ሳሞራ! ሳሞራ! ወደ አብይ መጣ! ትግራይ ውስጥ መሬት አርዕድ ተቃውሞ ተነሳ! ቃለአጋኖዊ ጊዜኣዊ
የስቃይ መስታገሻ!
Saturday, June 12, 2020
ጌታቸው ረዳ ( Ethiopian Semay - ኢትዮ ሰማይ)
እንደምን ሰነበታችሁ? በኢትዮጵያዊያን ጀሮ ገብተው ሲያስደልቁ የሰነበቱት የዚህ ወር ሁለት ትኩስ ዜናዎች (1ኛ) የወያኔው ወታደራዊ አዛዥ “መሓመድ የኑስ” (ሳሞራ) ወደ አዲስ አበባ መምጠቱና ከፋሺሰቱ ኦሮሙማው መሪ “አብዮት መሐመድ” (አብይ) በመልካም ወዳጅነት ስለመገናኘቱ (2ኛ) ለኤርትራውያን ዘመዶቹ ወግኖ ምፅዋ ወደብና ሳሕል በረሃዎች ድረስ በመሄድ የወያኔ ተዋጊ ሃይሎችን ለውግያ በማሰማራት በሺዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ወታደሮችና ሰለማዊ ዜጎቻችንን የጨፈጨፈና ያስፈጀ፤ የተማረኩ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት ለስቃይ የዳረጋቸው፡ ከጠላት ጋር የተባበረ፤ አረመኔው ጸረ አማራው በሟቹ “ሓዲሽ ኣርአያ” (ሓየሎም አርአያ ) ስም የተሰየመ “ፈንቅል” የተባለ (አክራሪ የትግራይ ብሔተኛነትን አውቀውም ሳያውቁትም በኩራት የለበሱት መጠሪያ” ፌስ ቡክ ላይ እየጨፈሩ ሲያስጨፍሯችሁ የሰነበቱት “የተለያዩ የቃለ አጋ’ኖ” (Exclamation) ቡድኖች “ትግራይ ውስጥ ድንገት ፈነዳ የተባለለትን መሬት አርዕድ ተቃዉሞ” እንዳጋጋልዋችሁ ታዝቤአለሁ።
በፈጠራ “ቪዲዮውም በፎቶውም” እየተደገፈ የስንቶቻችሁ ጀሮ እንደበጠበጠ ባላውቅም ከሚገባው በላይ ተለጥጦ ወያኔ አለቀላት እስከሚባል ድረስ ከተቃዋሚ የዜና ማሰራጫዎች እስከ የአብይ አሕመድ “ኦሮሙማው ኢ ቲ ቪ” እና መሰል ማሕበራዊ መገናኛ ድረገጾች ምራቃችሁ እስኪንጠበጠብ ድረስ ሲያስግቱዋችሁ ሰንበተዋል።
እነዚህ ሁለት ዜናዎች የሳምንቱ ዋና ርዕስ ሆነው ቆይተዋል።
ፈንቅል የተባለው የአብይ አሕመድ ደጋፊዎች የሚወራጩበት የቃለ አጋኖው ቡድን ዋና መዘውሩ ውጭ አገር ሲሆን፡ ትግራይ ውስጥ ተነሳ የተባለው “መሬት አርዕድ” የተባለለት አብዮት፤ ካሁን በፊት የአማራ እና የኦሮሞ ቄሬዎች በዓለም ፊት በድምፅ ማጉልያ ይዘው “ወያኔ” ይውደም የሚል “መፈክር” ሳይሆን ለበርካታ አመታት የቆዩ የአስተዳደር ጥያቄዎችን የሚመለከት ነበር። እናነተ ጸረ ወያኔ ነው ማለት መብታችሁ ነው። ለመጃጃል ዲሞክራሲም ተዋናይ ነው።
ይህ ቃለ አጋኖ፤ እኔ የምለው ሳይሆን አዲስ አባባ ውስጥ “የዚህ እንቅስቃሴ” አማራር አባል የሆነ ከአጋር ወገኑ የቲ-ፒ-ዲ አ’ ተጠሪ ግለሰብ ጋር በቲ/ቪ ለውይይት ተጋብዘው ስለ ጉዳዩ ሲያብራራ እንዲህ ነበር ያለው፡-
”የሕዝቡ ጥያቄ በጣም ቀላል ነው። በቀላሉ የሚፈቱ እነዚህ ጥያቄዎች ወዲያውኑ መፈታት ሲገባቸው እየተጓተተ መዘግየቱ እንጂ በቀላሉ መፈታት የሚቻሉ ቀላል ጥያቄዎች ነበሩ” ነበር ያለው።
የዜና ማሰራጫዎች ሲገልጹት ግን በተለይ “እኔ የምወደው” ኢትዮ 360 የተባለው ሚዲያ እነ ኤርሚያስ ለገሰና ሃብታሙ አያሌው እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ሁኔታው ሲገመግሙ “ድሮም የትግራይ ሕዝብ እና ወያኔ አንድ አይደሉም ስንል ብዙ የተሰደብንበት አቋማችን ነው፤ ይኼው ዛሬ ማስረጃችን ይህ ነው” እያሉ አጉል የቦተለኩበት መናኛ አቋማቸው አስደምጠውናል። በዚህ ወደ ሗላ እመለስበታለሁ።
አሁን ወደ ሳሞራ የኑስ ወደ አብይ መምጣት ጉዳይ እንመልከት።
በወያኔ ትግራይ ፖሊሲ ተቀርጾ በልኩ ተሰፍቶ እንዲለብሰው የተሰጠው የወያኔ ጨርቅ ለባሹ ‘አብይ አሕመድ’ ለቀድሞ አለቃው ሳሞራ የኑስን ከትግራይ አስጠርቶ በማይታወቅ ጉዳይ እንዲያማክረው ወደ አዲስ አባባ እንደመጣ እራሱ ሳሞራ ተናግሯል። ለምን እንደጋበዘው እስካሁን ድረስ ግልጽ ባይሆንም፤ በዜና ተንታኞች እንዳሉት ከሆነ ‘ስለ ግብፅ እና አባይ ግድብ” እንደሆነ ይገልጻሉ።
እዚህ ላይ ብዙ ሰዎች ሲገረሙ አድመጬአለሁ። አብይን ሳሞራን በመጋበዙ ሲያደንቁት አደምጬአለሁ። ሁለት ነገሮችን እንመለክት ፤ ስለ ተባለው ግድብ እና የጸጥታ ጉዳይ ከሆነ፤ ሳሞራ ግብዣውን ለምን እንደተቀበለ ሊገርማችሁ አይገባም። ሁለት ነገሮች አሉ፡
አባይ ግድብ ሲመሰረት የአብይ አሕመድ ምላስ አስታውሱ። ምን ድነው ያለው? “ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ነበር የገነባው” ሲል አብይ ገና ወደ ሥልጣን ሲመጣ መናገሩን ታስታውሳላችሁ። ያንን የለመድነው እስስታዊ ምላሱን እራሱ ቀርጥሞ የግድቡ ተቆርቋሪ ሆኖ ቀረበ። ሳሞራን ያማከረበት ምከንያት አንደኛው ምክንያት፤ አባይ ግድብ የተመሰረተው በወያኔዎች ነው፡(በመለስ ዜናዊ)። ወያኔዎች ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይልቅ ያንን ግድብ ለማስቀጥለና ለማስፈጸም የማይተኙበት ምክንያት በመሪያቸው በመለስ ዜናዊ ስለተጠነሰሰ ነው። አባይ ግድብ ሲነሳ የወያኔን ስም አብሮ ከግድቡ ጋር የተያያዘ ነው። ስለሆነም ሳሞራ ፈቃደኛነቱን ገለጸለት። የሚገርም አይደለም።
ሁለተኛው ምክንያት አብይ እና ሳሞራ የሚጣሉበት ምክንያት የለም።
የሚከተሉትም የሚያራምዱትም “ፋሺስታዊ አክራሪ ብሔረተኛነት ነው”። ስለዚህም አይጣሉም። የሚጣሉበት ወቅት “አብይ እስካልነካቸው ድረስ ብቻ ነው” (ቀይ መስመራቸውን ካላለፈ!!!)።እስከዛሬ ድረስ ብዙዎቹ ወያኔዎችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው አልተነኩም (ስልጣን ላይ አሉ፤ ደሞዝም ይከፈላቸዋል)። የሚሰጣቸው ባጀት “በጉቦ እና ቁጣን ለማስታገሻ” መልክ ከአማራ ሕዝብ በላይ ከጋምቤላ ፤ ከሶማሊ ከወዘተ.. በላይ ለትግሬዎች አዳልቶ አለቆቹና ወዳጆቹ ለሆኑት የወያኔ ትግራይ መሪዎች ለሚያስተዳድሩት ለትግራይ “ክልል” ለልማት ዘርፍ ከፍተኛ ሥራ ማስኬጃ እንደመደበላቸው አብይ እራሱ ኢፍትሃዊነቱን ሳያስበው ኑዛዜውን በፓርላማው ሳያፍር፤ሳይደብቅ አድላዊ መሆኑን ነግሮናል። (ትግሬዎች ድሮም ዛሬም ተጠቃሚዎች ናቸው የምንለው ለዚህ ነው)።
በርዕዮተ ሓሳብም አንድ ናቸው። ሁለቱም ብልጽግናም ወያኔም አክራሪ ብሔረተኞች እና በአክራሪ ብሔረተኛነት የተቃኘው ፋሺስታዊው ሕገመንግሥት ተንከባካቢዎችና አስቀጣይ ናቸው። ስለዚህ ሳሞራ አብይ ጋር ወዳጅነት አለው፤ ወይንም “አብይ ላይ መፈንቅለ መንግሥት እንዳካሂድ ተጠይቄ አላካሂድም አልኩኝ” አለ እየታበለ በአድናቆት እየተሞካሸ በዜና ማሰራጫዎች በተለይ “አለምነህ ዋሴ” የተባለው በዘሓበሻ ሚዲያ በጎረናው ድምጹ የቀረበው ቃለ አጋኖ ብታደምጡት “እንዴት እያሳመረ በድምጽ ቅላጼ እንዳቀረበው” ስታደምጡ መስማት እጅግ የሚያሳምም፤ “በኢትዮጵያ ሉኣለዊነት እና ኢትዮጵያውን ነብስ የተጫወቱ የወያኔ አራዊቶችን ሰብኣዊ ባሕሪ ለማልበስ” የሚደረገው የዜና ማሰራጫዎች ትያትራዊ ቃለ አጋኖነት እጅግ ይገርማል። የእኛን (ኢትዮጵያን ያጠቁ/ያንበረከኩ/ለውርደት የዳረጉ/ወደባችንን የዘጉብን) ተሎ የመርሳት አባዜ ስንት ግዜ እየተጠቃን እንደምንኖር ለኔ ግራ ገብቶኛል።
አሁን መቸ ነው ሳሞራ (ወያኔዎች) እና አብይ የሚጣሉት? የሚል ጥያቄ ብታቀርቡ መልሱ ‘አብይ ወያኔን እንደናዚ ድርጅት ፈርጆ ከፖለቲካው ተሳትፎነትና ለሰሩት ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድግ ሲሞክር” (አያደርገውም ግን እንዲጥማችሁ ብየ ነው) ያኔ የአብይ አሕመድ መጨረሻ ይሆናል። ያንን ለማድረግ ወያኔዎች ወደ ደደቢት መሄድ አያስፈልጋቸውም! አብይን በደቂቃ ከብበው ማሰር የሚችሉ የወያኔ ታጋይ ወታደሮች ትጥቃቸውም ልብሳቸውም፤ የማዘዣ (የኮማንድ) ቀዳሚ መምርያዎች ሳይነጠቁ ከነማዕረጋቸው በወታደራዊ ስብሰባዎች የምታይዋቸው መኮንኖችና ወታደሮች ዛሬም የወያኔ ታጋዮች ናቸው። ለመለስ ዜናዊ ተንሰቅስቀው ከነመለዮቻቸውና ማዕረጎቻቸው አለም እያየ በቀብሩ ሰርዓት ‘መሬት ላይ እየተንከባለሉ ያለቀሱ” ወታደሮች ዛሬም አብይን እየወደዱት እንዳይመስላችሁ። የወያኔ ትግሬ ታጋዮች ተንኮል ማወቅ ብዙ መንገድና አመት ይጠይቃል።ወያኔነት ሃይማኖት ነው!! እንኳን ለትግሬዎች ‘አባ ዱላ ገመዳ” እንዳለው ከኦነግ ይልቅ ወያኔዎች ለኦሮሞ ይቀርቡታል” ብሏል።
ስለዚህም አብይ አሕመድም ሆነ አማራን እንወክላለን የሚሉት ለ26 አመት ለትግሬዎች ያደሩ “ዛሬም 2 አመት ደግሞ” ለኦሮሞዎቹ በሎሌነት ያደሩት አማራ ነን የሚሉ (ብኣዴንም) ሆነ ወያኔዎች “ውስጣቸውን ደፍረው ማየት የሚያስችል ሓሞት ስለሌላቸው ሊለወጡ አይችሉም።፡አርከበ. ዕቁባይ .ወዘተ..እያላችሁ ቁጠሩ አብይ ጉያ ውስጥ ገብተው ወሬና እስትራተጂ የሚቀርጹ ሁሉም የተመደቡ የወያኔ ሰላዮች ናቸው። ወየኔን ለማታውቁ ሰዎች ይገርማችሁ ይሆናል።
ወያኔዎች በባህሪ ሊለወጡ ስለማይችሉ “መሸኘት” ከመጣ የሚለያቸው ሁኔታ ካለ “ወያኔም፤አብይም” አብረው ይሞታሉ። ሥብሓት ነጋ- “የኢሕአዴግ የቁልቁለት ጉዞ” በሚል የወያኔ አምላኪ የነበረው ባለሹመት ብርሃነ ፅጋብ” የተባለ በጻፈው መጽሐፉ እንዲህ ይላል።
ስብሓት ባንድ ስብሰባ ውስጥ እንዲህ አለ ይላል፡
“ህወሓትም” ሆነ “ኢሕአዴግ” እንደገና መፈጠር አለባቸው። ሕዝቡ በሚገባ አውቆናል። ሕዝቡ እያለን ያለው ‘በዚህ ተሃድሶ ስብሰባቸውም ቢሆን ራሳቸውን ማየት ድፍረት ስለሌላቸው፤ ተቻችለውና የስቃይ መድሃኒት ውጠው ማቆያ አድርገውት ሊወጡ ይችላሉ፤ እያለን ይገኛል። እራሳቸው የምር ማየት ከጀመሩ እራሳቸው ይሞታሉ፤ እራሳቸውን ይገድላሉ እያለን ይገኛል።” ሲል ስብሓት ይናገራል።
ደብረጽዮን እኮ አብይን ተአምራዊ ከሰማይ የመጣ ሙሴ አድርጎ ነበር ሲያሞግሰው የነበረው? የተለቀቀው ቪዲዮውን አድምጣችሗል አደለም? ወያኔዎች እስስቶች ናቸው፡ መያዣ የላቸውም። ስብሓትም ሆነ ሌሎቹ ወያኔ እና ኢሕአዴግ እንደገና መፈጠር እንዳለባቸው በተሃድሶ ስብሰባቸው ላይ ቢያሳስቡም ፤ እውን ወያኔ እና ኢሕአዴግ እንደገና ራሱን ፈጥሮ መሻሻል የሚያስችል ቁመናም ሆነ ድፍረቱ አለው ወይ? የሚለው መልስ ማግኘት ቀላል ነው። ሁሉም የወያኔ መሪዎች ለውጥ ያስፈልጋል ይበሉ እንጂ ራሳቸውን ማየት ከጀመሩ እራሳቸው እንደሚያከስሙ ስለሚያውቁ፤ ይኼው አብይ አሕመድ እራሱ መቀየር የማይችል ማስረጃ ነው።
አብይ እራሴን እቀይራለሁ ብሎ ቢነሳም “እራሱን ማየት ሲጀምር አስፈሪ ሕዝባዊው ጥያቄ ከፊት ድቅን ሲልበት “የሕገመንግሥቱ ጠበቃና አሞጋሽ” ሆኖ በግልጽ በመናገር “በስንት ታጋይ ደም የመጣ ሕገመንግሥታችን” እያለ ባለፈው ሰሞን “የወያኔና የኦነግ የፋሺቶች ሕገ መንግሥትን” ጥብቅና ቆሜ እሞታለሁ ሲል ፓርላማው ተቀምጦ ሲለፈልፍ መኖሩን ታስታውሳላችሁ።
ይህ የሚነገረን ነገር፤ ፋሺሰቶች በዲሞክራሲ የማጃጃያ ዘዴ የሚያታልሉ፤ እራሳቸውን መለወጥ እንደማይቸሉ ማስረጃ ነው። ስለዚህ ሳሞራ መጣ፤ ወዲ ወረደ (ታደሰ ወረደ) አብይ ጋር አብረው “ምሳ በሉ” ወዘተ…. ለቃለ አጋኖዊ ቡድኖች ግን እርካታ ነው።
አሁን የትግራይ እና የወያኔ ድርጅት አንድ ነው አይደሉም ክርክር፤ በሚቀጥለው በሰፊው ባቀርብ ለዛሬ ግን እነዚህን ጥያቄዎች ላቅርብላችሁ_ እነሆ፤-
ወያኔ እና ህወሓት አንድ ነበሩ? አንድ ከነበሩስ መቸ አመተምሕረት ተለያዩ? የትግራይ ሕዝብ ወያኔን ሲከተል የፈቀደበት (አስገዳጅነት ከሚለው ሌላው ምክንያት) የተቀበለው ምን ነበር? የድርጅቱ መነሻ ጥያቄ ምን ነበር? የትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ዲሞክራሲ ነበር? ዛሬም ዲሞክራሲ ነው ለምትሉ ሰዎች “ዛሬም ትግሬዎች ‘በጎሳ ፌዴራሊዝም’ ያምናሉ፤ይቀበላሉ። አይደለም እንዴ? ታዲያ ‘እውን ፌደራሊዝም፤ በዲሞክራሲ ያምናል? የትግራይ ሕዝብ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምን ያምናል ወይስ አያምንም? አዎ የምንል ከሆነ፤ የማንን ርዕዮት እየተከተለ ነው ልንል ነው? የወያኔ!! አይደለም እንዴ? በቋንቋ መተዳደር ያመጡት ጣሊያኖች ናቸው- ታዲያ ትግሬዎችና ወያኔ አንድ ካልሆኑ ወያኔ ጣሊያንን የሚያመልክ ወያኔ ያስተማራቸውን በቋንቋ የመስተዳደር ትግሬዎች ለምን ዛሬም አፓርታይዱን ተቀብለውት እስከመጨረሻ እንታገልለታለን ይላሉ?
ይህንን ልጨምርላችሁ___፦-
አጅግ አምርሮ ኢትዮጵያዊነት የሚጠላ የትግራይ አዲስ ትውልድ ተፈጠሯል ወይስ አልተፈጠረም? ብዛቱስ ስንት ይሆናል? ወያኔ ኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እያወረደ የወያኔ ባንዴራ እንዲይዙ ሲደረጉ ዛሬም ያንን ተቀብለው በዓለም ፊት ይታያሉ፤ በየገጠሩ በክብር ተውለብልቦ በሙዚቃ ስትታጀብ ይታያል፡ ታዲያ ትግሬዎች እና ወያኔዎች አንድ አይደሉም? 42 አመት ሙሉ የትግራይ ሰው ኢትዮጵያዊነቱ ጸንቶ ቆይቷል ለምትሉ ከዶ/አሰፋ ነጋሽ የቀረበላችሁ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡
“ከ1967 ዓ.ም ወያኔዎች የካቲት ወደ ደደቢት በረሃ ከሄዱበት ጀምሮ የተወለደ ትውልድ ስንመለከት በአማካኙ የ1- 12 አመት ዕድሜ ጀምሮ ያላቸውን ህጻናት በወቅቱ የነበሩትን ስንመለከት ጸረ ኢትዮጵያነት እና ጸረ አማራነትን (ጎቦታት ትግራይ መቓብር አምሓራይ! (የትግሬ ተራሮች የአማራ መቀበሪያዎች) እያሉ “ኣምሓራይ ፤አድጊ፤ የ ዑዎሽ በሎ እዚ ኣምሓራይ) በሚል ጥላቻ እየተመረዘ ካስተማራቸው ከዚያ አመት ማለትም ዕድሜአቸው 12 ጀምረው የነበሩ ታጋዮችም ሆኑ ሰላማዊ የትግራይ ህጻናት ወጣቶች ዛሬ ዕድሜአቸው 46 ሲሆን በጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአማካኝ 92% (ዘጠና ሁለት ከሞቶ) ዕድሜአቸው 52 እስከ 56 ዕድሜ በታች ሆኖአቸዋል ማለት ነው (ትግራይን የሚጨምር ማለት ነው)። ይህ 92% በወያኔ አስተሳሰብ “ተላቅጦ፤ተቦክቶ የተፈጠረ ትውልድ ነው”። ባጭሩ ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ አማራ አመለካካት ተሸካሚ ነው። አሁን ጥያቄው፤ ባንዴ ሊፈወስ የቻለ ፤ ከወያኔ እሴቶች/በረከቶች/አስተሳቦች/ ጋር እንዴት ተላቀቀ የሚል ልትነግሩኝ ትችላላችሁ?
ስለዚህ በዚህ ሃይል ድጋፍ ነው ወያኔ ይወድቃል ስንባል የነበርነው። ደርግን የሚያክል ስርዓት ታግሎ ከጣለ፤ ዛሬ ከወያኔ እራሱን ማውጣት ለምን አልቻለም?
ካናዳ ውስጥ ኗሪ የስደተኞች የሕግ ጠበቃ ባለሞያ የሆነው ተክሌ የተባለው (ኢሳት ውስጥ እንደ ጋዜጠኛ ሆኖ የነበረ)- ጌታቸው፤ ማሰረሻ፤ ወዘተ የሚሉ ስሞች በሓጎስ፤ በዲሳሳ በነገዎ.. ስም ተተክተው በሥልጣን ፊት ለፊት መግባት አለባቸው፡ “ጌታቸው ..ማስረሻ..” የሚሉ አማራ ስም ያለቸው አማራዎች ስልጣን ይበቃቸዋል፤ በመንበረ ሥልጣን አመራር ከሗላ እንጂ ከፊት መቀመጥ የለባቸውም ሲል አማራን አጥብቆ የሚጠላ “ማፈሪያ” የሆነ ግለሰብ ይህንኑ በትግራይ ተሸንፈናል ፤በትግሬዎች እንድናለን ሲል ነበር። ዛሬ የትግራይ ምሁራን እና ወጣቶች ራሳቸውን ነጻ ማውጥት አልቻሉም። የወያኔ ተቃዋሚ የሚባሉትም ግማሹ ትግራይ ለማስገንጠል የቆሙ ግማሹ ደግሞ የአብይ አሕመድ የርዕዮተአለም አስፈጻሚ “ኩሊዎች” ሆነዋል። ወየኔ ሄደ በወያኔ ተተካ!!
ታዲያ በማአከላዊ መቶኛ ማለትም 92% የሆነው ትግራይ ውስጥ ከ42 እስከ 54 ዕድሜ ያለው ከላይ የተዘረዘሩትን የወያኔ “እሴቶች በሙሉ” ይቃወማል ወይስ ይቀበላል? አይቀበልም ካልን ማስረጃችሁን ንገሩኝ።የወያኔ ትግራይ መመስረትስ ዛሬም ህያው ሆኖ ያከብረዋል ወይስ አያከብረውም? አዎ ከሆነ ለምን? ወያኔነት ኢትዮጵያን ሉአላዊነት ያስደፈረ ኢትዮጵያን ያለ ወደብ ያስቀረ፤ አማርኛን በላቲን ፊደል እንዲተካ በሕግ የደነገገ (ትግራይም ጭምር (ኩናማም ዓፋሮችም..ወዘተ..) የመከራችን ፈጣሪ ከሆነ- ከወያኔ ትግሬ ጋር “ብዙዎቹ ትግሬዎች” ዛሬም ግንቦት በመጣ ቁጥር ለምን ትግሉን ያከብሩታል?
አመሰግናለሁ
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay)
No comments:
Post a Comment