ብዙ አካለ ስንኩል ወጣት የያዘቺው ትግራይና በባዶ ካዝና እየተራመደ ያለው አፓርታይዱ ኦሮሙማው መንግሥት
ጌታቸው ረዳ
(EEthiopian Semay
6/14/2023
ኢትዮጵያ እንደሃገር ሳይሆን የከሸፈች ሃገር (ፈይልድ ስቴት) ሆናለች። ከሆነችም ቆይታለች (በዚህ ርዕስ ብዙ፤ብዙ ብለናል)። በዚያ ምክንያትም ነበር የአማራው ወጣትና ምሁር ክፍል ሕዝባቸውና እራሳቸውን ከተነጣጠረባቸው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመከላከልና ብሎም ለማስቆም ራሳቸውን ቶሎ ነፃ ማውጣት አለባቸው ስንል የነበርነው።
በከፊል ‘ወድዶ ሳይሆን’ መሆን እንዳለበት የጠበቅነው ሕዝባዊ ማዕበል እንኳ ባይሆንም ተገድዶ የአልሞት ባይ ተጋዳይ በትንሹም ቢሆን የሽምቅ ውግያው “ሀ” ብሎ ጀምሮታል፡ እንዲበረታበትም እንመክራለን።
አገርን ማስተዳዳር ችሎታ የሌለው በባዶ ካዝና እየተንከላወሰ የዕርዳታ ስንዴ እየሸጠ በመተዳዳር ላይ ያለው ማፈሪያው አብይ አሕመድ ኢትዮጵያን በማፍረስ ሂደት የአምበሳው ድርሻ በመውሰድ ከወያኔ ትግሬዎች ጋር ወዳጀነት ግምባር ገጥመው አማራን ለማጥፋት በተናጠልና በጋራ ዛሬም ተቀናጅተው ቀጥለውበታል።
በዘርና አገር በማፍረስ ተጠያቂ የሆነው መለስ ዜናዊን የተካ ሚሳይል ወደ ተተኮሰባት ምድር ባሕርዳር እንዲጎበኝና ፡እንዲሁም የኦሮሙማ አህዮችን የሚሸከመው “ቂሉ ማሞን” የተካው ይልቃል የተባለው “ጌኞ” መቀሌን እንዲገበኝ በአለቃቸው አብይ አሕመድ ትዕዛዝ በታዘዙት መሰረት ሁለቱም ስለ ወልቃይትና ራያ ወደ ትግራይ የማዋሃድ ስምምነት አውን ለማድረግ በሁለት አቅጣጫ ጦርነት የመከፍት ጥናት ለመነጋጋር እንደሆነ ግልጽ ነው።
ስለ አብይ አሕመድ ሁላችሁም ስለምታውቁት ብዙ አልሄድበትም። ይልቅኑ ውስጥ ለውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ ትግርኛ ለማታደምጡ ወገኖች እንድታውቁ ባጭሩ ላብራራ፡
ትግሬዎች ለመገንጠል ሦስት ሂደቶችን እያሳኩ ነው።
1- ሊሂቃን ስለመገንጠል ተከታታይ ስብሰባ እያደረጉ ይገኛሉ
2- የወያኔ ጳጳሳትና ቀሳውስት ተዋህዶ ቤተክርሰትያንን በማፍረስ ከማኣከላዊው ሲኖዶስ በመነጠል
“የትግራይ ሪፑብሊክ ሃገረ ስብከት” በይፋዊ አዋጅ ተነጥለው መስረተዋል።አዲስ አባባ ውስጥ የተቀመጡት በጳጳስነት ወንበር የተሾሙት አባ ማትያስ በዚህ ሴራ ላይ በግላቸውም ሆነ በሲኖዶሱ በኩል ያሉት ነገር እንደሌለ ነው እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ የማውቀው።
3- ጌታቸው ረዳ፤ በሚመራው መንግሥት “ፈራ ተባ” እያለ ለትጥቅ ትግል በመጠባበቅ ላይ ያለው “ውስጥ ለውስጥ” በመደራጀት ላይ ላለው ለአንጃው የሽምቅ ፓርቲ የውስጥ እገዛ ለመስጠት ያለው ገጽታ ሦስቱን እንመለከታለን።
“Undoubtedly, war is the greatest source of the evils which
oppress civilized nations. Not so much actually war, but rather the
never-ceasing and indeed ever increasing preparation for a future war.” Page 66
(Kant on History) published by the Library of Liberal arts) ይላል ፈላስፋው “ካንት” ይህንን በራሴ ልተርጉመው፡ እንዲህ ይላል።
"ጦርነት የሰለጠኑ ሀገራትን የሚያወድም የክፋት ምንጭ መሆኑ አያጠያይቅም። ክፋቱ “ጦርነት” ሳይሆን የማያቋርጥ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ላለው የጦርነት ዝግጅት ይበልጥኑ አሳሳቢነቱ የላቀ ያደርገዋል።" ገጽ 66 (ካንት
“በታሪክ ላይ”) በሊበራል አርትስ ቤተ መጻሕፍት የታተመ ትንሽየ መጽሐፍ)
ጦርነት የክፋቶቹ ሁሉ የክፋት ምንጭ ነው ሲል አውዳሚነቱን እየገለጸ ነው። የወያኔ ትግሬዎች በከፈቱት ጦርነትና አብይ አህመድ በሴራ በተባባራቸው የጦርነት አውድ ላይ ባለፈው ሁለት አማታት ውስጥ በሚሊዮኖች ወጣት ትግሬዎችና ኢትዮጵያዊያን አካለስንኩል እና ሙት ወይንም መፈናቀልና የሕሊና በሽተኛ እንዲሆን አድርገዋል። ለዚያ ሁሉ ወንጀል ዛሬም ተጠያቂ የለም። ስለሆነም ዛሬም ሁለቱ በሴራ ተስማምተው ያልጨረሱትን አማራን የማጥፋት አጀንዳቸው ዛሬም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ናዚዎች በአውሮጳ አይሁዶች ላይ እንዳወጁት “የፋይናል ሶሊሽን” የዘር ማጥፋት ዘመቻቸው ጀምረውታል።
ብዙ አካለ ስንኩል ወጣት የያዘቺው ትግራይ ክፍለሃገር ወዴት እየተጓዘች ነው? የሚለውን ላወያያችሁ። ከላይ የጠቀስኳቸው ሦሰት ነጥቦች እንመልከት።
የጌታቸው ረዳና የይልቃል ወደ ባሕርዳርና መቀሌ የመጎብኘት ትዕይንትን በሚመለከት፡
ሚሳይል የተኮሰባት ባሕርዳርን እያስተዳደሩ ያሉት የኦሮሙማ እልፍ አስከልካይ “ብአዴኖች” ወልቃይትና ራያን ወደ ትግራይ ለማስረከብ በሁለቱ አቅጣጫ የሚካሄድ የጦርነት ሰልት ለመንደፍ እንደሆነ የውስጥ አዋቂ ምንጭ አያስፈልግም (ግልጽ ነው)።
ምክንያቱም እነ ጌታቸው ረዳ በጉጉት እየጠበቁት ያሉት ወልቃይት የውጭ አገር መውጫ በር ካገኙ ሳይውሉ ሳያድሩ በፕሪቶርያው ስምምነቱ መሰረት (ማሃይምዋ አበበች አዳኔ እንዳለቺው መገንጠልን የሚከለክላቸው ስለማይኖር)
ሕዝብ ሰብስበው የመገንጠል ሪፈረንደም የማካሄድ መብት እንዳለቸው ተፈራርመው ስላሉ ያንን ለማካሄድ ከአብይ አሕመድ “የገዳይነት የምሰክር ወረቀት” ተሸላሚ የሆኑትን ቡዱኖች ይዞ ባሕርዳር ላይ ይገኛል።
የትግራይ ሊሂቃኖችም ሰሞኑን በተከታታይ “ትግራይ የት ላይ ቆማለች? እያሉ ከሕልማቸው በድንገት የተሰወረችባቸውን ትግራይ “በዳሰሳ” ላይ ናቸው።
ሰሞኑን መቀሌ ውስጥ ሁለት ትዕይነቶች ታዝቤአለሁ።
1ኛው ስብሰባ ከህጻንነተቻው ዕድሜ ጀምሮ ኢትዮጵያንና አማራን በመጥላት በየትምህርት ቤቶቻቸው የጥላቻ ትምህርት እየተጋቱ ለ27 አመት ያደጉ ጎረምሶችና እንዲሁም የድሮ የወያኔ ታጋዮች ትግራይ ከኤርትራ ወይስ ኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ የሚል “ቅዠት” ውስጥ ገብተው መቀሌ ባንድ አዳራሽ ውስጥ በመሰብሰብ አገር በማፍረስ “ሴራ” ላይ ሲተነትኑ “ዩ ቱብ” ላይ አድመጠናል።
ይህ ቡድን ማሕበረሰቡን በፕሮፓጋንዳ እያጠበ ለማይቀረው የግንጣላ ጦርነት ለዳግም የሕሊና ዝግጅት በማካሄድ ላይ ነው።
2ኛው ሴራ የትግራይ የወያኔ ጳጳሳትና ቀሳውስት ውሳኔ ነው።
ሰሞኑን ከሕግ ውጭ ከዋናው ሲኖዶስ በመነጠል ኢትዮጵያ የምትባል አገር የትግራይ ቅኝ ገዢ ነችና አናውቃትም ብለው አዋጅ በማስነገር ከወሰኑዋቸው ውሳኔዎች ውስጥ “ኢትዮጵያ” የሚል ቃል ከእምነት ማሕደሮችና ቤተክርትያን ተቋማት እንዲሰረዝ በማድረግ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆኑ ሃይማኖታዊ መጻሕፍት እንደገና እየተጣሉ ወይንም እየተሰረዙ በምትኩ “ትግራይ” በሚል ቃል ተተክተው ለአዲስ ሕትመት እንደሚዘጋጁ ሳያመነታ ገልጸዋል፡ (ይህ የታሪክ፤የቅርስ፤ የጽሑፎች፤የሃውልት፤የመንገዶች ስም ስረዛና ድለዛ በወያኔዎች የተጀመረ ቢሆንም ሃይማኖት መሪዎች ነን የሚሉ ካድሬ ቀሳውስት እየሰሩት ያለው ግን ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን በዓለም ውስጥ በታሪክ አዋቂነቱና መምህርነቱ የታወቀው ሟቹ Eric Hobsbawm “The Age of Extremes
1914-1991” በተባለው መጽሐፉ ወንጀል መሆኑን ይገልጻል። የኛ የሃይማኖትና የፖለቲካ ወንበዴዎች ግን ነባር ቅሪቶችንና ስሞችን በመለወጥ ወንጀል በመስራት ማሃይምነታዊ ድፍረታቸውን ሲገልጹ እናያቸዋለን።
አማርኛ የሚባል ቋንቋና ኢትዮጵያ የሚል ቃል ጭራሽ እንዳይደመጥ በሙሉ ተስማምተዋል። የትግራይ ሪፑብሊክ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሚል እየተዘጋጀ ያለው ኢሕጋዊ አገራዊ ግንጠላ “የወያኔ ፖለቲካዊ የሃይማኖት ክንፍ በመሆን ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በወያኔዎች የሚታዘዝ “በእነ ደብረጽዮን እና በእነ ጌታቸው
ረዳ” በውስጥ አበራታችነት እየተከናወነ ያለ “ሁለተኛው ረድፍ” አገር የማፍረስ ሴራ ነው።
እነዚህ የትግራይ ጳጳሳትና ቀሳውስት ኢትዮጵያን ስያስወግዱ ኢትዮጵያ የምታቀርበው የባንክ፤የስልክ፤ የገንዘብ፤ የሸቀጥ፤የመብራትና መድሃኖቶችና ሆስፒታሎች፤ የመገናኛ አውታሮች፤ ነዳጆች እንዳይታገዱ የመጠቀም መብት እንዲኖራቸው፤ በእነ ጌታቸው ረዳና በአብይ አሕመድ ፈቃጅነት ዛሬም ኢትዮጵያን እየጠሉ ምርትዋን እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው (አገር ወዳድ ተጋሩ የኔን ዘመቻ ሰምታችሁ እገዳ እንዲደረግባቸው ተቃውሞአችሁን እንዳተስተጋቡ ጥሪ አቀርባለሁ፤ “መንግስት ቢኖር ነው ግን!!”)።
አሁን ያለው መሪ አገር ወዳድ ቢሆን ኖሮ ወይንም እኔ መሪ ብሆን ኖሮ
አገልግሎት እንዳያገኙ በሕግ እንዲታገዱ አደርግ ነበር። (እናንተ ምን እንደምትሉ ባላውቅም እውነታው ግን እየሆነ ያለው አሁንም የኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎት ልክ እንደ ሕዝቡ
እኩል አግልገሎት እያገኙ ነው።)
3ኛው በዚህ ጽሑፌን ልደምድም።
ጌታቸው ረዳና አንጃው ጦረኛ የድብቅ ሴራቸው፡
ጌታቸው ረዳ፤ በሚመራው መንግሥት “ፈራ ተባ” እያለ በመጠባበቅ ላይ ያለው “ውስጥ ለውስጥ” በመደራጀት ላይ ላለው ለአንጃው የሽምቅ ፓርቲ የውስጥ እገዛ ለመስጠት ያለው ገጽታ ገልጬ ልደምድም።
ሰዎች ይህንን ሴራ አያውቁም የሚል ግምት አለኝ። ታስታውሱ ከሆነ ካሁን በፊት November 16, 2022
“የትግሬዎች ፎኒክሲዝም” በጻፍኩት ሐተታ ላይ እንዲህ ጽፌ ነበር።
ትግርኛውን ልጀምር << ሞይትና ዘይንሞት ሓመድ ልሒስና ዝተሳእና
ዓለም ዘገረምና
መስተንክር አፋጣጥራና >>
“ሞተን እንደገና በዳግም ልደት አመድ ልሰን የተነሳን!
ዓለምን ያስገረመ መስተንክር ስነ አፈጣጠራችን!
ትናንትም ዛሬም አስገራሚ ልዩ ፍጡሮች ነን!!
እያሉ በንግግራቸውም ሆነ በሙዚቃዎቻቸው የሚያስተጋቡት የፎኒክስዋ ታሪክ 99% ትግሬዎች የፎኒክስዋ ዳግም ልደትና የትግሬዎች ዳግም “አመድ ልሰን የተነሳን” ቅቡልነት የመፈክራቸው ተመሳሳይነት በዚህ 3 አመት በጆሯችሁና በዓይናችሁ ያያችሁትና ያደመጣችሁት አጋጣሚ ነው።”ብየ ነበር።
በመቀጠልም የፕሪቶሪያ ስምምነት ተብየው ከተፈራረሙ ማግስት ብዙ ሰው “ሲደሰት” እኔ ተቃውሜ ነበር። በዚህም ጽሑፍ November 2,
2022
<< ከዚህ በኋላስ ወዴት? ከዚህ በኋላ ወያኔ ውስጥ ለውስጥ ተዋጊ አንጃ ይፈጥራል>> በማለት በጻፍኩት ጽሑፍ ላይም:-
“ሁለቱም ፋሺስቶች መጨረሻ ሕዝብ አስፈጅተውና ፈጅተው አርስበርሳቸው ተቃቅፈው ያለ ምንም ተጠያቂነት ጦርነቱ ይቋጫል ብየ ደጋግሜ ከነሓሴ ጀምሮ ጽፌአለሁ፡ ስንት ሰው እንዳነበበው ባለውቅም እውነታው ይኼው ዛሬ ተፈራረሙ። ሆኖም ችግሩ እስካልተፈታ ድረስ የሁለቱ የፋሺስት ሰላም እንጂ የማሕበረሰባችን ሰላም ሊፈታ አይችልም።” በማለት ስጽፍ፡ አስደግፌም እንዲህ ብየ ነበር፡
“እንድታውቁልኝ የምፈልገው ፤ ወያኔ የሰላም ስምምነት ያድርግ እንጂ ፤ ትግራይ ውስጥ “የትግራይ ሪፑብሊክ” ዓላማ ለማስቀጠል በውጭም በውስጥም ፍላጎት ያላቸው ትግሬዎች ስላሉ ወያኔዎች ቦታውን (ትግራይ ውስጥ) አስተዳደሩን ከተቆጣጠሩት በሗላ አንጃ ለሚፈጠረው ድጋፍ ሰጪ ሆነው ይቀርባሉ ብየ ነበር። ይህንን ዛሬ እውን እየሆነ አዝማሚያው እያየሁ ነው። ያንን ላብራራ።
ከዚያ በፊት ግን ስለ ጌታቸው ረዳ የጻፍኩት በ April 19, 2022
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተነገረ የወያኔ ትልቁ ንድፍ
“ነፋስ ላይ በአእዋፍ የተሠራች ዩቶፒያ ከተማ” ጌታቻው ረዳ Ethiopian Semay) በሚል የጻፍኩት ላይ የጌታቸው ረዳ ንግግር ልጥቀስ፡
ጌታቸው ረዳ ለግንጣላ ከሚያሴሩት አንዱ ነው፡ በጣም ደብቅ ሴረኛነትና ጮካነት ከወያኔ የቀሰመው ትምህርት ተሎ ቀስሞ ተግባራዊ ካደርጉት አንድ ጌታቸው ነው። መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋብዘውት የተናገረውን በድጋሚ ላስታውሳችሁ እሻለሁ።
እንዲህ ይላል
“ብዙ ወዳጆች አሉን፤ ብዙ ነገሮች ውስጥ ለውስጥ ለማምጣት እየሞከርን ነው። እነሱ ይህንን የሚያደርጉልን “መለስን ስለሚወዱ እኔን ሰለሚወዱ ወይንም ትግራይን ሕዝብ ስለሚወዱ እንዳይመስላችሁ” ፤ የትግራይ አገርነት ፍላጎት በመደገፍ የነሱን ፍላጎት ይጠቅመናል ከሚሉት ጋር በማገናዘብ ሊደግፉን እየተንቀሳቀሱ ነው። ለምሳሌ ተከብበናል ስንል በድንገት … (?) ብሎ (ድሮን ?) ለማለት “አግኝተናል” ለማለት ይመስላል::
“ሶርያ አግኝታለች” “የመኖች አግኝተዋል” በማለት በደፈና ስለ የውጭ ዕርዳታ ምን እንደተሰጣቸው ፍንጭ ሳይሰጥ ስለ የመኖች ሲያወራ “ድሮን” እንደተሰጣቸው የሚመስል
“ፍንጭ” ንግግር ሲናገር ይደመጣል። (ተረክበናል ከሚላቸው መሳሪያዎች አሁን በርክክብ አልታየም- ምክንያቱም አግኝተናል የሚላቸው ዘመናዊ መሳሪያዎች ደብቀዋቸዋል)።
በመቀጥል እንዲህ ይላል፤
“ትግራይ እንደ አገር ዓለም እንዲያውቋት የሚገደድበት ስራ መስራት አለብን። ያንን ማድረግ ከቻልን “ኢን ኤቭሪ እስቴፕ ኦፍ ዘ ወይ” (በያንዳንዱ ዘርፍ)ተፈላጊዎች እንሆናለን ማለት ነው። መጀመሪያ “ብሔረ ሃገረ ትግራይ” ለመመስረት አስፈላጊ “ኢንስትቱሽን” መስራት አለብን። “ሠራዊታችን” የዚህ አካባቢ “ጎብለል” እንዲሆን ካደረግነው ራሳቸው ይፈልጉናል። Red Sea/ የቀይ ባሕር/ ሃያሎች መሆናችን አሁን እያመኑ ነው። የዚህ አካባቢ “እስታብሊቲ” (የሰላም ምሰሶዎች) መሆናችን ማየት ጀምረዋል።”
ሲል ጌታቸው ረዳ የግንጣለው ሴራ የውጭ ሃይላት እየገፉበትና ወያኔዎችም በዚህ ሴራ እየገፉት እንዳሉ ሳይደብቅ የተናገረውን አስነብቤአችሁ እንደነበር ይታወሳል።
ስለ ሃይማኖቶኞቹ መገንጠል ገልጫለሁ፤ ስለ ሊሂቃኖቹ ገልጫለሁ፤ አሁን ድግሞ ጌታቸው ረዳ እና መሰሎቹ አስተዳዳሩን የተቆጣጠሩበት ዋናው ምክንያት፤ዛሬ በየአዳራሹ ስለ ግንጣላ የሚሰብኩ በርካታ የትግራይ ምሁራን ቅስቀሳው እያካሄዱ ወጣቱን በሕሊና ዝግጅት ለዳግም ጦርነት እያዘጋጁት ሲሆን፤ ከውስጥ እነ ጀነራል ምግበይ እና የመሳሰሉ በወንጀል የተጨማለቁ ወንጀለኞች በየገጠሩ እና አውራጃው እየሄዱ የቆየው ድብቅ የጥርናፈ (የማደራጀት) ስራ በመካሄድ በሰላም ሰበካ ስም እየሄዱ ገጠሬውና ከተሜው እንዲሁም ታጣቂው ውስጥ ለውስጥ ሲሰብኩት ጌታቸው ረዳ ደግሞ “በሰላም ጡሩምባው” አገራዊ ኢትዮጵያዊነት እየሰበከ ‘ባንኩን ስልኩንና ሸቀጣ ሸቀጦችን ወደ ነበሩበት ደረጃ እንዲያድጉ ካደረገ በኋላ፤፤ እነ ደብረጽዮን እነ መንጆሪኖ እና የመሳሰሉ መሰሪ ወያኔዎችን “ኣንጃ” እንዲያዘጋጁ በማድረግ ከጌታቸው ረዳ ወይንም ከመጪው ወያኔዊ አስተዳዳር ጋር “በዲሞክራሲ ስም” ጸብ የፈጠሩ መስለው በረሃ በመውጣት አገራዊ ግንጠላ ለማካሄድ እየተዘአጋጁ ነው።በውስጥ የሽኩቻ ባሕሪ የለም ማለት ግን አይደለም፤ አብሮም ወያኔን ከሚቃወሙ እኔን መሳይ ጥቂቶችም ግፍትና ፍትግያ እንዳለበትም አትዘንጉ። በዛው ላይ አካለ ሰንኩላን ሆነው ባለሰቡት ህይወት የወደቁት እሮሮ ሲጨመር ውጥረቱ የት የሌለ ያደርገውና ምናልባትም ትግራይ በብርት የሚጨራረሱ ሥርኣተ አልባ “የአናርኪ” ጋንጎች ምድርም ልትሆን ትችል ይሆናል። በተለይ ኤርትራ ኢሳያስ ሞት በኋላ እነዚህ ቡዱኖች የሚኖራቸው ሚና አካባቢው ለውጥርት ይዳርጋል። ይህ የሚሆነው ሁነኛ አገራዊ መንግሥት እንዳሁን ካጣች ሁኔታው ይባባሳል።
ከኢትዮጵያ ሳይገነጠሉ አገሪቷ ለትግራይ ሕዝብ
የምታቀርበውን ሸቀጥና ገንዘብ ትግራይ ውስጥ በውስጥ አባሎችና እራሳቸውም በመዝረፍ 17 አመት ሽምቅ ተዋጊያቸውን እየቀለቡ ለድል ደርሰው እንደነበር ይታወሳል።ግንጠላ ለማካሄድም ዕደል ነበራቸው፡ ምቹ ነበር።
ያኔ ምቹ ሆኖ በድል ሲገቡ ዛሬ ያ ሁሉ ጥንካሬና ብረት ይዘው ለምን ተሸነፉ ብንል፤ ዛሬ ከመአከላዊ መንግሥት ጠቅላላ የባንክ ፤የንግድ የስልክ የገንዘብ ጠቅላላ “የኑሮ ቧንቧዎች” ሁሉ ዝግ ስለተደረገ እንኳን ተዋጊው ሕዝቡ ችግር ውስጥ በመግባቱ ተዋጊዎቻቸው የሚቀልቡበት መንገድ ስላልነበራቸው በቀላሉ ተከብበው ተሸነፈዋል።
ያ በለመሳካቱ ምክንያቱን
ወደ በመፈተሽ በመግባት ለመሸነፋቸው ዋናው ምክንያት “የምጣኔ አቅም ዝግ ስለነበርና ሕዝቡ ሊቀልባቸው ባለመቻሉ” የስምምነቱን ዕድል በመጠቀም አስተዳደሩን ከተረከቡ በኋላ ትግራይ አስፈላጊውን “ፋሲሊቲና ጥቅማጥቅም” ካገኘች በኋላ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ሆና እንደነበረቺው በክልል ደረጃ እንድትቆይ እያደረጉ የምታገኘው ጥቅም በሕዝቡ በኩል እያገኙ ልክ እንደ 17 አመቱ ትግል በመጀመር “አንጃቸውን” ወደ በረሃ በመላክ የተጣሉ አስመስለው የሽምቅ ውግያ ከፍተው አገራዊ ግንጠላውን በቀላሉ ላማሳካት እንዲመቻቻው እየሰሩ ነው።
ያንን ከማድረጋቸው በፊት መጀመሪያ የወልቃይትና የራያን ነገር እልባት ማወቅ ይኖርባቸዋል። ወልቃይትን ካገኙ የሽምቅ ተዋጊ መስርተው ወደ ሱዳን መውጫ በር ከፍተው ካሁን በፊት ያሳየሁዋችሁ የፖርትሱዳን እና የወያኔ ዕቅድ በመቀጠል ምናባዊዋን “ዓባይ ትግራይ” (ታላቅዋን ትግራይ) ይመሰርታሉ። ሆኖም
“በዳመና ውስጥ በአእዋፍ የተሠራች ምናባዊ ከተማ” መጪው ህይወትዋ ምን ይመስል ይሆን? የሚለው ትልቁ ጥያቄ መልስ ሊገኝለት የማይቻል ጥያቄ ነው።
ጽሑፉን ብትቀባበሉት ምሁራንና ሌሎቹ እንዲያዩት ይረዳል።
ጌታቻው ረዳ
Ethiopian Semay