Thursday, August 4, 2022

ጌታቸው ረዳ ሳይደብቅ የነገረን የምዕራባዊያኖቹ ቤተሰባዊ ውይይት በመቀሌ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 8/4/22

 

ጌታቸው ረዳ ሳይደብቅ የነገረን የምዕራባዊያኖቹ ቤተሰባዊ ውይይት በመቀሌ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay 8/4/22

እኔ እንደምታውቁኝ “ፖለቲካል ኮሬክትነስ” የሚባል ዝባዝንኬ እንደማልቀበል ታውቃላችሁ። አማርኛው “እውነት ተናግሮ በመሸበት” እንደማለት። በዚህ ካወቃችሁኝ አንባቢዎቼም ሆናችሁ ተገንጣዮች መልስ እንድትሰጡኝ የምፈልገው በዚህ ጥያቄ ልጀምር።

“ለምንድ ነው እገነጠላለሁ ለሚል የትግራይ ሕዝብ ግዴታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባንክ እና ቴሌፎን እንዲሁም መብራት የመስጠት ግዴታ ያለበት?

እገነጠላለሁ ብሏል ብሎ የነገረን ደግሞ ጤፍ፤ ብር እና መብራት ላኩልኝ የሚለን የወያኔው ጌታቸው ረዳ ነው።

እነሆ እንዲህ ይላል፡

“ 80%  የትግራይ መገንጠል ደጋፊ ሲሆን 10% እምየ ኢትዮጵያ ቅድስት ሃገር (የራሱ ቃላት ናቸው) የሚሉ 15% ኮንፌደረሽን፤ፌደረሽን የሚሉ 5% መሃል ላይ የሚዋልሉ ናቸው”፤ ሲል የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ነግሮናል።ይህንን መልስ አስቡበት እና እስከዛው ድረስ ሰሞነኛው የኮሎኒያሊስቶቹ  ወደ መቀሌ (ወደ ልጆቻቸው / ቱ ዘየር ቦይስ) ሄደው ስለተናገሩበት እና እቀፈኝ ልቀፍህ ቤተሳበዊ ፎቶ መነሳት ከመነጋገራችን በፊት ትግሬዎች ራስን ችሎ አገር የመሆን ምኞታቸውን በጉጉት እንደ አበደ ውሻ ምራቃቸው እያንጠባጠቡ ያዙኝ ልቀቁኝ የማብዛታቸው ዕብደት ትንሽ ማለት አስፈላጊ ነው።

ለመሆኑ ትግሬዎች እነማን ናቸው ለሚለው ብዙ ጊዜ ስለጻፍኩበት አሁን ወደዚያው አልመለስም።  ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ናት ብሎ የደነገገው የፈጣሪ ሕግ ከየት አገኙት? የሚለው ግን መልስ ያሸዋል። ትግራይ ብዙ ኢትዮጵያዊይነ ደማቸው የገበሩባት የኢትዮጵያ አካላዊና ታሪካዊ አንጡራ መሬት ነች። ሬፈረንደም ካሉም (ቅዠትና ምኞት ቢሆንም- ነግር ግን  ምናልባት አብይ አሕመድ ሊሰጣቸው ይችል ይሆናል!) ኢትዮጵያዊያኖችን የሚጨምር ነው እና እንደ ድሮ የኤርትራው “እቃ ዕቃ” ጨዋታ አንቀበልም የምንል ትግሬዎች ስላለን ይህንንም አስቡበት።

እነሱ ራሳቸው እኛ “ማንነታችን እናውቃለን” እያሉ በማይጨበጥ ምናብ እየተጎረኑ “ጥራት/ወጥ/ በሆነ የደም እና የዘር አጥንት አለን” በሚል ቅዠት ማንነታችን እናውቃለን ቢሉም የሚያሳምኑበት ‘‘ባይኦሎጂካዊ’ የሆነ ታሪካዊ ማስረጃ ሊያቀርቡ አይችሉም። ለዚህም ምክንያቴ ብዙ ነው።

ኢትዮጵያ “ያቺ የተረገመች አገር” እያሉ ቢረግሟትም ኢትዮጵያ ግጠው አጥንትዋን ያስቀርዋት የ27 አመት ታሪክ ሳንጠቅስ፤ ከረገሙት ሕዝብ ጋር ከዘመነ አክሱም ጀምሮ (ብቸኞች የአክሱም መስራቾች ነን የሚሉትን ቅዠት ብንወስድ እንኳ ‘የኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ’ የሚታወቀው እነሱንም የጨመረ  ቀጣይነት የነበረው እና አሁንም ቀጣይነት ያለው ተለዋዋጭ መስተጋብር፣ ሱፐርኢምፓዘሽን፣ በጦርነት፣ በጋብቻ እና በንግድ ከዘመነ አክሱም ጀምሮ ሆነ ከዚያም በላ እንኳን ከተቀረው ሃበሻ ሕዝብ ከየመኖች እና አረቦች ‘የሱዳን ቤጃዎች’ ፤እስራኡሎች  (ብዙዎቹ ነገሥታተ አክሱም ‘እስራሎች ናቸው”)  የተዋሃዱ ናቸው። በዚህ መስተጋብር “የትግሬ” “የአገዎች” “የአማራዎች” “የአሮሞዎች” ነገዶች እርስ በርስ በደም አጥንት የተዋሃዱበት ታሪክ ነው። ስለሆነም ትግሬዎች እኔ ንፁህ ትግሬ ነኝ የሚሉበት ባይኦሎጂካል ማስረጃ ከቶ ሊያስደግፉ አይቻላቸውም። እንኳን ንጽህናው ቀርቶ ስማቸው እራሱ ትርጉሙ አያውቁትም። ለዚህ ነው ዛሬ በተለያዩ ስሞች እራሳቸውን መጥራት የጀመሩት ። ለምሳሌ አጋዚያን የሚባለው ቡድን “ትግራዎት/ትግራይ/ የሚለው ቃል አይቀበለውም።

አብዛኛው ይህ በሰው ልጆች መካከል ያለው መስተጋብር በዓለም ውስጥ ያለ በመጽሐፍ ቅዱስ  የተደገፈና ሕግ ወጥቶለት የተረጋገጠ ነው (ብዙ ተባዙ መሬትን ሙልዋት! በሚለው ሕግ መሰረት ተባዝተናል። ታዲያ ይህ ሕግ ለትግሬው አይጨምርም? ወይስ ክርስትናውንም በሚከተሉት ርዕዮት ከድተውታል?)።

የነገዶች መስተጋብር በጦርነት እና በግጭት ብቻ ሳይሆን፤ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ሰላማዊ መስተጋብሮችም ነበሩ። ሆኖም ውስብስቡ የሰው ልጆች መስተጋብር ዩተፈጥሮን ሕግ በሚቃወሙት በትግራይ ፋሺስቶች ሕግ ግን የሚወገዝ ነው።  በኢትዮጵያ ነገዶች (አሉ ብለን “ነገድ” እንበላቸው እና እራሳቸው የቻሉ ከነገዳቸው ውጭ ያልተዋሃዱ ነገዶች ባይኖሩም) በመካከላቸው ያለው መስተጋብር ለዘመናት  የባህል እና የቋንቋ መስፋፋት ቅይጥነትና መለዋወጥ አስከትሏል። የሰዎች አካላዊ ገፅታዎች ቅርጾች (የትግሬዎች ቅይጥ አካላዊ መልክ እና ቆዳን ተመልከቱልኝ) እርስ በርስ ተቀላቅለዋል፤ የድሮ ቋንቋዎች እና ቋንቋዎ ተደበላልቀው አዲስ ቋንቋ ፈጥረው ጥንቶቹ ጠፍተዋል።

አዳዲስ የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ ክርስትና፣ እስልምና፣እና ባህላዊ ክስተቶች በአዲስ ድብልቅ ተፈጥረዋል።ስለዚህም በመካከላቸው ግልጽ የሆነ የጎሳ ልዩነት መፍጠር አይቻልም። የኢትዮጵያ ሕዝቦች ቋንቋን መሠረት አድርገው፣ሃይማኖት ወይም ባሕል መከለል ፍፁም ከተፈጥሮ ሕግ አንጻራዊ ነው። በአጠቃላይ የቅኝ ገዢዎች ካሰራጩት ሃሰተኛ ትምህርት እና የ60ዎቹ የወያኔ ተማሪዎች ቅዠት ውጭ ኢትዮጵያ ውስጥ
‘የጎሳ ደሴቶች” አልነበሩም ሊኖሩም አይገባም።

 ይህንን ካልን ዘንድ ላይ የጠየቅኳችሁን ጥያቄ ልመለስ ነው።  ጌታቸው ረዳ በተደጋጋሚ በሰጠው ቃለ መጠይቅ 80%  የትግራይ መገንጠል ደጋፊ ሲሆን 10% አምየ ኢትዮጵያ ቅድስት ሃገር (የራሱ ቃላት ናቸው) የሚሉ 5% ኮንፌደረሽን፤ፌደረሽን የሚሉ 5% መሃል ላይ ያሉ ናቸው ሲል የትግራይ ሕዝብ ፍላጎት ነግሮናል።

የኔ ጥያቄ ደግሞ የሚከተለው ነው። ጥያቄው ለወያኔዎቹ ኩሊ በቀላሉ በፍርሃት ሸብረክ ለሚለው ለቦቅቧቃው ለአብይ አሕመድ አይደለም። እኔ የምጠይቀው ለእውነተኛ ኢትዮጵያዊያኖችን ነው። በጌታቸው ረዳ ማስረጃ ከሄድን፤ ለምንድ ነው እገነጠላለሁ ለሚል ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባንክ እና ቴሌፎን እንዲሁም መብራት የሚሰጠው?  ሕዝቡ ወጥቶ እኛ ጌታቸው እንደሚለው የመገንጠል አባዜ የለንም ብሎ አልተቃወመም? ለምን አልተቃወመም?     

መቀሌ

በጦርነቱ ወቅት የሳተላይት ጥቆማ እየጠቆሙ የሽብርትኛው የወያኔ ተዋጊ ቡድን ሲረዱ የነበሩት አውሮፓና አሜሪካ ጌቶቻቸው ወደ መቀሌ ጉዘው “ቤተሰባዊ ውይይት” ብሎ የጠራው ጌታቸው ረዳ እውነትም ቤተሰባዊ እንደሆነ ድሮም ዛሬም የነበረንን ጥርጣሬ ሳይደብቅ አረጋግጦልናል። ለዚህ ነው ሳይሰለችን እነዚህ የቅኝ ገዢዎች በወልቃይት መሬት ለስለላ ቀጠና ስታረጂክ ቦታ እንደሚፈልጉት እና ለቀይ ባሕርም ሆነ ሱዳንንም ከሗላ ለመቆጣጠር እንዲያመቻቸው ዓላማ ስላላቸው ከበረሃ ጀምሮ ኮትኩተው ያሳፍዋቸው ወያኔዎች ጋር ““ቤተሰባዊ ውይይት” አንደሚያደርጉ ተንበይነው እውን እንደሆነ አረጋግጦልናል። ሶማሊ ላንድ ተቆጣጥረዋል፤ ጁቡቲ ውስጥ አሉ ፤ ቀርታ ያለቺው የትግራይ አካባቢ ነች፡ ያቺም በቡተሰብነት ገብተው እየኮቶቱ ናቸው።

ከዚህ ሌላ የሚገርመው “መንግሥት ተብየው” ጰርጳራው አብይ አሕመድ “ባንክና መብራት//” ለመጠገን ወደ ትግራይ ለሚሄዱ ሰዎች “የደህንነት ዋስትና” እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን’’  ብሎ ማለቱ የአብይ አሕመድ “ብላፍ/ bluff” (አስመሳይ) ብለው ቀልደውበት ሲያስቁን ስብሰባው ላይ ዋሉ’ እያለ የነገረንን የሚገርም ነው። ፈረንጆቹ እንዳልነው ከበረሃ ዘመን ጀምሮ  እንደ ልጆቻቸው ያሳደግዋቸው ትግራይ ውስጥ ታሽገው ላሉት የወያኔ መሪዎች “ስስ ልብ” እንዳላቸው አረጋግጦልናል።ለዚህ ነው በእፍ እፍ ፍቅር ተቃቅፈው ፎቶ መነሳትን ያማራቸው።

 ወይ እምየ የተባበሩት አፍሪቃ ማሕበር! ምናባሽ ውጦሽ ይሆን?!!!   

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ