Monday, October 10, 2011

እናንተን ተሸክሞ እያነከሰ በማዝገም ላይ ያለው ታሪክ

 
To change zoom level Press Ctrl and + symbol keys the same time (together) (small size font or minimize page Press Ctrl and - (Minus) symbol.
New Book by Getachew Reda
 
አዲስ መጽሃፍ
 
የወያኔ ገበና ማህደር
 
Getachew Reda
 
P.O.Box 2219
 
San Jose, CA
 
95109
 
(ዋጋ $30.00) Tel-(408) 561 4836
 
GetachewReda
 
P O Box 2210
 
San Jose, CA 95109
 
 
 

ከታች ያለው ፎቶግራፍ የቀድሞው የህወሓት የኢንተልጀንስ (ስለላ) ኃላፊ የነበረው አቶ  ብስራት አማረ ነው፡
‹‹ፍኖተ ገድል››
የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታሪካዊ አነሳስና ጉዞ (1967-1977 ..) መጽሐፍ በማሰተም በምረቃው ስነ ሰርዓት ላይ                        እናንተን ተሸክሞ እያነከሰ በማዝገም ላይ ያለው ታሪክ 

ወያኔዎች ታሪክ ሰርተናል ይላሉ ሲጽፉም ሲዘፍኑም ሲደሰኩሩም። ቋንጃው ላይ አንደተመታ እንሰሳ እያነከሰ በማዝገም ላይ ያለው ታሪክ ፍጥነት የለውም እና ዓይን ያለው ተመልካች የታሪኩ ምንንት ከግር እስከ ራሱ አይቶ ምንነቱ ለመግለጽ አያዳግተውም።  
ሰሞኑን ዓብይ ዜና የሆነው በሰው ልጆች ግፍ የፈጸሙ የደርግ ሰዎች በወያኔ እስር ቆይተው በምህረት/ይቅርታ ተደርጐላቸው ወደ እየ ቤተሰቦቻቸው እና ወደ ማሕበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተፈተዋል። አንዳንድ የዜና ዘጋቢዎች በነፃ ተለቀዋል፤ ይላሉ። ሰዎቹ ታስረው እንጂ በነፃ አልተለቀቁም። በነፃ መለቀቅ ማለት ከወንጀሉ ነፃ ሆኖ ሳይታሰር ሲሰናበት ነው።የሆኖ ሆኖ ሰዎቹ ተለቀዋል። ይቅር ለእግዚአብሔር ነው ይላሉ አበው ሲተርኩ። ይቅር ባይነት መመሪያችን እንደነበር በቁጥር አንድ የተዘገበ ነው። ዛሬ ያ ቁጥር አንድ ደብዛውም የለም።ምሕረት ማድረግ ዛሬ ለምድር አምላኮች ለፖለቲካ ትርፍ የሚፈጸም ባሕርይ እንጂ ለሰማይ አማላክ ተብሎ የሚደረግ ስነ ምግባር አይደለም።
ወያኔዎች እስከዚህ ድረስ ደርሰው አሳሪ እና ፈቺ ፤ፈራጅ እና ምሕረት ሰጪ ዳኛ እና አዳኝ ለመሆን የበቁት እዚህ ድረስ ያደረሰው መንገድ ሲመረመር “ዓለምን ያስደነቀ የጦርነት ስልታችን ተጠቅመን ደርግን በማሸነፋችን ነው” ይበሉ እንጂ ከዚያ እስከዚህ ድረስ ያደረሰው መንገድ ሲመረመር የስለላውና የደህንነቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረው የወያኔው ታጋይ ብስራት አማረ ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትኦጵ እና በሃዋርያ ጋዜጣ ላይ እንደገለጸው አሁን በመንግሥትነት ያለው “ህወሓት” የድርጅቱ የበላይ መሪ ሆኖ ዛሬም ድርጀቱን በመወከል እና በመምራት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የህወሓት መንግሥት ጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ፤ ኢትዮጵያን የማያውቅ እና ኢትዮጵያዊ ስሜት የሌለው ጸረ ኢትዮጵያ ግለ ሰብ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦታል።እንግዲህ አንደ ብስራት አገላለጽ መለስ ዜናዊ ኤርትራዊነት የሚያጠቃው ኢትዮጵዊነት የማያወቅ፤ስለ ኤርትራ ሁለት መጽሐፍ የጻፈ፤ ስለ ኮሚኒስት አገር ሲጽፍ ስለ ትግራይ ወይንም ሰለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያልጻፈ ጸረ ኢትዮጵያ ግለሰብ በድርጅቱ ውስጥ ሰርጐ በመግባት ድርጅቱ በመለስ ዜናዊ ጭንቅላትና መንፈስ የተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል። በእንዲህ ዓይነት መሪ የተመራ ድርጅት “የትግራይ ስሜት ከሌለው” “የኢትዮጵያዊነት ስሜት” ከሌለው “”ኢትዮጵያን የማያወቅ” ከሆነ፤ ስለ ኢትዮጵያ የቆሙትን ገድሏል፤አፍኗል፤እንዲገረፉ አድርጓል፤ብዙ ግፍ በኢትዮጵያውያን እና በምድሪቱ መልክአ ምድር  ላይ ሕግ ወጥ ድርጊት ፈጽሟል። በስሩ የነበሩ ታዛዦቹ “አድርጉ የተባሉትን ሁሉ አድረገዋል”።
ለነገሩ መለስ ዜናዊን ብቻ በመሪነቱ ዓይን ውስጥ ገባ እንጂ ከመለስ ዜናዊ የባሰ አረመኔ እና ፊውዳል/መስፍን ስብሓት ነጋ እንደሆነ ብዙ ተጋዮች ይናገራሉ። መለስ ዜናዊ የተሳተፈባቸው ወንጀሎች ወደ ኤርትራዊነቱ ከማዳላቱ እና ጥቂት ግፎች ከማስፈጸሙ ውጭ ሲነጻጸር ስብሓት ነጋ እና የስብሓት ነጋ ሎሌዎች የፈጸሙት ግፍ እና ወንጀል አይገናኝም/የባሰ ነው ይላሉ፤አዋቂዎች።በዚህ ዓይነት ተከታዮች የተማረኩ ሰዎች የሚማርኳቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች በቁጥጥር ስር የሚያውሏቸው ሰዎች ከዱላ ድበደባ ጀምሮ፤በወንድ ፍሬ ላይ ውሃ የሞላ የከረጢት ብራሾ ማንጠልጠል፤ ጣራ ላይ በጠፈር አስሮ ሰው ዘቅዝቆ መግረፍ፤የሰው ገላ በጋለ ብረት እና ማጭድ መተኰስ/ማቃጠል፤እንጨትና ጭድ  በእሳት አቀጣጥሎ በነበልባል እሳት እና በጭስ አፍኖ ማሰቃየት፤በፈላ ውሃ ጭንቅላቱ ላይ እየደፉ ማሰቃየት…ታሳሪን የጉልበት ስራ በነፃ እንዲሰራ በበረሃ ማሰቃየት…ሰዎች በተናጠል እና በጅምላ ከተማ ውስጥ ሰላይ ቡድን ልኮ ተቃዋሚዎቹን በመርዝ መግደል ወይንም በጥይት መረሸን፤ በጅምላ አፍኖ መረሸን በየመሳሰሉ አረመኔ ምርመራዎች  እና ግፎች መፈጸም የድረጅቱ ዓይነተኛ መለያ ባሕሪው አንደሆነ አሌ የማይባል የተዘገበ ማሕደር እና የግፍ ታሪክ አለው።
ድርጅቱ ከደርግ ባልተናነሰ የግፍ ስራ የፈጸመ መሆኑን እያወቀ፤ መንግሥት ሆኖ ከጫካ ወደ ከተማ ከገባ በላም ቢሆን አንዳንድ የድርጅቱ ካድሬዎች እና መሪዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የፈጸሙት ግፍ እና የማን አለኝነት በደል በሕግ እንዲመረመር “ልዩ ባጀት ከፍተው” የደርግ ወንጀለኞች ተከስሰው ጥፋታቸው ታይቶ ቅጣታቸው እንዲያገኙ ልዩ ፍርድ ቤት ሲቋቋም”  የወያኔ ክፍሊ ህዝቢ እና የድርጅቱ አመራሮች የስለላ እና የደ ንነት እንዲሁም የወያኔ እስር ቤት ሃላፊዎች ፤ካድሬዎች እና የምርመራ ክፍሎች በረሃ እያሉ የፈጸሙት በቤተሶቦቻችን ያደረሱት ሕግ የተላለፈ በደል ስላለ “ለተጐጂዎች እና አቤት ባይ ቤተሰቦች መብት የሚያዳምጥ ነፃ የሆነ ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ይፈቀድልን” ተብለው የወያኔ መሪዎች ትግራይ ውስጥ በህዝብ ሲጠየቁ “በረሃ ውስጥ ትግል ስናካሂድ የተደረገ ጥፋት ሁሉ አሁን ልንጠየቅበት አይቻልም” በማለት ‘ወጊዱ፤ጥፉ’ እንደተባሉ በተለየዩ ጊዜያቶች በዝርዝር መጻፌ ይታወሳል።
ይህ አቤቱታ ዛሬም እያነከሰ በማዝገም ላይ ካለው ታሪክ አብሮ እያዘገመ ነው። ይህ ጉድ የያዙት የወያኔ ወንጀለኞች ቤተሰቦቻችን ሰውራችሁ አጥፍታችሁ የት እንዳደረሳችቸው፤ምንስ ስለበደሉ ፤ምን ዓይነት የፍርድ ሂደት እና ፍረድ ሰጪዎቹ እነ ማን እንደነበሩ እንዲሁም የፍርዱ ማሕደር ቅጂ ይሰጠን ብሎ ለሚጠይቃቸው ለአቤት ባይ ሰለባ ጀሮ ዳባ በመስጠት በውስጥ ፍርሃት ተውጠው “መልስ ላለመስጠት ሲሸሹ እያየናቸው ነው”። የወያኔ መሪዎች ይህ አቤቱታ ሲቀርብላቸው ለምን መልስ መስጥ አቅቷቸው “ዝም” ማለቱን መረጡ? ማኦ ዜዱንግ አንዲህ አለ ስታሊን ወያኔነት/አብዮት ዋዛ የለም ብሏል፤ እያሉ በበረሃ ኮንፈረንሳቸው ፎቶግራፋቸውን ለጥፈው እንደ መላእክት ተመልክው እነሱን የተቃወመ ሰው እየተመነጠረ ደብዛው የጠፋው የትግራይ ገበሬ፤ታላለቅ ሰዎች፤አረጋውያን እና ወጣቶች ፤ ታጋይ ቄስ አና መኖክሴ ፤አልታገልም ያለች እና አልታጠቅም ያለ ወጣት እረኛ እና ዲያቆን እንደ ሰይጣን በውድቅት ሌሊት በተኙበት ቤት በር  እያንኳኳችሁ ካብ እና አጥር እየዘለላችሁ እንደ ደሮ እያፈናችሁ የት እንዳደረሳችሁት ልትነግሩን ትችላላችሁ? በእሳት እና በፈላ ውሃ አቃጥላችሁ በጥየት የገደላችቸው ቤተሰቦቻችንስ ይቅርታ ጠይቃችሁናል? ካልተየቃችሁንስ ለምን? እናንተን ተሸክሞ እያነከሰ በማዝገም ላይ ያለው ታሪክ  አንድ ቦታ ላይ ሲቆም ለዳግም የሕሊና ጸሎት ትጠይቁት ይሆን? ለመሆኑ ጓዶቻችሁ ለመዘከር የሕሊና ጸሎት ስታደርጉ እናንተ እና በግፍ የገደላችቸው  የቤተሰቦቻችን እና የጓደኞቻችን መንፈስ ብቅ እያለ ሕሊናችሁን ሲታገለው ምን እያለችሁ ትገላገሉታላችሁ? 
እንደ አውሬ ምድር ጆሮአችሁ የተደፈነ ነውና አምላክ በይቅር ባይነቱ እናንተም ይቀር ይበላችሁ፤ ሃያላን-ከሚያንቀጠቅጥ-ቁጣውና-አቱ-ይሰውራችሁ።ጌታቸው-ረዳ፤ www.ethiopiansemay.blogspot.com