Thursday, April 4, 2024

የጭፍጨፋ ህዳሴ ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay April 4, 2024

 

የጭፍጨፋ ህዳሴ

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

April 4, 2024

27 ሲደመረው 6 አመት 33 አመት ሆኖታል በውጭ ቅኝት አስተዳደር የተቃኘ አገር በቀል ኮሎኒያሊዝም ኢትዮጵያን ማስተዳድረ ክጀመረ፡፡

የተመራውም በትግሬዎችና ኦሮሞዎች የተመራው የቅኝ ግዛት ሕገ መንግሥት ነው፡፡ እንዲያ ብየ ስል አንዳንድ ምናልባትም ብዙ ሰዎች እንዴት ሕዝብ እንደ ሕዝብ በጥቅሉ ስሙ እንደ ገዢ ይጠራል በሚል ገራገር አስተሳስብ በመያዝ ላይጥማቸው ይችላል፡፡ ሆኖም ካሁን በፊት እንደገለጽኩት መሪዎቹም ‘ክታች ብዛታዊ ተቀባዮቹም’ (resonance from below/አስተጋቢ) ተጠቃሚዎቹም ጠንካራ ተባባሪዎቹም በእርከኑ ከፍታውን ድምቀት የያዙት እነሱ ናቸው፡፡መሪዎቹና ሕዝቡ የተቆራኙበት የተስማሙበት ፤ መገናኛ (conjunction) ብዙ በሮች (ነበሩ አሁንም አሉ፡፡

በነዚህ 33 አመታት ብሕገ መንግሥት የጸደቀ ኢትዮጵያ ወሰጥ በተዋቀሩ ባንቱሰታዊ/ከልላዊ ግዛቶች ወስጥ ‘አንዱን ነገድ ባንዱ ላይ እንዲዘምት (አውሮጳዊያን ኮሎኒያሊስት በልጂያኖች ሩዋንዳዊ ጀነሳይድ እንዲካሄ ‘’ሁቱ በቱትሲ’’ ‘ቱትሲ በሁቱ’’ ላይ እንዲዘምት እንዳቀዱት ሁሉ) እኛ ጋርም ጣሊያኖች አማራንና አማርኛን እንዲሁም ኦርቶዶከስን ዒላማ ያደረገ ‘ጀነሳይድ” እንዲፈጸም ባቀዱት መሠረት ፤ “ሃይማኖትና’’ “ነገድ” መነሻዎች ያደረጉ ጅምላዊ ፍጅቶች፤(ብዙዎቹ ዘር ማጥፋት /ጀነሳይድ) ላለማለት ይሰጋሉ ወይንም አልተፈጸመም ይላሉ) ሃቁ ግን ተካሂዷል፡፡ ‘ዘር’ እና ‘ነገድ’ ‘አካባቢያዊ/ጂኦግራፊያዊ’ ተኮር እየተጠቀሰ ፍጅትና “የደም ድብልቅ እንዳይኖር የዘር ማጽዳት” ተካሂዷል፡፡

በተለይ “ዘር” ሲጠቀስ  ሃይማኖት ሲጠቀስ ግራ ሊገባችሁ ይሆናል፤ አጽጂዎቹ ግን የተገበሩት ጣሊያን በጠላትነት ያሰቀመጣቸው (አማራ ኦረቶዶከሰና አማርኛ) ክሚክተሉት አካባቢ ነገዶች እንዲውገዱ ተደርጓል፡፡ ‘’ከኦሮሞያ ክልል፟ በኦነግ መርሃ ግብር’’ ‘’ከሶማሊ በኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር መርሃ ግብር መሠረት (በ አካባቢ የክልልና የገጠር መሪዎች (ethnic authorities) በተግባር የፍጸሙት “አማራ የተባለ <<ዘር>>” ከተጠሱት ንጹህ <<ዘሮች>> ለማጽዳት እንደዘመቱና፤ አማርኛ ቋንቋም እንዲጠፋ ኦረቶዶከስም አምሓራዊ ነው ሰለተባለ ክአካባቢው ሃይማኖቶች እንዲውገድ ምጽአት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ይህ የሆነው የውጭ ኮሎኒያሊስቶች ባሰመሩት (cultivation and direction) እቅድ (የተጓዘው <<አገር በቀል ኮሎኒያሊስት>> (ፖስት ኮሎኒያል ሊሂቅ) ያንን የጣሊያን ቅኝ ቅድ ከማክሸፍ ይልቅ አሳድሶ <<በዲሞክራሲ ስም>> ተከናንቦ አዳዲስ ስሞችን ሰጥቶ በዚህ 33 አመት የቋንቋ፤ የዘር የሃይማኖት ፍጅት ተካሂደዋል፡፡ በመንግሥት ደረጃም ኦሮሞ ሚኒስትሮችና የከልል፤አውራጃና ወረዳ በመሥርያ ጽህፈት ቤቶቻቸው የወደፊት “”የኦሮሞ አገር”” ተብላ ኦነጎች ያቀደዋትና እየገነብዋት ያሉት <<የኦሮሚያ>> ካርታ በግሃድ ተቀርጻ ጠረጴዛቸው ላይ በክብር ተለጥፋ ትታያለች (ባንጻሩ ኢትዮጵያ የምትባለዋ ቆራጣዋ ካርታም ጠረጴዛቸው ላይ የለቺም፡፡ የጭፍጨፋው ሕዳሴ በማን አይዞህ ባይነትን በምን መንገድ እየተካሀደ እንደሆነ litmus test ብታስገቡት ያልጠበቃችሁት ቀለም ታገኛላችሁ፡፡የጭፍጨፋው ሕዳሴ ሊቀመንበር አብይ አሕመድም የኢትዮጵያና የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ <<ፍንፍኔ>> ይላታል፡፡ እንግዲህ ነጥቦቹን ክዚያ እስክዚያ ድረስ ስታገጣጥሟቸው <<ዋነኛው ንድፍ>> ምን እንደሆነ ታገኙታላችሁ ማለት ነው፡፡

ስለዚሀም “አገርኛ ሊሂቃኖች” ባዋቀሩት ‘የባንቱሰታዊ/አፖርታድ’ አስተዳደር በሁለት መልኩ በቀለበት ያሰገቡት አምሐራ ማሕበረሰብ ተጠቅቷል፡፡ (1) መንግሥታዊ/ሕገመንግሥታዊ ‘’ሲቪክ ሎው’’  ክመንግሥት ተብየ ባለሥልጣናት የተወሰደ የሥራ አድሉዎና ማባርር ፤ እንዲሁም ነገድን ያነጣጠረ የጅምላ እስር)  ሲሆነ (2ኛው ጥቃት) “በባነቱስታው ከልል ባለሥልጣናት’’ (ነቲቭ አውቶሪቲሰ/ ኮሚኒቲ አውቶሪቲዎች) የተሳተፉበት ‘ነገዳዊ/በሔረሰባዊ’ ጭፍጨፋና ማባረር ንብረት መዝረፍ፤ በአማራ ሴቶች ላይ አመጽ በማካሄድ አማራ ላይ ጥቃት እንዲከሰት (ለ33 አመት ሕገመንግሥቱ <<ኢንዲጂነስ እና ናን ኢንዲጅነስ>> ባለ አገር እና መጤ /ሰፋሪ/ እያለ በሕግ ሸንሽኖ አፓርታይ ክ1983 እስከዚቺው ቀንና አመተ ምሕረት 2016 እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

ጣሊያን ወደ አገራችን ሲገባ “ለመስፈር/ሰፈራ ፈልጋ” ነው (ሴትለር ኮሎኒያሊስት) ሆኖ ነው የመጣው፡፡ የመጣበትም ምክያት ‘ለኢኮኖሚ’ ብዝበዛ ነው፡፡ ያንን ለማካሄድ እንደተቀሩት አምሳያ ኮሎኒያሊስቶች ኗሪው እሺ ብሎ ስለማይገዛለት በጂኦገራፊ አሰፋፈር፤ በቋንቋ ፤ በዘር ፤ በሃይማኖት፤ በነገድ እና በቆዳ በመለያየትና በማመሳሰል በየምድቡ መድቦ ሯሪው <<ያንን ብረዛ>> ተቀብሎ <<በሰፋሪው ዘር በኮሎኒያሊሰቱ>> ላይ ሳይሆን እርስ በርሱ ላይ በማትኮር ለሰፋሪው (ለኮሎኒያሊስቱ) የለማ መንገድ በመጥረግ አገሩንና እራሱን ለጥቃት እንዲጋለጥ በማድረግ የታቀደ ነበር፡፡

በዚያ መልክ አገራችን ውስጥ ጣሊያን አማራ ፤ አማርኛና ኦርቶዶክስን ቀጥተኛ ጨቋኝ በማድረግ፤ እስልምና እና ኦሮሞ እንደተገዙ አድርጎ በማቅረብ ልዩነትን በማጉላት እነሆ በጦር ሃይል የገቡብን ኮሎኒያሊስቶችና በሰላማዊ መንገድ አስመስለው የገቡ ሰላይ ሃይማኖተኞች የተውልንን የማበጣበጪያ ገመድ ክመበጠስና ክማሰወገድ ይልቅ “ድሕረ ቅኝ ግዛት” (ፖስት ኮሎኒያሊስት) የተከሰቱት አገር በቀል ሊሂቃን ያንን “ከፋፋይ ቫይርስ” ወደ ሕብረተሰቡ በማስተላለፍ የነገድ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነገዶችን ያነጣጠረ የእርስ በርስ ጭፍጨፋ derivative byproduct ምንጩ ከጣሊያን ኮሎኒያሊስቶችና ክዙርያ ጠላቶች የተገኘ ቅሪት ነው፡፡

እዚህ ላይ ክጣሊያን መወገድ በኋላ ማኣከላዊ ተጠቂ ሆኖ የተገኘው  “ዋነኛ” (ሌሎች ቢኖሩም) አማራ ማሕብረሰብ ነው፡፡ ይህ ብሔረሰብ ጣሊያኖች ያጠመዱለት ወጥመድ እንደ እነ ዋለልኝ መኮንን በመሳሰሉ የገዛ አብራኩ በጨቋኝነት ማሕበረሰብ ስለተፈረጀ፤ ከሌሎች ማሕበረሰብ የተገኙ ተማሪዎች ጋር ግምባር ፈጥረው በኋላ እነዚህ ተማሪዎች የዛሬ ሊሂቃን ሆነው የጣሊያን ኮሎኒያሊስቶችን ቅሪት በማደስ “አማራውን” ስፋሪ (ሴትለር) (ሰፋሪ/ነፍጠኛ’/ኮሎኒያሊስት) በማለት ክሚኖርባቸው “ባንቱስታዊ/ከልላዊ ገዛቶች” እንዲባረርና እንዲጨፈጨፍ አድርገዋል፡፡

ሩዋንዳ ውስጥ የሆነው ይሄው ነበር፡፡ ‘ድሕረ ቅኝ ግዛት’ የበቀሉ ሊሂቃን ያንን ከበልጂም ያገኙትን ቀሪት በማደስ ዓለም ያስደነገጠ እልቂት እንዲፈጸም አድርገዋል፡፡

አማራው ምን እንደተፈጸመበት ለ33 አመት ስለተናገርንበት እዚህ ለመግለጽ ቦታና ጊዜ አይበቃም፡፡ ሆኖም 33 አመት ምን ነበር ብንል የያኔ የዋለልኝ የርዕዮተ ፟ዓለም ጔዶች ትግሬዎችና ኦሮሞ ተማሪዎች የዛሬ የትግሬና ኦሮሞ ሊሂቃን፤ የጣሊያን ፖለቲካዊ ቅኝ አስተዳደር ኣዳሾች ሆነው “ማሕበረሰብ በጭፍጨፍ ወንጀል እንዲሳተፍ ወይንም እንዲጠቃ” አድርገዋል፡፡ ጭፍጨፋዎቹ departure from normal ክተለመደ አነሳስ የሚሉት ሳይሆን ክውጭ ገዢዎች የተለቀሙ እኔ << የጭፍጨፋ ህዳሴ>> ብየ የሰየምኩት በ1983 በትግራይ ሊሂቃንና ኦሮሞ ሊሂቃን የጀመረ 33 አመት ዕድሜ ያስቆጠረ የ1928 ዓ’ም የጣሊያን ፖሊትካ ቀሪት ነው፡፡ የእልቂቱ ቀያሾች ዛሬም ሥልጣን ላይ አሉ፡፡

ይህንን እውነታ እያወቁ ስሞኑን 6 አመቱ የፖለቲካ ኦሮሙማው ገዢው ‘ሥርዓተ በዓሉ’ ሲያከብር፤ <<በዲከታተርነት አፍኝነት ሥልጣን ሆዳምነት ሲመድቡት>> ነገር ግን ሥርዓቱ “አገርኛ ቅኝ ገዥ” (ነቲቭ ኮሎኒያሊስት) ነው ለማለት ብዙ ተንታኞች አልደፍሩም፡፡ አማራ ላይ ጀነሳይድ የሚፈጽም/የፈጸም “ፓወር” የለም (አልተካሄደም) እያሉ ባንድ ነገድ ያነጣጠረን መንግሥታዊ (ኢንስትቱሽናላዊ) ጀነሳየድን “የጦር ወንጀል/ ወይንም በመናኛ ጥቂት ወረበሎች የተፈጸመ ጭፍጨፍ” እያሉ ‘ውጤቱን በማቆነጃጀት” ክሚከዱ ከፈሎች ወይንም “ፈጣሪ እስራይሎችን በሙሴ መሪነት በመዲያን ሕዝብ ፤ ሴቶች አረጋውያን ነብሰጡሮችን ሕጻናትን ላይ ጦርነት ታወጆ ‘ምጽአተ መዲያን እንዲካሄድ’ ሲደረግ የነገድ/የሕዝብ እለቂት ሳይሆን “የፈጣሪ ግሰጻ ነው” ብለው በሞራልም በሰባዊነትም በፈጣሪው ውሳኔ ሕግም ሕጋዊ ነው ብለው የሚተረጉሙት የፈጣሪ ተከታዮች አሉ፡፡ በተለምዶ በፖለቲካ ደደብነት የምናውቃቸው አንዳንድ ምሁራኖቻችንም በአማራ ሕዝብ ሕይወት የወረደው ‘ምጽአተ አምሓራ’ (ጀነሳይድ) ሳይሆን  “የጦር ወንጀል /ግድያና ግጭት” ነው ይላሉ፡፡

ቅድመ ሁሉም (ሲጀመር) ከድሕረ ጣሊያን መባረር በኋላ በ1983 ጀምሮ እስከ ዛሬ  2016 አም እየተከናወነ ያለው <<የጭፍጨፋ ሕዳሴ>> ከባሕር ማዶ ተሻግረው የመጡ ቅኝ ገዢዎች ሳይሆን በአገር በቀል (ነቲቭ ኮሎኒያሊስቶች) የቅኝ ግዛት አስተዳድር አዳሾች ነው፡፡ ለዚህም ተጠያቂዎቹና መሪዎቹ በዙዎቹ የትግራይ መሁራን እና አብዛኛዎቹ የኦሮሞ ፖልቲክኞች ተጠያቂ ሲሆኑ በዚህ 6 አመት የከፍ <<ምጽአተ ኢትዮጵያ>> በመምራት ላይ ያለው የጭፍጨፋው ሕዳሴ ተጠሪ አብይ አሕመድና ‘ትግሬዎችን ፈቅደን ብናኖራቸው” የምትለዋ የዜጋነት ፈቃጅና ከልካይ የሆነቺው <<ነቲቭ ኮሎኒያሊስትዋ>> አበበች አደኔም በተጠቂ ሕሊናዎች ውስጥ በጥቁር መዝገብ ተመዝግበው ይገኛሉ፡፡

ጌታቸው ረዳ

Amhara Genocide by the Oromo Testimony of victims interview Cannibalism involved in the attack አገሬው

https://youtu.be/Eh7h0YgsZp0?si=Q-vnMrG14qrEGohF