለታሪክ አስቀምጠውታል።

ይህ ነው የወያነ ትግሬ አስፈሪው፤አስደንጋጭ ፋሺዝም። በተከታታይ በሁለት ምዕራፎች ያስነበብኳችሁን ታሪክ የዘገበው የ40 አመት የወያኔ ትግሬዎች ፋሺዝም፤ ክፍል 1 በትግራይ ክ/ሃገር ፤ ክፍል 2 ደግሞ በሐረር ከተማ እና አካባቢ የተፈጸሙት የጅምላ ግድያ እና ፋሺስታዊ እርምጃዎች ስናስታውስ፤ ወያኔዎች የየካቲት በዓላቸውን ለማክበር  የዘረጉትን ሐሰት የተላበሰ “ዲሞክራሲ፤ፍትሕ፤ሰላም” አምጥተናል የሚሉትን ፕሮፓጋንዳ ጓዳው ሲከፈት ይህንን ይመስላል። ለዚህ ሁሉ ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ እስካሁን ድረስ አንድም ሰው ከወያኔዎች ተይዞ ለፍርድ የቀረበ የለም።ለምን? ምክንያቱም ፋሺስቶች በሕግ ስለማያምኑ፤ እራሳቸውን ለሕግ አያስገዙም። ስለሆነም የወንጀል ድርጊታቸው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ። ጊዜው ሊረዝም ይችላል፤ በግድያ ድርጊት የተሳተፉት ወንጀለኞች፤ ውለው አድረው አንድ ቀን ለፍርድ ቀርበው አንገታቸው ወደ መሬት አቀርቅረው ሃጢያታቸውን የሚናዘዙበት ወቅት ይመጣል። ዛሬ አድማጭ ያጣው ይህ ብሔራዊ እና ሰብአዊ የወንጀል ታሪክ፤ ያኔ ጎልቶ የሕዝብ መወያያ ይሆናል።


አመሰግናለሁ፤ ጌታቸው ረዳ Editor Ethiopian Semay getchre@aol.com