Friday, October 21, 2022

መልስ ለዶ/ር አርአያ አምሳሉ የተሰጠ ከጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 10/21/22

 

 

መልስ ለዶ/ር አርአያ አምሳሉ የተሰጠ

 

ከጌታቸው ረዳ

 

Ethiopian Semay 10/21/22

የኔና  የዶ/ር አርአያ አምሳሉ ክርክር መነሻው በ ኦክተብር 17 በዚህ ወር ማለት ነው “ለገዳዩ የሚዘምር አሽቃባጭ የጎንደሬዎች መንጋ” A herd of scornful goons singing to the Oromuma fuhrer ብዬ በለጠፍኩት ትችት ተነስቶ ለምን “ጎንደሬዎችን ዘለፍክ በሚል ነው። ርዕሱ እንደምታዩት “መንጋ’’ ነው የሚለው።

ሆኖም ጎንደር ከተማ ተወለድኩኝ የሚለን ጎንደሬው የምህንድስና ዶ/ር የሆነው አርአያ አምሳሉ ጎንደሬዎችን ለመስደብ የጎጃም ሴቶች በአጼ ቴዎድሮሰ ጭካኔ የገጠሙትን ግጥም ለምን ጠቀስክ በማለት (ከጎንደሬዎችን ከስድብ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን ግጥም) በወዳጄ በአገር ወዳዱ በግርማ በቀለ ፌስቡክ ላይ አጉል የጎንደሬነት ጥብቅና ቆሚያለሁ ለማለት በሃሰት ሲለፋደድ  የጻፈውን አይቼው ገረመኝና መልስ ሰጥቼው ለጠየቅኩት መልስ ሊሰጥ አልቻለም። የጎጃም ሴቶች ለምን በቴድሮስ ላይ ግጥም ተነኙ የምል ቅሬታ ከላው በዘመኑ ለነበሩ ቅሬታ አቅራቢ የጎጃም ሴት ገጣሚዎችና የታሪክ ጸሐፍት እንጂ ከኔ ጋር መሆን የለበትም።

አርአያ አምሳሉ ዛሬ ተነስቶ አማራ የሚባል የለም ሲለን የነበረው ሰውየ ያለ እኔ ጎንደሬ የለም ‘ስለ ጎነደሬዎች ምንም አትበሉ፤ አያገባችሁም፤ስለ ጎንደሬዎች ለኛ ለጎንደሬዎች ተወው” እየለኝ ያለው  ስለዚህ ተመጻዳቂ ሰውየ አስምልከቶ እንወያያለን።

ለወጡ ሊመጣ አንድ ሳምንት ሲቀረው “የጎንድር ወጣት የጸረ አማራው የአንዳርጋቸው ጽጌ እና የበቀለ ገርባ ፎቶ ለጥፎ በመሺዎች ጎንደር አደባባይ ወጥቶ አለም ቀውጢ ሆና ሲጮሁ፤ እኔ ደግም ምነው ጎንደሬዎች “ጀግና አጥታችሁ ነው ወይ እነዚህ ጸረ አማራ የሆኑ በትውልዳቸውም አሮሞዎች የሆኑትን እነዚህ ሁለት ሰዎች እንደ ጀግኖቻችሁ ቆጥራችሁ ፎቶግራፎቻቸውን ይዛችሁ ስታሞግሱዋቸውና የምትጮሁት ‘ለምን የፕሮፌሰር አስራት ወ/የስን አንድ ፎቶግራፋቸውን ለምን አጣችሁ!? አየ ጎንደሬዎች! ምነው ሰዳቢዎቻችሁን ጀግኖቻችሁ አደረጋችኋቸው?” ብየ ስለጻፍኩ ጎንደሬዎች እንደ ወፍ “ተንጫጭቡኝ” እኔም ታዝቤአቸው ስቄ አልፍኩዋቸው።

 ዛሬ ደግሞ ጎንደሬው አርአያ አምሳሉ ስለጎንደር አያጋባህም፤ “ሊቭ ዘ ጎንደር ኣሎን” አለኝ። ሕዝብ ሲዘላብድ ዝም በሉ  አትንኩ የሚሉን ኢትዮጵያዊያን ደናቁርት የአገሪቷን ችግር እያባባሱባት ነው። ለዚህ ነው “የትግሬ ሕዝብና ወያኔ ኦነግና የኦሮሞ ሕዝብ ለየብቻ ናቸው” እያሉ የሚዘላብዱ ሚዲያዎችና ዶከተር ተብየዎች ችግሩ ያባባሱት። ያ አልበቃ ብሎአቸው “እስላማዊው ውሃቢያ ቀስቃሾችን” አንደ ጀግኖች እየቆጠሩ እኔም “አሕደመዲን ጀበል፤ እኔም አቡበከር እያሉ እየጮጁ እኛ ጋር ሲገጥሙ ነበር። (እንግሊዝ አገር የሚኖር አንድ የትግራይ ተወላጅ ወዳጄ (ምንም እንኳ እርሱም ምሁር ቢሆንም” ዶክተሮችን <<ብቸግረዎች>> ይላቸዋል፤ በስልክ ስናወራ ዶክተሮች ብሎ አያውቅም ፤ <<“ብቸግሮች”>> እያለ ይጠራቸዋል። በንግግሩ ሁሌም እስቃለሁ።)

ለመሆኑ አርአያ አምሳሉ ማን ነው? የሚለው ለመመለስ የዶክተርነት ማዕረግ ይዘናል ብለው ተማርን ከሚሉ ኢትዮጵያን ውዥምብር ውስጥ እንድትዳከር አስተዋጽኦ ካደረጉት ቡድኖች አንዱ ነው። ይህ ሰው በብዙሃን የፌስቡክ ማሕበረሰብ ጋር አይታወቅም። ግን ኢሳት የተባለው የኢሳያስ አፈወርቂ፤ እና የጸረ አማራዎቹ የአንዳርጋቸው ጽጌ እና የብርሃኑ ነጋ ኢሳት የቦርድ አባል የነበረ የኢሳት ዋና የፖለቲካ አለቅላቂ የነበረ ሰው ነው። ኢሳት ደግሞ በጸረ አማራነቱ የታወቀው የዛሬ የአብይ አሕመድ ዋና አሽክር የብርሃኑ ነጋ ንብረት ነው።

እንደምታስታውሱት እኔና የኢሳት ሰዎች ምን ያህል ትግል እንዳደረግን የሚታወስ ነው። ትግላችን ሁሉ በድረገጾች አሁንም አሉ። የውጭ አገር ውዥምብራም ማሕበረሰብ በግንቦት 7 አብዶ ሲደልቅ እኛ ጥቂቶች ለግንቦት 7/ኢሳት ሲያሳዩት እና ሲለግሱት የነበረው መዋጮና ጩኸታቸው ትክክል እንዳልሆነ እልህ አስጨራሽ የሆነ ትግል አድርገን በመጨረሻ እኛ ስናቀርበው የነበረው የትግል እውነታ እውን ሆነ ዛሬ ፍርስርሳቸው ወጥቶ መጨረሻ ብዙዎቹ የአብይ አሕመድ አገልጋዮች ሆነው ትግላችን ተጠናቀቀ (ትግላችን ገና ቢሆንም)።

አርአያ አምሳሉ የዚህ ውዠምብራም ቡድን አንዱ የነበረ ነው። በተጨማሪ ዶ/ር አርአያ አምሳሉ ከኢሳት ሌላ Ethiopian Advocacy Network በሚባለው ድርጅት መሪ አባል ሆኖ ወያኔዎች ላይ ማዕቀብ እንዲደረግ ከሚታገሉ አንዱ የነበረ አብይ አሕመድ ከመጣ በሗላ ግን “በ ኦሮሙማው መሪ  ላይ አሜሪካኖች ማዕቀብ” እንዲያደርጉ ሲታገል አላየነውም። ይባስ ብሎ እንጭጭ የፖለተካ ብስለቱ አልለቅ ብሎት “አብይ አሕመድ ሳይሆን፤ ከስሩ ያሉት መዋቅሮችና አማካሪዎች እንዲሁም ክልሎች በቂ ሙያተኛና ቅን ሰው ስለሌሉት ነው ችግር እየተፈጠረ ያለው”” የሚል ደደብ ሃሳብ በማቅረብ እናውቀዋለን። ደደብ ሃሰቡ በመቀጠል፤ እነ አምባቸው እና እነ አንዳርጋቸው ከተወገዱ ወዲህ በምትካቸው የተተኩ የክልል ሹመኞች ክልልሉን አረጋግተውታል እየለ የሚቃዥ ዶክተር ነው።

አርአያ አምሳሉ በሙያው “መሃንዲስ” እንጂ የፖለቲካ ልምድም የፖለቲካ እውቀትም የለውም። ባለመብሰሉም ብዙ ሲዘባርቅ ከ90ዎቹ ጀምሮ በዝግ የድረገጽ ውይይቶች አውቀዋለሁ። ዞሮ ፤ ዞሮ ጎንደር የተወለድኩኝ ነኝ፤ ስለጎንደር ለኛ ተወው “ጎንደር ለጎንደሬዎች” የሚለን ሰውዬ በብሔረሰቡ ማንነት አማራ ይሁን ቅማንት አለውቅም። ግን “አማራ የሚባል ብሔረሰብ/ ነገድ/ “ኤትኒክ” የለም”  ከሚሉት የእነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ቡድን ነው።

 ብለሃል ተብሎ ማስረጃ የሚቀርብብትን ማስረጃ የሚቀርብ ሆኖ ካየው በድፍኑ “አሉባልታ ነው” እያለ ከመካድ ውጭ አላልኩም ብሎ አይከራከርም። እነዚህ ናቸው 30 አመት ትግል አማራ የለም እያሉ ከጸረ አማራ ቡድኖች ከነ አንዳርጋቸው እና ብርሃኑ ነጋ ጋር ሆነው ትግሉን ሲያኮላሹት የነበሩት። <<የአንድነት ሃይሉ ኢትዮጵያ የሚል ስም ሲያነሳ ያንገሸግሸኛል (እንደ ኮሶ እንደ እሬት ይመረኛል)>>፡ እያለ በይፋ ሲናገር የነበረው በትውልዱ ግማሽ ኤርትራዊ ግማሽ ኦሮሞ ነው እየተባለ የሚነገርለት የሻዕቢያው ደጋፊ የግንቦት 7 ዋናው ሰው ንአምን ዘለቀን <<ጀግናየ ነው>> እያለ የሚዘባርቅ ሰው ነው።

አማራ ያልደረሰበት ጉድ የለም። ተማርን የሚሉት <ብቸግሮች>> ቀንደኛ የችግር መንስኤዎች መሆናቸው ከገባኝ በጣም በርካታ አመታት ነው። ለዚህ ነው በጣም እጅግ የምንቃቸው። ይህ ሰው የጎንደር ሕዝብ ሰድበሃል ሲለኝ፤ ጎንደሬዎች የሚወቀሱበት ነገር ካለ ይጠየቃሉ፤ ይወቀሳሉ ሕዝብ ማለት የግለሰብ ስብስብ እንጂ “የጻድቃን ስብስብ” ማለት አይደለም። የኔ ነገድ የሁኑት ትግሬዎች ደግሞ ስለ ትግሬዎች ስተች  የአርአያ አምሳሉ  አይነት ልቅሶ ያለቃቅሱብኛል። ለመሆኑ ጎንደሬዎች ማን ነው ከወቀሳ ነፃ ያደረጋቸው? የፋኖው መሪ ነኝ የሚለው “አርበኛ መሳፍንት” የተባለው ሽማግሌ ሰውየ <<< “ትግሬዎች ከመንደራችን ከጎጃም ፤ከጎንደር፤ ከመላው ኢትዮጵያ ከያሉብት ቦታ ሁሉ እተለቀሙ ይውጡልን እዛያ ካገራቸው ሆነው ይግጠሙን፡ ትግሬ ለኛ ምንማችን አይደለም!!”>>>  እያለ ባደባባይ አዳራሽ ሲናገር ጎነንደሬዎቹ ወጣቶች “ደስ ብሏቸው” “ይደግም! ይደግም! እያለ አልነበረም ወይ “የትግሬዎች ይባረሩ” መፍክር ወድዶት ዕልል እያለ ሲያጨበጭብና ይደገም ሲል የነበረው!? ማን ምንን ነው ለማሞኘት የሚንደፋደፈው? ሕዝብ ከጸረ ሕዝብ ጋር ከተሞደሞደ ወይንም ዘረኛነት ድምፅ ካስሰማ “በደምብ ይሰደባል፤ ይወቀሳል፤ ይከሰሳል”። ሕዝብ አይከሰስ፤ አይወቀስ፤ አይሰደብ የሚለው “ፖለቲካል ኮሬከትነስ” እኔ ጋር አይሰራም። ይህንን የምትከታተሉኝ የምታውቁኝ ይመስለኛል። ትግሬዎችን ስወቅስ ልታጨበጭቡ ትግሬውን የሚዘለፍ ሲገኝ ደግሞ ለምን ወቀስከው ብላችሁ አረፋ ልትደፍቁብኝ አልፈቅድም። በዚህ የምታውቁኝ ታውቁኛላችሁ። የምናወራው ስለ አገር ነው!!

እስኪ የ ዶ/ር አምሳሉ “አማራ ነገድ/ብሔረሰብ//Ethnic/ የሚባል የለም የሚሉት የቡድን መሪ የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በወቅቱ እኔ እና ወዳጄ ክቡር አቶ ተክሌ የሻው የሰጠናቸው መልስ ለትውስታ ላስነብባችሁ፦

ለፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም፦

«ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ ምርጫ» በሚል ርዕስ

2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120 ላይ እንዲህ ብለዋል።

«ኅዳር 1951 ዓም ከአጼ ኃይለሥላሴ ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ

ባለሥልጣኖች ባሰራጨሁት የጥናት ጽሑፍ ስለኦጋዴን

የሚከተለውን ብየ ነበር። «በጠቅላላው የአማሮቹና የሱማሌዎቹን

ግንኙነት ላስተዋለው፣ አማራዎቹ የሚያሳዩት የበላይነት መንፈስና

በሱማሌዎቹ ላይ ያላቸው ንቀት፤ ሱማሌዎቹ በበኩላቸው ያላቸው

ኩራት በአማራዎቹ ንቀት እየተነካባቸው የሚሰማቸው ስሜት

በአንዴ ይታወቃል። ``ቆሻሻ ሱማሌ``በያለበት የሚሰማ ነው።

በዕድሜም ሆነ በክብር ከፍ ያሉትን ሱማሌዎች እርሰዎ እያለ

የሚያነጋግራቸው በቁጥር ነው።---እንደዚህ ዓይነቱ የሌለውን

የአማራ የበላይነትና የሱማሌ የበታችነት በግልጽም በድብቅም

የሚያሳይ መንፈስ የሱማሌዎቹን ልብ በጣም እንደሚያሞክረው

የሚያጠራጥር አይደለም። ሱማሌዎቹ ልክ እንደአማራዎቹ

መሆናቸውን ሁሉ የተገነዘቡት አይመስሉም፤ ሱማሌዎቹም ሁሉ

የሚውቁት አይደለም።»

………………………………………………”

( መስፍን /ማርያም «ሥልጣን፣ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካዊ

ምርጫ» በሚል ርዕስ 2003 ባሳተሙት መጽሐፈዎ ገጽ 120)

ያኔ አማራ እያሉ የጠሩት ነገድ ከነበረ፤  ዛሬ አማራ የሚባል ነገድ የለም የሚሉት ምክንያትዎ ምንድ ነው? ያኔ ኖሮ ኖሮ ዛሬ የት ተሰወረ? ምክንያትዎ ሊነግሩኝ ይችላሉ? ያኔ እርስዎ የዘሩት የማናከስ ስራ ዛሬ አማራ ከሶማሌ ሲባረር ምክንያት አልሆኑም ብለው ይገምታሉ?

ከአክብሮት ጋር!!!

መንግሥቱ ሃይለማርያም “አንዲህ ያለ ችግር ነው የገጠመን ጓዶች” ያሉትን ንግግር እዚህ መጥበስ ተገቢ ይመስለኛል።

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay