ለአባ ማትያስ ጥያቄ፦ አገርዎ የት ነው? ከበባውና ጭፍጨፋውስ ማን ጀመረው? የከበባውና የእገዳው
ተጫዋቾችስ እነማን ናቸው?
ጌታቸው ረዳ
Ethiopian Sema
3/3/23
አቡነ ማትያስ ጨካኝ አነጋገርና
ወገንተኛ ንግግራቸውን ከተናገሩት ንግግር መካካል በዚቺው ሐረግ ልጀ
አሁን ወደ ዝርዝር ንግግራቸው
የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ አባ ማትያስ
ለአቡነ ዮሐንስ ቀብር ትግራይ መቀሌ ከተማ ተገኝተው ያደረጉት የትግርኛ ንግግራቸው ከመጥቀሴ በፊት ለአባ ማትያስ ቅርብ የሆናችሁ
ሰዎች ስለ ትግራይ famine (የርሃብ ሁኔታ) እና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ጥሰት በሚመለከት በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ “የዓለም
አቀፍ ምግብ ተራድኦ መርሃ ግበር’’ በዋና ዳይረክተርነት ተመድቦ በቅርብ የትግራይን ሁኔታ በአካል እዛው ሆኖ የተመለከተና ያስተባባረ
ኬኒያዊው እስቲቨን ኦማሞ (S.W.Omamo) At the Center of the World in Ethiopia የተባለው አስገራሚ የአይን
እማኝ የጻፈውን መጽሐፍ ገዝታችሁ ብጹእነታቸው እንዲያነቡት ብትሰጥዋቸውና እሳቸው እየነገሩን ካላቸው አጭር አረዳድ ሰከን ብለው እንዲመረምሩት ይረዳቸው ዘንድ እየተማጸንኳቸው
በንግግራቸው የተጠቀሙባቸው የወያኔዎች የሚጠቀሙዋቸውን ቃላቶች “ቃል በቃል” ሳይለውጡ ሳይቀንሱ “ከበባን ዕጽዋን” የሚሉትን
<< የከበባውና የቁለፋው>> ተዋናይ ወንጀለኞቹ የሆኑት የወያኔዎችን ፕሮፓጋንዳ አድምጠው ከመሳሳት እንዲድኑ
እውነታው በዛው መጽሐፍ ተዘግቦ ስለሚያገኙት በንጽሕ ልቦና ጸልየው መጽሐፉን እንዲያነቡት አደራየን እያስተላለፍኩ አሁን ወደ ንግግራቸው እገባለሁ።
ለአብነ መትያስ እንኳን ደህና መጡ
ንግግር ያደረጉት ከዋናው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከተገነጠሉት አንዱ የሆኑት የዌያኔ ተከታይ አቡን ናቸው። እሳቸው እንዲህ በሚል ንግግራቸውን
ከፈቱ፡
<<ብጹእ ወቅዱስ ፓትርያሪክ
ዘኢትዮጵያ ተለያይተን በማንገናኝበት በዛች ሰዓት አባታችን ከሕዝባቸው ከትግራይ ሕዝብ ጋር ሆነው በሩቅ ዕንባቸውን እያነቡና እያለቀሱ፤እየፀለዩ
ለሰላም ሲፀልዩ ነበር። በፈጣሪ ፈቃድ በመሃላችን ተገኝተው እነሆ እንኳን ደህና መጡልን።>> በሚል ንግግር ከተቀበሉዋቸው
በኋላ፦
ብጹእ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስም የእንኳን ቆያችሁ ንግግራቸውን “እንባ” ባጨናበሰው
ዓይናቸው እንዲህ እያሉ ንግግራቸውን ጀመሩ፡
<< ትግራይ ውስጥ የደረሰው
መከራ በዓለም ምድር ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ ደርሷል። ለአስተርዕዮ ማርያም ለመምጣት ዕቅድ ይዤ ነበር፤ሆኖም ‘ባለሁበት
አገር‘ ትልቅ ችግር ስለተከሰተ ችግሩን ለማስተናገድ ሁኔታው ስላልፈቀደ መምጣት አልቻልኩም።ተከብባችሁና ተቆልፎባችሁ የኖራችሁትበን
ህይወት በዓለም ውስጥ ያልተሰማ ያልተደረገ በታሪክም ያልተፈጸመ ድርጊት ትግራይ ውስጥ መድረሱ ለመግለጽ እንዴት ብለን እንግለጠው?
ስም የለውም፡ ለመግለጥ ለመግለጥ የሚቸግር ተሰምቶም ተደርጎም የማያውቅ በትግራይ ውስጥ ደርሷል፤ ያ ችግር እንዲያልፍ ያደረገው
አምላክ ምስጋና ይድረሰው እንላለን። የትግራይ ሕዝብ ጥንካሬ ግን ታአምራዊ ነው፡ከሁለት አመት በላይ ‘ተከብባችሁና ተዘግቶባችሁ’
ኖራችሁ ከዚያ ከተቆለፈባችሁና ከተከበባችሁበት ያወጣችሁ አምላክ ደግሜ ምስጋና ይድረሰው። የትግራይ ሕዝብ ፅናት እንደ ብረት የጠነከረ
ነው። ለፅናታችሁ ለጥንካሬአችሁ እግዚአብሔር አምላክ ‘ከናንተው ከትግራይ ሕዝብ’ ጋር ነው ያለው። በሁለመናው ስንመለከተው የእግዚአብሔር
እጅ ያለበት ነው። አምላክ ከናንተው ከትግራይ ሕዝብ ጋር ነው ያለው። ያለፈው ሁኔታ አመጣጡ ሃያልና ክፉ ነበር። ግን እነሱ እንዳሰቡት
እግዚአብሔር ክፉ አላደረገውም፡ ሆኖም አሁን ያለው ሰላም እንዲጠናከር እየጸለይን የቤተክህነትና የዘመናዊ ትምህርት ተማሪዎች ወደ
ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንዲሁም እናንተም የትግራይ ሕዝብ ትግራይን ለማቅናትና ለማልማት ሃይልና ብርታቱን እንዲሰጣችሁ ያለፈው
መከራም ተመልሶ እንዳይመጣ እግዚአብሔር እናንተንም እኛንም ይጠብቀን። >>
ሲሉ የእንኳን ደህና ቆያችሁ በማለት
ለትግራይ ሕዝብ ያደረጉት አጭር ንግግር ይህ ነበር።
አሁን አንድ ባንድ ነጥቦችን ለፓትሪያሪኩ
ልጠይቅ።
<< ትግራይ ውስጥ የደረሰው
መከራ በዓለም ምድር ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ ደርሷል።>> ሲሉ ደርሶ ሊሆን ይችላል። ሆኖም እርስዎ እንደ
የተዋህዶ ክርስትና ሃይማኖት ዋና መሪነትዎ በትግራይ ውስጥ የደረሰው መከራ በዓለም ምድር ውስጥ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍ የትግራይ
ሕዝብ እንደ ሕዝብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቻቸውን ስንቅ አስንቀውና አስታጥቀው መርቀው ወደ “አማራ እና ወደ ዓፋር ሕዝብ” “ክልል”
ገብተው ያደረሱት ግፍና አመጽ ዝርፍያ መነኮሳትና አዛውንት እናቶች መድፈር እንዲሁ በዓፋርና በአማራ ሕዝብስ በትግሬዎች “ተከብቦና
ተዘግቶበት” እንደነበርስ ያውቃሉ? ካላወቁስ ለምን እንዲያውቁ ጥረት አላደረጉም? ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ሲመለከቱ እውነትም ከትግራይ ይልቅ የጠቀስኳቸው
“የክልሎቹ” ሕዝብ በበለጠ በርሃብና በአመጸኛ የትግራይ ተዋጊ አረመኔ እርምጃዎች እንደተሰቃዩ ይናገራል።
ሰላማዊ የምግብና የመገናኛ አውታሮች
ያለ ምንም እንዳይንቀሳቀሱ፤የከተማዎች መብራትን ስልክ በመበጣጠስ፤ ተደጋጋሚ ጦርነት በመክፈትና አውራ ጎደናዎቹን ድልድዮችን በማፍረስና
በመቆጣጠር ያወኩትን ያህል ወያኔዎች ትግራይ ውስጥ በየመጋዝኑ ተከምሮ የነበረው ምግብ እና እንደዚሁም የተላከ እና አዲስ ምግብ
ተጨምሮ በስርዓት ለትግራይ ሕዝብ እንዳይዳረስ ለዚህ ጉዳይ መዋል የሚቸለው ነዳጅና ከተባባሩት መንግሥታት ምግብ ይዘው ወደ ትግራይ
የተጓዙ የጭነት መኪኖች እየተመላለሱ ምግብ እንዳያመጡና በየአውራጃው እንዳያዳርሱ መኪኖቹ ባግባቡ ከመጡበት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ
ሲጠየቁ ወያኔዎች አሻፈረኝ ያሉበትን በዳሪክተሩና በትግራይ የምግብ አቅርቦት ዋና ሓለፊው በቲዊተር የተመላለሱብትን መልዕክት እነሆ፡
In the previous few
months, I had tweeted and re-tweeted pieces like this:
<< Concerning.
None of the 149 trucks in the convoy that reached #Mekelle#Ethiopia last week
returned only 38 out of 466 trucks that entered #Tigray since 12 July
returned> We need trucks to deliver lifesaving assistance to people in
#Tigray.>> (P-35)<<
ባለፉት ጥቂት ወራት፣ ከትዊት ወደ
ትዊት እንደገና ተደጋጋሚ ትዊት እያደረግኩላቸው ነበር።
<< የሁኔታው አሳሳቢበት!!
- ባለፈው ሳምንት ምግብ ጭነው በኮንቨይ/በጥበቃ/ #ከአገሪቱ ወደ #መቀሌ ከገቡት 149 የጭነት መኪኖች ውስጥ አንዳቸውም አልተመለሱም።
ከሓምሌ ወር ጀምሮ #ትግራይ ውስጥ ከገቡት 466 መኪኖች ውስጥ 38ቱ ብቻ ሲመለሱ ሌሎቹ ሳይመለሱ እዛው ትግራይ ውስጥ ቀርተዋል።
(ገጽ 35)
<< Continued
encouraging progress with support of Federal, #Afar and #Tigray authorities. We
need hundreds more trucks to come out of Tigray so that large volumes of food
can be moved quickly to 5.2 million food insecure people in the
region………..>> (ከፌዴራል፣ ከአፋር እና ከትግራይ ባለስልጣናት ጋር በመሆን አበረታች እድገት ቀጥሏል። ከፍተኛ
መጠን ያለው ምግብ በፍጥነት ወደ 5.2 ሚሊዮን የምግብ ዋስትና ችግር ወደ ክልሉ እንዲሸጋገር በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ መኪናዎች
ከትግራይ እንዲወጡ እንፈልጋለን።(ገጽ 35)_
እያለ ወያኔዎችን ለተዋጊዎቻቸው አመላላሽ አድርገው የያዝዋቸው የጭነት መኪኖች
ተሎ እንዲመልሱዋቸው ከተማጸናቸውና ወደ የበላይ አካልም ስለ ሁኔታው ካመለከተ በኋላ
እንዲህ ይላል፡
<< For me the
issue was very simple: - On trucks, if WEP- contracted trucks did not come out
of Tigray, there was no way for us to deliver food into the region at the required
scale predictability. Millions of Tigrayans will go hungry…. The bureau Head
had himself indicated to my team in Mekelle that the available fuel in the
region stood at mill of litters, but that the TPLF’s position was that this
fuel would not be provided to WFP and other humanitarian actors, because there
were other “more important strategic priorities’’ for the fuel than
humanitarian assistance “our fighters are fighting for Freedom”.
(<< ለኔ ጉዳዩ በጣም ቀላል ነበር፡- በWEP በኮንትራት ያሉ ምግብ የምናመላለስብቻው የጭነት መኪናዎች ከትግራይ ካልወጡ፣ በሚፈለገው መጠን ወደ ክልሉ ምግብ የምናደርስበት መንገድ አይኖርም። በዚህ በምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ይራባሉ። የትግራይ የቢሮ ኃላፊው እራሱ መቀሌ ለሚገኘው ቡድኔ/ለወኪሎቼ/ እንደደገለጸው <<በክልሉ ያለው ነዳጅ በሚሊየን ሊትሮች መጠን ላይ እንደሚገኝ ፤ ነገር ግን የህወሓት አቋም ‘’ይህ ነዳጅ ለደብሊው.ኤፍ.ፒ. እና ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንደማይሰጥ ነበር የነገራቸው። ምክንያታቸውም ሲገልጹላቸውም “ከሰብአዊ ርዳታ ይልቅ ለነዳጁ አስፈላጊ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች ጉዳዮች ስላሉን እና “ተዋጊዎቻችንም ለነፃነት እየተዋጉ ” ስላሉ ነው የሚል ነበር።>>
ይላል።
Later, I shared news
of the TPLF’s position on fuel with WFP leadership, expecting that this would
lead to a denouncement of some kind…….ይልና ኒውዮርክ ወይንም ጀኔቫ ላላው መ/ቤቱ ቢያመለክትም ምክንያቱ
ባላወቀው ምክንያት አጥጋቢ መልስ ሳያገኝ ሲቀር ለትግራይ እርዳታ ሓላፊው ተመልሶ የጭነት መኮኖቹ ተሎ እንዲመለሱ እራሱ ቢጠይቀው
አንተ “የአብይ ሮቦት” (አንተ የአብይ አሻንጉሊት ነህ) በሚል ስርዓት በጎደለው መልስ ሲመልስልኝ በጥንቃቄና ጭዋነት በተሞላ እንዲህ
አልኩት ይላል።
<< I respectfully but forcefully restating my basic points. We need trucks for our operation. Trucks were not coming out of Tigray. We need fuel for our operations. He himself admitted that the TPLF had fuel. He should let us have it so that we could move food to vulnerable food insecure people. “We have other priorities”, he responded. “Ask Abiy Government for fuel”. This was war. Brutal. (<< አሁንም በአክብሮትና በጥንቃቄ ግን በአጽንኦት መሰረታዊ ነጥቦቼን ደግሜ ነገርኩት። የጭነት መኪኖቹ ለሥራችን እንፈልጋቸዋለን። መኪናዎች አሁንም ከትግራይ እንዲወጡ አልፈቀዳችሁም። አብሮም ለሥራችን መቀናት ነዳጅ እንፈልጋለን ስለው፤ እሱ ራሱ በቂ ነዳጅ አለን ብሎ ሲያረጋግጥልኝ፡ ይህ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የምግብ ዋስትና ለሌላቸው ሰዎች ምግብ እንድንወስድ ሊፈቅድልን ይገባል ስለው። "ሌሎች ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች አሉን" ሲል መለሰልኝ። በመቀጠልም "ነዳጅ ከፈለግክ የአብይ መንግስትን ነዳጅ ጠይቅ" ብሎኝ እርፍ አለው።>> ይላል ገራሚው ዘገባው ደራሲው በመገረም “ጦርነት ነበር! እጅግ አረመኔ! ይልና “ለመሆኑ ሕዝብ በረሃብ እንዳይሞት ከሰብአዊ ዕርዳታ በላይ ቅድሚያ ሌላ ጉዳይ አለን ሲሉን ከዚህ ወዲያ ቅድሚያ እና አንገብጋቢ ምን ኖርዋቸው ኖሮ ኢሆን?” ሲል የተገረመበትን በሰፊው ይተነትነዋል። አንግዲህ በኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የምግብ ተራድኦ መርሃ ግብር ዋና ዲሬክተር ኬኒያዊው “ኦማሞ” የታዘበውን አለም አቀፍ የውሸት ዜና ዘጋቢዎች ባሕሪ እና የወያኔ መሪዎች ሓላፊነት የጎደለው ወንጀለኛ ባሕሪ በመደመም በዛች በመጽሐፉ “This is a book about what I saw, what I felt, what did as Representative and Country Director of United Nation World Food Programme (WFP) in Ethiopia from 2018 t0 2021. How I did, what I did, why and so what effect. What went well, what did not, and why. What I learned. What surprised me, what exited me. What disappointed me. And why. እያለ የዘገበው የመግቢያ ገጽ መጽፉን ትግራይ ውስጥ፤ አማራ እና ዓፋር እና የወያኔ መሪዎችና ተዋጊዎች የታዘበውን በሚገርም ሁኔታ ዘግቦታል።
እንግዲህ አባ ማትያስ “የተከበበ፤
የተዘጋበት ሕዝባችን” እያሉ አባ የሚናገሩለት ሕዝብ የችግሩና የከበባውና የመዘጋቱ ምንጭ ቅድሚያ ከሕዝቡ ይልቅ ለራሳቸው ተዋጊዎች
ቅድሚያ በመስጠት ሕዝቡ ችግር ውስጥ እንዲገባ ሃላፊነቱ መውሰድ ያለባቸው እራሳቸው የትግራይ ብሔረተኛ መሪዎቻቸው እንደሆኑ ዓለም
ምግብ ተራድኦ የኢትዮጵያ ወኪል ዲሬከተር የተመለከተውና የገጠመው አስቸጋሪ ሁኔታ በመጽሐፍ መልክ ሰፊ ዘገባ ማቅረቡን አባ ማትያስ
እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ።
በመቀጠል ወደ ሌሎቹ የአባ ማትያስ
ንግግር ልቀጥል
እንዲህ ያሉትን እንመለክት
<<………
ያንን የአባ ማትያስ ንግግር አንድ
ባንድ በሚቀጥለው ክፍል ሁለት ከመተንተኔ በፊት አባ ማትያስ ትግራይ ውስጥ በታሪክና በዓለም ምድር ተፈጽሞ የማያወቅ ድርጊት ሲሉ
የሚከተለው ድርጊት ጭምር ይሆን?
<< በበርካታ ካምፖች
የትግራይ እናቶች ሠራዊቱ ሲታፈን (ጥቅምት 24 ማለት ነው) ፈንድሻ እየበተኑ ቄጤማ እየነሰነሱ፤ከበሮ እየመቱ የሠራዊቱን አስከሬን
እምቧለሌ እየዞሩ ጨፍረውበታል፡ ገድላችሁ ደማቸውን አሳዩን እያሉ የእናት አንጀት የሌላቸው እናቶች ደግሞ ወጠቱን አነሳስተው ሠራዊቱን
አስጨፈጭፈዋል፡…….. ገርሁ ሥርናይ ከተማ ፈደግሞ እጅ በሰጡ ሴት ጓዲቶች ላይ የተሰራው ግፍ ሕሊና ያቆሰለ እጅ ከሰጡት ሴት ወታደሮችን
ልበሳቸውን አስወለቁ። በብልታቸው እንጨት እየከተቱ
አሰቃዩዋቸው። ስቃዩን መቋቋም ሲያቅታቸው ለመንፈራገጥ ሲሞክሩ ፀጉራቸውን ይዘው መንገድ ለመንገድ ላይ ጎተቷቸው። ይህ
አልበቃቸው ሲል ራቁታቸውን እንደሆኑ የከተማው ሕዝብ እያያቸው እንዲሮጡ አደረጉ። ይህን የሚያደርጉት ከበሮ ይዘው እየጨፈሩና ራቁታቸውን
የሆኑ ሴቶችን ፎቶ እያነሱ ቪዲዮ እየቀረጹ ነው።>> የተከዳው የሰሜን ዕዝ ደራሲ ከታፈኑት ወታደሮች ውስጥ የነበረው ጋሻዬ
ጤናው (ቻቻው)
የአባ ማትያስ ንግግር አንድ ባንድ
ለመተንተን
በክፍል 2 ይቀጥላል።……….
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ
መልኽቲ ብፁእ ወቅዱስ ኣቡነ ማትያስ ኣብ ስርዓት ቐብሪ ብፁእ ኣቡነ ዮሐንስ ዳግማዊ ተረኺቦም ዘሕለፍዎ መልእኽቲ / ካብ መቐለ