Wednesday, December 8, 2021

ኢትዮጵያን ለማፍረስ የትግሬና ኦሮሞ አስተዋጽኦ ጌታቸው ረዳ (ETHIO SEMAY) 12/18/2021


ኢትዮጵያን ለማፍረስ የትግሬና ኦሮሞ አስተዋጽኦ

ጌታቸው ረዳ

(ETHIO SEMAY) 

  12/8/2021

“ታሪክ” ይላል ሄግል የተባለው ጀርመናዊ ፈላስፋ  “ታሪክ የእርድ ቤት ነው”; ይላል። ምን ማለቱ ነው? ታሪክ ‘ግለ ሰብ፤ የሕዝብና የድርጅት መሪ ወይንም ንጉሥ “ሃያልነታቸው ሲሟሽሽ” የሰሩት ስራ ሁሉ ምሕርት ሳይሰጥ እገሌ ከእገሌ ሳይለይ በነበራቸው “የሞራል መበስበስ’ የደበቁት ወንጀልና ስርቆት ካለ አንዱኑም ሳያስቀር ያለ ምሕረት ይፈርዳቸዋል” ማለቱ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከንጉሡ መወገድ በላ በከፋ መልኩ  “ሃገራዊ ፍቅር፤ ቅንነት ጨዋነት ታማኝነት እና ፈሪሃ ሕዝብ” ተወግደው “ሃገር አፍራሽ፤አታላይ፤ባለጌ፤ቀማኛ እና ሕዝብን የሚያሰቃዩ ሞራለ ቢስ” መሪዎችና ተከታዮቻቸው ተተክተው ኢትዮጵያ በክፉ ማዕበል እየተንገላታች ወደ መበታተን ደርሳለች። 

ብዙ ሰዎች በዲያስፖራ ትግላችን ዘመን ‘ለምንድ ነው አንተ “ሁሉንም የምትቃወመው” ሲሉኝ ነበር፡ ኦነጉን፤ ኢሳቱን፤ ታማኝን፤ ብርሃኑን፤አንዳርጋቸውን፤ ብርቱካንን እና የተቀሩት ግንቦት 7 አማራር በሙሉ፤ እና ደላላ ሊሂቃን አማራ ግሰቦች የመሳሰሉ ሁሉ “ውለው አድረው” የአገሪቱ አንቅፋቶች ሊሆኑ ነው፤ ሥርዓት ሲለወጥም ጸባችንም ባይገርማችሁ ከነዚህ ጋር ይሆናል፤ ስላቸው “ብዙዎቹ”  አይወዱኝም ነበር”። አሁን ገብቷቸዋል ብየ በጥቂቱ እያየሁ ነው፤ (በሞላ ጎደል)።

ከዚህ ተነስቼ የአገራችን ችግር ተደጋግሞ የሚያገረሸው የመጠፋፋት ምክያት፤ ‘ደግሜ ደጋግሜ’ ለበርከታ አመታት እንደገለጽኩት “ወንጀለኛ መሪዎች እስካሁን ድረስ ለፍርድም ይሁን ለኑዛዜ በሕዝብ ፊት “ባለመቅረባቸው” ሥርዓተ መንግሥቱ ይዞት የነበረ አንድ ወንጀለኛ መሪ ሲወገድ በሌላ ተመሳሳይ ወይንም የከፋ ወንጀለኛ ቡድን እየተተካኩ በመቀጠላቸው ምክንያት አገራችን የረጋ ህይወት ልታገኝ አልቻለችም። ህጉ የድርጅቶች የግል መጠቀሚያ በመሆኑ ወንጀለኛ ባለስልጣኖች ወደ ሕግ በቀረቡ ቁጥር አንዱ አንዱን የማጥቂያ ስልት በማድረግ ሕጉን የቂም መወጣጫ እያደረጉት በመሄዳቸው ችግሩ ቀጣይ ሆኗል።

 አሁን የረጋ ህይወት ይቅርና “ጥንታዊትዋ አገር አንደ አገር የመቀጠልዋ ዕደል በግምት ብናሰላው ፤ “ያልጠበቅነው ተአምር” ካልተከሰተ በቀር በአንድነትዋ የመቆየት ዕድልዋ ከ10% ከፍ አይልም። ያ ካልሆነ ደግሞ ጦርነቱ ቀጣይ የመሆኑን ሁኔታ አይቀሬ ሆኖ ለሕዝበችን ሌላ ስቃይ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው።

አሁን እንደማየው፤ ባጭሩ “ፈርሳለች” ብለን ብንል “ከወደቁ መንግሥታት” ያሰልፋታል። ይህ እርግጥ ነው።

በሁለቱም ወገን ያሉት ተፋላሚ ወንጀለኞች ሆን ተብሎ ጦርነት በመክፈት የሰሩት ወንጀል በሕግ እንዳይፈረዱ ጦርነቱ መሸሰጊያና ማምለጫ አድርገውታል። ህዝቡ እያለቀ የቂማቸው መወጣጫ ጭዳ አድርገውታል።  

በፍርዱ ሂደት ሲፈታተሹም  አንተም እንደ እኔው ወንጀል ስለሰራሕ ‘አንተ እኔን የመፍረድ መብት የለህም አንተ አትፈርደኝም’ ፡ የሚል ፍጥጫ ጦርነቱን አፋፍመውታል።ሕዝቡ የነሱ ሙርከኛ አድረገውት መፈናፈን እና በነፃ ማናገር አልቻለም።

ይህ ሊሆን የቻለው የተማረው ክፍል ከወንጀለኞች ጋር በማበር ወይንም ገለልተኛ ተመልካች ሆኖ በመቀጠሉ አገሪቷ የመዋለል ዕድል ገጥሟት መልሕቅዋ የለቀቀች አገር ሆናለች።

ወያኔ፤ኦነግ፤ አክራሪ ጉምዝ፤ እስላማዊ ኦነግ፤አልሸባብ… ወዘተ…ወዘተ.. አገሪቱን እየጨፈጨፉ ኑሮ  እያመሳቀሉ አናርኪው በየቦታው ነግሶ “ሕግ አስከባሪው ፤ሌላ ተጨማሪ ህግ አፍራሽ በመሆኑ ግድያና ዘረፋ በመስፋፋቱ ምክንያት “ፌይልድ ኔይሺን” ነች የምለው ለዚህ ነው።

አሁን በሰላማዊ ሰልፍም ይሁን በፖለቲካው ጉልህ ሱታፌ እያደረጉ ያሉት የምሁሩን ብዛት ላለፉት 27 አመት የት ነበራችሁ ብላችሁ ብትጠይቁዋቸው “መልስ የላቸውም”። ትግሬው እና አሮሞው ለ27 አመት ሙሉ ተደራጅቶ “አገር የማፍረስ አጀንዳው” ሲሰራ ነበር። ተሳክቶላቸዋልም።

በሁለቱም ሊሂቃን ጥርስ ተነክሶበት ሲገደል፤ሲባረር፤ሲሰደብ የነበረው የአማራው ማሕበረሰብ የወለዳቸው ምሁራን እና ወጣቶች “ችግሩ እያዩትም ቢሆን” ለትግል እንዲነሱ ስንገፋፋቸው፤ ብዙዎቹ ጸረ አማራ ከሆኑ ድርጅቶች እና አጭበርባሪ ግለሰቦች ጋር በመወገን፤ ለነሱ ጥብቅና ቆመው “በገንዘብም፤ በተዋጊነትም፤በፕሮፖጋንዳውም” እየተሳተፉ፤ እኛን እየዘለፉ “ጥርሳቸው እየፋቁ” በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ይቀልዱ ነበር።

የፕሮፌሰር አስራትን ፎቶግራፍ ይዞ ከመሰለፍ ይልቅ የጸረ አማራው በቀለ ግረባን ፎቶ ግራፍ ይዞ የጎንደር ከተማ  ወጣት “ኦሮማራ” የሚል የማታላያ ዘፈን እየዘፈኑ ሲጨፍሩ አይቼ በመተቸቴ “ጆኒያ ሙሉ ስድብ” ተሰድቤአለሁ። ያሰለፍነው እንዲሁ ሲነገር ቀላል ይመስላል፤ ለኔ ግን በሁለቱም ወገን እንደ ቀርቃር አስገብተው ጫናው ቀላል አልነበረም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ የአገር ፍቅር ትርጉም ‘ለግብዝነት’ ቦታ ለቆለታል። ትግሬው ከሥልጣን ሲባረር፤ ኦሮሞ በቦታው ተተክቶ “ኢትዮጵያና እግዚአብሔር” የሚሉ ቃላቶች በአማራው ዘንድ ስለሚወደዱ እነዚህ ቃላቶች አጉልቶ በማስደመጥ ኦሮሞዎቹ “አሁንም አማራዎቹን” በማኖህለል ሥራ የተካነው “የኦሮሞዎቹ ተወካይ” አብይ አህመድ ለሁለተኛ ጊዜ ሊሂቁና ያልተማረው “ያልነቃው ግብዝ አማራ ሴትና ወንድ” ወደ ጨፋራ ካምፑ ለማስገባት ችሏል።

ለዚህ ነው ደግሜ ደጋግሜ ስለው የነበረው “አማራ ሌላ ጠላት አሸንፎት ሳይሆን ፤አማራ የራሱ ጠላት ነው” ብየ ስሞግት የነበረው።

 ይህንን ስላልኩ ስንኙ ያልገባቸው ብዙዎቹ አልተደሰቱብኝም።

ዛሬ በርካታ ግብዝ ሕዝብና ምሁር በአጃቢነት ተሰልፎ በዚያ ጎራ ይሁን በዚህ ጎራ ማለትም በግራም በቀኝም የወንጀለኞች መጠቀሚያ ሆኖ አገሪቱን በማፍረስና በመገዝገዝ ሥራ ተጠምዶ እያያን ነው። ትግሬዎች እና ኦሮሞዎች ኢትዮጵያ አፍራሾች ናቸው ስንል ማመን ያቃታቸው ሰዎች እነሆ ዛሬ ፊታችሁ ላይ ቆሞ እያያችሁት ነው።

እንዲህ ስል ምን ማለቴ ነው?

ትግሬዎች ከ1967 እስከ 2010 ዓ.ም የነበረው ሲዋጉም ሆነ የገዢ መደብ ሆነው ዓላማቸው አንድ እና አንድ ነበር። “ኢትዮጵያ ትግሬዎች እስከገዝዋትና እስከመዘበርዋት ድረስ እንደ ኢትዮጵያ ዜጎች ሆነው ይቀጥላሉ፤ ያስቀመጡት “የሙሶሎኒ ሕገመንግሥት” የሚያስወግድ ሃይል ከመጣ ግን “ወደ እየመንደራችን እንበታተላለን ወይንም ያንን ለማስከበር ወደ ሁለተኛ ዙር “ጦርነት” አንገባለን አሉ። ባሉት መሰረት ጦርነት ከፈቱ።

 አሁን ትግራይ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ጦርነት በመግጠሟ “ኢትዮጵያ አይደለችም” “ዲፋክቶ ሃገረ ትግራይ ” ሆናለች። እነሱም “ሃገረ ትግራይ” ብለው ሰይመዋታል።

ኦሮሞዎቹም በ1965 ዓ.ም አደገኛ ፋሺሰቶችና አክራሪ እስላማዊ ኦሮሞዎች ተሰባስበው እነሱም ልክ እንደ ጣሊያኖቹ “አማራና ኦርቶዶክስ” ቀንደኛ ጠላትና መጥፋት ያለባቸው ናቸው ብለው አጀንዳ በመቀየስ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ “ራስን በራስ ማስተዳር በሚል ኮሚኒስታዊ የማጃጃያ ጥበብ በመመስረት “ኦሮሚያ” ተብሎ የሚጠራ አገር ለመመስረት አቅደው ብረት በመያዝ ከደርግ ዘመን ጀምረው እስከ አሁንዋ ደቂቃ በነበሩት አሰቃቂ ስርዓቶች መሪ ተዋናዮች ነበሩ።

 በቀየሱት ዘዴም ቀስ እያሌ አማራን ማጥፋት ጀመሩ፤ አማርኛ ሚባል ቋንቋም ከኦሮሞ አካባቢ እንዳይደመጥ አደረጉ። በምትኩ የላቲን ፊደል አስተዋወቁ። የኦሮሞ ተማሪ ብሔራዊ መግባቢያ ቋንቋ አማርኛ እንዳይማር ስላገዱት ከኦሮሞ ‘ክልል’ ውጭ ሌላ ‘ክልል’ ተቀጥሮ መስራት አይችልም። ማሕይመነትን አነገሱበት።

 

ለ17 አመት በደባልነት ይዘውት የነበረው ሥልጣን አሁን ሙሉ በሙሉ ሥልጣን ይዘው አብይ አሕመድ ከውስጥ ድጋፍ እያደረገላቸው “አማራውን እና ክርስትያኑን እንዲሁም ጋሞውን…” እንዲጨፈጭፉት ተደረገ። ዛሬ ኦሮሞ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ  በታሪክ የማይታወቅ “ኦሮሚያ” በሚባለው “ክልል” መኖር አይችልም። ሙሉ በሙሉ አገር ሆኖ “ኦሮሚያ ለኦሮሞ” የሚለው አጅንዳቸው እውን አድርገዋል።ጋሞ ወይንም አማራ ወይንም ክርስትያን የሆነ ሰው ለህይወቱ የማይራራ ካልሆነ በቀር ማንም ደፍሮ ወደ ኦሮሞ ክልል መዞር አይቻልም። የተከለከለ አጥር ነው (ዲፋክቶ አገር ሆኗል ማለት ነው)

የተቀሩት አዲስ አባባ እና ጥቂት ቦታዎች ናቸው ፤ ያም እውን እየሆነ የመሬት ወራራ ተካሂዶ ኦሮሞ ከንቲባ፤ኦሮሞ ጠ/ሚኒስተር፤ ኦሮሞ ፖሊስ ጠቅላላ አዲስ አባባ በአረመኔያዊ ብትራቸው እያስተዳደሩት ይገኛሉ።

 ተቃናቃኝ ካገኙ ልክ እንደ ትግሬዎቹ  “ፓርላማ ውስጥ የሰገሰጋቸው አክራሪ ኦረሞዎችን ተጠቅሞ ‘አብይ  አሕመድና ጀሌዎቹ’  አላፈርሰውም እያለ የተናገረበትን ሕግ መንግስት ተጠቅሞ አገር ይመሰርታል። ላታምኑ ትችሉ ይሆናል፤ ግን የጊዜ ጉዳይ ነው። የሚከተሉት ሕገመንግሥት ማየት በቂ ነው።

አሁን “ትግራይ ዲፋክቶ አገር ነች”፤ “ኦሮሚያም እንደዚሁ”። እንዴት ሊሆን ቻለ? ማንስ ነው ተዋናዩ?

መልሴ ይኼው፡

በ666 እሉሚናቲዎች አጀንዳ መሰረት ሊፈርሱ ከታቀዱ  አገሮች መካካል ኢትዮጵያ በተጠቀሱት አገሮች እንዳለች ካሁን በፊት ተንታኞች ባስነበቡን አንድ ሰነድ አይተናል። ሶማሊያ ሱዳን፤ የመን፤ሲሪያ ሊቢያ ወዘተ…ተራዋ የደረሳት ኢትዮጵያ እየተንገዳገደች ጣሊያንን አስወግዳ ቆየች።

ተራዋ ደርሶ “እንደ ከብት አንገትዋን ከቆረጡዋት 30 አመት ሆኗታል። የተቀረው ካንገት በታች የቀረው ገላዋ ደግሞ በአፍሪካ ውስጥ የኢሉሙናቲዎቹ “ወኪል” በነበረው መለስ ዜናዊ በኩል “ጣሊያን ያቀደውን ኢትዮጵያን የማፍረስ ተግባር እውን በማድረግ” የባሕል፤ የሰንደቃላማ፤ የሃይማኖት ብረዛ በማከናወን” ሕዝቡ እንዲባላ ሃላፊነት ወስዶ እውን አደረገ።

 

ወጣቱ ነገዱ እንጂ ‘ኢትዮጵያ’ የምትብል አየኖረባት ያለቺውን አገር እንዳያውቃት ተደረገ።

መለስ ሲሞት ወደ ሥልጣን ከመሸጋገሩ በፊት  የአሜሪካኖቹ ስለላ ተግባር ለአባልነት “|ሥልጠና ወስዶ” ነብር ተብሎ የሚወራለት ሌላው “ኡሉሙናቲው ‘ወላይታው” ሃይለማርያም ደሳለኝ አጅንዳቸውን ቀጠለበት።

 

ከዚም አብይ አሕመድ የተባለው የሞሳድና የአሜሪካኖች ጀሮ ጠቢ ነው ተብሎ የሚታማው ኦነግን በገንዘብም በመረጃ አስተላላፊም “ሕቡእ አባል” ሆኖ ሲያገልግል የነበረው የ “ኦሮሙማ” ኣጀንዳ አራማጅ ባለ ተራው “አብይ አህመድ” መጥቶ ወያኔዎችን ተካቸው።

 

ኦሮሞን ለመግንጠልና ትግራይን ለመገንጥል ሁለቱም ወንጀለኞች ድብቅም ግልጽ የሆነ ሴራ እየሰሩ ናቸው ስል ከምንም አልተነሳሁም።

ወያኔ በግልጽ እንደሚገነጠል አውጆ ጦርነት ከፈተ፡ መክፈት ብቻ ሳይሆን አማራው አምርሮ ትግሬን እንዲጠላና ዘላቂ ቅራኔ እንዲፈጠር ለማድረግ “አብይ አህመድ” በከፈተላቸው የመግቢያ “ኮሪደር” ተጠቅመው ከትግራይ ገስግሶ አማራ የተባለ ከተማና ገጠር እንስሳ ሳይቀር በመጨፍጨፍና በመዝረፍ ሴቶችን በማመጽ፤ የጤናና የትምሕርት እንዲሁም የትራንሰፖርት ድርጅቶችን (አየርፖርትን) በማፈራረስ የኢንተርሃሙዌው አጀንዳው አከናወነ።

ወያኔ ጥላቻን ሲያስፋፋና የአማራ አካባቢ ሲያወድም፤ አብይ አሕመድ ደግሞ ያንን የከፈተላቸው ኮሪደር ተጠቅመው ንብረትና ሰው ካወደሙ በላ “በሁለት ሳምንት (?) የያዙትን በርካታ ቦታዎች አስለቀቃቸው።እንዴት ሊአስለቅቃቸው ቻለ የሚለው አስገራሚ ክስተት  ጥናቱንና ግምታቸውሁን ለናንተ ብተወው መልካም ነው።

ያ ሁሉ ካደረገ በላ የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት ይብቃኝ እንዲል “ትግራይ የሚባል በሙሉ ጤነኛም በሽተኛም ፤ፖለቲካ ያለውም የሌለውም በጅምላ ልክ እንደ ‘የጀርመን ናዚ’ አብይ አሕመድም ትግሬ የሆኑትን የኔን ቤተሰቦች  ሰብሰቦ አገሪቱ ውስጥ ባሉት ከተሞችና ገጠሮች ትግሬዎች እየተደበደቡ በጅምላ እየታፈሱ እንዲታሰሩና ከሥራቸው እንዲፈናቀሉ በማድረግ “የትግራይ ሕዝብ” ኢትዮጵያዊነቱን ጠልቶ ፡በቃኝ እንዲልና ‘የወያኔ አጀንዳ’ “አገረ ትግራይ” እንዲመሰርት፤ የሕሊና ጫና በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የሩዋንዳው ዓይነት የኢንተርሃሙዌ “ሴራ” እንዲቀጣጠል እየገፋበት ይገኛል ነው።

እነዚህ ሁለት ሴራዎች ተጠቅመው ወያኔና የኦሮሙማው መሪ ኢትዮጵያን አፍርሰዋታል  የምለው ለዚህ ነው።   

አብይ እንዴት ጉልበት አግኝቶ እንደ መሪ ሊሞገስ ቻለ?

 አብይ አሕመድ ጦርነቱን በመጠቀም ብዙ ግብዞችን በማሰለፍ ያልጠበቀው ድጋፍ በማግኘት ከወንጀለኛ የመጠሪያ ስም ወደ “አርበኛነት” ደረጃ ተሸጋግሯል።

እንደሰማሁት ከሆነ ለምሳሌ እነ ታማኝ በየነ ያዘጋጁት ይመስሉኛል “የታወቁ ገናና ኢትዮጵያ ነገሥታትና ቅርሳቅርስ የያዘ ፎቶግራፍ ለጨረታ ቀርቦ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ሲደረግ የሰማሁት አስገራሚ ዜና ሰምቻለሁ።

አንዱ “የአብይ አሕመድ ምስል፤ የአጼ ቴድሮስ፤ንግሥት ጣይቱ፤ አፄ ሚኒለክ /ፋሲል ግምብ/” ( የአጼ ዮሐንስ  ምስል አልቀረበም፤ምናልባት ትግሬ ስለሆኑ በሚል እንደ ጠላት ታይተውም ሊሆኑ ይችላሉ ምስላቸው ለጨረታ አልቀረበም።(የኔ ግምት ነው፤ ለጨረታ ከቀረበ ንገሩኝ፤ስለ ጨረታውም የሰማሁት ከኢትዮ360 ሚዲያ በጨረፍታ ነው ) በዛው ጨረታ ውስጥ 3ሚሊዮን ብር  የጨረታ አሸናፊ ሆኖ በከፍተኛ ገንዘብ የተሸጠው የአብይ አሕመድ ምስል እንደሆነ ሰምቻለሁ።

 ይህ የጀሌውና የግብዙ ብዛት ተዋናይ ማሳያ ማስረጃ ነው።

ትግሬዎች የንጉሥ ዮሐንስ በጨረታ ያለመቅረብ ሲሰሙ የበለጠ የመግንጠሉን አባዜ ለፕሮፓጋንዳ ሳይሆን እውነታነቱን ያጠናክርላቸዋል ማለት ነው። ይህ ሴራ ካሁን በፊት ሔኖክ አለማዮህ የተባለ የዘሓበሻ ድረገጽ አዘጋጅ’ የዛሬ አብይ አሕመድ ጀሌ (ድሮ ደግሞ የመኔሶታ ኦነግ ጀሌዎች አጨብጫቢ) የነበረው “ያመኛል በለው” የሚል ዘረኛ ሙዚቃ “ጦረኛው ንጉሥ ዮሐንስ” (ጎጃም ውስጥ በደል ፈጽመዋል በሚል ይመስላል፤ (ጸረ አማራ የሚል የከብቶች እምነትም ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ) በምትካቸው ተከታያቸው የሆኑት “በባንዳነትም ከጣሊያን ጋር የተዋዋሉት የራስ አሉላን” ፎቶ በሙዚቃው ቀርቦ  ታትሞ ነበር።በወቅቱ  በታተመው ዘረኛ ሙዚቃ ትችት አቅርቤበታለሁ።   

 “ይህ አንኳን ዘንቦብሽ ድሮውም ጤዛ ነሽ” የተባለው ምሳሌ ዛሬ ትግሬዎች በነበረው ተጨማሪ ለሕሊና መኮብለል ማምለጫ ምክንያት የአብይ ጀሌዎች “ሳያውቁት” ግፊት ያደረጉ ናቸው ማለት ነው።

አሁን መፍትሔው ምንድነው? የሚለው ከባዱ ጥያቄ ነው።

ወንጀለኞች በሁለቱ በኩል ተዋናዮች እስከሆኑ ድረስና የነዚህ ሁለት ወንጀለኞች ተከታይ ግብዝ ልሂቃኖች በርካታ በመሆናቸው መፍትሄው የተቆለፈ ነው።

የዕልቂቱ ቀጣይነት እንጂ በቅርቡ መፍትሄ ሊታየኝ አልቻለም።መልስ ካላችሁ ንገሩኝ። “ትገንጠል” የሚለው የግብዞች መልስ አልፈልግም፤ “ያው ከተገነጠለች ስለቆየች”፤ ልሰማ የምፈልገው ግን “ሌላ መፍትሄ ካላችሁ ልስማችሁ እፈልጋለሁ። በሁሉም ወገን ያሉት ወረበሎች ለማስወገድና አገሪቱን አንድ አድርጎ ለማስቀጠል መፍትሔው ምን ቢደረግ ምን ይመስላችሗል?

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ ETHIO SEMAY