Saturday, November 30, 2024

የ6 አመቱ የኦሮሙማ አንደበቶች ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 11/30/2


         የ6 አመቱ  የኦሮሙማ አንደበቶች

       ጌታቸው ረዳ

      Ethiopian Semay 11/30/24

 ሰሞኑን አንድ ወጣት እንደ በግ አጋድመው አንገቱን ሲያርዱት የሚያሳይ ቪዲዮ እንደተሰራጨ ሰምተናል። አሰራጪዎቹም አራጁ ፋኖ እንደሆነ  የአብይ ኦሮሙማ ባለሥልጣኖች በኦነግ ሚዲያ ላይ ቀርበው መናገራቸው አድምጠናል። አራጅ ሆኖ የተገኘው ግን ኦሮሙማው ቡድን እራሱ እንደሆነ በማስረጃ ቀርቦ አይተናል።

በኦሮሙማ መርህ የሚመሩ የኦሮሞ ዩኒቨርሲቲ ት/ቤት ወጣቶች ግድያው በፋኖ ተፈጽሟል ተብሎ ስለተነገራቸው አድማ መምታታቸው አይተናል። ያ ዜና አየር ላይ እያለ፤ ከትናንት በስትያ በሚገርምና በሚያሳዝን መልኩ ግን አርሲ በሚባለው 99% እስላም በሆነው 1% አምሐራና ኦርቶዶክስ የሆነ ኗሪ ግን አንድ ቃል ከተናገረ በሜንጫ አንገቱ የሚቀላበት የጃዋር ትውልድ ቦታ በርካታ ሰዎች ተቀልተውና ታርደው መሞታቸው ቢዘገብም እነዚያ አድማ በመምታት ፋኖን እና አምሐራን በመዝለፍ መሬት ሲያውኩ የነበሩ “ተማሪዎች” ድምጻቸውም ከቶ አልተሰማም።  ይህ የኦሮሙማ ፕሮጀክት አንዱ ክፍል ነው። ኦነግ ማለት ብዙሓኑ የኦሮሞ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ድርጀት ነው። "ኦነግ" ማለት ኦሮሞ": "ወያነ" ማለት "ትግራይ ሕዝብ" ነው ስለው የከረምኩት ለዚህ ነው። ብዘሓን የሚባሉት ትግሬዎችም ሆኑ ኦሮሞዎች “ጣቱ” ክፍል ነው። ወጣቱ ደግሞ የነዚህ ድርጅቶች አማኝ ነው።

        የዛሬዋ ኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ማንበብ የማይፈልግ ፎቶግራፍ ብቻ የሚያደንቅ ብዙ ደንቆሮ የተሸከመች ምድር ነችና እስኪሰለቸን ደጋግመን ስለዚህ “ኦሮሙማ” የሚባለው ፕሮጀክት/ግብ/ ፈልሳፊው ማን እንደሆነ ግቡና “ቅኔው/ፊቹን” ማሳወቅ ስላለብን ቢሰለቻችሁም እየመረራችሁ ዋጡትና ኦሮሙማ ምን ማለት እንደሆነ ከነግቦቹና ነግግሮች ለማየት ይህንን ማስረጃ አንቡቡ።

 ዘመናዊ ትምሕርት በቀሰሙ የኦሮሞ “ምሁራን” እምነት “ኦሮሙማ” የሚል ቃል <<ኦሮሚያን በቅኝ ግዛት የያዘው የአቢሲኒያ (ኢትዮጵያ) ተስፋፊነት ማለትም የቢሲያኒ ሃበሻዎች ሥልጣኔ ባሕል ፤ቋንቋ፤ እና ሃይማኖት የሚጻረር ነጻ አሮሚያ ለመመስረት የምንጠቀምበት አታጋይ መርህ ነው>> በማለት << (ኦሮሙማ) ኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን የዐምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነው።>> ሲሉ

 አንዳንዶቹ ደግሞ <<ኦሮሞነት>> ማለት እንጂ የኢትዮጵያን አንድነት የሚጻረር ባሕሪ  ነገር የለውም ሲሉ ሰምተናቸዋል። ከላይ ያለው የመጨረሻው አባባል   የዋሃን ሊያታልል ይችል እንደሆን እንጂ ከሥር መሠረቱ የቃሉ አመጣጥና የቃሉ ለውጥ ከጥንት የተጻፉ መጻሕፍት ስንመረምር እነሱ እንደሚሉት ሳይሆን ትርጉም ያለው የዜግነትና ሌላ ሃገርነትን የሚመኝ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ የሚያልም አጠራር ነው።

        ስሙን የተፈለሰፈው በ18ኛው ክ/ዘመን ጀርመኖች የላኩት በጀርመናዊው የፕሮተስታንት ሚሺነሪ በምስራቅ አፍሪቃ የተመደበው የቅዥ ግዛት አስፋፊና ሰላይ የነበረው <<ዮሃን ክራፕፍ>> ነው።

ቃሉ “ዛሬ ኦነጋውያን ኢትዮጵያዊነትን ለመተካት የብሔረተኝነት መገለጫ አድርገው የሚያቀነቅኑት ኦሮሙማ ዕሳቤም መሠረቱ የተጣለው ኦርማኒያ  (ጀርመኒያ ከሚለው ተመሳሳይ የቅጂ ትርጉም) ከሚለው በክራፕፍ እሳቤ ውስጥ ነው የዛሬው “ኦሮሙማ” ስያሜ የመነጨው።

“ዐምሐራ ሕብራዊ ማንነቶችና ተግባሮች” የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው ይህንን በማስረጃ ለማጠናከር ሲያቀርበው በገጽ 365 ክራፕፍ የዘገበውን እንግሊዝኛ እና አምሐርኛ ትርጉም እንዲህ ይላሉ፡

<< …their language they call “Afan Orma” the mouth of the Ormas; so as the Ga*ll*as have no general name to indicate their nationality or its seat, I propose to include both the designation of Ormania” (Travels, Researches, and missionary Labors, During an Eighteen Years’ Residence in Eastern Africa p.61)

ይህንን ወደ አማርኛ ሲተረጉመው

<<ጋ..ሎ…ች ቋንቋቸውን “አፋን ኦርማ” ይሉታል የኦርማዎች አፍ ብለው ይጠሩታል እናም ጋ..ሎ…ች ዜግነታቸውን ወይም መኖሪያቸውን የሚያመለክት አጠቃላይ የሆነ የጋራ  ቦታና ስም ስለሌላቸው መኖሪያ ቦታቸውን ይገልጥ ዘንድ “ኦርማኒያ የሚለውን መጠሪያ ሰጥቻቸዋለሁ።” ብሏል (ዮሀን ክራፕፍ)

 ቅስ እንደላይኛው። (ሰረዝና ድምቀት የተጨመረ)

“ዮሀን ክራፕፍ” ማለት የኢትዮጵያን አንድነትና ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለመበተን የተላከ ለዛሬዎቹ ኦሮሞዎች ላቲን ፊደል ቀርፆ የሰጣቸው ጀርመናዊ ፕሮተስታንት ሚሺኔሪ ነው። የሸዋ ኦርቶዶክስ አምሐራዎች ስለተከራከሩት የሸዋ አምሐራዎችን “ቆሻሾች” ይላቸዋል። ኦነጎች አምሐራን የመጥላት አባዜ ከየት እንዳገኙት ምልክቱን እዩት።

የክራፕፍ ውጤቶች የሆኑት የዛሬ ዘመን ኦሮሞ ምሁራንም ከላይ የተጠቀሰውን ሲያጠናክሩት በአንደበታቸው እንዲህ ሲሉ ያረጋግጣሉ፡

<< ኦሮሙማ “ኦሮሞነት” ነው ኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው የተለየ የሚያደርገው የኦሮሞን ማንነትና አጠቃላይ የሆነ ባህላዊ፤ ማህበራዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ልሳናዊ፤ ታሪካዊ ግዛታዊና ስነ ልቦናዊ ባህርያቶችን አንድ አድርጎ የያዘ መገለጫ ነው። ኦሮሙማ ኦሮሞዎች እንደ ሕዝብ የሚኖሩበትን ማረጋገጫ የሚሰጥ ማንነት ነው።>>

<<የኦሮሞ ስነ ጽሑፍ እና የወንጌላውያን እንቅስቃሴ በብዙ ኦሮሞች ዘንድ በተለይ በመሪዎች ዘንድ የኦርቶዶክስ ካሕናት ሊጭኑባቸው የሚሞክሩትን የዐምሐራውን ባሕልና ቋንቋ በመቃወምና ተጽዕኖውን በመቋቋም እንደ አስተማማኝ ግብረመልሳዊ አማራጭ ተደርጎ ይታይ ነበር>> (The Journal of Oromo Studies  VOLUME 9, NUMBERS 1 AND 2, JULY 2002 P.73) (The Journal of Oromo Studies  VOLUME 1 NUMBERS 1 AND 2, Winter 1994 p.97) (ምንጭ ዐምሐራ! ሕብራዊ ማንነቱና ተግዳሮቱ- ባንተአምላክ  አያሌው - ገጽ 365-366)

እንግዲህ ክራፕፍ የፈለሰፈላቸው “የኦሮሙማ ትርጉም” እና ለመጻፊያ የፈጠረላቸው የላቲን ፊደል እንዲሁም እንዲከተሉት ያስተማራቸው የጀርመን ፕሮተስታንት ባሕሪዎች የተቀኙት ኢትዮጵያን እንዲጠሉ የተቀረጸ አጀንዳ ስለነበር ኢትዮጵያዊነትን አብዝተው ይገፉታል፤ ኢትዮጵያዊ ፊደል የኦሮሞነት ጠላት አድርገው ይመለከቱታል። በሜንጫ የምትቋቋም “የኦሮሚያ እስላማዊ ሀገር” እንድትኖርም በግሃድ ይሰብካሉ። <<ከሩዋንዳ እስከ ኦሮሚያ>> የታየው የዘር ዕልቂት “የሰለፊ እስልምና” እና “በ18ኛው ክ/ዘመን ወደ አፍሪካ የመጡ የጀርመን የፕሮተስታንትና የካቶሊክ ሚሺኔሪዎች የተቀነቀነ” እንደሆነ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው ይገልጻል።

  አሁን ያለው ኦነጋዊው አብይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት የተቃኘው በዛው መስመር  በመሆኑ እራሱና  የሾማቸው የባለሥላጣናቶች ንግግር ኦሮሙማ ምን ማለት እንደሆነ ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ደራሲ ባንተአምላክ አያሌው በመጽሐፋቸው   ለታሪክ ተዘግቦ እንዲቆይ  የዘገቡልንን እነሆ ለናንተም ይጠቅማልና እንመልከት፡

በመሪያቸው በአብይ አሕመድ ንግግር እንጀምር፡እነሆ፦

1ኛ- “ትናንት ያዋረደንን አዋርደነዋል፤ ትናንትና አትወጡም አትገቡም ብሎ አጥር ያጠረብን ዛሬ ወጥቶ መግባት ከእኛ ፍቃድ ውጭ አይችልም” (አብይ አሕመድ)

2ኛ- “ ሰው እየሞተ ችግኝ አይተከልም የሚለን ጠላት ነው፡ እንዳትሰሙት፡ ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን ቢያንስ አስከሬኑ ጥላ እንዲኖሮው” (አብይ አሕመድ)

3ኛ- “ታስሮ ጀግና ለመሆን የሚሯሯጥ ጋዜጠኛ አለ….፡ ምርጫ ሳታሸንፍ ባለአደራ ምናምን የሚባል ጨዋታ ውስጥ የምትገባ ከሆነ ግልጽ ጦርነት ውስጥ እንገባለን። ይህ መታወቅ አለበት”(አብይ አሕመድ)

4ኛ- “አዲስ አበባ ውስጥ ያለው ማሕበረሰብ ኦሮሞ ጠል ነው” (አብይ አሕመድ)

5ኛ- “ሰዎቹ (ዐምሐራዎች) የሚችሉት ሦስት ነገር ብቻ ነው፦ “ጩኸት፤ልቅሶባ ስም-ማጥፋት” ለአልቃሾች ብትችሉ መሀረብ (ሶፍት) ማቀበል እንጂ ምን አስጨነቃችሁ? ያልቅሱ ተዋቸው። እኔ የሚያስጨንቀኝ ዝም ሲሉ፤ ሳይነፋረቁ ሲቀሩ ነው።ዝም አሉ ማለት  እኔ እነሱን እያስደሰትኩ እንደሆነይሰማኛል…!” (ሽመልስ አብዲሳ)

6ኛ- ኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነበር የተሰበረው፡ እዚህ ነበር መዋረድ የጀመረው፡ እዚህ ነበር ቅስሙ የተሰበረው፤ ‘ቱፋ ሙናን’፤ የዚያን ዘመን ታጋዮች የነፍጠኛ ሥርዓት እዚህ ነበር የሰባበራቸው። ዛሬ የሰበረንን ሰብረን፤ ከመሠረቱ ነቅለን፤ኦሮሞ በተዋረደበት ቦታ ተከብሮ ይገኛል።” (ሽመልስ አብዲሳ)

7ኛ- አዲስ አበባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ሠፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት በዋቆ ጉቱ እና በታደሠ ብሩ ስም ትምህርት ቤቶች ከፍተን የሚማርልን ተማሪ አጣን። ስለዚህ ተማሪ ከቡራዩ እየጫንን እናመጣ ነበር፡፤ አምና የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዐብይ በሰጡት ውሳኔ መሠረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች አስጀመርን። ከ 5700 በላይ መምህራን አዲስ አበባ ውስጥ አስገብተናል።” (ሽመልስ አብዲሳ)

8ኛ- ዓባይን ተሻግረን ባሕርዳር ድረስ ሄደን ግማሹን Convince ገሚሱን Confuse አደርገን ቁማር ቆምረን ቁማሩን በልተን ተሳክቶልን ተመልሰናል። እንዴት አደናብራችኋቸው ነው የምትሉት? ምን አገባችሁ?” (ሽመልስ አብዲሳ)

9ኛ- አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን ህዳሴ ግድቡን ኦሮሞ መቆጣጠር እንዲችል ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ኦረሞዎችን በማስፈር ዲሞግራፊውን እየቀየረ ነው! ክልሉ ውስጥ ኦሮሞ 37% ደርሷል። (ሽመልስ አብዲሳ)

10ኛ- ብልጽግናን የሠራነው ለእኛ እንዲመች  አድርገን ነው። ብልጽግና የኦሮሞ ነው። ብልጽግና ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው የሚመራው።… አምስት ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም። ለኦሮሞዎች ብለን ነው። አማርኛ እየደከመ ነው፡ እየቀነሰ ነው። ኦሮምኛ ከአማርኛ በላይ እየተነገረ ነው።(ሽመልስ አብዲሳ)

11ኛ- “ለአዲስ አበባ ብዙ መፍትሔ አለ። አንደኛው በሕገወጥ ሆነ በሕጋዊ መንገድ ሰው ማስገባት ነው። ሌላኛው አዲስ አበባን የማትጠቅም ከተማ ማድረግ ነው። አራት አምስት የፌደራል ከተማ እንመሰርታለን። ድንበር የመካለያ አዋጅ ወጥቷል። ለስሙ ነው እንጂ ይጸድቃል። (ሽመልስ አብዲሳ)

12ኛ- የኦሮሞ ትግል ማዕከል አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ብቻ ናት” (ሽመልስ አብዲሳ)

13ኛ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት። አደስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆንዋን ተከትሎ ኦሮሚያ መዝሙር በት/ቤቶች መሰጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።” (ሽመልስ አብዲሳ)

14ኛ- በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ ዛሬ “ባለአደራ መንግሥት ብሎ ራሱን መሾም አልያም ባለተራ መንግሥት ብሎ ለውጥን ማጣጣል በምንም ስሌት ተቀባይነት የለውም። መንግሥታችንን ለመፈታተን ባለተራ ባለአደራ እያለ የሚያላዝነው ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እንሰራለን።” (አዲሱ አረጋ ቂጢሳ)

15ኛ- “እኔ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ ጠዋትንም ማታም ሻይ አብረን ስንጠጣ፤ የኦሮሞ ጥቅም አዲስ አበባ ውስጥ ለማስጠበቅ፤ በተለይም ካሁን ቀደም ተገፍቶ ከአዲስ አበባ ሲወጣ የነበረውን አርሶ አደርና ኦሮሞነት ከከተማ ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ…ነው” (አዲሱ አረጋ ቂጢሳ)

16ኛ- ከሶማሌ የተፈናቀሉትን አምስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች  በአዲስ አበባ ዙርያ እና  በአዲስ አበባ ውስጥ አስፍረናል። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስድስት ሺሕ ሰዎችን አስገብተናል።”  (ለማ መገርሳ)

17ኛ- አዲስ አበባ  የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት። አዲስ አበባ ኦሮሚያ  ዋና ከተማ መሆንዋን ተከትሎ ኦሮሚያ መዝሙር መስጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።” (አበበች አደኔ)

እነዚህና የመሳሰሉ ሌሎች እዚህ ያልተጠቀሱ ንግግሮች <<የ Ormania መርህ>> የተከተሉ ያልተሸፋፈኑ ጉልህ የሆኑ ኦሮሙማዊ የአጀንዳ አፈጻ ጸም ምልክታዊ ንግግሮች ናቸው

ከዚህ አንጻር የ6 አመቱ የኦሮሙማ ፕሮጀክትና አንደበቶችን ስንመረምር በአምሐራ ሕዝብ ላይ የተካሄደው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ስንመለከት እጅግ አክራሪ የተባሉት “ኦነጎች” እና “የሰለፊ ኦሮሙማ እስላሞች” በሕልማቸው ይሆናል ብለው ያልጠበቁት ያለ አብይ አሕመድ እገዛ የመንግሥትን መንበር ተጠቅሞ ለኦሮሙማ ፕሮጀክት (ግብ) መሳካትና መፋጠን ከአብይ አሕመድና ድርጅቱ በላይ የሚተባበራቸው ወንጀለኛ ቡድን አያገኙም።

ጌታቸው ረዳ Ethio Semay