Monday, October 4, 2010

“በይቻላል!የዋህነታችን” ይቀለድብናል፡የጠላቶቻችን ልሳን መሆን መቸ ነው የምናቆመው?!

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
Those of you havoing difficulty reading the fonts (because of small size font) in order to read the article with large font, you need to use Internet Explorer to point your mouse to the the lower /buttom-bar and change the Zoom Level (100,150,200%....) as you wish. And to those of you who use Mozzila Firefox- point your mose to the uper top left sidebar "View" then Zoom then chose text zoom only or "zoom in" what ever your choice. Or symply use the keyboard "Shift: and "Alt" together and press (+ )sign or to downsize ( - )sign key. use this in every kind of browzer you have በ"ይቻላል!የዋህነታችን”ይቀለድብናል፡የጠላቶቻችን ልሳን መሆን መቸ ነው የምናቆመው?!ጌታቸውረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ getachre@aol.com አንድ ሰሞን የኤርትራ (ሻዕቢያን የሚቃወሙ)ተቃዋሚ ድረገጾች የሚለጥፏቸው መጣጥፎች/አቃቂሮች ለመመልከት አንደኞቹን ጎብኝቼ ነበር።አንድ ጸሓፊ የለጠፈው ጽሑፍ ዓይኔን ስቦት ሳነብ ጸሓፊው ስለ ኢትዮጵያዊያን ገራገርነት የገለጸበት አሽሙር ሳነብ ሰዎቹ እያደሩ የማስብ ችሎታቸው ማቆሙን ከድሮ ይልቅ ዛሬ እየባሰባቸው ይመስላል። ስተረጉም እንዳላበላሸው እንደ ወረደ በእንግሊዙ ቋንቋ ላስቀምጠው። እንዲህ ይላል “Addis 2010, the capital of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, is now the centre of a multiethnic, multi-religious, multicultural country and by hosting the NCDC it was embracing a multiethnic, multicultural, multi-religious Eritrea. You can still question and say how much democratic and how much multi-cultural has Ethiopia become, but no doubt it is in the process. True, it has hosted the Eritrean Democratic Alliance for years, but this was the first time it has hosted such a large and diversified gathering of Eritreans from all over the world, welcoming them irrespective of ethnicity or religion. Many of the participants have not been to Ethiopia before. Still, many of them fought the Ethiopian army during the occupation when some of us went to study or work there; and most of them had vivid memories of the brutality of the ‘Tor serawit’ – Ethiopian occupation army. Some of the youth fought in the last Eritrean-Ethiopian border war—for many, it was breaking a psychological barrier. Many were struck by the humility and respectfulness of the Ethiopians they met. A humorous colleague of mine who visited Ethiopia for the first time two years ago, jokingly said, ‘Why did we separate from Ethiopia, ‘You see, if you ask for anything,… they say yichalal – it is possible. We used to call him yichalal.” (Addis 2010: Eritrean-Ethiopian relationship (I) By Dr. Mohammed Kheir, September 8, 2010Awate.com)
ከላይ እንዳነበባችሁት ኢትዮጵያን ጠላት አድርገው የሚመለከትዋት ኤርትራኖቹ በወካያቸው በመለስ ዜናዊ (ህወሓት መሪ) አስተናጋጂነት ከሁለት ዓመት በፊትም ሆነ ከጥቂት ወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ሄደው በነበሩበት ወቅት የሕዝቡ ገራገርነት፤መልካም አሳቢነት፤ሰባዊነት፤እንግዳ ተቀባይነት እና የዋህነት ቁም ነገር ሳይቆጥሩት ዛሬም ምንኛ እየደቀለዱበት እንዳሉ ይህችን አንኳር ጥቅስ በድጋሚ ልብ በሏት“A humorous colleague of mine who visited Ethiopia for the first time two years ago, jokingly said, ‘Why did we separate from Ethiopia, ‘You see, if you ask for anything,… they say yichalal – it is possible. We used to call him yichalal.” አንድ ተዋዛይ/ተጫዋች/ቀልደኛ ጓደኛየ “ለምን ከኢትዮጵያ ተለየን? አየህ! ኢት ጵያዊአን ማንኛውም ነገር እንዲያደርጉልህ ስትጠይቃቸው “ምን አለበት! እሺ! ችግር የለም!ይቻላል!” ነው የሚሉት። በዚህ የተነሳ ጓዳችንን “ይቻላል” የሚል ቅጥያ ስም ሰጠነው። ሲል ምንኛ የዋህነታችን እየቀለዱበት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
ይህ ጉድ ልጠቅሰው የፈለግኩበት መነሻ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት “ትንንትም”“ዛሬም”የተስተናገዱበት፤የበሉበት የቤተሰባዊነት ማዕድ “ደፍተው”ሁሌም የሚራመዱት ሕሊናቸው ከሻገተው፤ ምስጋና የማያውቁ ጨዋነትን፤የዋህነትን የሚያንቋሽሹ “ዋልጌዎቹ”ኤርትራዊያን ሊህቃን ክፍሎች ለመተቸት ሳይሆን፡ ያለ ማቋረጥ የጠላት ፕሮፓጋንዳ መግለጫዎች እና ትችቶች (አውዲዮ ቪድዮ ካሴቶች፤ጋዜጣዊ መግለጫዎች፤…)ባጠቃላይ ኢትዮጵያን በጠላትነት ዓይን የሚመለከቱ ሕዝብን (ህጻናት፤ሽማግሌ፤ዓይነ ስውራን፤እመጫቶች ፤እርጉዞች….) በጅምላ የጨፈጨፉ ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑ አገር በቀል የፋሺስት ድርጅቶች ቅስቀሳ በየድረገጻቸው በመለጠፍ እና በመተጋገዝ ለኢትዮጵያ ህልውና አደጋ የሚጥሉ የፕሮፓጋንዳ ስራዎች ሰፊ ዕድል እንዲያገኙ በመፍቀድ አያሌ ጀግኖች የሞቱላትን አገር እንድትናቅ ታሪኳም እንዲረገጥ አስተዋጽኦ እያደረጉ ያሉት ከሃዲ እና አድርባይ የጠላት አገልጋይ ድረገጾችን ለናንተ ላንባቢዎቼ ለመጠቆም ነው። ከላይ ፎቶግራፋቸው የሚታየው ዘፋኞችና አትሌት ለመተቸት ሳይሆን፤እነኚህ የሕሊና ድውዮች ወደ ጎን ትትን ለዛሬ ለመተቸት ያተኮርኩበት ዋናው መልዕክቴ “ኢካድ-ፎረም”“ኢትዮ-ፎረም”“ግንቦት7እና መሰል ውጥንቅጦች”(ሌሎችም መሰል ድረ ገጾች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል)ኦነግ የተባለ ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅት ያወጣውን አወናባጅ መግለጫ እየለጠፉ፦ ኦነግ ዛሬም ከግንቦት 7ጋር የ “ኤ ኤፍ ዲ”ትዝታውን ይዞ አንድነት ፈጠርኩኝ ባለበት ሰዓት “ድል ለኦሮሞ ሕዝብ”እንጂ “ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ”ባላለበት፤ፌርማውና መፈክሩ ለኢትጵያ ሳይሆን ላኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ቆሜአለሁ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያዊያን እንወክላልን ብለው እነ ብርሃ ነጋ “ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ እንከፍላለን”“ከየቦታው የተጠረቃቀሙት ቆሻሾችን አንጠራርጋለን” በማለት አገር ውስጥ ያለው ወያኔን መጠራረጉን ትቶ የውስጥ አገር የተቃዋሚዎችን አንድነት አፍርሰው ዛሬም የውጪውን አንድነት አደፍርሰውና በጣጥሰው ራሳቸውም ወደ ሻዕቢያ በመሮጥ የ ኢሳያስ ጀሌ ለመሆን ደጅ ጥናት ሲመላለሱ ፤መጨረሻ ላይ ይህ የአንድነት በታኝ ቡድን” እና መሰል ጥርቃሞ ግለሰቦች ያሰባሰበ የተቃዋሚ ድርጅት ጥምረት በመፍጠር የሚከተለው መግለጫ የተጠቀሱት ድረገፆች አሸብርቀው አውጥተውላቸዋል። Aliance for Liberty, Equality, and Justice in Ethiopia (ALEJE) በማለት ራሱን የሚጠራ ሰነፍና ውዥምብራም የነ ብርሃኑ የግንቦት7 ቡድን የሚከተለው መግለጫ አገልጋዮቹ በሆኑት ዌብሳይቶች ኦነግን “እንኳን ደስ አለህ!” ሲል አሰራጭቷል። እነሆ አውጥተውላቸዋል። Aliance for Liberty, Equality, and Justice in Ethiopia (ALEJE)extends a warm and heartfelt congratulation to the OLF eldership, its members, and supporters on this momentous victory that will certainly paves the way for successive victories. ALEJE would also like to acknowledge and thank all the Oromo elders that made this moment possible..” የፈነደቀበትን የልቡን ደስታ ገልጸላቸዋል። ግንቦት 7 ነን ብለው ራሳቸውን ራሳቸውን ነፃ ማውጣትያልቻሉትን ነፃ አውጪዎች ተሰባስበው ጠባቦች የኢትጵያን አንደነት ለመበተን አንድነት ፈጥረናል ባሉበት ጠባብ ሕሊናቸው ጠባብ ለጠባብ ሲጨፍሩ ግንቦት7የተባለው ጸረ አንደነት ቡድንም አብሮ የኦነግ ጠበል በመቅመስ ጽዋውን ለመጋራት ሳያፍር ደስታውን እንዳያችሁት አንስቷል። ከላይ የተጠቀሱ ድረገጾችም በተለይም ክንፉ አሰፋ በተባለ ግለሰብ (ከሆላንድ የሚተላለፍ ድረገጽ)ተመልክታችሁ እንደሆነ ኦሮሞ የምትባል አገር እምሰርታለሁ ብሎ “የኦረሞ ነጻ አውጪ” ነኝ የሚለው “ማሰብ ያቆመ” ለዘመናት የበሰበሰ የፋሺስቶች ድርጅት በውስጡ የተሰባበሩትን ለዘመናት ውጭ አገር የመሸጉ ብትንታኝ ኦነጎች አንድነት ፈጥረናል፤እንደ አዲስ ተሰባስበን “አንደነት ፈጥረን”ኢትዮጵያን ልናጠፋ ተዘጋጅተናል (የ40ዓመት ዘፈን) ያሉበትን “ፋሺስታዊ የድርጅታቸው መግለጫ”በመለጠፍ ዛሬም በድጋሚ አበስሮናል። ክንፉ አሰፋ የተባለው የኢትዮ-ፎረም አዘጋጅ በጣም አደገኛ እና አድርባይ መሆኑን መላው ያንድነት ሃይላት በጥብቅ ለማስገንዘብ እወዳለሁ። Ethiopianforum.orgድረገጽ ለአመታት ያሳየው ማሕደሩ የኢትጵያ አንድነት ሃይሎች እንዲበተኑ ብዙ ጥሯል። ያለፈው ባለፈው ወቅት ቅንጅት በማፍረስ የተጫወተው ሚና ወደ ጎን ትተን በቅርቡ የሻዕቢያና የኦነግ አቀንቃኝ (ሲምፐታይዘር) በመሆን ሰፊ መድረክ ሰጥቶ ኢትዮጵያ እንድትሰደብ አድርጓል። ዛሬም በማድረግ ላይ ነው። ይህ ግለሰብና የኢትዮጵያን ረቪው አዘጋጅ “ኤልያስ ክፍሌ”በምንም መልኩ የሚለያቸው ሁኔታ እንደሌለ ነው። ሁለቱም ድረገጾች እና መሰል ግልገል ድረገጾቻቸው ጸረ ኢትዮጵያ ቅስቀሳዎች የሚገልጹ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የሚያሳትሟቸው ሕትመቶች ወደ ሕዝቡ ጀሮ እንዲደርሱ መሸጋገርያ ጎዳና በመሆን እያገለገሉ ነው።ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ባንድ ጹሑፋቸው “ትናት የለም ፤ነገ የለም፤ዘሬ ብቻ” ሆኗል የኛ ነገር እንዳሉት ሁሉ “በአድርባይነት” “ዲሞክራቲክ ሚዲያ ነኝ”በሚል እየተመጻደቁ “ መርዝ ያለው ቅስቀሳ ሳይቀር ለጠላት ዘብ” የመቆም” ልምድ በር ከፋች ሆነው ወደ አደገኛ ጥቃት ሕዘቡ እያጋለጡት ነው። ደጋግመው አገር ወዳድ ያንድነት ሃይሎች እንደገለጹትና እንዳስጠነቀቁት እንኚህ ሃይላትና በውጭ ቄሳሮች እየተደገፉ የኢትዮጵያን አንድነት በይበልጥ ለማፈረስ ሁለተኛ ዙር ከበባው ና ዱለታው እየጠጠናከረ መሆኑን ኢትዮጵያዊያን ልብ ማለት ይኖርባችሗል። ገራገርነታችን አስጠቅቶናል!ያ ባሕል በጥንቃቄ መታየት አስፈላጊው አሁን ነው። አድርጉ ስንባል “ችግር የለም! ይቻላል! ግድየለም!.. ሱሳችን የምናቆመው መቸ ነው? እኔ አጅግ የማከብራቸው ወዳጆቼም በድረገጻቸው የማይሆን ነገር ሲለጥፉ ያገር ጉዳይ ነውና (ግል ንክኪ አይደለምና) ምህረት የሌለው ወቀሳ ነው በይፋ የማውርድባቸው። አብዛኛዎቹ ለምን እንደምበሳጭ ሳይረዳቸው የሚቀር አይመስለኝም የሚል እምነት አለኝ። የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ የቆሙ ከሆነ የጠላት ቅስቀሳና ልሳን እየሆኑ ወደ ሕዝብ ጀሮ የመሸጋገርያ መንገድ እየሆኑ ስንመለከታቸው ለምንድነው ያለ ምንም ይሉኝታ የማናወግዛቸው? ስንት ጊዜ እንሞኝ!እነኚህ ሃይሎች -የውጭ ቄሳሮች ቅጥረኞች ሆነው እኛኑም የቄሳሮቹ ግልገሎች ልሳን አድማጮች እንድንሆን ለምን ይደረጋል?ድርጅቶች በቅጥረኝነታቸው ራሳቸው አብደው ተከታዮቻቸውን ሲያሳብዱ የሚዲያ ሰዎችም አብረው ካበዱት ጋር የማሽቃበቱ ቅሌት ለምን ስንታዘብ በጣም አስጋራሚና እውንም ያበደ ዘመን ነው ከማለት ምን ማለት ይቻላል። በገዛ ድረገጻችን ፤ቲቪያችን/ራዲዮናችንና ጋዜጦቻችን ወላጆቻችንና፤ ያገራችን አርበኞችን ሰንደቃላማችንን ፤ ታሪካችንና አገራችን ኢትዮጵያን ሲዘልፉ መፍቀድ ደብተራም ሓኪምም የማያውቀው በሽታ መሆኑን ትግሉ እጅግ ውስብስብ አድርታል። ድረገጾች እና የፖለቲካ ድርጅቶች አብዛኛዎቹ ጸረ-ኢትዮጵያ አንድነት የሚሰብኩ ወይንም ከጸረ አንድነት እና ጠባብ ጎሰኛ የፋሺስቶች ግልገሎች ጋር የተቆራኙ መሆናቸውና በፕሮፓጋንዳውም እየጎለበቱ ሲመጡ የኢት ጵያ አንድነት ሃይላትም በተጠንቀቅ ቆመው ልብ ማለት ይኖርባቸዋል። ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎለብቱ መስለው ከጠላቶች ጋር የሚዳሩ የፖለቲካ ሸርሙጣዎች ለይተን ማውቅ ግድ ይላል።ዛሬ በጠላት ተከበናል! ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ነን። ውጭ አገር እየኖሩ ያገሪቱን ስምና አንድነት በማይጠጋ ስም እየቀቡ ኢትዮጵያን “ሞንሰተር” ኢምፔርያል/ቄሳር/ጨቋኝ/ጨፍጫፊ/የደብተራ አገር/የአማራ አገር ወዘተ…እያሉ እንዳልተማሩባትና እንዳልተወለዱባት የሕዝቧን ደግነትና ማንነት በመጥፎ እንዲነሳ የዋህዋን አገር ጥላሸት የሚቀቡ ግልገል ፋሺስቶችን ልሳን በድረገጾቻቸው መለጠፍ ለጠላት ማገልገል ይቅርታ የማይባልበት መሆኑን በኔ በኩል ቅሬታየ ለኢትዮጵያ አንባቢዎቼ ለመግለጽ እወዳለሁ። ድርጅት የሚል ስም የያዘ ሁሉ ሲመሰረት፤አንደነት ፤ጥምረት አደረገ ሲባል “ካንዱ ዛፍ ወዳንዱ ዛፍ እንደ ጦጣ ዝለላ እየዘለሉ”ጎጂው ከመልካሙ ሳይለዩ በድረገጻቸው የሚያስተጋቡና የሚዘግቡ ግለሰቦች ለወሳኙ ትግላችን አኮላሺዎችና የጠላቶች መንፈስ ገምቢዎች እየሆኑ መቀጠላቸውን በግልጽ ማውገዝ ይኖርበችሗል። በክንፉ አሰፋ ድረገጽ ማለትም በ“ኢትዮፎረም . ኦርግ/Ethioforum.org” ኦነግ የላከለት በድረገጹ የለጠፈው የኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት ያወጣውን ፋሽስታዊ የድርጅቱ መግለጫ ሲለጠፍ እና በስተመጨረሻም ኦነግ “Victory to the Oromo People! ሲል ያሳረገው የዘወትር መፈክሩ ይህ ግልገል ፋሸስት ዛሬም ማንነቱን እንዳልለወጠ እና ድሉ እወክላለሁ ለሚለው ለኦሮሞ ሕዝብ እንጂ ለኢትጵያ እንዳለሆነ ሳያፍር ሳይሸማቀቅ የሗሊት “ባለበት ሂድ” ሲረግጥ ከአዲሱ ጋዜጣዊ መግለጫው የተመለከትን ኢትዮጵያዊያን ነን የምንል ዜጎች ሁሉ ምን ያህል “ገራገሮች” እንደሆንን እና ለመጣው ሁሉ “ይቻላል “እያልን የምንቀበል መሆናችን ስላወቁብን፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የበቀሉ ኢትዮጵያዊነታቸው የካዱ “ፋሺስቶች”በራሳቸው ድረገፆች የአንባቢ ብዛት ስለሌላቸው ፤ወደ ገራገሮቹ ወደ “ይቻላል ድረገጾች” እየላኩ ፋሽስታዊ ቅስቀሳዎቻቸው እና ዘለፋቸው በኛ ላይ እንዲዘንብብን ሲፈቀድ እንዴት ነው እነኚህ “ኢትዮጵያዊ ሚዲያዎች/መድረኮች ናቸው ማለት የምንደፍረው?። ግልገል ፋሺስቶቹ በራሳቸው ድረገጾችና ራዲዮኖች ስለ ኦነግ እኛ ምንጽፋቸው ጽሑፎች እና ፋሺስታዊ ድርጊታቸው እና ማሕደራቸው መለጠፍ ማስተላለፍ አይፈቅዱም!ታዲያ እኛ እስከ መቸ በራሳችን ሚዲያ ዛቻና ፉከራ እንዲደረግብን እንፈቅዳለን? ለኛ ውድቀቱን ሲመኙልን ላኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ድል ሲመኙለት ፋሺስቶቹ በኛ ላይ ዘመቻቸው እያጧጧፉ መሆናቸው ስተን እንዴት ደስ ላችሁ ተብለው በ ኢትዮጵያዊያኖች ይበሰራሉ? አገራቺን ኢትዮጵያ በነዚህ ግልገል ፋሺስቶች ልሳን ስትዘለፍና እንኳን ደስ አላችሁ ሲሏቸው ዝምብለን ማድመጣችን ሕሊናችን የራቀብን ‘ዕብዶች” ነን ወይስ ምንድ ነን ?ባንድ ዘርና ባንድ ሃይማኖት ያነጣጠረ ለአመታት የተፈጸመው ተደጋጋሚ ጥቃት ተጠያቂው ማን ነው?“አምና”በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የተፈጸመው የማፈናቀል ወንጀል ( ጀርመን ራዲዮ ያስተላለፈው ዘገባ በራሴ የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ በአውዲዮ ቪፈዲዮው ክፍል ወደ ቀኝ ያድምጡና ይፍረዱ)እና ጭፍጨፋ እንኳ ልብ ሳንል ነገም ለነዚህ ፋሺስቶች ፕሮግራምና ዕቅድ መሳካት እንዲቀጥል ተባባሪ ስንሆን፤ ነገ በልጅ ልጆቻችን ቀጣይ ፍዳ ማውረስ የተያያዝነው መሆናችን አላወቅንም (እርግጥ እነኚህ ከነሱ ጋር በፖለቲካው ሜዳ የሚዳሩት/የሚላፉት ልጆቻቸውና ልጅ ልጆቻቸው ፈረንጅ አገር ነው በምቾት የሚኖሩና በዛ ግድ የላቸውም- ይብላኝ እዛው ለሚኖረው ሕዝብ))። ሻዕቢያዎችም/ጀብሃዎቹም “ኤርትራዊያኖቹም”ሆኑ የኦነግ እና በኢትዮጵያ ክርስትያኖች ላይ ትንኮሳ እያካሄዱ ያሉት የእስላም አካራሪ ሃይሎች የሚያሳዩት ጸረ ኢትዮጵያ ባሕሪና እርምጃ ስንጨምቀው የማስታወስ ችሎታቸው ከድተውታል። ባጭር አማርኛ “የማሰብ ችሎታቸው አቁሟል!በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አገላለጽ ደግሞ<<አበቶቻቸው ክድተዋል፤ የአባቶቻቸውን እምነት ክደዋል፤ የአባቶቻቸውን ታሪክ ክደተዋል፤አባቶቻቸው ለኢትዮጵያ መሞታቸውን ክደዋል። እኛ ለሆዳችን፤ለምኞታችን ባጠቃላይ ከሌሎች በልጦ ለመታየት ፋታ የማይሰጥ ግብግብ ውስጥ ነን። በዚህ ግብግብ ውስጥ አገር አይታሰብም።ታሪክ የሩቁ ሳይሆን የትናንቱ አይታሰብም። …” ይኼ ነው! ውድ አንባቢዎች “ዶሮ ጫጩቶቿን” ከጭፍሊት ስትከላከል “በድፈረት” ነው። ጫጩቶቿን ስትነካባት አንተ ጋር (ከሰው ጋር) በቁጣ እየጮኸች ትገጥማለች (ጭሆቷን ፤አካላታዊ መወራጨትዋን ማስተዋል ይቻላል) “ከጭልፊትም” ጋር በድፍረት ትገጥማለች (አቅም ይኑራት አይኑራት እንዳለ ሆኖ በቀላሉ ልጆቿን ላለማስገደልና ላለማስገንጠል ላለመዋረድ ባላት ድፈረትና አቅም ትገጥመዋለች) ።እኛ እንደ ኢትዮጵያ እና እንደ ሰው አገራችንና ያገራችን ሰንደቃላማ ታሪካችንና በጎነታችን የዋህነታችን በመጥፎ ተተርጉሞ ለጥቃት ተጋልጦ ሲጠቃ በድፈረት መቆም እና አገራችን እንድትሰደብ በየሚድያቸው/ቲቪ እና ራዲዮን ጠላቶቻችን እየጋበዙ እንዲሰድቡን ሰፊ በድረክ የምንሰጣቸው እንዳያንስ አገራችን ለማፍረስ የእንኳን ደስ ያላችሁ መግለጫ አንበትንላቸው? ምንድር ነው ነገሩ!? እኛ ከጯጩቷ ያነሰ ሕሊና አለን?ካሁን ወዲህ ከዚችው ደቂቃ ጀምሮ “ይቻላል ባይነታችን”፤”ግደየለም ውንድሞቻችን ናቸው ባይነታችን”፤ “ገራገርነታችን”፤”የዋህነታችን” እና “የአህያ ትዕግስታችንን” ማቆም ጊዜው ዛሬ አይመስላችሁም!? ወንድሞቼ የዋህነታችን አስጠቃን እንጂ እየጠቀመን እኮ አይደለም። ከጣሊያን ጀምሮ ለጠላት ያሳየነው እንግዳ አክባሪነታችን፤የዋህነታችን ሚዛኑ ያጣ ራሳችንን ጥፋተኞች የሚያደርግ ይቅር ባይነታችን ባህሪ ዛሬም በሰፊው ቀጥለንበታል። እኮ ለምን?! የጎጃም የጎንደር የወሎ፤የወላጋ …..ሕዝብ ነፃ ያወጡናል ብለው ለታሪክ ጭላጦች/አተላዎች የሆኑት ለወያኔና ለኦነግ “በጋሚዶዎች “ምግብ እያስሰነቁ ውሃ ፤ምግብና መሳርያ እየተሸከሙ መንገዱን ጠርገው ፤መርተው የአገሪቱ መዲና እንዲቆጣጠሩ ያሳያቸው “ኢትጵያዊ የዋህነት” ምላሹ ምን እንደነበር በሽግግሩ ወቅት የሆነውን የምታስታውሱት የቅርብ ትዝታ ነው። ዛሬ ያንን መጥፊያችን ሲገነጉንብን አንደገና ያንኑ ፋሺስታዊ ተግባሩ በሕዝባችን ላይ ለመድገም ኦነግን “እንኳን ደስ ያለህ” እንበለው? አርስ በርሳቸው “አማራና ኦሮሞ፤እስላምና ክርስትያን” እየተባባለ 9 ባነዲራ ፈጥሮ መንግስታት ብሎ ሰይሞ በፊርማው አጽድቆ ከወያኔ ጋር የሰራው የፋሽስቶች ድርጊቱ እንዳይበቃው ዛሬ ተመልሶ ከተበታተነበት የውጭ አገር ኑሮው በስልክ ተጠራርቶ ፋሺስት ለፋሺስት እጅ ተጨባብጦ ይኼው “መጣሁባችሁ! ሲለን እንዴት “እሰየው” እንበለው? እኛ ሞተን ካሕኑ ኦነግ በሬሳችን ላይ ጸልዮ ምግቡን ይቋደስብን?።

ምን የሚሉት ሞኝነት ነው!ትዕግሰት እኮ ላህያም አልጠቀማት።ለመጣው ማርገድና የይቻላል “የዋህነታችን” መጠን ይኑረው። ባለፈው ሰሞን መለስ ዜናዊ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ንግግር ለማድረግ ሲመጣ ሰለሞን ተካልኝ የተባለው “ማሰብ ያቆመ” የዋህ ነብስ የቪዲዮ መረጃ ተቀርጸ ለታሪክ የተመዘገበ ማሕደር ስንመለከት እጁን አውጥቶ ፤ድምፁን ጮክ አድርጎ በማጉልያ ተደግፎ ወደ እኛ አቅጣጫ በመዞር “በመለስ ነፃ ወጥተናል!!!!! ወደ ዝምባብዌ ሂድ!!!!!!እያለ ከወያኔ አሽከሮች ሆኖ እኛን (እኛ ውጭ አገር የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የመለስ ዜናዊ ተቃዋሚ ሰልፈኛውን)ወደ ዝምባብዌ ሂዱ!ሲለን አገሪቱና ምድሪቱ ምን ቀውስ ውስጥ እንደገባች እና ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ቀውስ ገብቶ በጋሚዶዎች /”ጠመንጃ የያዙ ወረበሎች”ምን ያህል የዋሁን ሕዝብ በተለይም ሚዲያ ውስጥ ቦታ ሊኖራቸው የሚችሉ (ጋዜጠኞች፤ዘፋኙን፤ሯጩን/አትሌቱን…)እያወናበዱ አገልጋያቸው እያደረጉት እንደሆነ አስፈሪ ምክልክቱ ይኸና የመሳሰሉ ችግሮች ፊት ለፊታችን ኮለል ብለው ይታያሉ።ዛሬም ኦነግን እንደ “ኤ ኤፍ ዲ” አይነቱ የጥፋት ዱለታ ሲደሉትብን የዋሁ ልባችን ዛሬም ከፍተን እንዲዋኙብት ስንፈቅድ የትናነት ታሪክ የማስታወስ አቅማችን ምን ያህል ደነዞች መሆናችን ያሳዝናል። የዋህነታችን አስጠቅቶናል፤ በየዋህነታችን ተቀልዶብናል፤ የጠላቶቻችን ልሳንና ምቹ ሆኖ የመገኘታችን ባህሪ የምናቆመው መቸ ነው?ለውጭ ጠላቶች አድረው ካብራክዋ የወጡ ልጆቿ ደመኛዋ ሲሆኑ ይህች አገር ምን ይሻላታል?ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemayy.blogspot.com