Sunday, June 3, 2018

ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካና ጨፋሪዎች በኢትዮጵያን ሰማይ እይታ ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካና ጨፋሪዎች በኢትዮጵያን ሰማይ እይታ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)

ኢትዮጵያውያን ለትጥቅ ትግል ጫካ ከገቡ ከነብርም ቢሆን ባዶ እጅ ትግል መግጠም የሚችሉ ደፋሮች ናቸው።ከተማ ውስጥ ግን ተራ ሰለማዊ ሰልፍ አድርጎ የታጠቀን መንግሥት ለመጋፈጥ በአፍሪካ ምድር የመጨረሻ ቦቅቧቃ ፍጡር እንደ ኢትዮጵያዊ ኣይገኝም (ይህ ግን ከ1991 ዓ.ም ወዲህ ማለት ነው)። ለ27 አመት አንገቱን አቀርቅሮ እንደባርያ ሲታሰር ሲፈታ፤መሪዎች ሲታሰሩ ሲገደሉ፤ የአማራ ሕዝብ በሺዎች/በሚሊዮኖች ከገጠራቸው ሲባረሩ፤ ሲዋከቡ፤ እየታረዱ ወደ ገደል ሲጣሉ፤ ጉበታቸው ኩላሊታቸው በጉሙዝ ሰዎች ሲበላ፤ አማራ ህጻናት ሲገደሉ…ደፍሮ ቀና ብሎ የትግሬዎችን መንግሥት መዳፈር አልቻለም።

ባጭሩ የኔን ልፋት ኣይቶ እኔም ሁሉንም በየመልኩ እየታገልኩና እየተበሳጨሁ መምጣቴን ኣይቶ አንድ የቅርብ ወዳጄ በኢመይል እንደጻፈልኝ “ይህ ትውልድ የወላጆቹና የድሮ ቅድመ ኣያቶቹ DNA ከውስጡ አለ ብልህ ለማስተማር ከጣርክ ድካምህ ከንቱ ነው፡ ጤንንትህም ላይ ቀውስ ያመጣብሃል። አገሪቱ ትኖራለች ትውልዱ ግን የተለወጠ ‘እርኩስ፤ለብቻየ የሚል ግለኛ፤ ስሜተኛ፤ ወላጆቹን የሚዳፈር ብሎም የሚገድል፤ አጭበርባሪ፤ ባሕል አልባ የሆነ ባለ አዲስ DNA በምድሪቱ ላይ መኖሩ ኣይቀሬ ነው”። ብሎ የጻፈልኝን ልክ ነበር። ይህ ትውልድና አንዳንድ ከቀድሞ ትውልድ የቀሩ የዚያኛው ትውልድ ዕድሜ ያላቸው ሰዎች የተቀላቀለበት ማሕበረስብ በስሜት የሚኖግድና በጥቂቱም የሚረካ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የወቅቱ ፖለቲካ ሲገመገም መለስተኛ ለውጥ ቢታይም የለየት የጦዘ ስካር ውስጥ መግባቱ የሚያሳየን ነገር ተሸንፎ ስለነበር ነው። ከገዢው ስርዓት ውስጥ የወጣ ሰው ለውጥ ማምጣት እንደሚችልና ያም አገራዊ የሆነ መፈንቅለ መንግሥት ያደረገ ወታደራዊ ቡድን መውጣቱ አይቀሬ ነው” ብየ ባለፈው ብዙ አመታት መጻፌና  በቅርቡም አብይና ለማ  ወደ መድረኩ ብቅ ብቅ ሲሉ የኢትዮፓትርዮቲክ (ኢትዮጵያ ራዲዮ ስቶክሆልም ስዊድን) ባደረግኩት ቃለ መጠይቅ ላይ መሪ ከየት ይመጣል ታዲያ ብለው ለጠየቁኝ፦ “ተቃዋሚው በራሱ ጉልበትና ጥበብ ለውጥ ማምጣት አይችልም፡ የተሸነፈ ተቃዋሚ ነው። ኢትዮጵያ ተአምረኛ አገር ነች፡ መለስን በታምራትዋ እንደወሰደችው ታምረኛ መሪ ካንድ ቦታ ታፈልቅ ይሆናል” ብየ ነበር። ሆነ። ትንቢትየ ትክክለኛ ግቡ መምቱ ቃለ መጠይቅ ያደረጉልኝ ሰዎች ይመሰክሩልኛል ብየ እገምታለሁ ። አብይ ወታደር ነው የውስጥ ሰው ነው። ፈለቀ። ከተነበይኩት ትንቢት ልዩነቱ በጠመንጃ ጉልበት ወደ ስልጣን ያለመምጣቱ ላይ ልዩነት አለው እንጂ ከውስጥ እና ከወታደሩ እንደሆነ ግን ትክክል ነበርኩ።

 ከፋሲካ በፊት ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት የመሰከረ በፈጣሪ የሚያምን ስለ አንድነት የሰበከ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰማየ ሰማይ የተላከልን የፋሲካ የስጦታ ጥዑም ሽቶ/ ን’ግግር” ብየ አመስግኜዋለሁ። እኔን የምትከታሉ የምትመሰክሩት ነው።

ችግሩ የመጣው ባሕር ዳር ተገኝቶ ያደረገው ንግግር እኔና አብይ መለያየት ጀምርን (ሁላችሁንም የምታውቁት ስለ ባሕርዳር ስብሰባው የጻፍኩት ጽሑፍ ታስታውሳላችሁ)። ከዚያም አማራ በቀጣይነትና በባሰ መልኩ ህጻናትን አዛውንትን በቀስትና በቢላዋ ማረድ ተጀመረ። አስቁመው ብለነው አላስቆመውም። ቤንሻንጉል ውስጥ ለስብሰባ ተገኘ። ጥዑም ንግግር አደረገ። አፈናቃዮች በደብዳቤ የሚያፈናቅሉ የወረዳ ባለስልጣኖች አንዳሉ አመነ። ግን ምን አደረገ? ምንም ! የታሰረ ሰው አልሰማሁም፤ አላነበብኩም። ችግሩ መፈናቀሉ አሁንም ህያው ሆኖ ቀጥሏል። ከአብይ ጋር ልዩነቴ ይህ ነው።ይግረምህ በሎ ወዳጄ ይህንን ለአብይ ተገጠመለት ብሎ የላከልኝን ላስነብባችሁ፡

ጠጅ መስሎን ነበር ምርጊቱ ሲከፈት
ጠላ ነው መልሱት ወደ ነበረበት!


በየፓልቶኩ የታጨቁ አብይ አብይ የሚሉ ከነፈሰው ጋር የሚነፍሱ ነፋሶች ጉዳይ!

አብይ ደላላ አያስፈልገውም። እራሱ በየፓልቶኩና በየዩቱቡ ከምንሰማቸው አብይ አብይ የሚሉ በአብይ ትኩስ ፍቅር የከነፉ አብይን ለመሸጥ እየደከሙ ያሉ፤ አብይ በበለጠ እራሱን መሸጥ እንደሚችል አሳይቷል። ሰውየው የተካነ ፤ ራሱን ለንግሥና አዘጋጅቶ መንገዱን ሲጠርግ የነበረ ፤ እመኑኝ ግሳለሁ ሲላቸው ሰዎች እያፌዘ እየመሰላቸው ያላመኑት እጅግ የተካነው ኢትዮጵያዊው ጎርቫቾቭ (በኢሕአፓ ዲሞክራሲው አመራሩ በሰለሞን አባባል። ጥሩ ጽሑፍ አለው ኢትዮ-ፓኖራማ ላይ የለጠፈው አንብቡት-ግሩም ትንተና) ነው። ራሱን መሸጥ የሚችለውን ሰውየ ከሚገባው በላይ እጅ እጅ እስኪለን ድረስ የሚያግቱን “አሻሻጮች” እያስጠሉኝ መጥተዋል።

በወያኔ እና አብይ የሥልጣን ሽኩቻ አለ። ስዘረዝረው በቃለመጠይቄ እንደተናገርኩት “በሕአዴጉ ውስጥ በትግሬውና በኦሮሞው/ አማራው ?)) መካካል የሥልጣን ፉክክር አለ። ያ ደግሞ አልጠራም። ወደ ብረት እንደሚዘልቅም ተናግሬአለሁ። እሱም የሚሆነው “ሪል ዲል” ብየ በምጠራው እርምጃ ሲደረስ የሚከሰት ነው። ልታምኑም ላታምኑም የራሳችሁ ጉዳይ ነው። አብይ ኦሮሞ ወታደርና ሕዝብ አምኗል። ወያኔ ደግሞ ገንዘብ፤ መሳሪያ እና የተካነ የትግሬ ተዋጊ ጉሬላ ወታደርና ትግሬ ሕዝብ አምኗል። ጉዱ ገና ነው። “አይበልናን ዶ” የለመደው ጉሬላ “ኤፌርት” እና የአገሪቱን ገንዘብ የዘረፉትን ማሰር ከጀመረ አብይ አለቀለት ማለት ነው። ግን ትላልቆቹን አይነካም። ፡”ሪል ዲል Real Deal” የምላችሁ ይኼ ነው። ትላልቆቹን ወንጀለኞች ከነካካ የሚከተለው ስለሚያውቅ አይነካቸውም። አንደኛ ጛዶቹ ናቸው።ምን ተባብለን ነበር እየተባባሉ በጎሪጥ እየተያዩ መቀጠል ካልሆነ “ሪል ዲል” ላይ ሕዝብን ያላስረከበ ድል ሊቀጥል ይችላል።

ሁለተኛ ሴናሪዮ፦ ለውጥ የሚፈልግ ትግሬ እየጨመረ መምጣቱ “ገዛ ተጋሩ በሚባል የወያኔ ካድሬዎችና ጀሌዎች ቤት ውስጥ ከማደምጠው ‘ድምፅ” ማረጋገጥ ችያለሁ። የዌብሳይት ካድሬዎቻቸውም ጭምር ለውጥ አስፈላጊነቱን እንደተቀበሉ አድምጫለሁ። አለቆቻቸው እንዲለወጡ ቢፈልጉም የወያኔ ትግል ከንቱ ማርከስ፤ መሪዎችን ማንኳሰስ ማሰር ግን አይፈቅዱም። አብይ ይህንን ደፍሮ መስራት አይችልም። የወያኔ አንዳንድ ትልልቅ ሰዎች እና አሮሞዎችን ያስከበረ ድል ግን ኣይቀሬ ነው። ያ ከሆነ የሚፈለገው ማለቴ ነው። ኦሮሞዎች በምንም መልኩ አብይ ይሁን ሌላ ኦሮሚያ የተባለ የኦነግ ፈጠራው ¾ ኦሮሚያ መሬት ጉዳይ ለውጥ ማምጣት የሚፈልግ ሃይል እንደማይፈቅዱ አርግጠኛ ሆኜ እሞግታለሁ። ያ ነው “ሪል ዲል” ላይ ሲደረስ ሁለቱም (ወያኔና ኦሮሞዎቹ) የየራሳቸው “ሪል ዲል” የሚሉት ማስነካት ስለማይፈልጉ “አብይ አብይ” የሚሉት አሻሻጮች መጨረሻ ላይ እንደማይደሰቱ ትንብቴን አስቀምጣለሁ። ከተሳስትኩም መልካም። አንድ ትንቢት ግን እውነታው አስመስክሬአለሁ። አብይ (ከውስጥ ሰው እንደሚመጣ) ትንቢት ሰጥቼ ነበር በቃለ መጠይቄ ሆኗል።  ሕዝብ ስለደገፈው ማለት ግን “ሪል ዲሉን” ያስነካል ማለት አይደለም። አደራ የምላችሁ ግን ‘ደግፉ! እልል በሉ! ፍረጡ ውረዱ! ከወያኔ ጋር ካርዱ እየቀደደ ነው!” እያላችሁ “እጅ እጅ” እስኪለን ድረስ የተጋነነ ጡሩምባ ባትቦቶልኩን ይመረጣል። የኛ የመስጋት የመውቀስ ምብትም ጠብቁልን።     

አሁን ወደ ወጣቶቹ ልውሰዳችሁ፡
መሪዎች ሲታሰሩ ያልጠየቃቸው እና ሰላማዊ ሰልፍ ያላደረገላቸው፤ በተከታታይ ከፖሊስ ጋር ያልተጋፈጠ መሪዎች እና እስረኞች ሲፈቱ ግን “በሆሆታና በጭፈራ ከተሞች ወደ እያሪኮ” የሚለውጥ ትውልድ ሆኖ ማየት ያስገርማል። በቅርቡ እስረኞች ከእስር ሲፈቱ የታየው ሆሆታውን አይቶ የተገረመ አንድ ገጣሚ ስንኝ ተሰኘ ብሎ ወዳጄ የላከልኝን እንዲህ ይላል፡

ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
ሲታሰር ለሽ ብለሽ ሲፈታ ሆይ ሆይ!

የሚል ስንኝ የተቃኘው ገጣሚ እውነት የልቤን ነው የዳሰሰው። አንዳርጋቸው ይህንን አልጠበቅኩም ያለውም ለዚህ ነው። ሌሎች ታሳሪዎችም እንደዚህ ነበር ያሉት። በጣም ያስገረመኝ ደግሞ ነብሱ ይማረው የሟቹ ‘የጌታ መሳይ አበበን “ሆ ብየ እመጣለሁ ሆ ብየ በድል ጥንትም ያባቴ ነው ጠላትን መግደል” የሚለውን’ ሙዚቃ እየጨፈረ ሲቀበላቸው ከመገረምም አስገራሚ ትውልድ ነው። ሲታሰር አናሳስርም ብሎ አምቢ ብሎ የታገለለት ይመስል፦ ተማርኮ ታስሮ ሲዋረድ የነበረን እስረኛ ሲፈታ “ሆ ብየ እመጣለሁ ሆ ብየ በድል ጥንትም ያባቴ ነው ጠላትን መግደል እያለ በየትኛው ጦር ሜዳ ቆይቶ ጠላት ገድሎ እንደመጣ ቢጠየቁ ምን እንደሚመልሱ ሲገርምኝ ይህ ስመዝነው ከአስገራሚም አስገራሚ የሆነ ፈረንጆች “ስትረንጅ” የሚሉት ዓይነት  ጨፋሪ ውልድ ነው በ27 አመት ውስጥ ያየነው ወጣት ትውልድ።

ይህ ብቻ እንዳይመስላችሁ፤-አንድ አስገራሚ ጸሃፊ አንዳርጋቸውን “የኢትዮጵያ ማንዴላ” ሲል የማንዴላ ማዕረግ ሸልሞታል። ይኼ ደግሞ ከሚገርሙ ጫፈሪዎችም አስገራሚ ነው። የደቡብ አፍሪካው አውነተኛው ማንዴላ ከእስር ሆኖ ትግሉን ሲያንቀሳቅስ የነበረ ነው። ከእስር እንፍታህ ሲባል የነጭ ስርዓት ካላበቃ አልፈታም ብሎ እምቢ ብሎ ነጮችን አስጨንቆ ወደ ጠረፔዛ ትግል አስገድዶ በዓለም ውስጥ ያልታየ አስገራሚ የትግል ስልት ልዩ ታሪክ የሰራ ልዩ ሰው ‘ማንዴላ’ እና የዚህ ግለሰብ ማንዴላው አንዳርጋቸው ጽጌ ሲያዝ ባንድ ጸሐፊ አገላለጽ “አንዳንዶቹን  ዓረፍተነገሮች ለክብር ሲባል ዘልያቸው እንዲህ ይላል፤-

አንዳርጋቸው ፅጌና ጉራው
 በሚል ርዕስ

አንዳርጋቸው ልክ እንደተከታዮቹ ጉራው አይጣል ነው። "የመለስ አጥንት በየአደባባዩ እጎትተዋለሁ" ብሎ እንዳልፎከረ ድንገት ሲማርኩት እንደ ተምርፕሮ ፊቱ ሁሉ ተለዋውጦ እንደ ህፃን ልጅ….. እውነት ለመናገር ያን ያህል ጉራ ነፍቶ ሲማረክ …. በተሌቭዥን አብዝቶ የቀባጠረውም ከዚሁ የተነሳ ነው። አሁን ኢህአዴግ በምሕረት ሲለቀው የተለመደ ጉራውም ለቀቀው። እንዴ፣ ጀግና ነህ ሲሉት ምን ያድርግ? እንኳንስ ጀግና የሚለው አግኝቶ ድሮውም ጉራው አይጣል ነው።የሚገርመው ሰውየው እንደ ነፃ አውጪ ተቆጥሮ የጀግና አቀባበል ሲደረግለት ነው። ጫካ የገባሁሉ ጀግና ነው ከተባለ የህወሓት ታጋዮች 17 ዓመታት በጫካ ውስጥ እየኖሩ ታግሏል። ግባቸምው ደርግን በመደምስስ አሳክቷል። አንዳርጋቸው ምን አሳካ? ምንም! የተለየ ትኩረት የተሰጠው የእንግሊዝ ዜጋ ስለሆነ ነው? የውጭ ዜጋ ነው ሲባል ጭራውን የሚቆላ ሰው ብዛቱ አይጣል ነው። 

ከሻዕቢያ ጋራ በማበር ኢትዮጵያን ወግቷል እያላችሁ ህወሓትን ስታብጠለጥሉ እንዳልነበር አንዳርጋቸው ከሻዕቢያ ጋራ በማበር ኢትዮጵያን ስለ ወጋ እንደ ጣኦት ታመልኩት ጀመር። ህወሓቶችን ስልጣን በሐይል ተቆጣጥሯል እያላችሁ እንዳላብጠለጠላችዋቸው የህወሓት መንገድ ተከትሎ ስልጣን ለመቀማት ኤርትራ የገባው አንዳርጋቸውን ስታጀግኑት ትንሽ አይሸክካችሁም? ስላልተሳካለት እንጂ ሃገሪቱን ለእርሰበርስ ጦርነት ለመዳረግ እኮ ነው ብረት አንግቦ ኤርትራ ውስጥ የመሸገው። አንዳርጋቸው ነውጠኛ ለመሆን ሞክሮ አልተሳካለትም።ሰላማዊ ታጋይ ሆኖም አልተሳካለትም ብረት አንግቦም አልተሳካለትም። ሀገሪቱን ወደ ፊት ለማራመድ ሲባል ምህረት የተቸረው ምስኪን እኮ ነው።

እናስ እንደ በላይ ዘለቀ ስቀሉኝ ብያቸው ነበር የሚሉት ጉራ ምን አመጣው? ጀግና ከሆነ እንደ እጼ ቴድሮስ ራሱን አያጠፋም ነበር? እነ ቴዲ አፍሮም "ተዋከበና ግራና ቀኝ ቢል ሰው የለምና" ብለው ይዘፍኑለት ነበር። 😉

አንዳርጋቸው ህወሓት የፈፀማቸው ስህተቶች ሁሉ ፈፅሟል። እንደ ህወሓት ስልጣን መንጠቅ አልቻለም እንጂ። ህወሓትን የሚቃወም አንዳርጋቸውና መሰሎቹንም መቃወም ነበረበት። መመዘኛው " ማን ምን አጠፋ የሚል ሳይሆን ያጠፋው ማናው?" የሚለ ሆነና እነ አንዳርጋቸው ጀግና ተባሉ።“

 ይላል አንድ ጸሐፊ ጻፈው ተብሎ ወዳጄ ከላከልኝ የገኘሁት ጽሑፍ። እነ አንዳርጋቸው ከነ ማንዴላ የሚያወዳድሩ ሰዎች ሳይቀውሱ የቀወሱ ጸሀፊዎች ናቸው።

ስለ ሃይለ ገብረስላሴ ሶሺያል ሚዲያ ሊያባለን ነው ስላለው ድጋፍ።
አዎ ሃይሌ ትክክል ብሏል። ሶሺያል ሚዲያው በትክክል ካልተያዘ ወደ አራዊት ጫካነት ከተለወጠ ቆይቷል። ጤነኞች የሚመስሉ ነገር ግን በእርግጠኛነት ብዙ የቀወሱ ፤ እንዳውም ኣእምሮ ሆስፒታል ውስጥ መታከም የሚገባቸው በጣም በርካታ ለመቁጠር የሚያዳግቱ በሕሊና ቀውስ የሚሰቃዩ ሚዲያውን በነፃ ስላገኙት የሚናገሩት ንግግር እጅግ አስፈሪና ዘግናኝ ከመሆን አልፎ ሕዝብን የሚያባላ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሌት ተቀን እዛው ፌስ ቡክ/ዮቱብ ተጥደው ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ሲሰዳደቡ አንጀታቸው ተገታትሮ ዓይኖቻቸው ፈጥጦ አንዳንዶቹም እምባ እየቀረሩ እያለወሱ የሚያሳዩት የምናይባቸው ባሕሪ እጅግ አስፈሪ ነው። ሕዝብን በግልጽ ሲዘረጥጡ፤ አንጨርሰዋለን ሲሉ፤ አግልሉት፤ይህ ሕዝብ ያ ሕዝብ ወዲያ ይገንጠል፤ አንፈልገውም ሲሉ.. ለጦርነት፤ ለፍጅት፤ ለመጠፋፋት ሲጋብዙና ሕዘብን ሲቀሰቅሱ የሰማ ጀሮ እንዴት ሶሺያል ሚዲያ ሊያባለን ነው አይባልም? መባል አለበት እንጂ። ሃይሌን ከማንኛችሁም በላይ በመጽሐፌ ስለተለያዩ ሁኔታዎች እና ንግግሩን እየተቀስኩ በታሪክ እንዲወቀስ መዝግቤዋለሁ፤ ያውም ከነ ንግግሮቹና ፎቶግራፉ ጭምር። እዚህ ላይ ግን ትክክል ብሏል።

ሌላው አስገራሚ የዘረኞቹ ሙዚቃ ትንተና ነው።
አሞናል በለው (ትግሬን አግልለው) የሚባል አዲስ የዘረኞች ሙዚቃ ከትግራይ በመወለዳቸው ብቻ (በትግሬነታቸው) አጼ ዮሐንስን እና ወላጆቻችን ሲኮሩባቸው የነበሩት አፍሪካዊው ጀኔራል የተባለላቸው ራስ አሉላን ያገለለ አዲስ የዘረኞች ዘፈን ታትሞ (በሄኖክ አለማየሁ ደገፉ የዘ-ሓበሻ ድረገጽ ዋና አዘጋጅ ዳሬክተርነት የታተመ ሙዚቃ) ወጥቶ እስረኞች ሲፈቱ መጨፈሪያ ሆኗል:: መድህን ራዲዮ የተባለው (ከየት ሆኖ እና ማን ንደሚያካሂደው አላውቅም) እማ የፕሮገራሙ መከፍቻ ሙዚቃ ሳያደርገው አልቀረም “ዓርብ” ቀን አድምጠው ብሎ ወዳጄ ነግሮኝ እንዳደመጥኩት፤ ለረዢም ጊዜ ተዘፍቆበት ነበር።  እነዚህ መገናኛዎች እና የመሳሰሉ የፓልቶክ ጭንቅላተ ትንሽ ሰዎች የሚጨፍሩበት አዲሱ ጸረ አጼ ዮሓንስ እና ራስ አሉላ የጥላቻ ሙዚቃ መውጣቱ ደጋግግሜ ኢትዮጵያውያን አንዲያወግዙት ጠይቄአለሁ።እስካላወገዙት ድረስ ደጋግሜ በዚህ ጉዳይ ማንሳቴ ኣይቀርም።

የትግራይ ሕዝብና የትግራይ መሬት የኢትዮጵያ አካል ነው ብላችሁ በካርታችሁ ካስቀመጣችሁ ይህ የትግራይ ነገሥታት ያስጠበቁት ኢትዮጵያዊ ጥንታዊ መሬት ያስረከቡንን ነገሥታቶቻችን ትግሬዎች በመሆናቸው ብቻ ለብቻቸው ማዕቀብ የጣለና ያገለለ ዘረኛ ሙዚቃ ማውገዝ ይጠበቅባችል። ዮሃንስ አማራውን እስላሙን እንዲህ አደረገ እያሉ አንዳንዱ በውሸት አንዳንዱም ታሪክ የፈጸመው የዘመኑ ጭንቅላትና የሃይማኖት ፍጥጫን ያስከተለው ውጤትን በዛሬው ዓይን እያዩ የሚፈርዱ ግብዞች እና ጎሰኞችን ኬኒያ በስደት እየኖረ ከዚህ አለም ታህሳስ 2010 / በሞት የተለየ አውቁ ጋጠኛ፤ ኢብራሂም ሻፊ (ኢብሮ) በዚህ ጉዳይ አንስቶ እንዲህ ብሎ ነበር

ታሪክ ያለቀ ነው፤ የተፈፀመ። ስለዚህም ስህተት ከነበር ለይተን ልናርመው፤ በጎውን አውጥተን የበለጠ ልናጎለብተው እንጂ።ቴዎድሮስ ካሳሁን አፄዎቹን ያወድሳል። አፄዎቹ ደግሞ ሙስሊሙን ጨቁነዋልሙስሊም እንደ መሆንህ መጠን ልትቃወመው ይገባልየሚልምሁር መካሪንራሴው ዓቃቤ ህግ ሆኜ፣ ክስ መስርቼ፣ ጥፋተኛ አስብዬ፤ ራሴው ደግሞ ዳኛ ሆኜ እስር ቤት ብወረውረው ደስ ይለኛልምኞቴ ነው። ይሄንንምክርእንኳን ለዕድሜ አቻዎቼ ለመጠቆም አደባባይ ልወጣ አይደለም አብረውኝ ላደጉት በጣም ለምወዳቸው በዕድሜ እጅግ ታናናሾቼ ለእህቶቼ ልጆች ዘኪዬ እና ኢብሮዬ አይመጥንም። ሳት ብሎኝ ይኽን ስል ቢሰሙ እንኳን (ፍፁም አልልም እንጂ) በእነርሱ የግንዛቤ አቅም እንኳን እየነሆለልኩኝ መሆኔን ልብ ብለው የሚስቁብኝ ይመስለኛልአጎቴ ምን ነካው? ብለው ክትከትከትአምላክ ይዘንላቸው እና ጋሼ አሰፋ ጫቦ በአንድ ቃለ ምልልሳቸውስለ ኢትዮጵያ አንድ መጽሐፍ አንብበህ ከሆነሁለት አድርገውሁለት ከሆነ ሦስትሦስት ከሆነ አራት አድርገው። ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውጤት ነች። በጣም በርካታ መጽሐፍትም ስለ ኢትዮጵያ ተጽፏል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች እና ፍላጎት ጋርሲሉን ነበር። አዎን ኢትዮጵያ ብዙ ነች። ያለፍንበት ዘመንም ረጅም ነው። ያለፍንበት ዘመንን የሚገልፁልን ብዙ መጽሐፍትም አሉን። እነዚያን መጽሐፍት የምናነበው፣ የምንመረምረው እና የምናጠናው አሁን እኔ ቂም ወርሼ፣ ጥላቻን በልቤ አርግዤ፣ በቀልን በመሻት ከወንድሜ ጋር ልጋደልባቸው አይደለምዘኪዬ እና ኢብሮዬም ጊዜያቸው ሲደርስ ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲፋጁ አይደልምአንድ የሚያደርጉንን ነጥቦች ነቅሼ፣ የሚያስማማንን አበጥሬ እና በጋራ የሚያኮሩንን ለይቼ ብላቴናው የሚመኛትን በፍቅር የተሞላች ምርጥ ሀገር ለማየት እንጂ…!!! ለማንኛውም ወደ ፍቅር ጉዞ እያላችሁ ደግሞ ዛሬ………..!!!” በማለት ፅፏል፤ ኢብራሂም ሻፊ (ኢብሮ)።ብላቴናው የሚመኛትን ሀገርማለቱም ቴዲ አፍሮን ሲጠቅስ ነው።(ጻሐፊው ጋዜጠኛና ደራሲ መስፍን ማሞ ተሰማ)።
ስለ ህወሓትና አነግብጋቢው የወቅቱ ለውጥ ሁኔታና የማይቀረው የብረት ፍልሚያ ኣይቀሬ መሆኑን ሰነዱን እየሰራሁ ስለሆነ ጠብቁኝ።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)