Tuesday, June 29, 2021

በርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ቴድሮስ ጸጋየ ዛሬም ቅሬታ አለኝ (ክፍል ሁለት) ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 6/29/2021

 

በርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ ቴድሮስ ጸጋየ ዛሬም ቅሬታ አለኝ

(ክፍል ሁለት)

ጌታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

6/29/2021

ዛሬ ጥዋት ከዚህ ጽሑፍ ሌላ አብይ አሕመድ መጨረሻው ላይ “ሕዝብ አስጨርሶ ሸብረክ ይላል ብያችሁ ነበር፤ ይኼው እንታረቅ አለ!” የሚል ጽሑፍ የለጠፍኩት ስላለ እሱም እንዳያመልጣችሁ አንብቡት””

 አሁን ወደ እዚህ ትንተና እናምራ።፡ይህ ጽሑፍ ክፍል ሁለት ያልኩበት ምክንያት ከወራት በፊት ተችቼው ስለነበር ይህ እንደ ቀጣይ ክፍል ሁለት ተብሎ ይወሰድ። ለሁላችሁም ማሳሰብ የምፈልገው ቴድሮስ ጸጋዬ ካሁን በፊት በክፍል አንድ እንደገለጽኩት ኢትዮጵያዊነቱን በፍጹም ለድርድር የሚያቀርብ አይደለም ብያለሁ። ሆኖም ካነጋገር ወይስ እኔ ግራ ከገባኝ ውስጣዊ የትግራዋይ ብሔረተኛነት ስሜት እየገፈተረው የሚለው ጥያቄ መልስ ላገኝ አልችልኩም። ላሁኑ ማለት የምችለው ንግግሮቹን ማረም እንዳለበት ግን እርግጠኛ ነኝ፡ ጥንቃቄ እና እርማት ማድረግ አለበት እላለሁ። ለዚህም ወደ ትችቴ ልግባ፦

ከዚያ በፊት አንድ ነገር ልበል።

መቀሌ ለቅቆ የወጣው አብይ አሕመድ በሽብርተኛ የከሰሰውን ወያኔ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ለትግራይ ሕዝብ አሸባሪ ስላልሆንክ ወድዶ የመረጠህ ነህ እና አንተ አስተዳድር ብሎ “ባንክ ፤ ስልክ፤ አይሮፕላን፤መብራት፤ማጓጓዣ፤ ከነደሞዛቸው “ለሕዝብ በሚል ማመካኛ ሽፋን” ይከፍትለታል። ቃሌን እመኑ።

አሁን ወደ ትችቱ እንግባ!

 ትናንት በርዕዮት ሚዲያ “የመቀሌ ሁኔታ እና የአብይ አሕመድ የቶክስ አቁምልኝ ልመና” በሚል ርዕስ በ6/28/2021 ያስተላለፈውን የርዕዮት ክፍለ ጊዜ አድምጫለሁ። በንግግሩ ውስጥ ያደመጥኳቸው ጥቂቶቹን ልጥቀስ እና ከዚያ ክርክሬን ልስጥ።

እንዲህ ይላል፡

“የተካሄደው ጦርነት በህወሓት እና በብልጽግና ነው የሚል ሰው ለኔ የተገደሉት ያልታጠቁት ህወሓት ናቸው፤ የተገደሉት ቀሳውስት “ህወሓት ናቸው” ፤ ያ በማለቱ “የትግራይ ሕዝብ ሁላ ማንኛውም ትግርኛ ተናጋሪ ሁሉ” “ህወሓት ነው” እያለ ነው፤ “ህወሓት በዚያ መልክ ድጋፍ አግኝቶ ከሆነ ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው አጋንንት ጥምረት ነው።ማለትም የበልጽግና (ኦሆዴድ) (ብአዴን) ፤የሻዕቢያ የነ ብርሃኑ ነጋ ጥምረት ነው የትግራይ ሕዝብ “ወያኔን እንዲደግፍ ያደረገው”። “ወደ በረሃ የገባው በእነዚህ ክፍሎች ምክንያት ነው” ብሏል (ቴድሮስ ፀጋየ ርዕዮት ሚዲያ ዋና አዘጋጅ)።  ስለዚህም ይላል ንግግሩን ይቀጥል እና “ለዚህ ነው አንድ “እፎይታ” “ፌርማታ ነው” የምልበት ምክንያት።” ይላል (ወያኔ መቀሌን መቆጣጠሩ እፎይታ ነው ይላል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋየ)።

ካሁን በፊት ደግሞ በራሱ ክፍለጊዜ አቶ የሱፍ ከተባለ ወዳጁ ጋር በርዕዮት ሚዲያ ሲናገር የላይኛውን አባባሉ በተጻራሪ ሲናገር አድምጡ፡

እንዲህ ይላል፦

“የአማራ ጥቃት የአማራ ብሔረተኛ (ጉዳይ) ብቻ ነው ብየ አልልም፤ የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን ጥቃት ነው ብየ ነው የማስበው። ማንኛውም ማሕበረሰብ የሕልውና አደጋ ሲገጥመው የሁሉም ማሕበረሰብ የሕልውና አደጋ ነውና የሁሉም ማሕበረስ ግዴታ ነው ብየ ነው የማስበው።……የተፈራረቀ የታጠቀ ሁሉ የአማራን ደም ሲያፈስ የኖረ ሁሉ ማንም ጤናማ ሰው ሊከራከር/ሊክደው አይችልም። የሕልውና አደጋ ያለበት ሕዝብ፤ አማራ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልሞተበት ቦታ የለም፤ (ነገር ግን) እንዴት ግፍ መሮኛል፤ ከዚህ ግፍ መውጣት እፈልጋለሁ የሚል ሕዝብ እንዴት ይህንን ይፈጽማል? እንዴት ለሌላው አደጋ ሊሆን ይችላል?  ተከዜን እያሻገረ ይጥላል? ችግር አለብኝ የሚል ሕዝብ፤እንዴት የተገፋ ሕዝብ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ይጨቁናል፤ ወዘተ….” ይላል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋዬ፤

መጀመሪያ ከላይ ያስቀመጥኩት ንግግሩ ግን ያለው፦

 ““የተካሄደው ጦርነት በህወሓት እና በብልጽግና ነው የሚል ሰው ለኔ የተገደሉት ያልታጠቁት ህወሓት ናቸው፤ የተገደሉት ቀሳውስት “ህወሓት ናቸው” ፤ ያ በማለቱ “የትግራይ ሕዝብ ሁላ ማንኛውም ትግርኛ ተናጋሪ ሁሉ” “ህወሓት ነው” እያለ ነው፤….” ሲል ጦርነቱ ታዲያ በማን እና በማን ነው የሚል ጥያቄ ብናቀርብለት ልክ እንደ ወዳጁ ኢትዮ-ሚዲያ ባለቤት አቶ አብርሃ በላይ እንዳለው ካሁን በፊትም እራሱ ቴድሮስ ጸጋዬም እንደተጋራው “ጦርነቱ በአማራ እና በትግራይ መካከል ነው” የሚል ነው። ከጻድቃን ወ/ተንሳኤ እስከ ወዘተ… ወዘተ ጀምሮ እምነታቸው እና ንግግራቸው የቴድሮስ እና የአብርሃ በላይ ነው። ሁለቱም የትግራይ ተዋለጆች እና ምሁራን ናቸው። ይህንን እምነታቸው ከወያኔወ መሪዎች በጋራ ይጋራሉ። በግልጽ ነግረውናል።

ስለሆነም ችግሩ በብልጽግና እና በህወሓት አይደለም ጦርነቱ በትግራይ ሕዝብ እና በነዚህ አጋንንት መካከል ነው የሚለው ክርክሩ ጉልህ አድርጌ ላስቀምጠለት። ለማለት የፈለገውም ያ ነው። ግን ጦርነቱ “ብልጽግና፤ ሻዕቢያ እና ብ.አ.ዴ.ን.” የትግራይ ሕዝብ ለማጥፋት የመጡ ናቸው የሚለው መስመሩ እንዳለ ቢያስቀምጥ እና ጦርነቱ ከወያኔ ጋር መሆኑንንስ ለምን አይገልጸውም? ጥፋት ተደርጓል? አዎ፡ ግን በሁለቱም በኩል ማን ጥፋት እንደፈጸመ ገለልተኛ አጣሪ ይቋቋም፤ ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ነው። ያም ቢሆን አሁን አስቸጋሪ የሚሆነው “ወያኔ ትግራይን መልሶ ይዞታል” ስለዚህ መረጃው ያጠፋዋል፤ አፉን ከፍቶ ጸረ ወያኔ የሚመሰክር ሰውም የለም። እነ አሉላ ሰለሞን ባሁኑ ሰዓት ባንዳዎች እየለቀማችሁ አጥፏቸው የሚል መልእክት ስያስተላልፍ ሰምተነዋል፡ አብይን አምኖ ወያኔን ሲቃወም የነበረ ፤ ትንሽ ንፋሽ ሲተንፍስ የነበረ ሁሉ ባሁንዋ ሰዓት ሰንት ሰው እንደታፈነ እና በቢላዋ ተቆራርጦ እንደተገደለ የኼኔ ቤቱ ይቁጠረው።

አንድ ነገር ማወቅ ያለብን መሪ ነኝ የሚለን ምስጡሩና አሰራሩ የማይታወቅ ከመለስ ዜናዊ የባሰ አደገኛ እባብ እና “ለምዕራባዊያን ተሸብራኪው” አብይ አሕመድ ከሕግ ውጭ ፆታዊ ጥቃት እና የመሳሰሉ ወንጀሎች ተሳትፈዋል የሚባሉ ወታደሮች “በከፊል” ለጾታ ጥቃት ተጠያቂ አድርጓል። ይህንን ሰምተናል በራሱ በመንግሥት ሚዲያ። በቂ ነው አይደለም? መከራከር ይቻላል። ግን ወያኔዎች በራሳቸው ዱርየ ፖሊሶቻቸው እና ዱርየ ተዋጊዎቻቸው የተፈጸመ ወንጀል እና ዘር ማጥፋት ግን ምርመራ አላደረገም። የህንን ጥያቄ እነ ጸጋዮ እና “የትግራይ ትዕወት” መፈክር አስተጋቢዎች እነ አብርሃ በላይ “ለምን” የሚለው ጥያቄአችን  ወያኔዎችን ይጠይቁ ይሆን?

ወንጀለኛ ድርጅት ነውና እስካሁንዋም ሆነ ለወደፊቱ ወያኔ አንደም ሰው እንኳ ተጠያቂ አላደረገም/አያደርግም። ለምን? እነ ቴድሮስ እና አብርሃ በላይ ትኩረታቸው “ትግራይ ትዕወት” ላይ ብቻ ነው ትኩረት ያደረጉት። ለዚያም ነው ቴድሮስ ጸጋየ በዛው በትናንቱ ክፍለ ጊዜ ንግግሩ “ለዚህ ነው መቀሌ ነፃ መውጣትዋ አንድ “እፎይታ” “ፌርማታ ነው” የምልበት ምክንያት።” ይላል (ወያኔ መቀሌን መቆጣጠሩ እፎይታ ነው ይላል ጋዜጠኛ ቴድሮስ ጸጋየ)።

ወያኔ እኛ በምንጠራው ቋንቋ “አሸባሪው ወያኔ” ለትግራይ ሕዝብ እፎይታ የሰጠው ከሆነ ለኛ ኢትዮጵያዊያን ግን የማይለቅ አደገኛ “የኒኩልየር ንጥረ ነገር” ነው። ወያኔ መቀሌ ተሰጠው አልተሰጠው ጉዳዩ አደለም “ተፈጥሮው” ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዳትቀጥል ማፈራረስ ነው። አማራን ማጥፋት ነው! እርኩሱ አብይ አሕመድ “ከሲ አይ ኤ” ጋር ተመሳጥሮ “ጦር አስፈጅቶ” ሙሉውን ክ/ሃገር ለቀቀላቸው። ክላሽ ብቻ የታጠቀ አንደ ዓይጥ ሲሸሸግ የነበረ “የሽምቅ ተዋጊ” አሸንፏል ብየ አልቀበለውም። ምንም ጥርጥር የሌለው የአብይ እና የ ሲ አይ ኤ  እንዲሁም ኦነጋዊ ወታደራዊ አዛዦች ውስጠዊ ምስጢር እና ጣልቃ ገብነት እጅ አለበት። ናትናኤል አስመላሽ እኮ “ሲ አይ ኤ” መቀሌ ጽ/ቤት ከፍቶ አይቻለሁ ብሎ ነግሮናል። “ሲ አይ ኤም” ምን ሥራ አለው “የማንስ ዳቦ” ይጋግራል እዛ ቁጭ ብሎ?

እንግዲህ ጦርነቱ በማን እና በማን ነው የሚለው በቴድሮስ ጸጋየ እና በአብርሃ በላይ “ጦርነቱ በአማራ እና በትግሬ ሕዝብ መካካል መሆኑን” ነግረውናል። ስለዚህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተፈጸመ የሚባል ሁሉም ወንጀል በአማራ ሕዝብ መሆኑን በግልጽ ቴድሮስ እና አብርሃ በላይ ነግረውናል።

ስለዚህ የቴድሮስ ክብ ቀለቤቶች ሁለት ናቸው 1) የአማራ ሕዝብ 2) የአጋንንት ጥምረት የሚላቸው ሦስቱ ክፍሎች ናቸው። ቴድሮስ አምርሮ በየቀኑ ሲያነሳው የነበረው ወያኔ የሚለው ቃል ከምላሱ ከተወገደ 6 ወር ሆኖታል።

ይቀጥል እና  

የትግራይ ሕዝብ “ወያኔን እንዲደግፍ ያደረገው “…. የሻዕቢያ የነ ብርሃኑ ነጋ ጥምረት ነው የትግራይ ሕዝብ “ወያኔን እንዲደግፍ ያደረገው”። “ወደ በረሃ የገባው በእነዚህ ክፍሎች ምክንያት ነው” ይላል። በተዘዋዋሪ ምን ማለት ነው “እነዚህ ክፍሎች የጾታ አመጽ እና ግድያ፤ዝርፊያ ባይፈጽሙ ኖሮ የትግራይ ሕዝብ ወያኔ ወደ በረሃ ሲሸሽ አይከተላቸውም ነበር የሚል ሞኝ ክርክር እያቀረበ ይመስለኛል።

በሌላው ሦስተኛ ክፍል ይህንን በሚመለከት ስለምመለስበት ላሁኑ እስኪ ቴድሮስ ጸጋዬ መቀሌ በወየኔዎች እጅ በመውደቋ ደስታውን ለመግለጽ መቀሌ ውስጥ በትምክሕት ሲጨፈር የነበረውን የተለመደው የመቀሌ የእንደርታዎቹ የዘፈን ጭፈራ ንግግር በቪዲዮ ለአድማጮቹ ያሰማውን ላሰማችሁ፡

ብዙዎቻችሁ ሄዳችሁ ስታደምጡት በደስታ የቀለጠው ትምክሕታዊ የደስታ ጭፈራ እንዲህ ይላል፦

“ናዓና ዝመስል የለን” (እኛን የሚመስል ተወዳዳሪ የለም) ፤ “ትግራዋይ ዝመስል ባዓል ስረ የለን” (ትግሬን የሚያክል ባለ ሱሪ ወንድ የለም) ፤ “ሃ! ሁ! ምስ ወየነ እየ ዝዓበኹ) ፤ ሃ! ሁ! ከወያኔ ጉያ ነው ያደጉት!) “ሃ! ሁ~ ወያነ እንዳበልኩ እየ ዝዐበኹ” (ወያኔ እያልኩ ነው ያደግኩት) …መቐለ ፤መቐለ!!! (መቀሌ! መቀሌ!) “ናይና! ናይና ናይና!!” (የኛ ነች የኛ!!) “ኣየኹም ናይና!!” (የኛዎቹ ኣይዝዋችሁ!!)

ይህ ኣየኹም ናይና “ወገናዊ መፈከር” ካሁን በፊት እኔው “የመቀሌ ሕዝብ የመገንጠል አባዜ
 በሚል (Ethiopian Semay) 2/13/2021) የጻፍኩትን ዛሬ ደግመውታል። ያህንን በሚመለከት ‘’የትግራይ ሕዝብ ወያኔ ወደ በረሃ ሲሸሽ ወጣቱ ለምን ተከተለው?’’ ራሱ በቻለ ርዕስ ሰሞኑን እምለስበታለሁ።

ቴድሮሰ ጸጋየም ይሁን የለየላቸው የወያኔ “ፓፒ” ምሁራን እንደሚሉት የክርቢቱ ማቀጣጠያ ምክንያት በሕዝቡ ላይ የተለያዩ ወንጅሎች የተፈጸመበት ጉዳይ እንዳለ ሆኖ “ወንዙን የሚያናግረው ከውስጡ ያለው ድንጋይም” በቀላሉ የሚገፈተር ጉዳይ አይደለም። 

እንደ ቴድሮስ ጸጋዬ “ትናንት እንዳለው “ሕዝብ መተች የለበትም ሳይሆን ሕዝብ ወኪል (አጄንሲ የለውም) ብየ ስለማምን ነው።” ያለውን በኔ በከል አልቀበለውም። የትግራይ ሕዝብ ወኪል አለው። ሌላው ማለትም “እየተከሰሰ ያለው የአማራ ሕዝብ ግን ወኪል የለውም። ለዚህ ነው ብዙ ጊዜ ስለ አማራ የምናገረው።

በክፍል 4 የትግራይ ሕዝብ ለምን የወያኔ ፍቅር አልለቅ አለው? ይቀጥላል……….. ሼር አድርጉት ሕዝቡ ይነጋገርበት!!

አመሰግናለሁ

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)


No comments: