Friday, March 5, 2021

መልስ ለዶክተር አለመሰገድ አባይ ጌታቸው ረዳ (Ethio Semay) 3/5/2021 (በፈረንጅ አቆጣጠር)

 

መልስ ለዶክተር አለመሰገድ አባይ

ጌታቸው ረዳ

 (Ethio Semay)

3/5/2021  (በፈረንጅ አቆጣጠር)

በመጀመሪያ የታላቅ እህቴ ልጅ የሆነው ትግራይ ውስጥ እየተካሄደ በነበረው የመጀመሪያው ወር ጦርነት ሲጀመር ከተማ ውስጥ ተምቤን ወርቅ አምባ ቢሮው ውስጥ ስራ ላይ እያለ በድሮን/አይሮፕላን ተደብድቦ መሞቱን ከትናንት በስትያ ከቤተሰብ በስልክ ተነግሮኝ የተሰማኝን ሃዘን ለአንባቢዎቼ ለማጋራት ስፈልግ ፤ ሆኖም የአሟሟቱን ሁኔታ፤ እንዴትና የት፤ ምንስ ስያደርግ እንደተገደለ ማጣራት ስላለብኝ በችኮላ ድምዳሜ ከመድረሴ በፊት እውነታው ጠለቅ ያለ ምርምራ ማካሄድ ስላለብኝ ሂስ ከመሰንዘር ተቆጥቤ ወደ ተነሳሁበት ወደ ርዕሴ ልግባ።

አለምሰገድ አባ እኔ ከተወለድኩበት አክሱም የተወለደ ከትግራይ ምሁራን አንዱ ነው። አለምሰገድ አባይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀና በሗላም እዛው ‘ሌክቸረር’ የነበረ፤ የታዋቂው የካሊፎርኒያ የበርክለይ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነው ፡፡ “Identity Jilted or Re-Imagining Identity? The Divergent Paths of the Eritrean and Tigrayan Nationalist Struggles-July 1, 1998” የሚል ዘረኛ መጽሐፍና በርካታ ምሁራዊ ጽሑፎችን በፋሺስታዊ አቀራረብ የተቀመሙ መጣጥፎች ደራሲ ነው ፡፡

በቅርቡ አለምሰገድ “The Tigrayan genocide” By Alemseged Abbay (02-20-21) http://aigaforum.com/article2021/Tigray-genocide-022021.htm የሚል በወያኔ ድረገጽ በ Aigaforum.com ለጥፎት ትናንት ማታ አንድ ወዳጄ እንድመለከተው ጠቁሞኝ (የቤት ስራ ሰጥቼሃለሁና አንብበህ አሳብህን ስጠኝ ስላለኝ) በተመለከትኩት መሰረት ነው ይህንን መልስ ለአንባቢዎቼም ጭምር እንድትመለከቱት በሚል ለመጻፍ የተገደድኩት።


እርግጥ ወያኔዎች በቀወሱ ቁጥር እየተከታተልኩ ስለሚጽፉት በተቃውሞ መጻፌ ሰልችቶኝ ስለበር ሌሎች እንዲተቹባቸው እጠብቅ ነበር። ሆኖም ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ዳተኞች ስለሆኑ በርካታ የወያኔ “ካልት ምሁራን” የሚያሰራጭዋቸው የውሸት ቅስቀሳዎች በቸልተኛነት ስለሚተውዋቸው ብዙ ጉዳት ደርሷል። ስለሆነም እነሆ ለ ዶ/ር አለምሰገድ መልስ ልስጥ።


ደ/ር አለምሰገድ አባይ አብሮ አደጌ ነው። አለምሰገድን በደምብ አውቀዋለሁ። ወላጅ አባቱ ከተማው ውስጥ ከነበሩት ዳኞች አንዱ ናቸው። በወጣትነት ዕድሜው አሁን ላለው እሳቤ ምን እንደነበር ባለውቅም፤ አሁን ከተማረ ወዲህ ግን አለምሰገድ አባይ ለኢትዮጵያ እና ለአማራ ብሄረሰቦች ካለው ጥላቻ የመነጨ በፋሺስታዊ የብሄር ተኮር ብሄረተኝነት አስተሳሰብ የተበከለ መሆኑ ይታወቃል።


ሁሉንም ጽሑፎቹን ያነበበ ሚዛናዊ ሰው የፋሽስቶች አስተሳሰብ በአለምሰገድ አባይ መጽሐፍና መጣጥፎቹ በቀላሉ መለየት ይችላል፡፡ በቅርቡ ከላይ በተጠቀሰው ወረቀቱ ላይ በሐሰተኛ ውንጀላዎች የተጠቀጠቁ ጽሑፎቹ ምሁር ከሚባል ሰው የሚጠበቅ የግጭት ትንተና አይደለም። በተለይም በአክሱም ከተማ ውስጥ በትግሬዎች ላይ ተፈፀመ የሚለው የዘር ጭፍጨፋ በሐሰት በተናገረው ልክ ከርዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ጋር አነጻጽሮታል።


እንዲህ ይላል፤-

 “As in Rwanda, no holy place can be a haven in Tigray. In the Cathedral of St. Mary at Axum, 800 believers were killed. Towns are emptied, villages flattened, and corpses left on the streets to be “eaten by hyenas.”

 

ልክ እንደ ሩዋንዳው የትኛውም ቅዱስ ስፍራ በትግራይ ውስጥ አስተማኝ መጠለያ ሊሆን አይችልም ፡፡ በአክሱም ቅድስት ማርያም ካቴድራል 800 አማኞች ተገደሉ ፡፡ ሞች ባዶ ሆነዋል መንደሮች ጠፍጣፋ ሆነዋል (ተደምስሰዋል) በጎዳናዎች ላይ የተጣሉ ሙታኖችምጅቦች እንዲመገቡዋቸው ተደርጓል፡፡ ይላል የለጠፈው የእንግሊዝኛው መጣጥፉ ለአማርኛ አንባቢዎቼ ስተረጉመው።

 

እውነታው ግን ባለፈው ሰሞን ያቀረብኩት ሕዳር 22 ለ23 አጥቢያ አክሱም ውስጥ የሆነው እውነተኛ ዘገባ እነሆ! ትርጉም  ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay) 3/3/2021 ከሚለው ጋር 800 ሰዎች ተጨፈጨፉ የሚለው የአለምሰገድ አባይ ውሸት በማንኛውም መመዘኛ ፍጹም የማይገናኝ እና የማይታመን የሞቱ ሰዎች ቁጥር የሚገርም ነው።

 

አለምሰገድ በመጣጥፉ መግቢያ  እንዲህ ሲል ይጀምራል።

“Tigrayans defeated Ethiopia’s Marxist junta, Derg, in 1991 and transformed the country from a posterchild of war and famine into a land of peace and economic miracle by 2018. However, the US was discontented with the developmental state model which put Ethiopia closer to China. Nor were the Amhara pleased with ethnic federalism that ended Ethiopia’s image of what the British-Czech scholar of nationalism, Ernst Gellner, described as “a prison of nationalities, if there was one.

ትግራዮች 1991 የኢትዮጵያን የማርክሲስት ጁንታን ደርግን አሸንፈው ሀገሪቱን ከጦርነት እና ከረሃብ ማማ ወደ ሰላም እና ኢኮኖሚያዊ ተዓምር እስከ (በ)2018 ቀይሯት ነበር፡፡ አሜሪካ ግን ኢትዮጵያን ወደ ቻይና ያቀረበችውን የልማታዊ መንግስት ሞዴል አልተደሰተም ፡፡”

 የብሔረተኝነት ምሁር የሆነው እንግሊዛዊው ቼክ ኤርነስት ጄልነርተረት ሆኖ የቀረው የብሔረሰቦች እስር ቤት” ሲል የገለጸውን የኢትዮጵያን ገጽታ ያበቃው በጎሳ ፌዴራሊዝም አማራው አልተደሰተም ፡፡” ይላል አለመሰገድ።


የትግራይ ምሁራን “በድርጅታቸው በወያነ ትግራይ” የተነደፈው ‘ፋሺስታዊ የነገድ ፌደራሊዝም’ እንደሚያመልኩ ሃቅ ነው። ኢትዮጵያን በትግሬዎች መሪነት በቋንቋ ከልሎ በዛሬው ዘመን በዓለም ብቸኛ የሆነ “የአፓርታይድን አስተዳዳር” መስርቶ አገሪቷ በታሪክዋ አይታው የማታውቀውን የነገድ መተላለቅ እና ጦርነት አስከትሎ ሕዝቧ በኑሮ ውድነት ከማይወጣው የህይወት አዘቅት የከተተ፤ ከባህላችን ውጭ የሆነውን ስነምግባር በወንድ እስረኞች ላይ ግብረሰዶማዊ ጥቃት ሲፈጽምና ሲያስፈጽም የነበረ “የዱርየዎች ሥርዓት” እንጂ አለምሰገድ እንደሚለው አይደለም።

 

ከላይ እንደጠቀሰው በትግሬ የተደገፈ ህወሓት/ የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርም (ትህነግ/ወያነ) ሆነ የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ​​(ሻዕቢያ) (ሌሎቹ አፍሪካኖችም እንዲሁ በየአገራቸው የሩዋንዳው ካጋሜ የኡጋንዳው ሙሴቬኒ)፣ በአሜሪካኖች ተደግፈው ነበር ወደ ሥልጣን የወጡት። ደርግ ሊወገድ የቻለው በአሜሪካኖች ቡራኬ ነበር። አብሶም ወታደሩ በተለያዩ ሴራዎች ስለተሰላቸ ላለመዋጋት ያሳየው ዳተኛነት ሚና ነበረው።

 

አለምሰገድ እንደሚለው ሳይሆን ታስታውሱ እንደሆነ በወቀቱ የነበረው “አሜሪካዊው ፕረዚዳንት ክሊንተን እና ወኪሉ አይሁዳዊው “ሄርመን ኮኸን” እነዚህን የጫካ ወረበሎች አዲሶቹ የአፍሪካ ዲሞክራቶችበማለት ነበር ሕዝብ እንዲቀበላቸው አፍሪካን ሲያጃጅል የነበረው።  

ከ28 አመት በሗላ “አዲሶቹ የአፍሪካ ዲሞክራቶች” ወደ ጅብነት እንዴት እንደተለወጡ ማንነታቸው ተለይተዋል። በአፍሪካ ውስጥ ቢያንስ የምስራቅና ደቡብ ምስራቅ የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ምሰሶዎች ሆነው ለአሜሪካን የሚዋጋ የአሜሪካ ተኪ ጦርፕሮከሲ” እንዲሆን ዘጋጀት የነዚህ ሃያላን አገሮች ትዕዛዝ እየተቀበሉ ወያኔ የመሰለ ወረበላ ድርጅትን በሕዝብ የተመረጡ ናቸው እያሉ (ኦባማን አስታውሱ) በመንከባከብ የአሜሪካን ፍላጎቶች ማስተዋወቅ እና በአፍሪካ ውስጥ የውስጥና የውጭ ቅኝ ግዛት (ፕሮክሲ ዋር) እንዲስፋፋ ሰበብ ሆነው ቆይተዋል።


ይህንን እውነታ ለመረዳት “ለኛ የቆሙ አመባገነኖችን መንከባከብ” የሚለው የሟቹ Charles Krauthammer "In Defense of Our Dictators", _(Washington Post, April 5, 1998, Charles Krauthammer), የሚለው ስታነብቡ ከላይ የጠቀስኳቸው ወያኔን የመሰሉ  አምባገነኖች በምስራቅ አፍሪቃ የተተከሉ የአሜሪካን “ጯሂ ውሾች” እንጂ አለምሰገድ እንደሚያቆነጃጃቸው አልነበሩም።


አለምሰገድ በማስከተል እንዲህ ይላል፦

“In 2018, the US found the opportunity to install its client, the unknown quantity Abiy Ahmed, in power. Abiy rushed to “normalize” relations with Tigray’s mortal enemy, Isaias Afwerki of Eritrea. Just as Wutchale Treaty (1889) between Italy and the Amhara emperor of Ethiopia, Menelik II, was not just about friendship and the Molotov-Ribbentrop Pact (1939) was not all about non-aggression, the Isaias-Abiy Pact (2018) was not just about “normalizing” relations.  Italy and the Amhara decided to partition Tigray among themselves, the norther half going to Italy and the southern half staying with the Amhara. The sale of what was going to become Eritrea earned Menelik military and monetary payoff. In the case of the Nazi-Soviet Pact, Poland was divided into two, the eastern part going to the USSR and the western part going to Nazi Germany. Similarly, the Abiy-Isaias Pact was primarily about devouring Tigray. Cunning Isaias was delighted to find a pliant Abiy for a partner in genocide. For this rapprochement, Abiy won the Nobel Peace Prize, which Donald Trump unabashedly ridiculed, because he believed that he was the one who deserved it. Who would blame him for being too logical? Should not the king maker, rather than the king, deserve to win it?


አሜሪካ ... 2018  አቢይ አህመድ የተባለ የማይተዋቅ ሰው በስልጣን ላይ ለመጫን እድሉን አገኘች ፡፡ አብይ ከትግራይ ቀንደኛ ጠላት ከኤርትራው ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ያለውን ግንኙነትመደበኛ ለማድረግተጣደፈ ፡፡ ልክ በጣልያን እና በአማራው ንጉሠ ነገሥት በዳግማዊ ምኒልክ መካከል የውጫሌ ስምምነት (1889) ስለ ወዳጅነት ብቻ እንዳልሆነ እና የሞሎቶቭ-ርበንትሮፕ ስምምነት (... 1939) ጥቃቶችን ስለ ማቆም በሚመለከት እንዳልነበረ ሁሉ፤የኢሳያስ-ዐቢይ’ ስምምነትና ግንኙነት (2018 ..) ስለመደበኛ ግንኙነትብቻ አይደለም። ጣልያን እና አማራው ትግራይን በመካከላቸው ለመከፋፈል እንደወሰነው ተመሳሳይነቱ አስታዋሽ ነው። ይህም የሰሜኑ ግማሽ ትግራይ ወደ ጣልያን ሲሄድ የደቡቡ ግማሽ ደግሞ ከአማራው ጋር እንዲጠቃለል ሆነ።  ወደ ኤርትራ ሊመጣ የነበረው የሽያጭ ገቢ የሚኒሊክ ወታደራዊ ግንባታ እና የገንዘብ ምንጭም ሆነ ፡፡ በናዚ-ሶቪዬት ስምምነት ጉዳይ ፖላንድ ለሁለት ተከፍላ ነበር ምስራቃዊው ወደ ዩ. ኤስ. ኤስ. አር እና ምዕራባዊው ወደ ናዚ ጀርመን እንደሄደው ሁሉ ማለት ነው ፡፡ በተመሳሳይም የአብይ-ኢሳያስ ስምምነት በዋናነት ትግራይን ስለመዋጥ/ስለመሰልቀጥ/ ነበር ፡፡ ተንኮለኛው ኢሳያስ በዘር ማጥፋት ወንጀል አጋር የሚሆን ተጓዳኝ  የሚሆንለትን አቢይ አሕመድ በማግኘቱ ተደስቷል።”

በማለት አለመሰገድ ጽሁፉን ይተነትናል።

እውነት ለመናገር ከሆነ መሰሪው አብይ አሕመድ በአለምሰገድ ሳይታወቅ ኖሮ ይሆናል። እውነታው ግን አሜሪካኖች የማያውቁትን ሰው ከመሬት አንስተው ወደ ሥልጣን አያመጡም። ወደ ሥልጣን የሚያመጡት ሰው ወይንም ቡድን ልክ እንደ ወያኔዎች አብሮ ሲመለመል የነበረ የነሱ ሰው ነው የሚሾሙትን የሚደግፉት። ኢሳያስ የነሱ ልጅ ነበር፤ መለስ እና ብዙዎቹ የትህነግ አመራሮችና የጦር አበጋዞች እንዲሁ በሞሳድና በአሜሪካኖች የተቀቡ ነበሩ። አብይ አሕመድም እንዲሁ የስለላ ሥራዎች በሓላፊነት ሲሰራ በእነሱ “መንጠቆ” እንደ ዓሳ የተያዘ (አንዳንዶቹ መሪዎችም በስለላው ስራ ሲሰራ ከድሮ ጀምሮ ወዳጃችን ነበር ብለው ሲናገሩ የነበሩ የታወቁ መሪዎች ሰምታች ይሆናል፤ እራሱም ከድሮ ጀምሮ የማውቃቸው ወዳጆቼ እያለ ሲጠቅስ ሰምታችሁ ይሆናል) በግልጽ አማርኛ ዛሬም ቅጥረኛቸው ነው።


ዶ/ር አለምሰገድ ‘ስለ አጼ ምኒሊክ የአማራ ንጉሥ መሆናቸው’ ፤የጻፈውን ስታነብቡ የትግሬ አክራሪ ብሔረተኞች ምሁራን ምን ያህል የታሪክ ደናቁርት እንደሆኑ በዚህ ማየት ይቻላል።

ስለጠቀሰው የውጫሌ ስምምነትም ቁንጽልዋን አንቀጽ በመጥቀስ ትግሬዎች ኝኝ ሲሉ ለዓድዋው ጦርነት ግን መንስኤ መሆንዋን አይጠቅሱዋትም። የትግሬዎች በሽታም ቁንጽል ንባቡን እየመዘዙ እንደሚመቻቸው ማቅረብ የታወቁበት በሽታቸው ነው። በቅርቡ ‘ምጽላል’ የተባለች “ሞናሊዛ” የሚል የውሸት ስም ሰጥተው አልጀዚራ ለጋዜጠኞች ቃልዋን የሰጠች የወያኔ ልዩ ሃይል የነበረች ምስኪን ወጣት  በኤርትራኖች/አንዴ ደግሞ ወታደሮች/ ሊደፍሩኝ ሲሉ እምቢ ስላልኩ እጄን በጥይት መትተው  እግሬንና ቀኝ እጄን ቆረጡኝ በማለት የተናገረቺው ምስኪን እንዴት መልምለው ለውሸት እንዳዘጋጁዋት ሁሉ የትግራይ ምሁራንም እንዲሁ የሚከትቡዋቸው የታሪክ እይታቸው በውሸት የተነከረ ቀለም መሆኑን የተጠመቁበት በሽታቸው ነው። ስለሆነም ምኒሊክ በዘር አማራ ብቻ አይደሉም ኦሮሞም ናቸው። የአማራ ንጉሥ ብቻ ሳይሆኑ የመላው ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትም ነበሩ።

 

በጣም የሚገርመው የተለመደው የዶ/ር አለምሰገድ አባይ ዝባዝንኬና አማራን የመወንጀልና የመጥላት ልማዱን እንደሚከተለው ይነበባል፦

“Visionless, Abiy chose to play the anti-Tigrayan ethnic card to win the support of the disgruntled unitarian Amhara political elite. Along with the Amhara militia, Fano (akin to Interahamwe and Janjaweed), Abiy organized a multi-national coalition—Ethiopia, Eritrea, Somalia, and UAE, to downsize Tigray-- economically, geographically, and demographically. As early as 2018, all land communication to and from Tigray was closed so that Tigray could starve to submission. Just like der lebensraum was one of the driving forces for Germany to commit genocide in 1904 (SW Africa) and the 1940s (holocaust), the Eritrean and Amhara expansionists wanted to truncate and annex western and southern Tigray, respectively.”

ይላል፦

ራዕይ አልባው አብይ አሕመድ ቅር የተሰኘውን አሃዳዊያኖቹ የአማራ የፖለቲካ ልሂቃን ድጋፍ ለማግኘት ሲል ፀረ-ትግራይ ብሔረሰብ ካርድ መጫወትን መርጧል ፡፡ ፋኖ ከተባለው (እንደ ኢንተርሃምዌ እና ጃንጃዌድ መሰል የሆነው) የአማራ ሚሊሺያ ትግራይን በኢኮኖሚ በጂኦግራፊ እና በሕዝብ ብዛት ዝቅ ለማድረግ የብዙ አገሮችን ጥምረት በማቀናጀት ማለትምኢትዮጵያን ኤርትራን ሶማሌን እና አሚሬትን’ አደራጅቷል ፡፡ 2018 መጀመሪያ ትግራይ በረሃብ እንዲሰቃይ ወደ ትግራይ የሚመጣ እና የሚመለስ ሁሉም የመገናኛ ግንኙነቶች እንዲዘጋ አደረገ። ልክ እንደ ‘ዴር ደርቤንስራም’ (በጀርመን) እና እ... 1904 ደግሞ (ደቡብ አፍሪካ) እና 1940 ዎቹ (እልቂት) የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈጽሙ ከሚያነሳሷቸው ኃይሎች መካከል አንዱ እንደነበረው ሁሉየኤርትራ እና የዐማራ ተስፋፊና ሰፋሪ ሃይሎች ምዕራባዊውን እና ደቡባዊውን ትግራይን በቅደም ተከተል ማጠቃለል እና ማካተትን የተከናወነ ወረራ ነው ፡፡” ስተረጉመው።


”The war broke out in complete news blackout on November 4, targeting civilians, livestock, farm crops, and infrastructures. In a life-negating testament, like the one given by the German von Trotha against the Herero of S.W. Africa (1904),”……..”the army along with the Fano moved in to kill civilians indiscriminately. In the “slaughterhouse” of Mai Kadra, around 1000 Tigrayans were killed with machetes and axes, fulfilling two objectives of the genocide: downsizing Tigray’s demography and geography provocateur who championed the muscular foreign policy of neoconservatism that helped lay the ideological groundwork for the 2003 U.S.-led invasion of Iraq, died June 21 at 68. (Adam Bernstein-Washington, D.C.-Obituary editor) artillery. Mai Kadra was Deir Yasin (1948) and Srebrenica (1995), all at the same time. Just like the Irgun and Lehi Zionist militia conducted massacres and ethnic cleansing in Deir Yasin to change its demographic looks, the Fano wanted Tigrayans to vanish so that Western Tigray becomes Amhara. What happened in Mai Kadra, however, was the tip of the iceberg. As in Srebrenica, where the Servs massacred some 7000 young Bosnian Muslims, it was designed to downsize the demography of Tigray.

‘Twenty first century’s unprecedented and most unimaginable atrocities are being committed in Tigray. Young people are “slaughtered like chicken.” They are herded to numerous “slaughterhouses,” where they can be heard screaming while being killed.”

 “…Young girls and women are gang-raped before execution or deportation to arid wastelands such as the Tekezze. Deportations are warrant of death as what von Trotha did with the Herero (1904) and the Ittihadists (1915) with the Armenians. …”

 

“ጦርነቱ በኖቬምበር 4 ቀን ሙሉ የዜና ሰርጭቶችን ማቋረጡን በጀመር ሲቪሎችን ፣ የከብት እርባታዎችን ፣ የእርሻ ሰብሎችን እና የመሰረተ ልማት አውታሮችን ያነጣጠረ ጥቃት ነበር፡፡ ምናልባትም በብዙ ሀገሮች (በዒራቅ) የቅንጅት ኃይሎች እንዳደረጉት ምናልባትም፣ በአየር ላይ የቦንብ ድብደባና የመርዝ ጋዝ ጥቃት ፣ ተከትሎ ወታደሩ ከፋኖ ጋር በመሆን ያለምንም ልዩነት ሲቪሎችን ወደ መግደል ገባ ፡፡ በማይ ካድራ “እርድ” ውስጥ ወደ 1000 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆችን በጅምላ በገጀራና በመጥረቢያ የተገደሉ ሲሆን የዚህ የዘር ፍጅት ዓላማውም ሁለት ዓላማዎችን ማሟላት ነበር፡ ይህም የትግራይን የስነ ህዝብ አሰፋፈር/ አቀማመጥ እና ጂኦግራፊ የቆዳ ስፋትን ዝቅ ማድረግ ያለመ ነው። ማይ ካድራ ዴር ያሲን (1948) እና ሴሬብሬኒካ (1995) ዓይነት የተፈጸመው ዓይነት ቦታ ነች። ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜ ፡ልክ የኢርጉን እና ሊሂ ጽዮናዊያን ሚሊዮኖች የስነልቦና መልክን ለመለወጥ በዴር ያሲን እልቂትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዳከናወኑ ሁሉ ፋኖዎች ምዕራባዊ ትግራይ አማራ እንድትሆን ትግራዮች እንዲጠፉ ፈለጉ ፡፡ በማይ ካድራ ውስጥ የተከሰተው ግን የበረዶው ጫፍ ነበር (ለማመን የሚከብድ ጭፍጨፋ ነበር የተፈጸመው) ፡፡ እንደ ሰርብሬኒካ ሁሉ ሰርቮች 7000 ያህል የቦስኒያ ወጣት ሙስሊሞችን በጅምላ እንደጨፈጨፈ ሁሉ፣በተመሳሳይ መልኩ ጭፍጨፋው የትግራይን ‘ስነ ህዝብ’ ዝቅ ለማድረግ ያለመ ነበር ፡፡”

እንዲሁም

“… ወጣት ሴት ልጆች እና ሴቶች ከመገደላቸው በፊት እንደ ተከዝዜ ወዳሉት አስቸጋሪ  መሬቶች ከመሰደዳቸው በፊት በቡድን ይደፈራሉ ፡፡ እንዲህ ወዳሉ አስቸጋሪና ረባዳ መሬቶች ማቅናት ደግሞ ቮን ትሮታ ከሄሬሮ (1904) እና ኢቲሃዲስቶች (1915) ጋር ከአርሜናውያን ጋር እንደተደረገው ሁሉ የሞት ቀጠና ናቸው ፡፡ … ”


በማለት ሳምረ በተባለው ወያዎች ያደራጁት “ኢንትርሃሙዌው” ጨፍጫፊ ቡድን አማራው ላይ “ማይ ካድራ” ውስጥ ያለቁ ምስኪን የቀን ሰራተኞች ሳይቀሩ ማለትም (በማይካድራ ከተማና ዙሪያዋ ያለውን ሰፋፊ የሰሊጥና የማሽላ እርሻዎች ተከትሎ የወቅት ሥራ የሚሠሩ በልማድ ‹‹ሳሉግ›› በመባል የሚጠሩ የጉልበት ሠራተኞች በብዛት የሚኖሩ ሲሆን፣ በተለምዶ ‹‹የጡት እናት/አባት›› በመባል በሚጠሩ ቤቶች ውስጥ በርከት ብለው የሚያድሩ አማራዎች  ናቸው፡፡ በጥቃቱ ሰለባ የሆኑት በአብዛኛው እነዚሁ በቀን ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚኖሩ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው፡፡) የአማራዎች ዕልቂት እንዳልተፈጸመ በመካድ ለትግሬ ወገንተኛነቱን በማድላት፤ በትግሬዎች ላይ የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው በማለት “በቦዝኒያ ወጣት እስላሞች” እንደተፈጸመው የዘርና የሃይማኖት ጥቃት አመሳሰሎ ዘግቦታል። የሚገርመው ደግሞ

“በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ታይቶ የማይታወቅ እና እጅግ የማይታሰብ ግፍ በትግራይ እየተፈፀመ ነው፡፡ ወጣቶች “እንደ ዶሮ ታረዱ” ፡፡ በሚገደሉበት ጊዜ ጩኸት የሚሰማባቸው ወደ ብዙ “እርድ ቤቶች” ታርደዋል ፡፡ ሰርቢያዎች እነሱን ለማዋረድ የቦስኒያ ሙስሊም ሴቶችን እንዳረገዙ ፣ የትግራይ ሴት ልጆች እና ሴቶች በዐማራው ወንዶች በግዳጅ እየተፀነሱ ከቤተሰብ አባላት ጋር ወሲብ ለመፈፀም እየተገደዱ ነው ፡፡”

በማለት አለምሰገድ አባይ ለ 45 አመት በትግሬ ወያኔ መሪዎች እና ካድሬዎች እንዲሁም አስተዳዳሪዎቻቸው በኩል በራያም ሆነ በወልቃይት አማራዎች ላይ የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ እንዳልተካሄደ በማድረግ በአማራዎች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በግልባጩ በመዘገብ እውነታውን ሲያምታታ፤ በሚገርም ሁኔታ እንደምሁርነቱ በሁሉም በል የተፈጸመ ወንጀል ላለማጋለጥ ሲል በወያኔ ትግሬ ፋሺሰቶች ትዕዛዝ ራ ላይ የተፈጸመው የ45 አመት እልቂት አማራዎች በትግሬዎች ላይ የፈጸሙት በማስመሰል መጪው ትውልድ እንዲፋጅ አድርጎ ለታሪክ መተው እጅግ የሚያበሳጭ ስራ ነው።

የወያነ ትግሬዎች በአማራ ማሕበረሰብ ላይ ያደረሱት የዘር ማጽዳት ወንጀል የ45 አመት ግፍ በርካታ መጽሐፍ የሚወጣው ግፍ ስለሆነ ያንን በመተው ሳምረ የተባለ የወያኔ ዱርየ ነብሰገዳይ ቡድን  አማራው ላይ ማይካድራ ውስጥ ምን እንደፈጸመ ያልተጠናቀቀው አጭር ዘገባ እነሆ ላስነብባችሁ።

ባጭሩ

በማይካድራ የሆነው በሰብአዊ መብቶች ድርጅት በከፊል የተዘገበው ሪፖርተር መጽሔት ዮሐንስ አንበርብር በሚል ጸሐፊ በ30 December 2020 ‘የማይካድራ ጭፍጨፋን አስመልክቶ በተጨማሪ ገለልተኛ ተቋም የተደረገው ምርመራ ግኝትና ተመድ ያነሳው የገለልተኛ ምርመራ ጥያቄ” በሚል ርዕስ የተለጠፈው ጽሑፍ እነሆ።

ኢሰመጉ ታኅሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን የምርመራ ግኝት ለሪፖርተር የላከ ሲሆን፣ አጠቃላይ የምርመራ ግኝት ሪፖርቱም እንደሚከተለው ተሰናድቷል።የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ያሰማራው መርማሪ ቡድን በማይካድራና በሌሎች አካባቢዎች ኢሰመጉ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች፣ በትግራይ ክልል መንግሥትና በፌዴራል መንግሥት መካከል የነበረውን የትጥቅ ግጭት በከፍተኛ ትኩረት ሲከታተለው ነበር፡፡

ኢሰመጉ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ ቀናት ባወጣቸው ማሳሰቢያዎች ግጭቱ በምንም ዓይነት ሁኔታ ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን ደኅንነትና የሲቪል ንብረቶችን አደጋ ውስጥ የሚከት እንዳይሆን ሲወተውት ቆይቷል፡፡ ሆኖም በግጭቱ ወቅት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂ ግድያዎችና ፆታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ ለልዩ ልዩ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶች፣ እንዲሁም ከፍተኛ ለሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በማይካድራ ከተማ የተፈጸመው የብዙኃን ግድያና ወንጀል ዋነኛው ነው፡፡

ኢሰመጉ ሁኔታውን ለማጣራት የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያ ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥፍራው በመላክ በወቅቱ የተፈጸሙት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምንነት የመለየት ሥራ ከኅዳር 24 እስከ ታኅሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ፣ ሁመራ፣ አብደራፊ፣ አብርሀጅራ፣ ዳንሻና ጎንደር ከተሞች ተዘዋውሮ የመስክ ምርመራ ሥራ አከናውኗል፡፡ የምርመራ ቡድኑ በተጠቀሱት አካባቢዎች ተዘዋውሮ የሟች ቤተሰቦችን፣ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን፣ የዓይን ምስክሮችን፣ የቀብር ሥርዓቶችን ያከናወኑ ሰዎችንና የቤተ ክርስቲያን አባቶችን፣ በጊዜያዊነት የተቋቋሙ የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችንና ሌሎችም የመረጃ ምንጮችን ተጠቅሞ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን አሰባስቧል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ ቡድኑ በቤተ ክርስቲያን ውስጥና ከቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውጪ የሚገኙ የጅምላ መቃብሮችን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ በምርመራ ሥራው ወቅት አሁን ድረስ ያልተነሱና የቀብር ሥርዓት ያልተፈጸመላቸው አስከሬኖችን ጭምር አግኝቷል፡፡ የምርመራ ቡድኑ በቆይታው መርምሮ ያገኛቸው ዋና ዋና ጉዳዮችም እንደሚከተለው ቀርበዋል።

 

የትጥቅ ግጭቱ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ በትግራይ ክልል መንግሥትና በፌዴራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በከተማዋ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ይደረግ በነበረው ከፍተኛ ግጭት የተነሳ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በተለይም የሌላ ብሔር ተወላጆች ከባድ ሥጋት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ የማይካድራው ድርጊት ከመከሰቱ ሁለት ቀናት አስቀድሞ የማይካድራ አካባቢ ፖሊስና የትግራይ ልዩ ኃይል መረጃ ታቀብላላችሁ በሚል የሱዳን ሲም ካርድ የያዙ ሰዎችን ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ ያጣራ ሲሆን፣ በፍተሻው የተገኙ ሲም ካርዶች ተሰባብረዋል፡፡ በሁኔታው ሥጋት የገባቸው ሰዎች በተለይም ወደ አማራ ክልል ለመግባት ያደረጉት ሙከራ፣ ሁሉም መውጫ መንገዶች በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት የተዘጉ በመሆናቸው መውጣት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

 

 በዕለቱ (ጥቃቱ በተፈጸመበት ቀን ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም.) የፖሊስና የልዩ ኃይል አባላት፣ እንዲሁም የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች (በአብዛኛው በልዩ ስሙ ‹ሳምሪ› ከሚባል ሰፈር የመጡ) ማንም ሰው ከቤት እንዳይወጣ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የጥቃቱ ተጎጂዎች ተናግረዋል፡፡ ወጣቶች በብዛት ሆነው በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ሲጨፍሩ እንደነበርና በአንዳንድ ቦታዎች ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች የሚኖሩበት ልዩ ስሙ ‹‹ግምብ ሰፈር›› በሚባለው አካባቢ ደግሞ፣ ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ የትግራይ ተወላጅ የሆኑና ያልሆኑ ሰዎችን ለመለየት መታወቂያ በማየትና በትግሪኛ ሲያናግሯቸው መልስ መስጠት የማይችሉ ሰዎችን ለይተው ጥቃቱን ማድረስ እንደ ጀመሩ ተጎጂዎች ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

 

የማይካድራው ጭፍጨፋ እንዴት ተፈጸመ?

 

 ጥቃቱ በአብዛኛው ገጀራ፣ ጩቤ፣ ፈራድ (መጥረቢያ) እና ገመድ የመሳሰሉ መሣሪያዎችን በመጠቀም የተፈጸመ ሲሆን፣ ዒላማ ያደረገው ደግሞ በአብዛኛው ወጣት ወንዶችን መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጥቃቱ በግልጽ የብሔር ማንነትን መሠረት ያደረገና በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጅ በሆኑ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆንኑ በቁጥር አነስተኛ የሚባሉ የሌሎች ብሔር ተወላጆችም የጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ድርጊቱ በዋናነት ማይካድራ ከተማ ውስጥ ‹ሳምሪ› ከተባለ ሰፈርና ከሌሎችም ቀበሌዎች በመጡ በቡድን የተደራጁ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች ሲሆን፣ እያንዳንዱ የወጣቶች ቡድን በትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት በጦር መሣሪያ የታገዘ ሽፋንና ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበር ተጎጂዎች ከሰጡት ቃል ለመረዳት ተችሏል፡፡

በጥቃቱ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ፍለጋና ቀብር ከኅዳር 2 እስከ ኅዳር 6 ቀን 2013 ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት የተከናወነ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል በማይካድራ ከተማ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ብዛታቸው 86 የሚሆኑ እያንዳንዳቸው በአማካይ ከአምስት እስከ አሥር ያህል ሰዎች የተቀበሩባቸው የመቃብር ሥፍራዎችንና በወቅቱ አስከሬኖች ተጭነው የመጡባቸው በርካታ አልጋዎችን ለማግኘት ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ውጪ በቅርብ ርቀት ላይ 42 ሰዎች፣ ስለላ መስመር በሚባለው አካባቢ 57 ሰዎች፣ ወልደ አብ መንገድ ላይ 56 ሰዎች፣ ቀበሌ 04 ድልድይ አካበቢ ስድስት ሰዎች፣ በአቅራቢው ካለ ጎርፍ መውረጃ አካባቢ 18 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡  ተጎጂዎች በፍለጋው ወቅት አስከሬናቸው አሁን ድረስ ያልተገኙና ያልተቀበሩ መኖራቸውንም ያሳወቁ  ሲሆን፣ የኢሰመጉ የምርመራ ቡድን አባላትም ያልተነሳ አስከሬን በዓይናቸው ዓይተው አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ ቦታዎች አካባቢው በጣም ሞቆታማ በመሆኑ፣ ምክንያት የሟቾች አስከሬን ለማንሳት እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ባለበት ቦታ እንዲቀበሩ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

 

ከማይካድራ በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎች የተፈጸሙ ተመሳሳይ ጥቃቶች

 

የምርመራ ቡድኑ ከማይካድራ ከተማ በተጨማሪ ተመሳሳይ ጥቃቶች በሁመራና በዳንሻ ከተሞች መፈጸማቸውን አረጋግጧል፡፡ በሁመራ ከተማ ስድስት ሰዎች በገጀራ፣ በመጥረቢያና በጥይት ተመትተው መገደላቸውን፣ አስከሬናቸው ሳይነሳ ፀሐይ ላይ በመቆየቱ ማንሳት ስላልተቻለ ልዩ ስሙ ‹እንድሪስ› በሚባል አካባቢ መቀበራቸውን ከሟች ቤተሰቦች ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ በዳንሻ ከተማ ደግሞ ዕድሚያቸው የ12 እና የ15 ዓመት የሆኑ ሕፃናት በመጥረቢያ ተመትተው መገደላቸውንና ቀብራቸውም በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህ መንገድ በተፈጸመው ጥቃት ኢሰመጉ ባደረገው የመስክ ምልከታና ባሰባሰበው መረጃ ከ1,100 በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በጥቃቱ ከ122 ያህል በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ በአብደራፊና በጎንደር ሆስፒታሎች ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም፣ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የነበሩት ወጣቶች ንብረት ያወድሙና ይዘርፉ እንደነበር ተጎጂዎች ከሰጡት ቃል ለመረዳት ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል የምርመራ ቡድኑ ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት በማይካድራ ከተማ አስገድዶ መድፈርን የመሳሰሉ ፆታዊ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች አሰባስቧል፡፡ ስለሁኔታው ቃላቸውን የሰጡ ስድስት የጥቃቱ ሰለባዎች እያንዳንዳቸው ከአሥር በላይ በሚሆኑ ጥቃቱን ሲፈጽሙ በነበሩት ወጣቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል፡፡ የምርመራ ቡድኑ አባላት በወቅቱ ቃላቸውን የሰጡ ተጎጂዎች በግልጽ በሚታይ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ውስጥ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ተጎጂዎቹ ከደረሰባቸው ጥቃት በኋላ ማንኛውም ዓይነት አካላዊም ሆነ ሥነ ልቦናዊ ሕክምና ያላገኙ በመሆኑ፣ አፋጣኝ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ትኩረት እንዲሰጡት ኢሰመጉ ያሳስባል፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ በወቅቱ በማይካድራ ከተማና አካባቢዋ የነበረውን ሁኔታ ተከትሎ ለጊዜው ግምቱ በግልጽ ያልታወቀ ንብረት መውደሙንና መዘረፉን፣ በርካታ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን በመተው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መፈናቀላቸውንና ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን መሰደዳቸውንም የኢሰመጉ መርማሪ አባላት ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በወቅቱ የጠፋውን የንብረት ውድመት፣ ዝርፊያና የአገር ውስጥ ተፈናቃይና ስደተኞች አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ ኢሰመጉ በቅርብ ጊዜ ይፋ በሚያደርገው ጥቅል የሰብዓዊ መብቶች ዘገባ የሚዳስሰው ይሆናል፡፡ 

በዚህ ብዙዎችን ሰለባ ባደረገው ድርጊት ሰዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው የተከላከሉ፣ የሸሸጉና መረጃ በመስጠት እንዲሸሹ በማድረግ ሰብዓዊ ተግባር የፈጸሙ የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውንም የኢሰመጉ የምርመራ ቡድን ለማወቅ ችሏል፡፡ ምንም እንኳን የምርመራ ቡድኑ በዚህ ሰብዓዊና በጎ ምግባር የተሳተፉ የትግራይ ተወላጅ ሰዎችን በሥጋት ምክንያት አካባቢውን ለቀው የወጡ በመሆኑ አግኝቶ ለማነጋገር ባይችልም፣ በዚህ ሰብዓዊ ምግባር ከጥቃቱ የተረፉ በርካታ ሰዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በማይካድራ ከተማና አካባቢው ተፈጸመው ግፍና ጭካኔ የተሞላበት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ያስከተለ ድርጊት መሆኑን ኢሰመጉ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ስለሆነም ይህን አሳዛኝ ድርጊት ያቀዱ፣ የፈጸሙና ያስፈጸሙ አጥፊዎች በሙሉ በተገቢው መንገድ ተጣርቶ በሕግ ፊት ሊቀርቡ እንደሚገባ ኢሰመጉ ያሳስባል፡

ኢሰመጉ የዚህ እጅግ አሳዛኝ ድርጊት ዝርዝር የጉዳት ዓይነትና መጠን፣ መነሻ ታሪክ፣ የሕግና ፍሬ ነገር ትንተናና ምክረ ሐሳብ የያዘ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች የተሳተፉበት ጥቅል የሰብዓዊ መብቶች ዘገባ በቅርብ ጊዜ አጠናቅሮ ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን አሳውቋል፡፡” ይላል።

እኔ ጨርሻለሁ፡ እናንተስ ምን ትላለችሁ?

ጌታቸው ረዳ