Sunday, April 4, 2010

ይድረስ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ይድረስ ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከጌታቸዉ ረዳ ሳንሆዘ - አሜሪካ www.Ethiopiansemay.blogspot.com ካዲስ አበባ አድዋ ድረስ በመጓዝ መሠረታቸዉ ትግራይ ክፍለ ሃገር ያደረጉ የቀድሞ የወያነ ትግራይ አመራር አባላት የነበሩ “አገር የመገንጠል፤አገር የማፈራረስ መርሆ በብዙ ዜጎች የተወገዘዉ “ሞግዚት ላጣችዉ አገር የተመረጠዉ የመግደያዋን መርዝ የያዘዉ ብልቃጥ”-አንቀጽ 39ኙን የድሮ ፖሊሲያቸዉን ዛሬም እዉን እንዲሆን ያሰፈሩ”-እነ ገብሩ አስራትና አረጋሽ የሚመሩት “ዓረና ትግራይ” የተባለዉ ድርጅት የጠራዉ ስብሰባ በዓድዋ ከተማ የታዘብከዉን ሕዝባዊ ስብሰባ ስትዘግብ በእግረመንገድህ ከዓረና አመራር አባል አረጋሽ አዳነ ጋር ያደረግከዉን ቃለ መጠይቅ (?)በዛዉ አያይዘህ መጠነኛ የአረጋሽ ሕይወት ታሪክ የዘገብከዉን ለኛ ዉጭ አገር ለምንገኝ ኢትዮጵአዊያን አንባቢዎች በእንግሊዝ ቋንቋ የተዘገበ ዘገባህን በየድረገጾች ተለጥፎ አነበብኩት።መልስም የሚያስፈልገዉ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አረጋዊ በርሄ ባለፈዉ ሰሞን እዚህ ሳንሆዜ ከተማ እኔ ጋር ቆይታ አድረጎ ነበር። በግል ከተወያየንባቸዉ ጉዳዬች ዉስጥ አንደኛዉ የእነዚያ ማለትም የእነ ገብሩ አስራት፤ስየ ባጠቃላይ ከመለስ ዜናዊ የተለየዉ ቡድንን አስመልክቶ በራሴ ፍላጎት አንድ ስምምነት ደርሼ ነበር። መለስን እየተቃወሙ ስላሉት በትግሉ ወቅት አንተን ለማገዝ አንድ ጠጠር ላቀብልህ ሲሉህ እሺ ማለቱ ተገቢ ነዉ በሚል ተረዳድተን “በነሱ ላይ ትችቴን ለማለስለስ ቃል ገብቼ ነበር”። ያ ቃል ግን ሳከብር እንሱ ደግሞ መስመራቸዉን እየለቀቁ “ስልጣን አላባለገኝም እያሉ መዋሸታቸዉን ከቀጠሉ፤በሥልጣን አልባለግኩም፤ሕዝብን አልበደልኩም” እስካላሉ ድረስ እና “የነሱ ደጋፊዎችም” (የትግራይ ተወላጆቸ ያልሆኑትንም ጭምር) ያ ሁሉ መዓት ያመጡብን የወያኔ ቱባዎች ወደ መላእክትነት እና ወደ ልዕልት ጣይቱነት የመለወጡና የማምለኩ አባዜያቸዉ ከተዉ ብቻ ነበር ቃሌን የገባሁት። አለመታደል ሆኖ፤አትረፍ ብሎኝ፤- ልክ እንደፈራሁት ዛሬም አምላኪዎቻቸዉ” አረጋሽ፤ ስየንና ገብሩን እንዲሁም በትግራይ የወያኔ ታሳሪ አዛዉንቶችና ወጣት ገበሬዎች “ገሃነብ”በመባል የሚጠራዉ ነብሰገዳዩን “አዉዓሎም”ን ወደ ጣይቱነት እና ማርያምነት”ወደ “ነፃ አዉጪነትና ክርስቶስነት” የመለወጡ ዝበዝንኬ እየሞነጫጨሩ ትግራይ ዉስጥ ከሌሎች ብሄሮች የተወለዱም ሆነ ከትግራይ ክፍለሃገር የተወለዱ የትግራይ ተወላጆች ትግራይ ዉስጥ የመታገያ ጽ/ቤት ከፍተዉ ወያኔ ትገራይን የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሌሉ ቆጥረዉ “የተሸነፍንበት ትግራይን”-ልብ ማሸነፍና ነፃ ማዉጣት የሚችሉ እነ ሥየ እነ አዉዓሎም ወልዱ እነ አረጋሽ እነ ገብሩ ካልሆኑ ሌላዉ ከቶ “ዘበት” “ከንቱ ኡቱ” ነዉ በማለት የሕዘቡን እና የነገብሩ አሥራት የነ አረጋሽ የሻከረ ግንኙነት ምን ያህል ሸካራ እንደሆነ “እሚንት” እዉቀት ሌላቸዉ ዉጭ አገር የሚኖሩ ትግራይን ሕብረተሰብ ባሕሪ እያደናገሩ የሚነግሩን (የዓድዋ ሕዝብ ከመለስ ይልቅ እነ አረጋሽን ይመርጣል እዉነታና መሠረት የሌለዉ እምነት) ያሁኑ ሁኔታ ጥለቀት ያለዉ መረጃ የሌላቸዉ በስሜት የሚጋልቡ የትግራይ ተወላጆችም ሆኑ ያልሆኑ ተቃዋሚዎች፡ “ዓረና ትግራይን”-በቅዱሳን መላእክት የሚመራ የተከበረ ቅዱስ ድርጅት አስመስለዉ የሚሰብኩን ሰዎች ራሳቸዉን አደንቁረዉ ዛሬም እናኑንና ሌላዉን አንባቢ እያደነቆሩን ስለሆነ “አንዴ- ኢሳያስ አፈወርቂን እንደ የኢትዬጵያ ነፃ አዉጪ” ሌላ ጊዜ ደግሞ “እነ አረጋሽ” ሌላኛዋ “የዓድዋ ልዕልት ጣይቱ ቡጥል” እያሉ የመዋዠቁ/myth በሽታቸዉ ሰሞኑን እያዋዠቃቸዉ ስለሆነ፤- ለስለስ ልል የወሰንኩትን ዉሳኔ በማንሳት “የልሆኑትን ስዕል” ሊያሳዩን የሚጥሩትን ትክክል እንዳልሆነ መናገሬን/መጻፌን እንሆ ለመቀጠል ወስኛለሁና አድምጡኝ እነሆ። ለዚህ ትችቴን መነሻ ሌሎች ጻህፍት ቢሆኑም ጋዜጠኛዉ እስክንድር ነጋ ስለ ዓድዋዉ የአረጋሽ ቃለመጠይቅ እና ዘገባዉ ለትችቴ እንደምክንያት ልጠቀምበት። አድርጌአለሁ። በቅርብ ወራት በሌሎች ጉዳዬች ደጋገምህ የተቸህባቸዉ ጽሁፎችህን ወደ ጎን ተወት አድርጌ በዚህ ዓድዋ ሄደህ በዘገብክበት ላትኩር። ወንድሜ እስክንድር ጎበዝ ጋዜጠኛ ነህ። ባለቤትህም እንዲሁ። ሆኖም ይሄ የብዕር ጉብዝናህ ዓድዋ ላይ አረጋሽ ጋር ሲደርስ ለስልሷል የሚል እምነት አለኝ?እስኪ በዚህ የአረጋሽ የሕይወት ታሪኳን በመጠኑም ቢሆን ስትገልጽልህ አያይዛ የተናገረቺዉ ቃል አንተ “መለስ ዜናዊ ምን ዓይነት ሰዉ ነዉ?” ብለህ ለጠየቅካት በመለሰቺልህ መለስ ልጀምር። "He leads the EPRDF, and the EPRDF insists on winning all the time, no matter what. What the people want seems to have no relevance." ኢህአዴግ እሳ ስልጣን ይወዳል? ብለህ ለጠየቅካት ደግሞ እንዲህ ብላለች “All this clamor is for power. What else could it be for? But why should voters in Adwa choose you over Meles, I ask her. And suddenly her face relaxes, a woman spoke to me from the heart: “Because people know what I have been through, what I have given up for the truth. They know that power had not corrupted me. These are the values that appeal to people. They have seen that too many have succumbed to the trapping of power, and they are disgusted by it. I could defeat him given a playing field. And though my party is seriously underfunded and is allotted a very limited time on state media, we shall prod to the end. We had overcome the impossible before. And we could very well do it once again.” There is nothing wrong with seeking power as long as it’s sought to serve a higher cause, as long as it’s people centered. But it’s a problem when it becomes an end by itself, and I fear that is where the EPRDF is. That is why we are having all these problems.” ቀጥሎም- “እኮ የዓድዋ መራጮቺሽ ከመለስ ይልቅ አንቺን ለምን መምረጥ አለባቸዉ?” ( But why should voters in Adwa choose you over Meles, I ask her. And suddenly her face relaxes, a woman spoke to me from the heart፡) ብለህ ለጠየቅካት አከታትላ ስትመልስ፦ “Because people know what I have been through, what I have given up for the truth. They know that power had not corrupted me. These are the values that appeal to people. They have seen that too many have succumbed to the trapping of power, and they are disgusted by it. I could defeat him given a playing field. And though my party is seriously under funded and is allotted a very limited time on state media, we shall prod to the end. We had overcome the impossible before. And we could very well do it once again.” ነበር ያለቺዉ። ትርጉሙን ወደ አማርኛ ስመልስ እንዳላበላሸዉ አንተዉ እንዳስቀመጥከዉ እንደወረደ ላኑሮዉና አንተ እንደጋዜጠኛ እና እዉነትን ቆፍሮ የማዉጣት ሃላፊነት እንዳለብህ ሁሉ አንድ ተወዳዳሪ ለዉድድር ለስልጣን ሲወዳደር የሕይወት ታሪኩን መጠየቅ ላልቀረ የሷን በጎ የሕይወት ታሪክ ለማቅርብ ስትፈልግ ለምን እሷ የሰራቺዉን ሕዝባዊ በደል እና የስልጣን ብልሽት በስልጣን በነበረችበት ወቅት ያደረገቺዉ ብልሺዉ ተግባር ቢኖር ወይንም ማድረግ ያልነበረባትን በፀፀት መልክ የምታስታዉሰዉ ካላት አልጠየቅካትም? ከቃለ መጠይቋ የተማርነዉ “የዓብዬት” አባል እንደነበረች እና የመጀመርያዋ ባችለር ዲግሪ የያዘች የህወሓት የሴት ታጋይ መኖርዋን ነበር ያስተማርከን (የዘገብክልን) እንጂ አንተ እንደምትለዉ “ከልቧ” የገለጸቺዉ የምትለዉ ነገር ምን እንደሆነ አልገባኝም። የምሯን ነበር የተናገረቺዉ ስትል ምን ማለት ይሆን? አረጋሽ አዳነን የሚያክል የወያኔ ፈላጭ ቆራጭ የወያኔ ያመራር አባል እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን ከልቧ እንድትናዘዝ የነበረባትን ጥያቄ እንደ አንድ ጋዜጠኛ ያዉም “አዉነት ታፈነች’ ብሎ ለብዙ ዓመታት የጻፈ እና የታሰረ ጋዜጠኛ፤ የዓድዋ ሕዝብ ከመለስ ዜናዊ ይልቅ አንቺን ለምን መምረጥ እንዳለበትና ታሪካቺሁ በምን ይለያል ብለህ ስትጠይቃት “ሕዝቡ በእንዴት ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለፍኩ ይገነዘበዋል፤ለእዉነት ስል ምን እንደከፈልኩ ያዉቃል፤ሥልጣን እንዳላበላሸኝም ያወቃል፤…” ስትልህ ከላይ የጠቀስኩት ጥያቄ መልሰህ መጠየቅ ነበረብህ። ሥልጣን አላበላሸኝም ስትል በማን እያሾፈች ይሆን? በዓድዋ ኗሪዎች በነ ብርሃነ ገብረሕይወት በ እነ ሃለቃ ሐጎስ….እና በቅርቡ ለምታዉቀዉና መንበረ ሥልጣንዋ አድርጋዉ የነበረቺዉን ከተማ ለመቀሌ ኗሪ እየነገረቺዉ እንዳልሆነ ግን በግልጽ በድፍረት በመረጃ ልነግርህ እችላለሁ (አረጋሽንና ገብሩን የማያዉቅ አዲስ 1000 ወጣት እና የተባረሩት ዘመድ አዝማድ ወዳጅ ዘመድ አዳራሽ ሰብስባ/ሰብስቦ ማስጨብጨቡን ለጊዜዉ ተወት አድረገን ማለቴ ነዉ) ። ጊዜዉ “አፋችሁን ያዙ” እያለ ስላስቸገረን እና በዚህ ዉጭ አገር የሚኖሩ ዜጎቻችን ቁጥጥር የሚካሄዱ በርካታ የሚዲያ ባለቤቶች “እንዚህን ሰዎች ስንጠይቅ፤ስንወቅስ’ “እጅግ ኩፉኛ” ስለሚረበሹ እና ከተወቃሾቹ ይልቅ ባለሚዲያዎቹ “ኩፉኛ ስለሚታመሙላቸዉ” የምንጽፈዉ ሁሉ ለሕዝብ እንዳይዳረስ የኛንም ድምፅ እንዳይሰራጭ እያፈኑ በመቸገራቺን ካልሆነ በስተቀር፤ (አሁንም ይህንን ላንተ መልስ የምልከዉ እንዳይሰራጭ “ካላፈኑት” በስተቀር)- አረጋሽ አዳነ የሰራቺዉ የስልጣን ብልሹነት በርካታ ሲሆን የገብሩ ቢሮክራሲ ዋና ሥራ አፈጻሚ በነበረችበት ወቅት ሥልጣንዋን መከታ በማድረግ የተጠቀመችበት መቀሌ ከተማ ስትኖርበት ከነበረ የናጠጠ መኖርያ ቪላዋ (የአታኽልቲ ሃይለ ጓንጉል ቤት) ጀምሮ፤ እስከ መቁጠር በሚያዳግት የመቀሌ ህዝብ እሮሮ እና እንዲሁም አምባገነናዊ ባሕሪዋ የሚገልጽ አዲስ አበባ ዉስጥ በወዳጄ በትግራዩ ተወላጅ የኢጦብ መጽሄት ከፍተኛ ዘጋቢ (ለደህንነት ሲባል ስሙን አልጠቅስም) የሰራቺዉን ክፉ ሥራ እንደተዘገበ የምታስታዉሰዉ ነዉ። ያ ዘገባ እኔም ያንኑ ደግሜ በራሴ “ኢትዬጵያን ሰማይ ዌብ-ላግ” ዘግቤዋለሁ። እዚህም በጥቂቱ እጠቅሰዋለሁ። ታዲያ አረጋሽ እኔን ሥልጣን ኣባልጎኝ እና አምሮኝ አያዉቅም ስትል፤ አንተ ያን እያወቅክ ለምን ከረር ያለ ጥያቄ ማስተናገድ አስቸገረህ? ለሥልጣን የሚወዳደር ሰዉ፤የግለሰቡ ታሪክ ከነ ወንጀሉ ከነጥሩ ምግባሩ ለሕዝብ እንዲብራራ ሚዲያዎች (አንተን ጨምሮ) ለሕዝብ ካልገለጹ የሚዲያ ቁምነገርነቱ ምኑ ላይ ነዉ? ያ ወንጀላቸዉ ሗላ እንጋገርበታለን ፤ሗላ እንጠይቃቸዋለን የሚባል ብሂል የመጣዉ/የተስፋፋዉ’የሚበረታታዉ’ ከነሱ “ሥልጣን ካባላጋቸዉ” የሕዝብንና የሃገርን ብሔራዊ ክብር አሳልፈዉ ከሰጡ ክፍሎች መሆኑ ለምን ማወቅ ተሳናችሁ? ተወዳደወሪ ማለት ምን ማለት ነዉ? አንድ ተፎካካሪ የሕዝብ መብት መንካቱን፤የሃገር ክብር ለጠላት አሳልፎ የሰጠ፤የገደለ፤ያጭበረበረ፤ያመጸ፤ለባዕድ ያደረ የዉጭ አገር የምስጢር አገልጋይ ቅጥረኛ /ሰላይ ከሆነ በየትኛዉ አገር ሕግ በየትኛዉ ሃይማኖታዊም ሆነ ማሕበራዊ ሞራል ሥልጣን ተመልሶ እንዲይዝ ይፈቀዳል? ያዉም በምርጫ ጊዜ ለዉድድር ሲመጣ ወንጀሉ ለሕዝብ በዝርዝር ያልገለፀ! ምን ጉደኛ ዘመን ነዉ ደረስነዉ? አንቺ ከመለስ በምን ትሻልያለሽ? ስትላት ፤የመለሰቺዉ መልስ በሽኩቻዉ ወቅት “ስልጣንዋ በመለስ ዜናዊ ትዛዝ መነጠቁን/በእርሷ አገላለጽ አርስዋ ሥልጣኗ በገዛ ራሷ እንደተወቺዉ አስመስላ የሰጠቺዉ አንስቶ የታየዉ የሁለቱ ቡድኖች በሥልጣን አያያዝ ያስተዳደር ዘቤ ልዩነት እንደነበር አስመስላ ለማቅረብ የዳዳትን ” እንጂ መሰረተ ልዩነታቸዉ ከጥንት በወንጀልም፤በድርጊትም በስልጣን መባለግም ያላቸዉ ልዩነት አንድ ባንድ ዘርዝራ አላቀረበቺም። ያድዋ ህዝብ ሲመርጣት አካቢዉ ተወላጆች ገበሬዎች እና ሠራተኞች አልበደልኩም መለስ ብቻ ነዉ ማለት እንዴት ያምርባታል? ታዲያ ንፀህ መሆንዋን፤ከመለስ መሻልዋን በምን ይለያል? እኔን እስካሁን ድረስ የተቃዋሚዎች ጉዳይ የሚገርመኝ ወያኔ ጋር እየተወዳደሩ ያሉት ተቃዋሚዎች በወያኔ ብቻ እንጂ አርስ በርሳቸዉም እኮ ያደረጉት ወንጀል፤የሥልጣን መባለግ፤ ታሪካቸዉ እንዲወያዩ አይፈቀድም ወይንም አያደርጉም? ለምን? ይህ ካላደረጉ የፖለቲካ ተፎካካሪ መሪዎች ባሕሪ እን ገበና በሚጠቀሙባቸዉ ሚዲያዎች ራሳቸዉን ማስተዋወቅ እና ለሕዝብ ማንነታቸዉን ገልጸዉ ማስተዋወቅ ካልቻሉ እንደናንተዉ ዓይነቱ አንጋፋ ጋዜጠኞች ጣልቃ ገብቶ የሕዝብን ጉዳይ እና የነሱንም የታሪክ ጅረት ካላስተዋወቀ መራጩ ሕዝብ ተወዳዳሪዎች ጠናማነታቸዉ በጎነታቸዉ እና ብልሕነታቸዉ በምን ይለያቸዋል? ምኑ ላይ ነዉ ስለ ተፎካካሪዉ ማንነት ዘገብን የምትሉት? እኔኑን የገረመኝ ከዓረና መሪዎች አንዱ አንተ እንደጠቀስከዉ ኤርትራ ነፃ (?) ከወጣች በሗላ የኤርትራ የመጀመርያዉ አምባሳደር ትኩዕ ወልዱ (የሜዳ ስሙ አዉዓሎም ወልዱ) የመጀመርያዉና የመጨረሻዉ አምባሰደር ብለህ ስትል “የመጀመርያዉና የመጨረሻዉ” አምባሳደር ብቻ ሳይሆን በቀዳሚ ሥፍራ “ግሃነም” ተብሎ በሽሬ እና በሌሎቹ አዉራጃዎች የሚታወቀዉ “ነብሰገዳይ” እና አዛዉንት ወላጆቻችን ‘በእሳት እያቃጠለ፤በጭስ እየታፈኑ” ሲወስኑ ከነበሩ “ገዳይ ኮሚቴዎች” አንዱ እና “አዛዉንቶች በእንቅልፋቸዉ ከተኙበት ዳስ ዉስጥ በጥይት ሲገደሉ“ ቅር የማይለዉ “ክፉ- ጋኔል” እንደነበረም በግረ መንገዴ በዘገባህ ላይ ልጨምርልህ እወዳለሁ (ልጨምርልህ ልበል እንጂ ላስተምርህ ብል ጋዜጠኛ ነህና አያምርብኝም)። “ስትላቸዉ የነበረቺዉን ቃላቶች የምሯን ነበር ” እያልክ የምትለን የአረጋሽ የህወሓት የሕይወት ታሪክ እና የዓረናዉ ምክትል የነበረዉ አሁን በብርሃነ የተተካዉ ዛሬም የድርጅቱ/የዓረና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በሁለቱ ላይ የተዘገበ የወንጀል ዘገባ እና የገብሩ አስራት ማንነትም አብሮ የተያያዘ ለሰለባዎች ያለዉ ንቀት ለናሙና ላቅርብ እና በአክብሮት ልለይ። ሆኖም ለዛሬ ባረጋሽ ላይ እና በገብሩ ላትኩርና የአዉዓሎምን በይደር ለሌላ ቀጠሮ አስተላልፈን ከዚህ ቀጥሎ ያለዉን እንድታነብልኝ ስጋብዝህ እስከዚያዉ ሰላሙን እመኝልሃለሁ። አረጋሽ አዳነ፦ ዲያቆን ብርሃነ ገብረህይወት፤- “….ቤቴ እንደደረስኩ በረቱን ከፍቼ ለበሬዎቹ ድርቆሽ ልሰጣቸዉ ስል….የ.ማላዉቃቸዉ ሰወች ስላቸዉ አንዱ እያናገረኝ ሌላኛዉ በሰባት ጥይት መታኝ። በሆዴ እና በአንጀቴ ላይ ደሙ እየተንዠቀዠቀ ሲፈስ እናቴ እንዳታይና እንዳትጮህ ውስጥ ግቢ!ግቢ!ግቢ! አሏት። ከዚያ በሗላ <እግሬና እጄን አንጠልጥለዉ ጎትተዉ ጫካ ዉስጥ ጣሉኝ>። አንጀቴ ተበጥሷል። እንጀቴ ይታያል፡ቅጠላቅጠል አልብሰዉኝ ተሰወሩ።ይህ ሁሉ ሲሆን ከሩቅ ይከታተሉ የነበሩ የአካባቢዉ ሰዎች እነማን እነደሆኑ አይተዋል። ስንት ነበሩ? ብርሃነ፦ ወደ 10 ይሆናሉ። ሕዝቡ ተከትሏቸዉ፤ << እነማን ናችሁ? ቁሙ! ነፍስ አጥፍታችሁ አትሄዱም>> ሲላቸዉ “እየሳቁ” ሄዱ ። በመጨረሻ ከወደቅኩበት አንስተዉ በሰልፍ ተሸክመዉኝ ዓድዋ አዉራጃ አሰተዳደር ወሰዱኝ።<<የዛሬ ብርሃነ ዕድል ነገ ለኛ ነዉ። ይሄ ልጅ ምን አጠፍቶ ነዉ በወጣትነቱ የተቀጠፈዉ?>> ብሎ ሕዝቡ አቤቱታ አቀረበ። በዚህ ወቅት ሕዝቡ ሞቷል ብሎ ስላመነ ጉድጓዴ ሳይቀር ተቆፍሮ ነበር። ጫካ ወስደዉ እንደጣሉኝ የተነገረኝም በሗላ ነዉ። ሕዝቡ አሰከረኔን ተሸክሞ <<ደርግን ግፈኛ ትላላችሁ እንጂ ይሄዉና የናንተም ግፍ!>> ሲሏቸዉ 15 ወጣቶች በሲሚንቶ የተሰራ የጣሊያን ጉድጓድ ዉስጥ አስገብተዉ አሰሯቸዉ። በአጠቃላይ ሕዝቡ 500 (አምስት መቶ) ይሆን ነበር። ወጣቶቹን ካሰሩ በሗላ ህዝቡን በዱላ በታተኑት። እኔንም የሚያዉቁኝ ሰዎች ወደ አክሱም አመጡኝ በአጋጣሚ ነጮች ነበሩ ኦፕራሲዮን ያደረጉልኝ። የት ነዉ ኦፕራሲዮን ያደረጉልህ? ብርሃነ፦ አክሱም ሆስፒታል። ሁለት ሰዎች ደም ሰጡኝ። ደም ጨርሼ ነበር። ይሄን ሲነግሩኝ እንጂ እኔ አላዉቅም። ለ3 ወር ያህል ሕይወቴን አላዉቅም ነበር። የተኛሁበት የጀርባየ ጠባሳ አሁንም አለ። ሕይወቴ መቆጣጠር ስላልቻልኩ መቀሌ ታከምኩ። እዚያም ስላልቻሉ አዲስ አበባ ጥቁር አምበሳ መጣሁ። ጥቁር አምበሳ የመጣኸዉ መቸ ነዉ? ብርሃ፦ በ1984 ዓ.ም ሚያዚያ 4 ቀን አዲስ አበባ መጣሁኝ። ጥቁር አምበሳ ሆስፒታልም አስከ መጨረሻ ጥረት አደረጉልኝ። ሕይወቴን ለማዳን በህክምና ብቻ ሳይሆን በተለያየ መልኩ ሲረዱኝ ቆይቶ መጨረሻ ሲያቅተዉ በ1986 ሰኔ 16 ዉጪ ድረስ ሄጄ እንድታከም ወስኖ አሰናበተኝ። ከዚያ በሗላ አማራጭ አጣሁኝ። ቀኑ ጨለመብኝ። ከጥቁር አምበሳ ስትወጣ ወዴት ሄድክ? አዲስ አበባ ቤተሰብ አለህ? ብረሃነ፦ የለኝም። ታዲያ የት አረፍክ? ብርሃነ፦ እዚሁ ሆስፒታል ኮሪደር ላይ ነበር የምተኛዉ ። ከተሰናበትክ በሗላ? ብርሃነ፦ አዎ። ከዚያ ወደ ትግራይ ሄድኩ ። የማላዉቃቸዉ ሰዎች አዋጥተዉ ቲኬት ቆረጡልኝ ። ትግራይ ከሄድኩ በሗላ ከብዙ ደጅ ጥናት በሗላ የክልሉ መንግሥት ጸሃፊት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነን አነጋገርኳት። <ምን ሆንክ> አለችኝ። <በጥይት ተመትቼ> <ማን መታህ?> <የህወሓት አባላት><እንዴ! ምን ብለዉ ይመትሗል? ክሰሳቸዉ።> <ምን ብየ እከሳቸዋለሁ? ታዉቁት የለም እንዴ ራሳችሁ። እንደ ብርሃነ አንዳትሆኑ እያላችሁ መድረክ ላይ ስበሰባ ላይ ትናገሩ አልነበረም አንዴ? ከ500 ህዝብ በላይ አቤቱታ ለማቅረብ ሲቀርብ በዱላ አላባበረራችሁትም? ወንጀለኛ ከሆንኩኝ ግደሉኝ፤ካልሆንኩ ግን አሳክሙኝ። አናዉቅም የምትሉኝ ከሆነ ደግሞ ስንብት ወረቀት ስጡኝና የትም ሃገር አቤት ልበል>> ስላት፡<የለም ምንግሥት አይመታህም> አለችኝ።<መንግሥቱ ሃይለማርያም አሰቃይቶ የገደለዉ ሰዉ የለም። የእርሱ ወታደሮች ግን ሰዉ ገድለዋል።የህወሐት ወታደሮችም እንደቅጠል ነዉ የቀጠፉን፤የገረፉን።ዕድሜ ልካችንን ሲያሰቃዩን ነዉ የከረሙት። ስለዚህ ለዉጥ የለዉም።ፍረድ ቤት በደርግ ጊዜ ነበረ አሁንም አለ። ያለዉ ፍርድ ቤት ነዉ እንጂ ማሕበራ የሕዝብ ፍርድ ቤት አይደለም።የመሰላችሁ ፍትህ ስጡኝ> ስላት፡ <ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠይቅ አለችኝ።> <ከ300 በላይ ግብረሰናይ ድርጅቶችን አነጋግሬ “መንግሥት ማንንም ሰዉ በግለሰብ ደረጃ እንዳትረዱ የሚል ማስጠንቀቅያ ሰጥቶናል” ብለዉኛል። ስለዚህ እኔ ከ60 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ስለማልበልጥ ብጠይቃቸዉም መልስ አጥቻለሁ።> ስላት<ይህንን ነገር እንዴት ልታወቅ ቻልክ?> <ይሄማ ግልጽ የሆነ እኮ ነዉ>ስላት <ይሄማ የፓለቲካ አዝማሚያ ነዉ> ብላ ወዲ ሻምበል የሚባለዉን የፖሊስ አዛዥ ጠራች ።አሱም መጣ።ሌሎችም ተከተሉ።ድምፅ እንኳ ወደማይሰማበት “አንደር-ግራዉንድ” አስገቡኝ። አንደር-ግራዉንዱ አዚያዉ ምክር ቤት ዉስጥ አካባቢ ነዉ ያለዉ? ብርሃነ፦ አዎ። ከ8፡00-1130 ድረስ ጎሮሮየ ደርቆ መናገር አስኪያቅተኝ ድረሰ በጥያቄ አፋጠጡቡኝ። የሚጠይቁህ ምን ነበረ? ብርሃነ፦ የደረሰብህ ነገር ተንትነህ በሙሉ ንገረን፤ያየሀዉ ነገር ሁሉ ተናገር፤ሙሉ መብት ሰጥተንሃል አሉኝ። እኔ በመጀመሪያ የቤተክህነት ተማሪ ነበርኩ።ወላጆቼ ቤተክርስትያንን እንድታገለግል ለቤተክርስትያን ሰጥተንሃል አሉኝ። እኔ በመጀመሪያ ደረጃ የቤተ ክህነት ድቁናየ ስቀበል ታጋይ ሐጎስ የሚባል የወረዳ አስተዳዳር “የድቁና የምስክር ወረቀቴን ቀደደዉ”።ቀጥለዉ ታገል ተባልኩ። እኔ አልታገልም ሰርቼ ነዉ የምበላዉ ስላቸዉ፡ “የለም መታገል አለብህ ” አሉኝ። መጨረሻ ወጣቱን በታኝ ነህ! አሳዳሚ ነህ!> አሉኝ።የበተንኩት ሰዉ የለም።ብርሃነ እንዳትታገል ብሎኛል የሚል ሰዉ ካለ አምጡት አልኳቸዉ።መጨረሻም ወጣቱን ማፈን ጀመሩ። ማፈን ማሳደድ ሲጀምሩ እኛም የምንገባበት ቦታ አጣን።ተረበሽን፤ የት እንሂድ? ገሚሶቹ ወጣቶች ወላጆቼ በእኔ ሰበብ ከሚሰቃዩ አኔ ልሙት እያለ ወደ ትግል ግምበር ሄዶ ሞቷል።እላዩ ላይ ሳር በቅሎበታል።የተቀረንም ሰዉነታችን በጥይት ተበሳስቷል።እሳት ጨብጦ፤ፈንጅ ረግጦ ለስልጣን ያደረሳችሁ ወጣት በየፌርማታዉ ወድቋል፡ግማሶቻችንም ጠፍተናል። ለምሳሌ ያህል ይግዛዉ ጣሰዉ - ከማይጓጓ ፍቱሕ ገ/ሕይወት - ከማይዳዕሮ አለቃ ሐጎስ- ከማይደዕሮ ገ/እግዚአብሔር= ከደዕሮ ሸዊቶ ዓለምሰገድ ይግዛዉ -ከዳዕሮሸዊቶ አረፋይኔ ከገረዓ፤ አበበ ገብረአብ - ከገረዓ ሲጠቀሱ ከነዚሁ አንዱ አኔ ነኝ። እነዚህ የተገደሉ ናቸዉ? ብርሃነ፦ ታፈነዉ ተወስደዉ የጠፉ፤አድራሻቸዉ የጠፋ ናቸዉ።……” በማለት አረጋሽ አዳነ ትግራይ መቀሌ በሥልጣን ላይ በነበረችበት ወቅት በዚህ ምስኪን ዲያቆን ያደረሰችበትን ግፍ ባጭሩ ገልጿል። በይበልጥ ለመረዳት በኔዉ ድረገጽ መጎብኘት ይቻላል በወርሃ መስከረም 1998 አርካኢቭ (ትግርኛዉና አማርኛዉ ሙሉዉን ለማንበብ)። ታዲያ አረጋሽ ዓዳነ የምትወዳደርበት አዉራጃ ዓድዋ የዲያቆን ብርሃነ ገብረሕይወት ፤ይግዛዉ ጣሰዉ፤ሃለቃ ይህደጎ ወዘተ…የመሳሰሉት የወያኔ ሰለባዎች መንደር ያለወቁ ሰዎች አረጋሽ እና እነ ገብሩ ካልሆነ ከቶ በምንም ታምር ሌላ ኢትዬጵያዊ ነፃ ዉድድር ቢፈቀድ የትግራይን ልብ የሚያሸንፍ የለም ብሎ ማለት አንድም ያካባቢዉ ታሪክ እና የወያኔ ባለሥልጣናት (እነ አረጋሽና ገብሩ..ስየን …ጨምሮ) ከሕዝብዩ ጋር ያላቸዉ ግንኙነትና የሻከረ ልብ አለማወቅ ነዉ ፤ወይንም ተስፋ በመቁረጥ ካለ እንሱ ሌላ ነፃ አዉጪ ሊኖር ሉፈጠር አይችልም ከሚል “ሰነፍ” አምነት የመነጨ ነዉ ማለት ይቻላል። ታዲያ እንዴት ሲኮን ነዉ የነገብሩ እና የነ አረጋሽ የነመለስ ዜናዊ የሺዎቹ ሰላባዎች እምባ ጠባቂ ከሌላ ክፍለሃገር የተወለደ ኢትዮጵያዊ ተወዳድሮ ገራፊዎቹና በሥልጣን የባለጉ “ልቅ - የእንግዴ ልጆችን”ማሸነፍ የማይችልበት ምክንያት? አቶ እስክንድር ነጋ- የ “መ ኢ አ ድ” የመቀሌ፤ያዲግራት ሕዝባዊ ስብሰባ እና እሮሮስ ለምን መቀሌ ድረስ አልዘገብክም? መሰሉ ረዳ የትግራይን ሕዝብ ቀልብ መሳብ የምትችልብት አጀንዳ የላትም ብሎ ያለ ማን ነዉ? ወይስ እስከ መገንጠል ፖሊሲ በድርጅቷ እና ስብከቷ ስላላስተጋባች? መሰሉ ልክ እንደ አረጋሽ የትግራይ ተወላጅ አይደለችም ወይ? እነ ብረቱካን ወደ አምላክነት ወደ ጣይቱ ቡጡልነት መለወጥ እና ማምለክ ከተጀመረ ምነዋ መሰሉ ጣይቱ ብጡል መሆን አትችልም ያለ ማን ነዉ? በእዉቀትም በሀገራዊነትም በምን እና በምን ከመሰሉ ጋር አረጋሽን ጎልታ ልትታይ ትችላለች? ጋዜጠንነት ማለት ይሄ ነዉ? ካሁን በፊት የትግርኛዉ ቪ ኦ ኤ ዓረና ዓረና ዓረና እያለ ሲዘግብ “ምነዋ ሌላ ተቃዋሚ የለም ወይ ምነዉ መሰሉንስ ላንድ ውቅት እንኳ አታስታዉሷትም ወይ ብየ ለትግርኛዉ ፕሮግራም የጻፍኩትን እሮሮ ለሕዝብ ካነበቡት በሗላ አንዴ ለቃለ መጠይቅ ዕደል ሰጥተዋት ያዉም ሙሉዉን ዘገባ ሳይሆን ጨረፍታዉን አቀረቡልን። አሁንም አስክንድረ ዓድዋ ድረስ ስትሄድ መሰሉ የምትኖርበትን ከተማ መቀሌን ጥሰህ አረጋሽ ከምትወዳደርብተ አዉራጃ ድረስ ተከትለህ ሰፊ ቃለ መጠይቅዋን ስትጋብዘን የማአድዋንም የ ኢዲዩዎችንም እና የሌሎችን ግን ድሮም ዛሬም ልብ አላልከዉም። ጋዜጠኞች ሆይ ከሚሞቀዉ ጋር እየጋላችሁ ከሚያብጡት ጋር እያበጣችሁ፤ ሲቀዘቅዙ እየቀዘቀዛችሁ ሲተነፍሱ እየተነፈሳችሁ ነዉና፤ አምላክ በጥበቡ እናንተንም ተቃዋሚዎችንም ብሩህ ሕሊና የስታችሁ ከማለት ምን ማለት ይቻላል። በቸር ሰንብት።ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com