Saturday, February 2, 2019

በትግራይ ኦንላይን ላይ የወጣው የኢትዮጵያን ምጣኔ ሓብት ለማቃወስ ለትግሬዎች የተላለፈ መልዕክት! ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎመው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)


በትግራይ ኦንላይን ላይ የወጣው የኢትዮጵያን ምጣኔ ሓብት ለማቃወስ ለትግሬዎች የተላለፈ መልዕክት!
ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎመው ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

ትግራይ ኦንላይን (Tigrai online)  የተባለ የወያኔዎች አቀንቃኝ የሆነ ጸረ ኢትዮጵያ እና በተለይም በጸረ አማራነቱ የታወቀው ድረገጽ Short advice to Tigraians in Ethiopia, important!.  http://www.tigraionline.com/short-advice-to-tegaru.pdf በሚል ከድረገጹ ማውጪያ ላይ በተጠቀሰው እንግሊዝኛ ርዕስ በመስጠት፤ አንባቢ ርዕሱን ሲጨቁን “ሓፀርቲ ምኽርታት ንተጋሩ ኣሓትን ንአሕዋትን፤ከምኡ እውን ንሓለፍቲ መንግስቲ ክልል ትግራይ፡” በሚል ርዕስ በትግርኛ የዘገበው ወደ አማርኛ ሲተረጎም “አጫጭር ምክሮች ለትግሬ እህቶች እና ወንድሞች እንዲሁም ለትግራይ ክልላዊ መንግስት ሐላፊዎች” የሚል 13 ዝርዝር ነጥቦችን በትግርኛ የተጻፈ “ማኒ ላውንደሪ” “ሕገ ወጥ” የገንዘብና የንግድ አሰራር በመስራት የኢትዮጵያን ምጣኔ ሐብት እንዲቃወስ የትግራይ ሕብረተሰብ ሊሳተፋቸው የሚገቡ ሕገወጥ ተግባሮች በዝርዝር በማስቀመጥ ለትግራይ ማሕበረሰብ ሕገወጥ መልእክት በድረገጹ ላይ ለጥፎታል። ከዚህ በተጨማሪ “እግራችሁ አጣጥፋችሁ የምትጠብቁ ካላችሁ እናንተን እና ልጆቻችሁ ገድለው ያፈራችሁትን ሃብት ሊወርሱት ነው በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተጋሩ ባለሃብቶች “እነ ልጆቻቸው ተጨፍጭፈው ንብረታቸው እንደሚዘረፍ” ያስተላለፈው ፍርሃት የሚለቅ ቅስቀሳ በማሰራጨት የትግራይ ባለሃብቶች ከነቤተሰቦቻቸው ለግድያ እንደታጩ በሃሰት ቅስቀሳ ለትግራይ ባለሃብቶች አስተላልፏል።

ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት ትርጉም ከዚህ በታች የተገለጸ ቢሆንም፤ የአብይ አስተዳዳር በትግራይ ኦን ላይን (Tigrai online) ላይ ሕጋዊ እርምጃ ካልወሰደ ኢትዮጵያውያኖች ለአብይ ያለው ድጋፍ እንዲያቆሙ በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ።

በዚህ ሰነድ ትርጉም አማርኛው አስቀድሜ ከዚያም ዋናው የትግርኛ ዝርዝር ነጥቦቹ ከድረገጹ ቀጥተኛ ቅጅ ከታች አያይዤ አቅርቤዋለሁ።

Short advice to Tigraians in Ethiopia, important!
 አጫጭር ምክሮች ለትግሬ እህቶች እና ወንሞች እንዲሁም ለትግራይ ክልላዊ መንግስት ሐላፊዎች”
   ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)

    ተቀማጭ ገንዘብ ካላችሁ ትግራይ ውስጥ በሚገኙ ማይክሮፋይናንስ ድርጅቶች (ደደቢት፤ፋና፤ አደዳይ) ብቻ እንዲቀመጥላችሁ አድርጉ። በተለይም በንግድ ዘርፍ ላይ ገንዘብ እንዳይኖራችሁ አድርጉ፤ አደራ።
   
     ከቻላችሁ ገንዘባችሁ በብር ሳይሆን በወርቅ መልክ እና በውጭ አገሮች ገንዘብ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ዲርሃም ወ.ዘ.ተ) የምታስቀምጡበት መንገድ ፈልጉ።
    
    • በተለይም ኣዲስ አበባ ከተማ የምትኖሩ ገንዘብ ያላችሁ ወገኖች- እከተማዋ ውስጥ የሚገኝ ወርቅ ሁሉ ገዝታችሁ በማከማቸት ወደ ትግራይ እንዲሸሽ አድርጉ።

• ከትግራይ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባ ወርቅ ኣይኑራችሁ።

• ውጫዊ የንግድ እና ሳፋየር በአንድ ትልቅ ድርጅት መልክ ሳይሆን በርከት ባሉ በትናንሽ (small scale) ዘርፎችና ማሕበራት እንዲካሄድ ይሁን። ዘርፎቹ የሚያስገኙት ገቢ (ሮያሊቲ ታክስ፣ ትርፍ ታክስ) ወደ ትግራይ እንዲገባ ይደረግ።

  በአንድ ትልቅ ድርጅት (large scale mining) የሚፈጸም ሆኖ ከተመዘገበ ገቢው ወደ ፌደራል
  መንግሥት ስለሚገባ እንዳይገባ ይህንን ዘዴ መጠቀም ያሻል። ይህም በሕገ-መንግሥቱ በግልጽ የሰፈረ ሕግ ነው (አንቀጽ 96፣ 97 ፌደራል ሕገ-መንግስትን ተመልከት)

• ትዳር አድርጉ፣ ውለዱ፣ ብዙ ተባዙ፤ ሆኖም ለሰርግ ተብሎ ከሚገባ በላይ መምነሽነሽ ይቁም። ተስካር ግን በሕግ መታገድ አለበት። ያለንን ሀብት እንቆጥብ።

• የሕክምና ድርጅቶች እንደሌሎቹ ድርጅቶች ገንዘብ የላቸውም። "ገንዘብ የለም" ብለን ስራዎቻቸው እንዲያቆሙ ማድረግ ስለማይገባ ያለ መንግሥታዊ በጀት ቆመው የሚሄዱበት መንገድ ለማድረግ ካሁኑ ጀምሮ ጥናት ይካሄድ። በተለይም እንደ  ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ፣እና ኣክሱም ሆስፒታል የመሳሰሉትን ይመለከታል። ሌሎችም እራሳቸው የሚችሉበት መንገድ ማፈላለግ አለባቸው።

• ተጋሩ ባለሃብቶች እመሃል አገር የሚገኝ ሃብታችሁና ድርጅቶቻችሁ፣ ህንጻዎቻችሁ ጫና መፍጠር ለሚችሉ አገሮች (ሃያላን መንግሥታት አገሮች) በከፊል ሽርክና ለነሱ ሽጣችሁ ንግዶቻችሁ በዛው መልክ እንዲካሄድ አድርጉ።

• ማታ ማታ የዊስኪ ጠርሙስ እያጋጫችሁ ዊስኪ በመጨለጥ ገንዘባችሁ የምታባክኑ የትግራይ ባለሃብቶች የምንሰጠው ምክር አለ። ይኸውም በሺሕ የሚቆጠር የትግራይ ሰው እየጠፈናቀለ ባለበት ባሁኑ ወቅት እናንተ በደቂቃ ብዙ ሺሕ ብር ለዊስኩ ማውጣታችሁ እንዲቆረቁራችሁ ይሁን። ነገ የናንተ ህንጻ ቢቃጠል እንዴት ብሎ ነው የናንተን ሃብትና ህንጻ የሚከላከልላችሁ። ድሃ ወገናችሁ ካልረዳችሁ ትግራዋይነታችሁ የት ላይ ነው? ስለዚህ ልብ አድርጉ ትግራይ ወገናችሁን እርዱት።

• ተጋሩ ትግራይ ውስጥ ብሕብረት/በሽርክና… በአምራች ኩባንያዎች፤ ማኑፋክቹሪንግ ኢንቨስትመንቶች ተሳተፉ፤ የትግራይ እምባሳደሮች ሆናችሁ የውጭ ‘ኢንሸስተሮችን’ ወደ ትግራይ እንዲሳቡ አድርጉ።

• ቆፍጠን ብላችሁ (ደፈር ብላችሁ) ደህና ገንዘብ መድባችሁ፣ ላይና ታች ብላችሁ በማስተዋል ጥናት አድርጋችሁ ለነዚያ ጸረ ትግሬ ለሆኑ መርዝ የሚረጩ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጀነሳየድ የሚያውጁ፤በትግራይ ሕዝብ ላይ የጥፋት ሴራ የሚጎነጉኑ ‘ተለቅ፤ተለቅ’ ያሉትን የሚደረግ አድርጉአቸው”።መርዝ ከሚረጩበት ሜዳቸው እንዲወገዱ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ካሁን ወዲያ በትግራይ ሕዝብ ላይ ሞት እና ጥፋት ማወጅ ዋጋ የሚያስከፍል እንደሆነ እንድያውቁት ማድረግ ይገባችኋል።

በተለይ ትግሬዎች የሆናችሁ ባለሃብቶች፤ ሃብታችሁ ለትግራይ ህልውና እና ለትግራይ ሕዝብ መከበር አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባችኋል። “ይህ አሁን የመጣ ሃይለኛ አውሎ ነፋስ እኛን ሳይነካ ያልፍ ይሆን?!” ብላችሁ እጅና እግራችሁ አጣጥፋችሁ የምትጠብቁ ካላችሁ ‘እነሱ” እናንተን እና ልጆቻችሁ ገድለው ያፈራችሁትን ሃብት ሊወርሱት ነው (ኢድኩምን እግርኹምን ዓፃፂፍኩም ንሳቶም ንዓኹምን ንደቅኹምን ቐቲሎም ኩሉ ሃብትኹም ክወርሱዎ እዮም)። ይህንን ለማድረግም ይህ ትምቢታቸው እውን ለማድረግ የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። እውነታውም እየሰፋ እየሄደ ነው። ይህ ከመሆኑ እና ይህ ከመሆኑ በፊት (ንብረታችሁ ተወርሶ እናንተ እና ልጆቻችሁ ከመጨፍጨፋቸው በፊት) ካለችሁ ንብረት/ሃብት/ የህዝባቸሁን ደህንነት /ህልውና/ በሚውል ተግባር በመርዳትና የናንተን ጥፋት በሚመኙት ላይ ለማስቆም በሚረዳ ተግባር እንዲውል ንብረታችሁ በከፊል ለዚህ ስራ እንዲውል ለግሱ።

• የፕሮፖጋንዳ ሃያልነት እንደምታዩት ሃያል ነው። ጠንካራ የተጋሩ መልዕክቶች የሚተላለፉባቸው ሚዲያዎች በገንዘብ እና በሃሳብ በመርዳት በውጭ እና በአገር ውስጥ እንዲደመጥ ተነሳሽነት እንዲኖሮው መልዕክቱ ለሁሉም ትግሬ እንዲዳረስ አድርጉ!
                   ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ)
Short advice to Tigraians in Ethiopia, important!
ሓፀርቲ ምኽርታት ንተጋሩ ኣሓትን ንኣሕዋትን፤ ከምኡ እውን ንሓለፍቲ መንግስቲ ክልል ትግራይ፣

  • ዝቕመጥ ገንዝብ እንተሃሊዩኩም ኣብ ትግራይ ኣብ ዘለዋ ማይክሮፋይናንሳት (ደደቢት፣ ፋና፣ ኣደዳይ) ጥራሕ ዕቖሩ፤ ብፍላይ ኣብ ንግዲ ዝቕመጥ ገንዘብ ከይህልወኩም ሓደራ፤

  • እንተኽኢልኩም ግን ገንዘብኩም ብብር ዘይኮነስ ብመልክዕ ወርቂ፣ ናይ ወፅኢ ሃገራት ገንዘብ (ዶላር፣ ዩሮ፣ ዲርሃም ወ.ዘ.ተ) እትዓቑሩሉ መንገዲ ድልዩ፣

  • ብፍላይ ኣብ ኣዲስ አበባ እትነብሩ ገንዘብ ዘለኩም ወገናት- ኣብታ ኸተማ ዘሎ ወርቂ ኹሉ ገዚእኹም ኣክቡዎ፣ ኣብ
ትግራይ ክቕመጥ ድማ ግበሩ፤

        • ካብ ትግራይ ናብ ብሄራዊ ባንኪ ዝኣቱ ወርቂ ኣይሃሉ፣

        • ምውፃእን ንግዲን ሳፋየር ብሓደ ገዚፍ ትካል ዘይኮነስ ብርክት ብዝበሉ ኣናእሽቱ (small scale) ትካላት ፣
ማሕበራት ክካይድ ይኹን። እዚ እቲ ዘፈር ዘእትዎ ኣታዊ (ሮያሊቲ ታክስ፣ ናይ ትርፊ ታክስ) ናብ ትግራይ ክኣቱ
ይገብሮ፤ ብሓደ ገዚፍ ትካል (large scale mining) ዝፍፀም ኮይኑ እንንተተመዝጊቡ እዞም እቶታት ናብ ፌደራል
መንግስቲ እዮም።እዚ ኣብቲ ሕገ-መንግስቲ እውን ብግልፂ ሰፊሩ ኣሎ (ዓንቀፃት 96፣ 97 ሐገ-መንግስቲ ፌዴሪኢ
ተወከስ)፡፡

        • ሓዳር ግበሩ፣ ውለዱ፣ ብዝሑ፤ ኮይኑ ግን ንመርዓ ኢልካ ፍሰስ ተፋሰስ ይትረፍ፤ ናይ ተስካር እንግዲት ግን ብስሩ
ብሕጊ ክእገድ እውን እዩ ዘለዎ። ዘለና ሃፍቲ ንዕቖር።

       • ትካላት ሕክምናና ከምቲ ካልእ ዓውዲ "ገንዘብ የለን" ኢለን ስራሕ ከቋርፃ ስለዘይግባእ ብዘይ ናይ መንግስቲ በጀት
ደው ኢለን ክኸዳ ዝኽእላሉ መንገዲ ካብ ብሐዚኡ እናሰርሓሉ ይፅናሓ። እዚ ብፍላይ ንሪፈራል ሆስፒታል ዓይደር ፣
ንሪፈራልሆስፒታል ኣኽሱም ዝምልከት እዩ። እተን ኻልኦት እውን ብፋይናንስ ዓርሰን ዝኽእላሉ መንገዲ እናኣለሻ
ይኺዳ።

       • ተጋሩ ሰብሳቢ ሃፍቲ እንተኽኢልኩም ኣብ ማእኸል ዓዲ ዘለዉ ትካላትኩም፣ ህንፃታትኩም ብኽፋል ንናይ ወፃኢ
ዓዲ (እሞ ድማ ናይ ግዝፍ ዝበላ ፅዕንቶ ፈጠርቲ ዓድታት) ሰብ ሃፍቲ ሸይጥኩም ብሽርክና ክካየዱ ግበሩ፤

        • ኣቱም ዊስኪታት ሚፅ እናበልኩም ትሓድሩ ዘለኹም ሰባት፣ ግደፉ ዘለናሉ እዋን ኣስተውዑሉ፣ ክንደይ ትግራዋይ
ተፈናቒሉ ኣብ መንገዲ ወዲቑስ ብደቓይቕ ኣሽሓት ፊፍ ኢልኩም ክትኣትዉ ንእሽቶይ'ባ ይሰቆርኩም። ኣበይ ድኣ እዩ
ዘሎትግራዋይነት? ሎሚ ቆላሕ ኢልካ ዘይረኣኻዮ ወድ ድኻ ፅባሕ ናትካ ህንፃ ከይቃፀል ከመይ ይቃለስልካ? "ንመን
ኢል እየ ዝመውት?" ዝብል ሰብ ከይበዝሕ ግበሩ፤ እዚ ድማ ብኻልእ ዘይኮነስ ወገናውነትካ ብምርኣይ፣ ዘለካ
ብምክፋል፣ ኣብ ቅድሚዝበልዖ ዝሰኣነ ወገንካ ብገንዘብ ዘይምፅዋት እዩ።

        • ኣብ ትግራይ ብሕብረት/ብሽርክና ኣብ ዓውደ መፍረይቲ ማኑፋክቹሪንግ ኢንቨስትመንታት ተሳተፉ፤ ናይ ዓድኹም
እምባሳደራት ኪይንኩም ናይ ወፃኢ ኢንሸስተራት ስሓቡ፤

        • ሓደ ሓደ እዋን ድፍር ኢልኩም፣ ደሓን ገንዘብ መዲብኩም፣ ላዕልን ታሕትን ኣስተንቲንኩምን ኣፅኒዕኹምን ነቶም
ዝኽፍኡ ፀረ ተጋሩ መርዚ ዝነዝሑ፣ ኣብ ልዕሊ ህዝቢ ትግራይ ጄኖሳይድ ዝእውጁ፣ ኣብ ልዕሊ ትግራይ ናይ ጥፍኣት
ተንኮል ዝፍሕሱፍርይ ፍርይ ዝበሉ ዝግበር ገይርኩም ካብቲ መርዚ ዝዝርአሉ ሜድኦም ክእለዩ ምግባር የድሊ።
ድሕሪ ሀዚ ኣብ ልዕሊ ትግራይን ተጋሩን ሞትን ዕንወትን ምእዋጅ ዋጋ ዘኽፍል ክኸውን ክትሰርሑ ይግባእ።

        • ብፍላይ ተጋሩ ዓበይቲ ሰብ ሃፍቲ ናትኩም ሃፍቲ ኣብ ህልውናን ኽብሪን ትግራይን ተጋሩን ኣወንታዊ ኣበርክቶ
ዝፃወት ክኸውን ኣለዎ። እዞም ሰባት ንስኹም "እዚ ህቦብላ ንፋስ ከይነኽአ ክገድፈና ዶ ይኸውን!" ብዝብል ተስፋ
ኢድኩምንእግርኹምን ዓፃፂፍኩም ንሳቶም ንዓኹምን ንደቅኹምን ቐቲሎም ኩሉ ሃብትኹም ክወርሱዎ እዮም
ዝሰርሑ ዘለዉ፣ ካብ ዕለት ናብ ዕለት ድማ እዚ ትምኒቶም ናብ ምድሪ ዘውርዱሉ ዕድል እናስፍሑ ይኸዱ ኣለዉ።
እዚ ቅድሚ ምዃኑ ካብቲ ዘለኩምሃፍቲ ዝተወሰነ ሰሊዕኹም ድሕንነትን ህልውናን ህዝብኹም ኣብ ምሕላው፣
ንወገንኩም ኣብ ምሕጋዝ፣ ጥፍኣትኩም ንዝምነ ኣብ ምቕዳም ኣውዕሉዎ።

         • ሓይሊ ፕሮፖጋንዳ ከምቲ እትሪኡዎ እዩ፤ ሓያላት ናይ ተጋሩ ድምፂ፣ ተረኽ ዝስምዐለን ሚድያታት ኣብ ውሽጢ
ዓድን ኣብ ወፃእን ክፍጠራ ብፋይናንስን ብሓሳብን ሓግዙ ወይ ባዕልኹም ተበግሶ ወሲድኩም መስርቱ።
እቲ ሓበሬታ ናብ ኩሉ ትግራዋይ ክባፃሕ ግበሩ!