Saturday, June 2, 2018

አይበገሬው ሃይሉ ያንተን አቀባበል ያላየ በሻዕቢያ አፈቀላጤዎች አቀባበል ይደነቃል! ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


አይበገሬው ሃይሉ ያንተን አቀባበል ያላየ በሻዕቢያ አፈቀላጤዎች አቀባበል ይደነቃል!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ሃይሉ! እንጂኔር ሃይሉ~! ሃይሉ! ኢንጀኔር ሃይሉ!!! እንወድሃለን ኢንጂኔር ሃይሉ!! ነበር በሃይሉ ሻውል አቀባበል የሰማናቸው ትዝታዎች። ይህንን ቪዲዮ ተመለክቱልኝ።

Engineer Hailu Shawel arrival Part I


ሁለት ጉዳዮችን አነሳለሁ። አሁን ስላለው ወጣት እና ሌላው ስለ ኢንጂነር ሃይሉ ቅንጅት ትዝታ። እዚህ ላይ የለጠፍኩት ቪዲዮ ውስጥ እንድታዩት የምፈልገው ትዝታችሁን ወደ ላ ወስጄ አገር ወዳዶች ምን ያህል ኢንጂኔርን ይወድዋቸው እንደነበር ለማስታወስ ነው። በዚህ ቪዲዮ አብራችሁ ለማየት የምፈልገው የግንቦት 7 አባሎች የብልግና ባህሪ ከወያኔ ተከታዮች የማይሻል በጣም ቫየለንት/ስልጣኔ ያልቃኛቸው ሞገደኞች የሆኑት የያኔው የብርሃኑ እና የበርቱካን ተከታዮች (የዛሬ ግንቦት 7 ተከታዮች) (የራሳቸው ሰው አበበ በለውንም እንኳ አልማሩትም። ታሪኩን ታስታውሳላችሁ። ለምን ግንቦት7 ወደ ኤርትራ ሄደ ስላለ ብቻ አስፈራርተውት መኖራቸውን ታስታውሳላችሁ፤) የኢንጂኔር ደጋፊዎችን ለመልከፍ የብርሃኑ /ብርቱካን ደጋፊዎች አብራችሁ ባህሪያቸውን በዚህ ቪዲዮ ቃኝዋቸው።

በኦሮሚያዎቹ የአብርሃ ሊነከን ቡዱኖች ነጻ የወጡት ሁለት ሰዎች እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። 1ኘው) ራሱን  ማስፈታትም ሆነ ሌላውን ማስፈታት አቅም ያልነበረው ከእስር እንፍታህ ሲሉት እምቢ አገሪቱ ነፃ ካልወጣች እምቢ  አልፈታም ያላለ "ኢትዮጵያዊ ማንዴላ" ብለው አንዳንዶቹ የዲያስፖራ ምስኪኖች የሰየሙት አንዲ አንዳርጋቸው እና ፤

2) ሌሎቹ ደግሞ የአውሮጳ ብርድ በርዶናል ብለው ወደ 3/4ኘኛው ኦሮሚያ ብለው ‘እራሰቸው ከልለው ያጸደቋት የፈጠራ ክልል” መጥተው እንዲሞቁ የተፈቀደላቸው አዛውንቶቹ የኦነግ ሽማግሌዎች” እንኳን ደስ አላችሁ።


የኢትዮጵያ ወጣት ሲነጻጸር የብዙ አገሮች ወጣት በስሜት ማስጋለብ እንደ ከባዱ አስቸጋሪው የሜዳ ፈረስ ሲሆን ፤ በአፍሪካ ምድር እንደ ለማዳ የቤት ፈረስ በቀላሉ በሰሜት መጋለብ የሚቻል ወጣት ፈልጉ ቢባል ‘የጎሰኞች የፖለቲካ ጡት እየጠባ  ያደገ ኢትዮጵያ ወጣት ጥሩ ምሳሌ ነው።

ስሜት በጣም አደገኛ እሳት ነው። በስለሞቀህ አሁንም አሁንም ደጋግሞ እሳት ላይ መጫወት ራስን ይበላል።ስሜት የትራይባሊስቶች የጎሰኞች የፋሺስቶች መሳቢያ ጥሩ መሳሪያ ነው። ብዙ ምሁራኖች ‘የዛሬ ወጣት ብልህ ነው” ይላሉ።  ሲያልፍ አልነካው። 27 አመት በጎሰኞች ሲገዛ እራሱ ዝምታን ንም መሳሪያ ሆነ ቆይቷል። ከዚህ ወዲያ ምን የተበላሸ ብልህነት ማግኘት ይቻላል? ብዙ ወጠቶቻችን በስሜት ፖለቲካውን ሳይመረምሩ በተለያዩ ድርጅቶች ተጥደው እየተናጡ ናቸው። 

ዘፋኞች ቴዎድሮስን እና ምንልክን “ዲሞክራቶች እና ሰው ያልገደሉ በጽድቅ ላይ ጽድቅ የተጎናጸፉ” በማስመሰል ዮሃንስን ፤አሉላን ሃይለስላሴን “ጨፍጫፊዎች ኢ-ዲሞክራቶች” ናቸው ተብ ከምርጥ የጎሳቸው ነገሥታቶቻቸው ሚያገልል ዘፈን በማስሰማት ፡አሞናል በለው” የሚለውን (ትግሬን አግልለው) እያሉ እየጨመሩበት በየፌስ ቡኩ ሰምተናል። ጎሰኞች የትግራይን ህዝብ እና ከትግራይ የተወለዱት ነገሥታት እና ራሶችን “ትግሬዎች” በመሆናቸው ብቻ አናካሽ ዘፈን በመቅረጽ ሴራ ላይ ይገኛሉ። በጣም አደገኛ! እነኚህ በዘረኞች እና የዛሬ ፖለቲካቸው እንኳ በቅጡ ማሸነፍ ያቃታቸው ጮርቃዎች፤ በቪዲዮኣቸው የኛ የሚሉዋቸው ነገሥታት ብቻ ለይተው በክብር በመዘከር ሌሎቹ የኛ አይደሉም (ትግሬዎች ናቸው በሚል) በቪዲዮዎቻቸው ሰነዶች እንዳይታዩ ማእቀብ በመጣል፡ትኩስ የጎሳ ቅስቀሳ ሴራ እሸረቡ ናቸው። ያለ ትግሬ ምን  ይነት ኢትዮጵያ ሊቀርጹ እንደፈለጉ ቢነግሩን እጅግ ደስተኞች ነን (ለመስማት)!

እነዚህ ትግሬዎች ብቻ ስለሆኑ ማዕቀብ የተፈረደባቸው ነገሥታት ዛሬ ዘፋኞች ሆነው ማን ባቀናላቸው መሬት ላይ ሆነው እየፈነጩ እንዳሉ ቢነግሩን ለውይይት እጋብዛቸዋለሁ። ጮርቃዎቹ በስሜት እየተነዱ ‘ባልነበሩበት ጊዜ፤ታሪክ እና ምድር” ዛሬ በዛሬው ጮርቃ ፍርዳቸው ለምን ያኔ እንዲህ አልተደረገም  ብለው እየተመጻደቁ አገሪቱን በመቅረጽ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ነገሥታት በማግለል፤ በመስደብ፤ ሃውልት እንዳይቆምላቸው የሚከራከሩ ካፍንጫቸው ማሰብ ያልቻሉ ብልጣብልጥ ወጣን ወጠን የሚሉ የዘመናችን አዳዲስ ጠባብ ጎሰኞች በሚኦረኩራቸው ስሜት ብቻ እየጋለቡ አገሪቷን ያስረከቡዋቸው አባቶችም ሲያጥላሉ ሲጥሉ ሲያነሱ ለማየት በቅተናል። ወያኔ ሲያባርራቸው እንደ ወጣቶቹ ጠምነጃ ተሸክመው በረሃ መውጣት እምቢ ብለው እዚህ አውጭ በሞቀ ኑሮ ሆነው በሙዚቃ ጭፈራ መገሥታትን ማብለጥለጥ አስገራሚ ነው። ኣይጋ ፎርም እና ትግራይ ኦን ላይን የተባሉ የወያኔ ምጣዶችም እንደዚሁ “ምኒልክን” አግልለው ቴዎድሮስና እና ዮሃንስን ከዚጣ የወያኔ ታጋዮችን ሓየሎም፤ ቀሺ ገረዝጊሔር፤ አሞራ ….. የጨመረን ቪዲዮ ቀርጸው ህዝብን ሲሰብኩት እና የሚያበጣብጥ ጎሰኛ ስራ ሲሰሩ አይተናል። እነዚህም ከነሱ ተቀብለው ወደ ጭቃ ገብተው የወላጆቻችን እና የባህላችንን ማሳጣት፤ማበላሸት ጀምረዋል።

 በዚህ የደነዘው ትውልድ ብቻ ሳይሆን በ60ዎቹ የነበሩት ኮሚኒስት ተማሪዎች የጀመረ የባህል ብከላ ውጤት እንደነበረ ለዛሬ ውርደታችን ያበቃን መከራ እያየን ነው። ያ ትውልድ እንደዚያ ተጨማልቆ ነገሥታትን የሰው ስጋ ይበላሉ እያለ ታሪክን እና የሰውን ክብር ሲዳፈር’ የውጭ አገር ኮሎኒያሊሰት ሰላዮች ኢትዮጵያ ምድር ተቀምጠው በወያኔ ጊዜ ከ3 አመት በፊት በውስጥ ተባባሪዎች “ኢትዮጵያ በ16ኛው ክፍለዘመን የነበሩት ሴት መነኮሳት የመጀመሪያ አፍሪካውያን “ለዝቢያን ነበሩ” እያሉ መፅሐፍ ሲጽፉ አገሬኞቹ አብረው ግዕዙን እያጣመሙ ሲተረጉሙላቸው ለማንበብ በቅናል”። አልፎ ዛሬም፤ ይህ ትውልድም ከ60ዎቹ ኮሚኒሰት ተማሪዎች ስህተት  የተማረው አንድም ነገር የለውም። ምናልባትም በሌላ መልኩ እየለወጠ ያው ያገሪቱን ነገሥታት ለያይቶ ማወደስ፤ ታሪክ ማበላሸት ህዝብን ማቃቃር በሙዚቃ ስልት ሕዝብን ወደ ማናከስ ስራ ገብተውበታል። “አሞናል በለው’ የሚለው ሙዚቃ አገር ውስጥ ባይገባ እመርጣለሁ። ለብጥብጥ ከፍተኛ በር ከፋች ነው። አገሪቱ በገዛ ልጆቿ  ከውርደት ወደ ውርደት እያሸጋገርዋት ይኼው እዚህ ደርሰናል። በዚህ ከቀጠለ፤ ዘረኛ ሙዚቃዎችን ካለወገዝን፤ያች አገር አገር እንደማትሆን ግን በእርግጠኛነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ።

ይህ ግልጽ ወገንተኛነትና ጠባብ ጎሰኛነት ለማንጸባረቅ በሙዘቃ አሳትሞ ለፖለቲካ መሪዎች መቀበያ ዘፈን ሆኖ ተቀርጾ ከማስጨፈር የሚዘገንን ነገር አይኖርም። ህዝብን ማለያየትና ማስቆጣት ጉዳቱ እውጭ አገር በደላ ህይወት የሚኖሩት አይደለም።  እሳት ቀማሹ እዛው አገር ያለው ነው።

አሁን ወደ ቅንጅት ልውሰዳችሁ።

ቅንጅትን አንድነትን ያፈረሰው ማን ነው? ብዙ ተከራክረናል። የዛሬዎቹ እነ አንዳርጋቸው እነ ብርሃኑ “ቆሻሾቹን ጠራርገን ከመንገዳችን እናስወግዳለን በተባለው መሰረት፡ በሴራ ከሻዕቢያ ጋር ተጣብቀው አገሪኛውን ጠራርገው የተነበዩት ሴራ እውን ሆኖ፤ “አማራው ለጥቃት” “አንድነት ሃይሉ ለጥቃት” ተጋልጦ፤ ይኼው የስሜት ፖለቲካ እየነዳው ይገኛል። በዚህ ሴራ ላይ ኤልያስ ክፍሌን በሚመለከት እራሱ የቻለ ዘገባ አቀርባለሁ። ከዚያም እነ አል ማርያም፤ ታማኝ፤ አበበ በለው፤ንአምን፤ሜሮን፤ ሉሊት ወዘተ…የተጫወተቱት ሚና እንመለከታለን ለጊዜው ይህ ኤልያስ እና ሴረኞቹ በአገር አርበኞችና አገር ወዳዶች ላይ ሲያሰሩባቸው የነበረውን ካርቱን ኤልያስ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ሴራ ተጠምዶ ይለጥፋቸው የነበረውን ካርቱኖች ላስታውሳችሁ (ከታች ታዩታላችሁ)። አስገራሚው ደግሞ እንደዚያ ሁሉ “አገር ወዳድ ነኝ እያሉ ‘ሃይሉን በባንዳነት ታየን በባንዳነት በገንዘብ …ሲከስሱዋቸው” መጨረሻ አገር ጥለው ብርሃኑም አንዳርጋቸውም ኤልያስም ከዛ ሁሉ በሰው ክብር ላይ መጸዳዳት አልፈው “ሁሉም እየሮጡ ኢሳያስ ጉያ ውስጥ ገቡ”። ለሁሉም ጊዜ አለው! ወጣቱ ዛሬም እመቦጭ የውሃ ፖለቲካ ወቀጣ ውስጥ ገብቶ ይወቅጣል። የት ይሄዳል ኣያውቀውም። ሃብል እና መኪና እስከ ሸለመ ድረስ ተፈናቃይ ረሃብተኛ በየቦታው ፈስሶ የረዳት ያለህ፤ የዳቦ ያለህ እስካለ ድረስ ያ ጉዳዩ ኣይደለም።የድሮ ተማሪዎች የባህል ብልሽታቸውን ወደ ጎን ትተን ስለ ርሃብተኛው እና ተፈናቃዩ ያሳየው የማይረሳው ታሪክ ማን ይድገመው! በህይወት የሉም ወይንም ሁሉም ሸምግለዋል።
Hailu Sahul and Taye Weldesmayat and Bedru Adem all respected politicians disrespected by the dispeakble Elias Kifle of Ethiopian Review (Mereja)- Read what he named the each on his own shocking writing to defame these patriots. This is how Kenijit and our unity destroyed to ashes. History will never forget this brutal behavior in politics. Elias or Berhanu Negga or Bertukan Mediksa or Andaragachew Tsge and the likes never never ask forgiveness. Sad indeed!

 እንዲህ  ዓይነት ብልግና እየተሰራ ነበር አንድነት እና ቅንጅት ሊፈርስ የቻለው። ሴረኞቹ ዛሬም እንደ ጀግኖች ይጠራሉ። ለሁሉም ጊዜ አለው!
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


ESFNA - የሕወሓት የሰሜን አሜሪካ ቅርንጫፍ! ዳማዊ ጉዱ ካሣ Ethiopian Semay


ESFNA - የሕወሓት የሰሜን አሜሪካ ቅርንጫፍ!
ዳማዊ ጉዱ ካሣ (Ethiopian Semay)


Note from the Ediotr:-

Though I have some reservation on Abey- The decision passed by the so called ESFNA leadership that rejected Abey's request to attend the sport Festival is political and idiotics decision to say the least which many people suspect perhaps pressured by the Ginbot 7 gang leaders and affiliated personalities. If Tamagne Beyene who has strong relation with Ginbot 7 could have liked the invitation of Abey to the Sport Festival and asks the Federation to allow him to come as guest, they would milly or willy have accepted it, for fear of boycotting by Tamge and his millions of bangers. But, I suspect he and his affiliates has something to do with it. You know and I know these personalities controls several of the Diaspora institutions in different names and ways. But, that was nasty decision to refuse the guy. They allow political songs, musical plays and anti TPLF singers, flags, slogans and books, why not then political figures? ESAT rents a huge tent every year of the festival day- why does it rent a tent? to sell a food? it is there to sell you politics of the trash Ginbot 7 /ESAT and Andaragachew Tsige T-Shirt? Is that not? so the said the federation is free of politics is BS - the federation was always political.
Please read the following of Dagmawi Gudu Kassa interesting view.

አንድን ሰው ወይም ድርጅት መፈረጅ ቀላል ነው፡፡ ፍረጃ ደግሞ እንደተመልካቹ ነው፡፡ አሁን በአጭሩ የምናገረው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች የስፖርት ፌዴሬሽን ስለሚባለው የቦሌ ሞልቃቆች - የፈረንሣይ ልዕልቶች ስብስብ ነው፡፡ የካሣ ዳምጤ ልጅ መሸፋፈን አያውቅም፡፡ ከአንጀቴ የወጣ ብሶቴን በጥሞና አድምጡ፡፡ ለዚያውስ ይህን ጽሑፍ የሚያወጣልኝ ድረገጽ ሳገኝ አይደል? ዓለም የምትንሰፈሰፈው ላለው ነው፤ ድሃን የምትጸየፍ ዓለም የኔን ብሶት ለማድመጥ ጊዜም የላት፡፡ የሚያስተናግደኝ አንድ እንኳን ባገኝ ዕድለኛ ነኝ፡፡ በውነት በጣም ተናድጃለሁ፡፡

የወያኔነት ማዕረግ በትውልድ ሐረግ ወይም በጎጥ አይሰጥም፡፡ በምግባርና በጠባይ እንጂ፡፡ ለአብነት “እገሌ ትሮትስኪ ነው” ስንል - ዱሮ - ያ ሰው ራሽያዊውን ማንትስ ትሮትስኪን ሆኖ አይደለም - በሚያሣየው የአመለካከት ለውጥና አኳኋን ተመሥርተን እንጂ፡፡ እናም ይሄ ኢስፋና የሚሉት የዮዲት ጉዲት ውላጅ በውነትም ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የቆመ መስሎኝ በጉጉት ስጠብቀው ለካንስ ሕወሓትን የሚደግፍ የሀገር ጠላት ኖሯል፡፡ ሀገርንም ሕዝብንም የሚንቅ የነሰው ጤፉ ዋሻ መሆኑን በሰሞኑ ውሳኔው አሳውቋል፡፡ ደግሞም “የዐይጥ ምሥክር ድምቢጥ” እንዲሉ ለሕዝብ መቆርቆር የነበረበት ጋዜጠኛ - ካሣሁን ይልማ - የነዚህን ጉዶች ውሳኔ ደግፎ “ውሳኔያቸውን እናክብርላቸው” ሲለን ገረመኝ - አዝናለሁ፡፡  ሰውን ምን ነካው ግን? ራሱ ከተመቸው፣ ተደላድሎ ከተኛ፣ ከበላና ከጠጣና ከርሱ ከሞላ፣ የሞቀ ቤት ውስጥ ከኖረ… ስለሌላው ምሥኪን ግድ የለውም ማለት ነው? ምን ዓይነት የድንቅቁርና ዘመን ላይ ደረስን በሉ! መጥኔ ለኢትዮጵያ!

በኢትዮጵያ ላይ በጠላትነት ያልተነሣ የለም፡፡ የነዚህ ሰዎች ውሳኔ ግን ከሁሉም የተለዬ ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትር አብይ የተሰባበረውን ድልድይ ልጠግን ብሎ ሲነሳ “የለም! በተሰባበረው ድልድይማ አትምጣብን! በርሱ አይደለም እንዴ የስደት ኑሯችን ያማረበትና ተንደላቅቀን የምንኖረው?” ብለውን እርፍ፡፡ ጤናማ ሰው የዚህን ብላቴና ጥረት በሙሉ አቅሙ ይደግፋል፡፡ ጤናማ የሆነ ሰው የዜጎች በስደት መንከራተት፣ ከፎቅ መወርወር፣ ተርዋዶ ከሰው በታች መሆን፣ በበረሃ በውኃ ጥምና በርሀብ፣ በዐውሬና በሰውነት አካል በላቾች ማለቅ፣ … ልቡ ይነካል፤ ከአንገት ሳይሆን ከምር ያዝናል፡፡፡ ጤናማ ሰው በዜጎች መከፋፈል፣ በዜጎች መበተን፣ በዜጎች መደህየት…. ይሳቀቃል፤ ያለቅሳል፡፡ እነዚህ ደነዞች ግን ሁሉ ነገር ለነሱ ከተመቻቸ ለድሃውና ለሀገር ደንታ ቢስ ናቸው ማለት ነው፡፡ “እኔውም ዕብድ ነኝ ከወፍ የገበየሁ፤ መቀመጧን እንጂ መብረሯን የት አየሁ” ብሎ የተረተው ሰው እንደኔው አንጀቱ በንዴት ቢጨስ ነውና ልጅ ይውጣለት፡፡ ለካንስ በሰው ቁስል እንጨት መስደድና ጨው መነስነስ እንዲህ ቀላል ነው! አቢይ የነሱን ደጅ ያንኳኳው “ልጃችሁን ለልጃችን” በሚል ለሠፈር ሽምግልና  መስሏቸው ይሆን እንዴ? ማይምነትንና ባህላዊ አስተሳሰብን የሚቀርፍ መድሓኒት አሜሪካ ውስጥ የለም ይሆን?  ሰው ሲችል ወደፊት ይሄዳል፤ ያ ቢሳነው ያለውን ይዞ ይቆያል፡፡ እንዴት ቁልቁል ይነጉዳል? ኧረ አታሰድቡን እባካችሁን! በስንቱ ነው የምንሰደበው? አቢይ ከበረ - እነሱ ተዋረዱ፡፡

ደግሞ ዴሞክራሲ ይባልልኛል፡፡ የት የሚያውቁትን? ዴሞክራሲ ማለት ከመነሻው ምን ማለት ነው? ሀገሩስ የት ነው? ትንሹ ጆርጅ ቡሽ በዴሞክራሲ አልነበር ወደ ሥልጣን የመጣው? ዴቪድ ትራምፕ በዴምክራሲ አይደል ወደ ዋ(ኋ?)ይት ሀውስ የገባው? እምዬ ምኒልክ በዴሞክራሲ መጡ? አብይ አህመድ ራሱ በዴሞክራሲ መጣ? ለምን ይቀለዳል? በምድር ዴሞክራሲ የሚባል ነገር የለም - ቁጩ ነው፤ ‹ፌክ›፡፡ (ገንዘብና ብልጠት ያላቸው) ጥቂት መሠሪዎች የሚፈልጉት ነገር በዴሞክራሲ ስም ጎጋው መንጋ እየተጭበረበረ እውን የሚደረግበት የማስመሰያ ጭምብልና ህገ-ወጥነትን ህጋዊ ልባስ መስጫ አፍዝ አደንግዝ ነው - ዴሞክራሲ፤ ቃሉ ሲጠራ ግን ደስ ይላል፡፡ ስለዚህ የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በፈረደበት ዲሞክራሲ ስም የጥቂት ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሕዝብ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች ፍላጎት ነው የተንጸባረቀበት፤ በግልጽ ይታወቃል፡፡ በዚህ ንቃትና ዕውቀት እንደልብ በሚሠፈርበት ዘመን ማንም አፈ ጮሌ - ይመስለዋል እንጂ - ሊያታልለን አይችልም፡፡ የኛ የጭቁኖች ፍላጎት እውን መሆን የእንጀራ ገመዱን የሚበጥስበት አካል በፌዴሬሽኑ ስም ሥራውን ሠራ፤ ልጅ አይውጣለት፤ ጥቁር ውሻም ይውለድ፡፡ ምላሴ ጥቁር ነው ደግሞ፡፡

ኢትዮጵያ ሰላም እንዳትሆን የሚፈልጉ ወገኖች በየጎራው አሉ፡፡ በድጋሚ እራገማለሁ - እግዜር ይይላቸው፡፡ የሥራቸውንም ይስጣቸው፡፡ይህን የሰይጣን ሥራ የሠሩ ወገኖች ምንም አይጠቀሙም፡፡
በተለይ በዲያስፓራው ዘንድ የብዙዎች ፍላጎት የሚታወቅ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም መምሸት መንጋቱንም ሳይቀር በቅጡ የማያውቁና ከናካቴው ፍላጎትም ያላቸው የማይመስሉ ዞምቤዎች ናቸው፡፡ እንጂ ይህ ጠ/ሚኒስትር የተበታተነውን ሕዝብ ላስማማ ባለ በምን ሂሳብ እንዳይገኝ ይከለከላል? በፈረስ የፈለጉት በእግር ሲገኝ “እልል በቅምጤ!” ይባል ነበር እንጂ ከነሰው ብሶ መከልከልን ምን አመጣው? አቢይ ምን ይጎዳል? የርሱን ነጥብ አሳድጎ የነዚህን የአስተሳሰብ ድኩማን ሰዎች ነጥብ አስጣለ እንጂ ያጣው ነገር የለም - ይበልጥ ከበረበት፤ ይበልጥ ነገሠበት፡፡ ከዚህ በላይ ወያኔነት ደግሞ የትም የለም - ሕወሓትም ከዚህ አይከፋም፡፡ ለሕወሓት የሽፋን ተኩስ ከመስጠት የከፋ ወንጀል የለም፡፡ ኢትዮጵያውያንን ላስታርቅ የሚልን ሰው እያባረሩ ስለኢትዮጵያ ሕዝብ አስባለሁ ማለት ደግሞ ፍች አልባ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ሆ! በጣም ነው የገረመኝ፡፡ ስንት ሰው አለ እባካችሁ! ደግነቱ ይሄ ልብስ የሚባል ነገር መኖሩ፡፡ ሁሉም ተሸፍኖ ሲሄድ ሰው ይመስላልና፡፡

የሰይጣን ዛፍ ከፍሬው ይታወቃል፡፡ ዕርቅና ሰላም የማይወዱ፣ በኢትዮጵያ መበታተን እንጀራቸውን የሚጋግሩ፣ የሕዝብ ስደትና እንግልት የደስታቸውና የክብረታቸው ምንጭ የሆነ፣ በመዋጮና በዲያስፖራዎች ድካም ዝናና ሀብትን ለማካበት የሚተጉ፣ ወያኔ በመንበሩ እንደተጎለተ ዕድሜ ልኩን እንዲቆይ የሚጸልዩ፣  … የወያኔ ተባባሪ ሰዎች አሁን ታወቁ፡፡ “ያውጡብሽ እምቢ፣ ያግቡብሽ እምቢ” ይላል ያገሬ ባላገር እንዲህ ያለ ግራ አጋቢ ነገር ሲገጥመው፡፡ በነሱ ቤት መሠልጠናቸው ነው፡፡ በነሱ ቤት መራቀቃቸው ነው፡፡ ሠልጥነውና ተራቀው ሞተው!

እነዚህ ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት እንደምንኖር አያውቁም - የቦሌ ሞልቃቆች ያልኳቸውም ለዚህ ነው፤ ስቃይና መከራ ምን እንደሆኑም የሚረዱም አይመስሉኝም፡፡ እኛ በምን ዓይነት ፍዳና መከራ ውስጥ እንደምንኖር ቢያውቁ ኖሮ ያን የመሰለ የዘበናይና የቅንጡ ሰዎችን ውሳኔ አይወስኑም ነበር፡፡ አንዳንድ አጋጣሚዎችን እየጠበቁ በዚህ በፈረደበት “Shame on you” መፈክር እያላገጡ መኖርን ሳይወዱት የቀሩ አይመስለኝም፡፡ እነዚህ ሰዎች የኛ ሰቃይ አይገባቸውም፡፡ ምናልባት ቀደም ብለው የወጡ ናቸው፡፡ ምናልባት በገንዘብ ደርጅተዋል‹፡፡ ምናልባት የሀገር ፍቅርና ናፍቆትም ሆነ ትዝታ የላቸውም - ከጊዜ ብዛት አንጻር በንኖ ጠፍቶባቸውም ይሆናል፡፡ በዚያም ሳቢያ ምናልባት በሚኖሩት ኑሮ ደስተኞች ናቸው፡፡ ምናልባት ስለኢትዮጵያ ያላቸው ዕውቀት ወደ ዜሮ ተጠግቷል፡፡ በአንድ ወይ በሌላ ምክንያት ግን እነዚህ ሰዎች ስለኛ ስለብዙኃኑ መበደልና መገፋት አይሞቃቸውም፣ አይበርዳቸውም፡፡ የስሜት ህዋሶቻቸው ሞተውባቸውም ይሆናል፡፡ ስለዚህ አቢይን መከልከል ብቻም ሣይሆን ኢትዮጵያ ትሸጥ ትለውጥም ቢባል ከመፈረም አይመለሱም፡፡ ከወገንና ከሀገር ስቃይና መከራ ይልቅ ጥቅም ያሳወራቸው ይመስላሉ፡፡ እንግዲያውስ ለነሱም እንዘን፡፡

መጠንቀቅ ያለብን የችግሩ ሰለባዎች ነን፡፡ በተለይ በሀገር ቤት ያለነው ዜጎች ከነዚህ ዓይነቶቹ ሥውር የወያኔን አጀንዳ አራማጆች ሀገራችንንና ራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ በውጭ ያሉን ዘመዶች የሚያስቡልን እየመሰለን ብዙ ተታለናል ማለት ነው፡፡ የሚያስቡልን መኖራቸው እውነት ቢሆንም ይህ በአቢይ ጥያቄ ላይ የተከለሰው ቀዝቃዛ ውኃ ግን በቀላሉ ሊታይ የሚገባው አይደለም፡፡ ወደፊት በስፋት ልንነጋገርበት ይገባል፡፡ ጉዳዩ ብዙ መልእክት አለው፡፡ የተሰጠው ምክንያትም ውኃ አያነሳም፡፡ ገና ድፍን አንድ ወር ለቀረው ጊዜ የፀጥታና የቦታ ጥበት ማንሳት የአያ ጅቦን ሳታመካኝ ብላኝ ተረት የሚያስታውስ የድንቃይ ቧልታይ ድርሰት ነው፡፡ ለማንኛውም ሌላ ጊዜ በስፋት እመለስበታለሁ፡፡ ለአሁኑ ግን ሰላም ለሀገራችን፤ ትክክለኛው የፈጣሪ ፍርድ በየጎራው ላሸመቁ የጋራ ጠላቶቻችን፡፡ (ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቴን የምትነፍጉ ሁሉ … ልብ ይስጣችሁ፡፡)

አባሪ
ቀጥሎ የሚገኘው ዜና ከethioexplorer.com ያገኘሁት ነው፡፡ ባለቤቱን (ቶቹን) ባላስፈቅድም አይቆጣኝም ብዬ በማመን ከኔው የብሶት ደብዳቤ ጋር አብሮ ለዘላለሙ እንዲኖር ከዚህ በታች አኑሬዋለለሁ፡፡ የኔን ጽሑፍ ባያወጡልኝም ባሉኝ አድራሻዎች ሁሉ ጽሑፌን ከላክሁ በኋላ ነው ይህን ዜና ያገኘሁት፡፡ ወዳጄ የኢትዮሰማዩ ጌታቸው ረዳ አደራህን ቢያንስ አንተ እንኳን ፖስት አድርግልኝና ለነገው ታሪካችን ይደር፡፡ በስማም! ምን ዓይነት የተወለጋገደና የተወሳሰበ ዘመን ነው ጃል፡፡ ሕወሓቶች በርግጥም ሰማይንና ምድርን ተቆጣጥረዋል ማለት ነው፡፡ አንድ ወቅት ሶሎሞን ክፍሌ በስልክ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግለትና ከየት ነው ብሎ ጠይቆት ከአሜሪካን ሀገር ቢለው “እንኳን ካመሪካ ከመንግሥተ ሰማይም ብትሆን አምጥቼ አስርሃለሁ!” ያለው ደደብ የወያኔ ኮሎኔል ልክ ነበር ማለት ነው፡፡

ESFNA ማለት የስልጣን አወቃቀሩ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴን አይደል እንዴ የሚመስለዉ!
Print Friendly, PDF & Email
http://welkait.com/wp-content/uploads/2018/06/esfna-2018-logo-01.png
እንዴ ESFNA ማለት የስልጣን አወቃቀሩ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴን አይደል እንዴ የሚመስለዉ፡፡ የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ኤርትራዊ፤ ትግሬ እና ደቡብ እንዲሁም ኦሮሞ ይበዛል ከአማራዉ ይልቅ፡፡ እስኪ ይሄን ጉድ እንየዉ፡፡
እስኪ ESFNA ቦርድ አባላት የብሄር ስብጥር እንምታዉ!
1.
ትግሬ 10
2.
ደቡብ 8 (ጉራጌ የተወከለ አይመስለኝም)
3.
ኦሮሞ 5
4.
አማራ 3 These are sell outs. They don’t even allow the legendary Amhara artist, Fasil Demoz, to Appear on stage
5.
የኤርትራ ዝርያ ያለበት 3
6.
ሶማሌ 1
7.
ቅልቅል 1
ይሄ እንግዲህ ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ወይም ከመከላከያ ሰራዊት የስልጣን መዋቅር ጋር ተመሳሳይ ነዉ፡፡ ሕወሃት ይሄን ስለምታዉቅ እንግዲህ ወይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወይ ይሄን ESFNA የሚባል ግሩፕ in awkward position ማስቀመጥ ፈልጋ ያዉ ለዘመዶቿ ደዋዉላ እንደዛ አድርጋለች፡፡ Both ESFNA and Abiy lost but TPLF won.
 posted at Ethiopian Semay