Friday, May 19, 2017

1)ኤፍሬም ማዴቦ ዛሬም ከአማራዎች ራስ መውረድ አልቻለም (2) ኦብነግ እና ግንቦት7 ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)


(1)ኤፍሬም ማዴቦ ዛሬም ከአማራዎች ራስ መውረድ አልቻለም

(2) ኦብነግ እና ግንቦት7

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ? በነዚህ ሁለት ርዕሶች እንወያያለን። የግንቦት 7 አመራር ጸረ አማራው ፓሰተር ኤፍሬም ማዴቦ ራሳቸውን ከጸረ አማራ ጥቃቶች ለመከላከል የተደራጁ አማራዎችን “የአእምሮ በሽተኞች” አላቸው።

The Nihilist Group

ፓስተር/ቄስ/ ኤፍሬም ማዴቦ አማራን መዝለፍ ይህ የመጀመሪያው ሳይሆን ካሁን በፊት በሰፊው እንደተነተንኩት አሜሪካ ውስጥ በ2012 በካሊፎርኒያ ክ/ሃገር በኦክላንድ ከተማ የሻዕቢያ የነጻነት በዓል ባዘጋጀው ስብሰባ ግንቦት 7ን በመወከል የክብር እንግዳ ሆኖ በተገኘበት ወቅት፤አማራውን በመዘርጠጠጥ እዚህ እውጭ አገር ያሉትን “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሉ ጥቂት ነፍጠኞችን በቁጥጥር ስር አድርገንላችኋል፤ኢትዮጵያ ፤ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ ቅደሚ በልጆችሽ ትግል ተከብረሽ ለዘላለም ኑሪ፤ ኢትዮጵያ 14 ክፍለሃገር እያሉ በራዲዮን የወደቀ መዝሙራቸውን የሚለፈልፉ ነፍጠኞችን ልክ አስገብተንላችኋል…” ሲል አማራዎችን ለሻዕቢያ ገጸ በረከት በማቅረብ ለሻዕቢያ አሽከርነቱን በይፋ የገለጸበት ወቅት እንደነበር ታስታውሳላችሁ። ንግግሩ ደግሞ “ድርጅቴን ወክየ ስለመጣሁ የድርጅቴ አቋም ነው” ሲል በይፋ ነግሯቸዋል።

ይህ የፕርሮቴስታንት ሰባኪ ቄስ እና የግንቦት 7 ፖለቲከኛ ሰው፤ አማራውን በመዝለፍ አላበቃም። እዛው ስብሰባ ውስጥ፤ ዓረቦች ነን ብለው የመሰረቱትን የኤርትራ ባንዳዎች እና ዛሬም እውነታው እንደታየው “ኢሳያስ የሚመራት የምድር ሲኦልዋ ‘ኤርትራ’/ባሕር ነጋሽ/ እንደ ሶማሌ ፤ እንደ ጂቡቲ እንደ ግብፅ፤ እንደ ሳውዲ… ሁሉ የዓረብ ሊግ አባል መሆኗ ብቻ ሳይሆን፤ የባሕር ወደቦቻችንን ለዓረቦች መናሃሪያና ወታደራዊ ማከማቻ መሆኗን፤ ኤርትራም በዓረቦች ጉያ እንደሆነች አሁን በዓይናችን አይተናል፤ [ዛሬ!ዛሬ! ከነፃነታቸው በኋላ!!] አይደለም እንዴ?

ይህ ሆኖ እያለ፤ ኤፍሬም ማዴቦ “የኤርትራ መገንጠል ለዓረቦች የሴራ መጎንጎያ መንኮራኩር ለመሆን ስለሆነ “ዓርባዊ ደላላነትዋን” በመዋጋት የአገራችነን ሉዓላዊንተን ማስከበር አለብን፤ ብለው በሺዎቹ አጥንታቸው የከሰከሱበትን የግኖቻችንን ክቡር መስምርን በመስደብ፤ “ነፍጠኞች የትግላችሁን ትክክለኛ መስምርን ጥላሸት በመቀባት የኤርትራ ነፃነት ታጋዮችን የዓረቦች ደላላ በመሆን ኤርትራን ሊሸጡዋት ነው እያሉ ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ ነበር” በማለት የአርበኞቻችን ሉዓላዊ መስመር በማንቓሸሽ የሻዕቢያዎችን እጅ አስጨብጭቧል።ያንን ባንዳዊ እርቃኑን የወጣ ንግግሩን ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ።

ለነገሩ፤ ኤፍሬም ማዴቦ አለቅላቂ እና አማራን ለመዝለፍ እዛው የከተቱት እንጂ በራሱ ‘ፓወር/ህይወት’ አይደለም። ዋናው ሞተሩ ብርሃኑ ነጋ ነው። በወዳጄ በተከበሩ በዶ/ር ሃይለስላሴ ማንከልክሎት አንደበት ልቅረብ፡ እንዲህ ይላሉ፤

In my opinion, first, the relationship between Berhanu Nega and G-7 has to be established clearly. Ginbot 7 is equal to Berhanu Nega. As I have repeatedly stated before, I will say it again. He is the brain and the mouth of Ginbot 7. As it is the case with TPLF, Meles Zenawi is the brain and the mouth of TPLF. Ginbot 7 does not exist without Berhanu Nega.” GINBOT- 7 AND THE ETHIOPIAN FLAG ISSUE- December 29, 2011 Mankelklot Haile Selassie (PhD)

 አዎ ብርሃኑ ነጋ ማለት ግ7 ነው፤ ወያነ ማለት መለስ ዜናዊ ማለት ነው። ያለ ሁለቱ የድርጅቶቹ ህለውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል። ስለዚህ ኤፍሬም ማለት አማራን ለመስደብ የተመለመለ ዘረኛ ኢቫንጀሊካል ፓስተር ነው።

የሰሞኑን የፓስተር ኤፍሬም ጽሑፉ ደግሞ በብዙ አማራዎች ቅሬታን አሳድሮአል። ቅሬታቸው ከገለጹት አንዱ የሚከተለውን ርዕስ ለመመልከት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ለጻፉት የጉዞ ማስታወሻ የተሰጠ ምላሽ በተለይ የአማራን የመደራጀት ጥያቄ ከአእምሮ በሽታ ጋር ስለማያያዝዎ  (ከሰለሞን ዳኛቸው)” የሚለውን ለማንበብ ወልቃይት.ካም (welkait.com) ድረግጽን ርዕሱን ጉግል በማድረግ መመልከት ይችላሉ።

ሁለተኛው ርዕሳችን ኦነግና ግንቦት7 ነው

የሰሞኑ አብይ ተብሎ የተወራለት ዜና ‘ ኦነግ (ONLF) እና ግንቦት 7 ብርሃኑ ነጋ እና ኦጋዴኖች የጋራ ትግል ፈጠሩ’ የሚለውን እንመለከት። ዛሬ የተናገረው ነገ የሚሽረው ብርሃኑ ነጋን ታውቁታላችሁ። ብርሃኑ እና አንዳርጋቸው ልዩ የወያኔ ተዋናያን ‘የመለስና የታምራት የበረከት ዊስኪ አጫላጮች ነበሩ። ብርሃኑ ማለት ከመጀመሪያውኑ የወያኔ ተጠቃሚዎች ከነበሩት አንዱና ትልቁ ነበር። በአንድ መረጃ ጸሐፊ መሰረት እንዲህ ያቀርበዋል፤
“Berhanu followed TPLF in 1991 and entered Addis Ababa as one of its loyalists he was immediately designated as part of the AFRICA GROUP Ltd., an entrepreneurial group designed by TPLF to attract business ideas in the honey moon days in TPLF-Ethiopia. While in AFRICA GROUP Ltd., Berhanu took huge sums of loan from Woyane regime treasury and became an entrepreneur and founded the Ethiopian Agro-Maize, a fertilizer producing company, and Addis Village Family Home Builders. Later he aspired to hold ministerial position but in vain
 ሌላው የግምባሩ ፈራሚ ደግሞ ብዙም እውቀቱ እና ትውውቁ የሌላችሁ ሰው ቢኖር እኛ የጋራ ጠላት ካለን ከአልሸባባም ጭምር እናብራለን አይነቱ አበባል ብሎ ደፍሮ የተናገረ ሰው ነው። እስላማዊ ዓረብ ነኝ የሚለው የኦጋዴኑ  አስገራሚ ሰው ዛሬ ከብርሃኑ ጋር ተፈራርሟል። ካሁን በፊት እንደገለጽኩላችሁ የኦጋዴን ነፃ አውጪ መሪ ነኝ የሚለን የሶማሌው ሲያድ ባሬን በባሕር ሃይል በወታደርንት ሲያገልግል የነበረው የኦብነግ መሪ ነኝ ባዩ አድሚራል መሀመድ ዑመር  ኦጋዴኖች እስላማዊ አረቦች ነንሲል Asharq Al-Awsat ለተባለ አውሮጳ በሚታተም የሶማሊ ሚዲያ በአንደበቱ የተናገረውን በድረገጼ ላይ ከቃለመ መጠይቁ (ብርሃኑ ነጋ በየአሜሪካ ግዛቱ ከኦብነግ አባሎች ጋር በ2011 (7 አመት በፊት)ኢትዮጵያዊያንን ሲያጃጅል በነበረበት ጊዜ) የጠቀስኩትን ለማስታወስ ይህንን ልጥቀስ፤

* Ogaden tribe region is “one of the last occupied Arab territories in the 21st century.” – ONLF Chairman said * “There are no noticeable schools. Moreover, there are no hospitals in the region” * “If these groups (Shabab) are fighting against Ethiopia, then we have a common enemy. “ * “Tribalism is not among the principles of the ONLF” * “The Ogaden people are an Arab Muslim people” Admiral Mohamed Omar Osman, leader of the Ogaden National Liberation Front (ONLF), (Source Somal Swiss Community/Somalida Switzerland “ONLF leader claims Ogaden are “Arab people” under Ethiopian occupation..http: Somaliswisstv.com interview with Asharq Al-swak- source Los Angeles Times). Asharq Al-Awsat-

The entire interview can be obtained http://somaliswisstv.com/2009/10/17/onlf-leader-claims ogaden are arab people under Ethiopian occupation/) በሰፊው የተነተንኩበት ማሕደር ለመመልከት The Deluded Elite of the Liberation fronts Getachew Reda MONDAY, MAY 2, 2011https://ethiopiansemay.blogspot.com/2011/05/deluded-elite-of-liberation-fronts.html  ያንብቡ።




እሩቅ ሆነው፤ የኦጋዴን ህጻናትን በጦርት ወላፈን ውስጥ እንደ እሳት እንጨት እየማገዱ፤ በፈጣሪ ፊት እየዋሹ፤ የጋራ ጠላት የሚሉትን ወያኔን ለመጣል ‘ከአጋፋሪያቸው’ ከግንቦት 7 መሪ ጋር ግምባር ፈጥረው፤ ፋሺስቱን ወያኔን ለመጣል ተፈራርመናል ይሉናል።

ድርጊቱ፤ ማበር ብቻ ሳይሆን፤ ግንቦት 7 ከኦነግ ጋር ግምባር ፈጠርኩ ባለበት ወቅት ኦነጎች ሲጠቀመበት የነበረውን ልዩ ልዩ የረቀቀ የማወናበጃ እና የማጃጃያ ፕሮፓጋንዳ ‘ኦብነግም’ ያንኑ ስልት በመከተል፤ የራሱን ጥበብ በመፍጠር፤ ትናንሽ ሰንደቅ ዓላማዎችን በየቦታው መትከል አንሻም   በማለት ግንቦት 7 ጋር በጋራ ለመታገል የተስማማው ኦብነግ አመራር አቶ አብዲራህማን ማኅዲ ከሲቢኤስ ራዲዮ ቃለ መጠይቁ ተናገረ፤ ሲሉ ዘጋቢዎች አስነብበውናል። ይህ ቀልድና አሳሳች ጥበብ፤ ወደ መደምደሚያ ስለምተነትነው፤ አሁን ስለ የጋራ ትግል የሚሉትን ባጭሩ እንመልከት።
በደላላው በዶ/ር ዜሮ (ጌታቸው በጋሻው) መድረክ አዳማቂነት ኦነግ ከግንቦት 7 ጋር አገር ላገር እየዞረ ለኦነግ ውሸት ሽፋን እየሰጠ ያበሰለውን አድማጭ በስሜት ሲያሰክርና ሲያስጨበጭብ እንደነበር ክርክራችን የምታስታውሱ ብዙ ናችሁ ብየ አምናለሁ።
ኦብነግን ከመተቸታችን በፊት ኦነግን በምሳሌ እንመለክት። ኦነግ ከግንቦት 7 ጋር እየዞረ “ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ አቅርቦ በፍጹም አያውቅም፤ የግንጠላ ጥያቄ አቅርቧል እያለ የወነጀሉን ‘አንድነት’ የሚባሉ ሃይሎች እንጂ ኦነግ የመገንጠል ጥያቄ ጠይቆ አያውቅም” ሲል ከኦነጎቹ ‘የውሸት ቀፎ’ አንዱ አሚን ጃንዳይ ሲያትል መድረክ ላይ ንግግር በማድረግ ሲወነጅለን ታስታውሳለችሁ። ግንቦት 7ትም ኦነግን ለሕዝባዊ መድረክ ማቅረብና መከራከር ሃጢያት አይደለም እያለ ሲያጃጅላችሁ ‘ኦነግ ሲዋሽ’ ዋሽተሃል ብሎ ከመከራከር ይልቅ ተባባሪ ሆኖ ሕዝብ በውሸት ሲበረዝ የአንድነት ሃይል የምንባለውን ስንወነጀል ‘አፉን እንደዘጋ’ ታስታውሳላችሁ።ያኔ ነገሩን በደምብ የተገነዘቡት ምሁር ደ/ር ሃይለስላሴ ማንከልክሎት እንዲህ ብለው ነበር፤
“…..He was deliberately evading the issue, he was more or less boasting, by confusing between talking to influence to bring to ones desired positive position, and providing a forum. Berhanu Nega was doing the later one. He was providing OLF a forum to regurgitate its fabricated grievances and lies. For example, here is one of the blatant lies. In Seattle, the representative of an OLF group, with full confidence of not being challenged, said that OLF never set out for secession. Berhanu Nega and Aregawi Berhe were there sitting like robots and listening. No one of them did have the gut and dare challenge the truth of this blatant lie based on OLF’s historical facts.
Berhanu Nega is doing is deliberately and arrogantly confusing the public with lies and inconsistencies that have been repeatedly demonstrated by OLF groups. Whether the fake Ginbot 7, hence Berhanu Nega agrees or not, consciously or unconsciously, it is supporting the lies and fabrications of OLF. It is really amazing to see when one is cheating oneself.
ስለሆነም ያለፉት የግንቦት 7 ከተገንጣዮች ጋር አደረግኩ እያለን ያለው ማሕደር የሚያመላክተን፤ ለተግንጣይ ቡድኖች “የውሸት እና የማጃጃያ መድረክ መፈለፈያ መድረክ/ፎረም” ማበጃጀት እንደሆነ አይተናል። በቅርቡም ሌንጮ ለታ ስለ ሰንደቃላማ ሲናገር፤ ብርሃኑ “አይጨክንልኝም” (ምን ማት አንደሆነ ይገባችል) እያለ ደጋግሞ ሲናገር አድመጠናል። ከዚህ በመነሳት ሰንደቃላማችን በሕዝብ ድምፅ የጸደቀ ስላላሆነ ‘ሕገ ወጥ ነው’ ሲል ብርሃኑ ጌታዋን እንዳጣች እንደምታሳዝን ውሻ ሎምቦጩን አሞርሙሮ ከማድመጥ ሌላ የተቃውሞ መልስ አልሰጠም። ሌላው የማጃጃያ እና የግንጠላ የስድብ ፕሮፓጋንዳ ፎረም በመሆን እኛን እና ሰንደቃላማችንን እና እኛንም ለመዝለፍ ግንቦት 7 መሸጋገሪያቸው አድርገውታል ማለት ይኼ ነው። ግልፅ አይደለም እንዴ?
የኦነግና የግንቦት 7 የትብብር ግምባር ልጨርስ እና ወደ ኦጋዴኑ ማጃጃያ/ሻጥር/ ይዤአችሁ እገባለሁ። አንዴ ወደ ሲያስትል ልመሰልሳችሁ። ከግንቦት 7 ጋር ኦነግ ሲያትል መድረክ ተዘጋጅቶለት አንድነት ሃይሉን ሲወነጅል፤ ‘አሚን ጃንዳይ’ ሲዋሽ አብሮ ትላልቅ ሚዲያዎች ሕዝቡን በማጃጃል ስራ ተጠምደው ነበር።ከነዚሁ አንዱ የኢትዮ-ሚዲያው ዋና አዘጋጅ አብርሃ በላይ ነበር።  
 
አብርሃ በላይ ንዲህ ይላል።
“Amin Jundi, Secretary of the Oromo Liberation Front (OLF), said reducing the quest of the Oromo people for democracy and justice to “secessionism” was unfair since “secessionism” has never been the agenda of the Oromo people nor of the OLF.
Impressive in presenting his ideas both in Oromiffa and Amharic languages, the articulate Amin Jundi brightened the mood of the audience that has for a long time been forced to portray the OLF as a separatist group. Aregawi Berhe of UEDF and Berhanu Nega of Ginbot 7 also dwelt at length how to consolidate the opposition camp and move on to dislodging the tyrannical regime of Meles Zenawi.” (Amin Jundi: secessionism has never been the agenda of the Oromo people Ethiomedia | November 17, 2011- SEATTLE –)

1.     ይላል የኢትዮ ሚዲያው የኦኤል ኤፍ ወዳጅና አድናቂ አብርሃ በላይ። አብርሃ በላይ- አሚን ጃንዳይ የዋሸውን ውሸት ሲከላከልለት፤

2.   the articulate Amin Jundi brightened the mood of the audience that has for a long time been forced to portray the OLF as a separatist group.

3.    

4.   ብሎ ያደመቀለትን ስንመረምረው ኦነግ ሳይሆን እኛ ነን በአድማጩ ሕሊና ውስጥ ኦነግ የመገንጠል አጀንዳ ያለው ብለን ያልዋለበትን ያላለመውን፤ ያለ ስሙ እና ያለ ዓለማው በመስጠትዋሽተን ለብዙ ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳስተን በማሳሳት፤ ኦነግን በአድማጭ ሕሊና ተገንጣይ ነው በማለት እንዲጠላ ያደረጉት ሲል አብርሃ በላይ እኛኑን ወንጅሎናል። ያውም (for a long time been forced to portray the OLF as a separatist group./ሃዝ ቢን ፎርስድ) የምትለዋን ሀረግ ንከስዋትና ፍረዱን ለናንተ ልተው” ብየ ነበር በወቅቱ።

5.    ስለዚህ ግንቦት 7 ብቻ ሳይሆን ሚዲያዎችም በሚገባ ሕዝብን በማጃጃል እና እኛውኑ/አንድነት ሃይሎችን ውሸታሞች እያሉ ወንጅለውናል።  እውነታው ግን ይህ የሚከተለው ነበር። “…hence, the OLF political objective is liberation from Ethiopia and establishment of the Republic of Oromiya. (1974 እስከ ዛሬ የቀጠለው ፕሮግራም) http://www.oromoliberationfront.info/objectives.htm

ሰሞኑንም ዛሬም ዘሐበሻና/ኢሳት እንደተለመደው እንደ አዲስ ዜና እየተከታተልን ዜናዎችን እናስደምጣችለን እያሉን ነው። ነገሩን (ሰበር ዜና) በማለት እንደ አዲስ ነገር በማሟሟቅ/ማጃጀሉን ጀምረዋል።
 
ኢሳት ማነው? የግንቦት 7 ተክለሰውነት ነው። ግንቦት 7 የተባለው እንደ እነ ሌንጮ ለታ የማሳሉትን ‘አማርኛ እንደማይችሉ እንደ ኢሳያስ አፈወርቂ ለመምሰል’ የተገንጣይ መሪዎችን ቃለ መጠይቅ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ቃለ መጠይቁን እያስደመጠ፤ በኢሳያስ አፈወርቂ አድናቂ ጋዜጠኞች  የሚመራ ኢሳት ደግሞ እንዲህ ዓይነቱ ማጃጃያ በጣም ስለሚወድ፤ “ሰበር ዜና” እያለ ከዘሐበሻ ጋር በስፋት ማስተጋባት ጀምሯል። ተድላ አስፋው እንዲህ ይገልጸዋል።
Neamin Zeleke position is the G7 position. They talk with nothing back home. His movement is known for Talking a.k.a ESAT and I do not give any credibility for his group being a unifying factor. The ESAT broadcast is more a divider than a uniter. Their airtime is filled with sensationalism incorporated with Kilil terminology. The only thing we have is the name Ethiopia on their station.”
 
ተድላ አስፋው “ኢትዮጵያዊያኖች ከኦሮሞ ክልል እንዲባረሩ” ጥሪ በማስተጋባት የታወቀው “የሁከት መሪ” የሆነው አደገኛው ጃዋር መሐመድ፤ እና ንአምን (ካልተሳሳትኩ) ቪ ኦ ኤ ጋብዞአቸው በነበረበት ወቅት “ለአሜሪካው መናፍሕ” ተቃውሞውን በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ከተቸበት የወሰድኩት። በጥቅሉ የወደፊት ስርዓት ሚዲያውን የሚቆጣጠሩት እነኚህ ናቸው። እነኚህ ደግሞ በሉአላዊነት ጉዳይ ‘ወገባቸው ቀጥ ያላለ’ ፤ አለጥላጮች ናቸው።

ወደ ኦብነግ/ኦጋዴን ብሔራዊ የነጻነት ግምባርና የግንቦት 7 ትብብር ፌርማ እናምራ።የሁለቱም ፌርማ መፈራረም በነዚህ ሚዲያዎች እየተናፈሰ ነው። የግንቦት 7 አሽቃባጮች ብቻ ሳይሆኑ፤ ደደብ ምሁራንም እያዳመቁት ነው። በዚህ ላይ ኦነግ አዲስ ለየት ያለ የኢትዮጵያዊያንን ልብ ለማኖህለል የተጠቀመበትን አዲስ ዘዴ አለ።

ምንድ ነው? ትናንሽ ሰንደቅ ዓላማዎችን በየቦታው መትከል አንሻም አብዲራህማን ማኅዲ ግንቦት 7 ጋር በጋራ ለመታገል የተስማማው ኦብነግ አመራር ከኤስቢኤስ ራድዮ ጋር ካደረገው ቃለምልልስ የተጠቀሰ። ይህ እንደ እውነታ አድርገው የሚወስዱት ማታለያ ወጥመድ የሚያምኑ የዋህ ልቦች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ። ልክ እንደ ኦነጉ አሚን ጃንዳይ አዳራሽ ውሰጥ ተነግሮ ቢሆን ኖሮ እነ አብርሃ በላይና የመሳሰሉት በጭብጨባም በድረገፆቻቸውም ለማድመቅ አይቦዝኑም ነበር።

ይህ ማታለያ ወጥመድ እስኪ በዚህ ጥያቄ እንፈትነው። ትናንሽ ሰንደቅ ዓላማዎችን በየቦታው መትከል አንሻም ሲሉን የኦብነጉ አመራራር፤ ከተናገሩባት ከሰሞኑ ጊዜ ጀምሮ እስኪ የግንጠላው ባንዴራቸው የጣሉ እና በምትኩ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያውለብልቡ እና እውነታው በተግባር ያሳዩን?
 

ወይስ ብርሃኑ ነጋ እና ኦነግ እንዲሁም “ከእስላማዊው ዓረብ” ከኦጋዴን መሬት ከኦብነግ ጋር በጋራ ከአስመራና ከመቃዲሾ ገስግሰው ወያኔ ከጣሉ በአብዲራህማን ማኅዲ የተናገረውን ትናንሽ ሰንደቅ ዓላማዎችን በየቦታው መትከል አንሻምከዛሬ ቀን ጀምሮ ባለ ኮኮቡ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ሰማያዊ ጨርቅ ትተናል” ሊሉን በጉጉት በትንቢት መጠበቅ አለብን? ለምን ዛሬ አይሆንም?
 

ኢትዮጵያዊያኖች ከሆኑ ብሔራዊ መለያ አለን፡ ያንን አንግቦ መታገል አንድ እርምጃ እና እርማት ካሳዩን አንድ እርምጃ በመውስዳቸው እንቀበላቸዋለን። አንቀበልም ብለው የትንቢት ዕርጎ እናጠጣችኋለን ካሉን ግን በዛው ከጸኑ ‘ግንጠላ’ እንጂ ሌላ አጀንዳ የላቸውም። ስለሆነም “በብርሃኑ ነጋ” በኩል ገብተው የወያኔ ተንኮል መስራት ካማራቸው፤ ይቀጥሉበት። ያ አጀንዳ አንደሆነም እናውቃለን። “ራስን በራስ ማስተዳዳር/የኦጋዴን ጎሳ ፌደራሊዝም” እያለ በሲቢኤስ ራዲዮ ቃለ መጠይቁ እስከዚችው ደቂቃ ሲነግረን፤ ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ከግንቦት 7 ጋር ግምባር ፈጠሩ ብለው ሲዋሹን ከወያኔው ታላቁ ሴራ እንዴት አንማርም?
 

በነገራችን ላይ ባንዴራቸውን ‘ጨርቅ’ ብየ በማለቴ እነኚህ ወንድሞች ይበሳጩ ይሆናል። ማሕደራቸውን ልምዘዝ እና እስኪ ዶሴው እንመልከት። ዛሬ ስለዲሞክራና አንድነት ከግንቦት 7 ሊሰብኩን እየዳዳቸው ያሉት የኦብነግ አንዳንድ አመራር አባሎች በወያኔ የሽግግር ዘመን የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ የተቃወሙ እና ይልቁኑም መሃሉ ላይ ነጭ ተጨምሮበት በጥቁር ቀለም እንዲሰረዝ ካሳሰቡ እና ሰንደቃላማችንም “የአያቶቻችን ገዳይ” ብለው በቂም በቀል የተናገሩት የዚህ ድርጅት አባሎች መሆናቸውን አንዘነጋም።
 

መለስ ዜናዊ ጨርቅ ብሎ ሲግማማብን፤ ኦጋዴኖች/ሶማሌዎች/ አዳራሹ ውስጥ አረመኔ ከተባሉት ያልተገረዙ ምላሶች አንደኞቹ የእነዚህ ድርጅት አባሎች እንደነበሩ በቪዲዮ የተቀረጸ ማስረጃ አለን።እነኚህ ወንድሞች የሽግግሩ አባሎች ሆነው አማራ በምስራቅ አገራችን ክፍል ‘አንገቱ በቢላዋ ሲቆረጥ’ ሚናቸው ምን እንደነበር ሊነግሩን ይገባል። ነብስ ጠፍቷል’ ሂሳብ ማዋራረድ ተገቢ ነው። ይቅርታ እንኳ አልሰማንም። የተገላቢጦሽ ኦነግ እና ኦብነግ “በዳዮች ሳይሆኑ፤ ተበዳዮች” ሆነው በመቅረብ እኛኑን ሲወነጅሉን ካሁን በፊት ብዙ ጊዜ ከግንቦት 7 ጋር አገር ላገር ሲዞሩ አደምጠናቸዋል። ተራው የኛ ኢትዮጵያዊያን ነው። ዝምታ ለበግም አልጠቀማት።
 
የግንጠላ ባንደራ እያውለበለብክ ‘ተጨቆንኩ’ እያልክ በሌላ በኩል አማራን እየገደልክ፤ አገራዊ ሰንደቃላማን “ገዳያችን” እያልክ፤ ክርስትያኑን እና አማራው እንዲጨፈጨፍ በታምራት ላይኔ አይዞህ ባይነት እየተገፋፋህ አማራን ስታሳልቅ ኖረህ አሁን “ተጨቁኛለሁ፤ እገነጠላለሁ” ብሎ ማለት አላህን ያለመፍራት ነው።
ኦጋዴኖች እና ኦሮሞ ወጣቶችን ልብ ብላችሁ ሰትመረምሯቸው፤ የግንጠላ ርዕዮትና የወያኔ ሴራ አቅጣጫቸውን አበላሽቶባቸዋል። ምሳሌ ልስጥና ልደምድም። የኦሮሞ ተገንጣዮች በወጣቱ ላይ የቋንቋ ጥላቻ እንዲያድርበትና፤አገራዊ የመረዳጃ “ቋንቋ” አማርኛን “የመማር እገዳ” የጫኑበት ወንጀል እጅግ አሳዛኝ የመሆኑ ሁኔታ እንዳይበቃ፤ሃላፊነት በጎደላቸው የነቀዙ ምሁራን ኦሮሞዎች በኩል ወጣቶችን ለፋሺስታዊ አመለካካት ዳርጎአቸዋል። ኦብነግም ከዚህ የተለየ አይደለም።
ለምሳሌ፤ ባለፈው የታየው ኦሮሞ ወጣቶች እንቅስቃሴ፤ ክልላዊ የነገድ ጥቅም አስከባሪ ከመሆን አልፎ፤ የመገንጠል ጥያቄን እና ባይተዋርነትን የሚያጎለብት “ኢትዮጵያዊ ግንዛቤ የሌለው” ሥር ነቀል የስርዓት ለውጥ የማያመጣ፤የአገሪቱን አስኳል አናግቶ “መሪ የሌለው ወደ አናርኮ ፋሺዝም” የሚያመራ፤ “ራእዬ ቢስ” የተገንጣዬች አብዮት የበከለው እንደነበር ከሌሎቹ ሃያሲያን ተለይቼ መተቸቴ ይታወሳል።
ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ብየ ነበር። ፓኪስታን/ኤርትራ/ሶማሊ/….የመሳሰሉ በጭቆና፤በወረበሎች፤ በነገድና በሃይማኖት ግጭት እየታመሱ በመዋለል፤ ለቀውስ የዳረጋቸው ምክንያት የዛው አካባቢ ምሁራኖች (ሃይማኖታዊ እና ዓለማዊ ምሁራኖች) “የነቀዘ ሕሊናቸውን” በሕዝቡ ላይ በማራባት ስራ ላይ በመዋሉ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥም ጤነኞቹን ብቻ በማስጠጋት እነኚህን ከወንጀለኞቹ በመለየት የራሳቸው ባንዴራ ያውለበለቡ ‘ተገንጣዮች’ “በወንጀል የተጨማለቁና የተሳተፉ ነብሰገዳዮችና ጊዜው ያለፈበት ባንዴራን ሰርተው ሚያውለበልቡ የነቀዙ፤ እና የፋሺስት ርዕዮት ያነገቡ ድርጅቶች እንደ ኦነግ እና ኦብነግ የመሳሰሉትን” ወደ ጤነኛ ፖለቲካ ከመቀላቀላቸው በፊት፤ ጊዜአዊ የሆነ  ‘ፖለቲካዊ እገዳ’ አካልተደረገላቸው፤ እጣ ፈንታው የነ ፓኪስታንና የነ ደቡብ ሱዳን “ግርግር” ትክክልኛ ቅጂ በአገራችንም ውስጥ ይደገማል።
ታገዱም አልታገዱም ወንጀል ስለሰሩ፤ ሓጢያታቸው ሲነገር “አሻፈረኝ’ ብለው ወደ ግርግር እንደሚሄዱ ርግጥ ስለሆነ፤ ቅድሚያ ዘው ብሎ ግምባር ፈጥሮ የፕሮፓጋንዳቸው መሰላል መሆን ከወዲሁ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው የፖለቲካ ብልት ነው። አብዛኛዎቹ በወንጀል የተሳተፉ ናቸው።ነብስ ጠፍቶ ደግሞ ግርግር ፈርቶ፤ የተገዳዮችን ጩኸት መልሶ መቅበር፤ ተበዳዮቹ ነፍጥ እንደሚያነሱም ከወዲሁ ማወቅ ብልሕነት ነው። አማሮች ወደ መደራጀቱ እያመሩ ያሉትም ምክንያት ለወደፊቱ አቤቱታቸው በነ በርሃኑ ነጋ ዓይነቶቹ ‘አድርባዮች’ በሰላምና መረጋጋት ስም ለሥልጣን ሽሚያ በድፈን ድፍን እንዳይሸፈን ስለሰጉ ነው።

ሁኔታው ሁሉ ወደዚያውም እያመራ እንደሆነ ተከታዮቻቸው በጥንቃቄ ሊያዩት ይገባል። ቴምፐራሪ ፊክስ/ጥገና/ጊዜያዊ ምርቃና እንጂዘላቂኢፎርያ”/ “እፎይታንአያመጣም።

በዚህ አጋጣሚ ኦጋዴን የማናት ለሚሉ ጠያቂዎች መልስኦጋዴንእንጂኢትዮጵያዊያንአይደለንም ለሚሉ! በሚል ርዕስ የተቸሁበትን መከራከሪያ http://welkait.com/?p=3172 welkait.com ወይንም Ethiuopatriots.com ወይንም በራሴው ድረገጽ ተመልከቱ። አመሰግናለሁ- ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com