ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል የዓለም አቀፍ ሴት ደፋሪዎችን ሬከርድ ሰብሯል!
ከጌታቸው ረዳ
(ኢትዮ ሰማይ)
Ethiopian Semay
1/5/2022
እናት አገር አልቅሺ! ያለው ደቡብ አፍሪካዊው “አላን ፓተን” ላለቀሰላት እናት አገር ዛሬ ‘እናት አገር ኢትዮጵያ’ አልቅሺ ለተባለላት ደቡብ አፍሪካ በባሰ መልኩ እናት ኢትዮጵያ “በጥላቻ” እና በToxic masculinity “መርዛማ ወንድነት” በተሰማቸው የትግራይ ተዋጊዎች 85 ዕድሜ ያላቸው መነኩሴና 13 አመት ዕድሜ ያላቸው “እግር የተከሉ ህጻናት ሴቶችን” እስከ መድፈር ደርሰዋል።
የትግራይ ሕዝብ ወደ አማራ አገር ዝመቱ ብሎ መርቆ” ያዘመታቸው ልጆቹ “ክልል” ተብሎ በተከለለው “አማራ ክልል” በገባባቸው መንደሮች፤’ ገጠሮችና ከተሞች ሁሉ “ሴቶች፤ የቆረቡ የሰገዱ ባለ ትዳሮች፤ህጻናት፤መነኮሳት እና በምርኩዝ የሚራመዱ አያት እናቶች እገሌ ከእገሌ ሳይለዩ “የተዘጉ መኖርያ በሮችን” በሌሊት እየሰበሩ በቡድን ሆነው ጠመንጃ ደግነው ጾታዊ አመጽ ሲፈጽሙ እንደከረሙ ሰለባዎቹ በእምባ ታጅበው የደረሰባቸው ግፍ እየገለጹ ይገኛሉ።
ወንዶች ያውም “አረጋዊያን” እያለቀሱ ነው። እፊታቸው በጥይት ገድለውባቸው ‘ሴትየዋ ልጆቼን አደራ” እያለች ሽማግሌ ባልየዋን ተሰናብታ ስታሸልብ ያዩ እኝህ አረጋዊ ፤ ደሴ ከተማ ለተሰበሰበው አደራሽ ሕዝብ “እያለቅሱ” ሚስታቸው በግፍ እንዴት እንደተገደሉባቸው እየገለጹ “በቪዲዮ” አይቻለሁ። ወንድ የሚያለቅስባት አገር “እርይ በይ አገሬ!” ሲያንስ ነው።
ለሕዝብ የተለቀቁ ሁሉንም ቃለ መጠይቆችና ስዕለ ድምጾች (ቪዲዮዎች) ሰብስቤ ባንድ ሌሊት ልጨርሳቸው አልቻልኩም። የጾታዊ ጥቃቱ አፈጻጸም አንዱ ካንዱ የበለጠ አሰቃቂ እና አስለቃሽ ሆኖብኝ እየተረበሽኩ ሁሉንም ማየት አልቻልኩም። ዕንቅልፍ ሁሉ ነስቶኛል።
እውጭ አገር የሞኖሩና አገር ውስጥ የሚኖሩ “የትግራይ ምሁራንና የትግራይ ሕዝብ’ ያለ ምንም “የውግያ ደምብና የሞራል ግዴታ ሳይማሩ” በዘፈንና በጭፈራ በስሜት ብቻ እየገፋፉ “የትግራይን ወጣት ቀጥል ዝመት” እያሉዋቸው ከሰውነት ወደ አራዊትንት የተለወጡት የትግራይ ተዋጊዎች የፈጸሙት የተዘጉ ስቆች፤ ሆስፒታሎች፤ ክሊኒኮች፤ የእህል መደብሮች፤ የልብስና የዕቃ መጋዝኖች እየሰበሩ፤ የሚዘረፍ ዘርፈው በመኪና ወደ ትግራይ እየጫኑ፤ መሸከም ያልቻሉትንም ሰባብረው ገነጣጥለው፤ ተቋማትን እንዳልሆኑ አድርገው ፤ድልድዮችን መኪኖችን እያጋዩ በመጨረሻ ሕዝቡ “ሆ ብሎ” ሲነሳባቸው ወደ ሗላ አፈግፍገዋል።
ይህ ሁሉ ግፍ ስመለክት “እናት አገር አልቅሺ” የሚለ፤ው ቃል አልበቃ ሲለኝ እነዚህን አራዊቶች የምገልጽበት ቃል ፍለጋ ስኳትት ሰነብቼ ምንም አላገኘሁም። ብትግርኛ “ሓኽሊ ድሙ” የምንለው ቤት አልባ ፤ “ራስ አደር” (ሆምለስ) ድመት’ በተከፈተ ቀዳዳ የሰው መዝጊያ ሾልኮ በመግባት “ለቤተሰብ የተሰራ ዶሮ ወጥ ወይም ሥጋ ወጥ የያዘ ድሰት” በልቶና ደፍቶት የሚሰወር፤ በየሰው ጣራ ወጥቶ “ጦር አውረድ” እያለ “ጣራውን በመቧጨር” ባለ ማቋረጥ ሃይለኛ ድምጽ በማስሰማት “በወድቅት ሌሊት” የተኘውን ሰላማዊ ሰው “ዕንቅልፍ” የሚነሳው “ወረበላው ድመት” ወያኔዎችን ለመግለጽ ይስማማ ይሆን ብየ አንዱን ወዳጄ ይህ ዓይነት ድመት በአማርኛ ምን ይባላል ብየ ጠየቅኩት።
ሸለመጥማጥ የሚባል አለ፤ ግን እርሱ ግን ረዢም ጭራ ያለው ድመት የሚመስል የቤት ድመት ሳይሆን ደሮን በመንጠቅ የታወቀ የዱር/የበረሃ/ ድመት አለ። ይህም ዕወቁ የቃላት ምሁር አቶ ተሰማ ሀብተሚካል ያዘጋጁት ‘ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት” ገጽ 302 ገልጸውታል”፡ -- ሆኖም አንተ ከምትለው አመጸኛው የቤት ድመት ጋር አይመሳሰልም። ይመስለኛል አንተ የምትለው ድመት ኦሮምኛ “ዲገላ” ብለው የሚጠሩት ይሆን? ብሎ ሃሳብ ሰጠኝ። ለመሆኑ ለምን ፈለግከው? አለኝ። ለጽሑፌ ርዕስ ልጠቀምበት ነበር ብየ ታርኩን ስነግረው ይህንን መለሰልኝ
“Nothing in our language can adequately convey the diabolic deeds of Weyane's. Today I heard on a radio how they killed va two weeks old baby whose mother could not run away. After killing the child they stood on its corpse. The poor mother had to witness all this. This happened in Northern Wello (Wag region). They sexually abused 85 years old nun who begged them to spare her. Even wild beasts do not describe the evil deeds of Weyanes' I am afraid you have to coin a new word that has not been in use.” አለኝ።
ትርጉም፡
““በእኛ ቋንቋ የወያኔን ዲያብሎሳዊ ተግባራት በበቂ ሁኔታ ማስተላለፍ የሚችል ቃል የለም። በተከታታይ እየተሰሙ ያሉት አስደንጋጭ ወያኔ የፈጸማቸው አስነዋሪ ወንጀሎች እየተሰሙ ነው። ዛሬ አዲስ ዜና የሰማሁት አለ። እናቱ መሸሽ የማትችለውን የሁለት ሳምንት ህፃን እንዴት እንደገደሉ ዛሬ በሬዲዮ ሰማሁ። ልጁን ከገደሉ በኋላ በሬሳው ላይ ቆሙ፤ ምስኪኗ እናት ይህንን ሁሉ ማየት ነበረባት። ይህ የሆነው በሰሜን ወሎ (ዋግ ክልል) ነው። የ85 ዓመቷን መነኩሲት እንዳይደፍሯቸው በፈጠራቸው አምላክ እየተማጸኑ ቢለምኗቸውም ወያኔዎቹ በዚች መነኩሲት ላይ የፆታ ግንኙነት ፈጸሙ።ወያኔዎችን ለመግለጽ “አውሬ” የሚለው አይገልጽም ። አውሬ የሚለው እንኳን የወያኔን እኩይ ተግባር አይገልጸውም። እስካሁን ድረስ ስራ ላይ ያልዋለ አዲስ ቃል ካልፈጠርክ። የነዚህ “እኩያን” ሰዎች ምንነት ለመግለጽ ቃል ታገኛለህ ብየ አልደፍርም።” አለኝ።
የወያኔ ጋኔሎችን የሚገልጽ መዝገበ ቃላት ለመፈለግ ያልገነጠልኩት መጽሐፍ የለም። ሰይጣናዊ ተግባራት የሚገልጹ ልብ ወለድም ይሁን እውነተኛ ታሪክ ቃላት ፍለጋ ወደ ዩኒቨርሲቲ ላብሬሪ ሁሉ ሄጃለሁ። የዳሰስኳቸው የግዕዝም ይሁን አማርኛ እና እንግሊዝኛ መዝገበቃላትም ይሁኑ መጽሐፍቶች” ያነሱና ለስላሶች ስለሆኑ የኢትዮጰያን እናቶችና የ13 ዕድሜ ያላቸው “እግር ተከል” ህጻናት ለመድፈር ከገሃነመ ሰማይ ወደ ምድራችን የተላኩ “የትግራይ ተዋጊ ጋኔሎች” ተስማሚ ቃላት ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩምና አንባቢዎቼ አግዙኝ።
የሚገርመው ደግሞ ኢትዮጵያ አይደለንም ብለው ወደ ትግሬነት ዜጋ የተለወጡት ትግሬዎቹ እነ አብርሃ በላይም ሆነ እነ ርዕዮት ሚዲያ (ቴድሮስ ፀጋዬ) “ጨፍጫፊ ሴት ደፋሪ የአብይ አሕመድ ወታደር ምንም ጊዜም ቢሆን እንደ ወታደርነት መቀጠል የለበትም ጠቅላላ ከታች እስከላይ መፍረስ፤ አለበት” እያሉ ሲያናፉ በተጻራሪው ግን “ነፃ አውጪያችን” ብለው “ቲ ዲ ኤፍ” እያሉ እየቆለጳጰሱ የሚጠሩት “ወረበሌው ህጻናትና መነኮሳትን ደፋሪው የትግራይ መከላከያ የሚባለው” ፋሺስታዊው የወያኔ ወራሪ ጦር ግን “መፍረስ አለበት” ሲሉ አልሰማናቸውም። ይልቁንስ “ትግራይ ትዕወት” እያሉ በወንጀል የተጨማለቁትን (ባለ ሪከርዶቹ) “የእነ ጻድቃን” ፎቶ ግራፍ በፌስቡካቸው (በአብርሃ በላይ ፌስቡክ) ማድመቂያ አድርገውት እያየናቸው ነው።
ለነዚህ ሰነፎች የምለው ነገር ካለኝ መጽሐፈ ምሳሌን ጥቅስ ነው።
“መጽሐፈ ምሳሌ 26፡11 ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ እንዲሁ ሰነፎች ስንፍናቸውን ይደግማሉ።”
አሁን ወደ አብይ አሕመድ እንመልከት
ይህ ሁሉ ውርደት እንዴት እንደመጣ የወያኔ የአፈጣጠር በሕርይ መሆኑን ከታች የምገልጸው ቢሆንም፤ ቀንደኛ ተጠያቂው ግን አብይ አሕመድ ነው።በአብይ አሕመድ ሕጻናዊ የአገር ደህንነት አመራርና የብቃት ማነስ “ወያኔዎች” ደፍረውናል። ሱዳኖች ደፍረውናል።ሱዳኖች የደፈሩት ሉዓላዊ መሬታችንም ለምን ደፈራችሁ ተብለው ሲጠየቁ “እራሱ አብይ ውሰዱት ስላለን ገብተን ወስደናል” ምን ታመጡ! ብለውናል።
ዕድሜው ሙሉ ያገለገለው ለአፓርታይድ ስርዓት ካለው ፍቅር የተነሳ ወለም ዘለም እያለ ከወያኔዎች ጋር ‘አንገት ላንገት ተቃቅፎ’ እስከ ሑመራ እስከ አክሱም ድረስ ሲተሻሽ ከርሞ አጅሬዎች “ህጻንነቱን” ስላወቁበት በገንዘብም፤ በመሳሪያም በመረጃም በደምብ ሲዘጋጁ “እርሱ ግን “ላንድ ሰው ብለን ጦርነት አንከፍትም” እያለ ሲያሾፍ “ያለ ምድቡ ፓርክ አሳማሪ ሆኖ” ሲዝንዘላዘል ቆየ። ይባስ በሎ ከየክልሉ “በፋሺስት ልዑላኖች” ትዕዛዝ “ኢትዮጵያዊያን ከየክልሉ እየተፈናቀሉ የትም ሜዳ ፈስሰው ያለ-መጠለያ ሲሰቃዩ አርሱ ግን ንግሥነቱን ለማጠናከር “ጎርፍ መጣባችሁ ብሎ እንደ ሳወዲዎቹ ንገሥታት “ለጋሽ ንጉሥ” ሆኖ “ለሱዳኖች የገንዘብ እርዳታ ሲረጭ” ከረመ። በመጨረሻ አጅሬዎች ወያኔና ሱዳኖች የህጻኑን ትንሽ ህሊና ገምተው “ኢትዮጵያን ወረሩዋት፤ ደፈሩዋት”።
“ንግሥነቴን መርቁልኝ” እያለ አመት ከቆየ በሗላ ወያኔዎች “እስኪሸድኑ” ድረስ (ቃሉ ትግርኛ ነው- ማን ይግጠመኝ የሚል አጠገቡ በሰለም የቆመ በሬን ሳይቀር ሁሉንም እየዘለለ የሚዋጋ በሬ) ጎርምሰው እርሱ ሲንዘላዘል ከርሞ መጨረሻ እየሆነ ያለውን ጉድ ሊደርስብን በቃ።
መጨረሻ ምስጢሩ በማይገባን ሁኔታ ወያኔዎች ከትግራይ ተነስተው እስከ ደብረብርሃን በር ድረስ ሕዝብ እየደፈሩ እየዘረፉ፤ከብቶች እያረዱ፤እየገደሉ ሲገሰግሱ፤አብይ አሕመድና “ የኢሳቱ "ካቡጋ" መሳይ መኮንን” የመሳሰሉ “የዘር ማጽዳት ቀስቃሽ ወንጀለኞች” “ክበበው፤ አስገባው፤ አፍነው” እያሉ ከትግራይ ውጭ ያለ በመላ አገሪቷ ያለ የትግራይ ተወላጅ "ፖለቲካ ያለውም የሌለውም" “ወያኔ ነው’፡ተብሎ “በኢንትርሃሙዌው ቡድን” እንደ ናዚ ወደ “ማጎርያ እስር ቤትና በየድልድዩ ሥር ጭምር” ታስሮ ፤ ንብረቱ እየተዘረፈ፤ ሥራው እየተፈናቀለ፤ የሞተ የታመመ፤ የታረዘ “ኮነስንትረሺን ካምፕ” ውስጥ ታጉሮ ይገኛል።
ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ ጦርነቱን እንዲቀጥል አገር አገር እንዳይሆን “በጀነሳይድ ላይ ሌላ ጀኔሳይድ” አብይ አሕመድ ምንም በሌላቸው ንጸሃን በወንድሞቻችን እስካሁን ድረስ (የራሴን ዘመዶች ነው እየተናገርኩ ያለሁት) ንጹሃን ላይ ግፍ እየፈፀመ ነው። በዚህ ምክንያት ቤተሰቦቼ በመታጎራቸው ብናደድም ወደ ወያኔ አልተቀለቃልኩም። ግን ብዙ ትግሬዎች በንዴትና በእልህ ወደ ወያኔ ድጋፍ ተቀላቅለዋል። ጦርነቱ የከበደ ያደረገው አንዱ ይህ የመበቀል ቁጣም ነው። አብይ አገር መምራት አይችልም የምለው ለዚህ ነው።
አብ አሕመድ እራሱ 32 ወታደሮቼ የትግራይ ሴቶችን በመድፈራቸው በቁጥጥር ስር አድረጌአለሁ ብሎ ይናገር እንጂ ፍርዱ በይፋ አልታየም። ትግራይ ውስጥ ወታደሮች የጦር ወንጀል ሲፈጽሙ በቪዲዮ አይተናቸዋል። የጦር መሪ ነውና አብይ በዘር ማጽዳት ወንጀል መከሰስ አለበት።
መደምደሚያ
ወያኔዎች በአማራ ላይ ያላቸው ጥላቻ ከላይ የተጠቀሰው ወንጀል እንዲፈጽሙ መነሻ ሆኗቸዋል። ከዚህ መነሻ በተጨማሪ የሚከተሉት የፖለቲካ ፍልስፍና ደግሞ ዋናው የአራዊታዊ ባህሪያቸው ምንጭ መሆኑን የሕክምና ዶ/ር እና የአእምሮ ሓኪም የሆነው ሆላንድ-አምስተርዳም ኗሪ የሆነው ወዳጄ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ወያኔዎች ስለሚከተሉት “የፋሺስቶች-ፍልስፍና” በተከታይ አባላቶቹ “ስነ ልቦና” የሚያደርሰው ጫና በእንግሊዝኛ የጻፈው ወደ አማርኛ ተርጉሜ ቀንጭቤ ላስነብባችሁ እና ልሰናበት።
እንዲህ ይላል፦
“የፋሺዝም/ ናዚዝም የማዕዘን ድንጋይ የሆነው Ultra-Nationalism (አክራሪ ብሔረተኛነት) ጤነኛ አእምሮ ያለው ግለሰብ ወደ “ኢ-ምክንያታዊ” ሰውነት ይለውጠዋል። ይህን የሚያደርገው ህሊናውን “በማገድ” ነው። ኅሊናውን ወይም “የሞራል ኮምፓስን/የሞራል መመርመሪያው” በአልትራ ብሔርተኝነት ተጽዕኖ ሥር ያስወረረ ግለሰብ ሕዝባዊ ንቅናቄውን (መንጋውን) በመቀላቀል የግለሰባዊ ማንነቱን በመጣል የፋሽስት መሪዎቹን ትእዛዝ በባርነት ይሠራል። በሂትለር ዘመን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጀርመኖች እና በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ጣሊያኖች በሙሶሎኒ ጊዜ የደረሰው ይህ ነው።
የሙሶሎኒ ፋሺስታዊ መፈክር ወይም “መፈክር ተከታዮቹ” ሊከተሉት የሚገባ እና በሃይማኖታዊ ቁርጠኝነት በተግባር ላይ ለማዋል “እመኑ፣ ታዘዙ እና ተዋጉ” የሚል ነበር። ዛሬ በህወሓት ስር ያሉ ትግሬዎች የሚያደርጉት ይህንኑ ነው። የጣሊያን ፋሺዝም እና የመስፋፋት ፖሊሲው በጥቅምት 1935 ኢትዮጵያን መውረር አስከትሏል።ይህ ወረራ በ1935-1941 መካከል ብቻ በ730000 ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ አስከትሏል። ይህ እልቂት እስከ ዛሬ ድረስ የታፈነ ዕውቅና ነው። በጣሊያን ፋሽስታዊ መካሪዎቻቸው ተብራርተው የፋሺስታዊ አስተሳሰብን የጫኑት የትግሬ ፋሽስቶች ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ለሞትና መፈናቀል ምክንያት በማድረግ ከጣሊያን ፋሺስት መካሪዎቻቸው በልጠው የጣሊያን ፋሺስቶች በኢትዮጵያ የወሰዱትን እርምጃ ትልቅ ትርጉም ያለው አድርጎታል።” አሰፋ ነጋሽ (ዶ/ር)
ወደ አራዊትነት የተለወጠው የትግራይ ተዋጊ ሃይል የዓለም አቀፍ ሴት ደፋሪዎችን ሬከርድ ሊሰብር የቻለበት ምክንያት ከላይ የተጠቀሰው የሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና ምክንያት ነው።
እኛ ድርሻችንን እያነሳን ነው፤ አንባቢዎች ደግሞ ሕዝቡን ለማስተማር ጽሑፉን ተቀባበሉት።
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ) 1/5/2022 Ethiopian Semay
No comments:
Post a Comment